Wachano Guenet Church

Wachano Guenet Church ድል ለነሣው በእግዚአብሔር ገነት ካለው ከሕይወት ዛፍ እንዲበላ እሰጠዋለሁ። ራእይ 2:7

Wachano Guenet Church✔️ሰኔ 06/2017 ዓ.ም 👉 ➯ እሁድ ማለዳ የዝማሬ ፣ የፀሎት ፣ የአምልኮ እና የቃል መልዕክት በአንድነት ተካፍለናል በዕለቱ በጌታ የተወደደ የቤተክርስትያ...
13/07/2025

Wachano Guenet Church
✔️ሰኔ 06/2017 ዓ.ም
👉 ➯ እሁድ ማለዳ የዝማሬ ፣ የፀሎት ፣ የአምልኮ እና የቃል መልዕክት በአንድነት ተካፍለናል በዕለቱ በጌታ የተወደደ የቤተክርስትያናችን አገልጋይ ወንጌላዊ ጰጥሮስ ቡሾ ጋር ጌታ ድንቅ የቃል መልዕክት እና የአምልኮ ግዜ ሰጥቶናል።
👉 በዕለቱ ላለፋት ለስድስት ወራት 39 ነብሳት ጌታን በህይወታቸዉ አምነው የደቀ-መዛሙርትና የደህንነት ትምህርት ስከታተሉ የነበሩ በዛሬ ዕለት የዉሃ ጥምቀት ስርዓት ተጠምቃለች የቤተክርስትያናች አባል ሆነዋል ።ክብር ለኢየሱስ ይሁን!
➯ ሉቃስ 19፥10
“የሰው ልጅ የጠፋውን ሊፈልግና ሊያድን መጥቶአለና አለው።
➯ ማቴዎስ 3፥1-2
“በዚያም ወራት መጥምቁ ዮሐንስ፦ መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ ብሎ በይሁዳ ምድረ በዳ እየሰበከ መጣ።”
“ከዚያ ዘመን ጀምሮ ኢየሱስ፦ መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ እያለ ይሰብክ ጀመር።”
➯ ማቴዎስ 4፥17
“ከዚያ ዘመን ጀምሮ ኢየሱስ፦ መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ እያለ ይሰብክ ጀመር።”
👉 ርዕስ:-የሚስክርነት ሥራ ምንድነዉ?
1. 👉 ስለኢየሱስ ምስክርነት መናገር ነዉ
➯ 1ኛ ዮሐንስ 1፥1
ስለ ሕይወት ቃል ከመጀመሪያው የነበረውንና የሰማነውን በዓይኖቻችንም ያየነውን የተመለከትነውንም እጆቻችንም የዳሰሱትን እናወራለን፤
ሕይወትም ተገለጠ አይተንማል እንመሰክርማለን፥ ከአብ ዘንድ የነበረውንም ለእኛም የተገለጠውን የዘላለምን ሕይወት እናወራላችኋለን፤
2.👉መለኮታዊ ትዕዛዝ ነዉ
➯ ማርቆስ 16፥15-16
እንዲህም አላቸው፦ ወደ ዓለም ሁሉ ሂዱ ወንጌልንም ለፍጥረት ሁሉ ስበኩ።
ያመነ የተጠመቀም ይድናል፥ ያላመነ ግን ይፈረድበታል።
3. 👉የሕይወት አድን ስራ ነው
➯ ምሳሌ 24፥11
➯“ወደ ሞት የሚነዱትን ታደግ፤ ሊታረዱ የተወሰኑትን አድን።”
4. 👉 የማያቋርጥ ሥራ ነዉ
➯ 1ኛ ቆሮንቶስ 9፥16
“ወንጌልን ብሰብክ እንኳ የምመካበት የለኝም፤ ግድ ደርሶብኝ ነውና፤ ወንጌልንም ባልሰብክ ወዮልኝ።”
➯ 1ኛ ቆሮንቶስ 11፥26
“ይህን እንጀራ በበላችሁ ጊዜ ሁሉ፥ ይህንም ጽዋ በጠጣችሁ ጊዜ ሁሉ ጌታ እስኪመጣ ድረስ ሞቱን ትናገራላችሁና።”
1ኛ ዮሐንስ 5፥10
በእምነት ፀንተን በሀይማኖት እንኑር ።
አሜን !
በእግዚአብሔር ልጅ የሚያምን በነፍሱ ምስክር አለው፤ በእግዚአብሔር የማያምን እግዚአብሔር ስለ ልጁ የመሰከረውን ምስክር ስላላመነ ሐሰተኛ አድርጎታል።
ልጁ ያለው ሕይወት አለው፤ የእግዚአብሔር ልጅ የሌለው ሕይወት የለውም።
አሜን !

 # የምስራች ታላቅ ዓመታዊ ኮንፈራንስ በዋጫኖ ገነት ቤተክርስትያን ግንቦት 28-ሰኔ 01/2017ዓ.ም ድረስ የሚቆይ ታላቅ መንፈሳዊ በረከት ስላዘጋጀን እናንተም የእግዚአብሔር ቤተሰብ የሆናች...
02/06/2025

# የምስራች
ታላቅ ዓመታዊ ኮንፈራንስ
በዋጫኖ ገነት ቤተክርስትያን ግንቦት 28-ሰኔ 01/2017ዓ.ም ድረስ የሚቆይ ታላቅ መንፈሳዊ በረከት ስላዘጋጀን እናንተም የእግዚአብሔር ቤተሰብ የሆናችሁ ኑና በአንድነት ጌታን አብረን እንድናከብረውና የበረከቱ ተካፋይ እንድትሆኑ ግብዣችን /ጥሪያችን ነው።

በቀብር ስርዓት ላይ ወንጌል ተሰበከ ክብር ለእግዚአብሔር ይሁን!በስርዓተ ከቀብር የተነገረ አፅናኝ ቃልP/r Meseret “ሰው ከንቱን ነገር ይመስላል፤ ዘመኑ እንደ ጥላ ያልፋል።”መዝሙር 14...
20/05/2025

በቀብር ስርዓት ላይ ወንጌል ተሰበከ ክብር ለእግዚአብሔር ይሁን!
በስርዓተ ከቀብር የተነገረ አፅናኝ ቃል
P/r Meseret
“ሰው ከንቱን ነገር ይመስላል፤ ዘመኑ እንደ ጥላ ያልፋል።”
መዝሙር 144፥4
👉 ሰው በከንቱነት የመሰለ ዘፍጥረት ነው
መዝሙር 39፥4
⁴አቤቱ፥ ፍጻሜዬን አስታውቀኝ፥ የዘመኔ ቍጥሮች ምን ያህል እንደ ሆኑ፥ እኔ ምን ያህል ወደ ኋላ እንደምቀር አውቅ ዘንድ።
⁵እነሆ፥ ዘመኖቼን አስረጀሃቸው፤ አካሌም በፊትህ እንደ ኢምንት ነው። ሕያው የሆነ ሰው ሁሉ በእውነት ከንቱ ብቻ ነው።
“ዘመኖቼ እንደ ጥላ አዘንብለዋል፤ እኔም እንደ ሣር ደርቄአለሁ።”
መዝሙር 102፥11
“በሕይወትህ፥ አንተም ከፀሐይ በታች በምትደክምበት ድካም ይህ እድል ፈንታህ ነውና ከንቱ በሆነ በሕይወትህ ዘመን ሁሉ፥ ከፀሐይ በታች በሰጠህ፥ በከንቱ ዘመንህ ሁሉ፥ ከምትወድዳት ሚስትህ ጋር ደስ ይበልህ።”
መክብብ 9፥9
ሰው የነገን አያውቅም
ሰው ከንቱ ነው
ሰው እንደ ንፋስ ነው
ሰው ዕድሜው የተወሰነ ነው
በቅኖች በከንቱ እንደምያልቅ አለማወቁ
“የሰው ዕድሜ የተወሰነ ነው፥ የወሩም ቍጥር በአንተ ዘንድ ነው፥ እርሱም ሊተላለፈው የማይችለውን ዳርቻ አደረግህለት።”
ኢዮብ 14፥5
“አሁንም፦ ዛሬ ወይም ነገ ወደዚህ ከተማ እንሄዳለን በዚያም ዓመት እንኖራለን እንነግድማለን እናተርፍማለን የምትሉ እናንተ፥ ተመልከቱ፥ ነገ የሚሆነውን አታውቁምና።”
ያዕቆብ 13-14
አሁንም፦ ዛሬ ወይም ነገ ወደዚህ ከተማ እንሄዳለን በዚያም ዓመት እንኖራለን እንነግድማለን እናተርፍማለን የምትሉ እናንተ፥ ተመልከቱ፥ ነገ የሚሆነውን አታውቁምና።
ሕይወታችሁ ምንድር ነው? ጥቂት ጊዜ ታይቶ ኋላ እንደሚጠፋ እንፍዋለት ናችሁና።
በዚህ ፈንታ። ጌታ ቢፈቅድ ብንኖርም ይህን ወይም ያን እናደርጋለን ማለት ይገባችኋል።
ምስክርነት
ከዉዳ ባለቤቱ ወ/ሮ ዳራሮ እና ከታናሽ ወንድሙ ቆሳ ኪሞ ህዝብን የሚያፅናና መልዕክት በስርዓቱ ላይ ለጉባኤ አስተላልፈዋል ። ኑሮ ከጌታ ጋር ይሁን በማለት
ክብር ለእግዚአብሔር ይሁን።

ዜና ዕረፍት😭የቤተ ክርስትያናችን አገልጋይ ጰጥሮስ(ኪዳኔ ) ኪም ወደ አገለገሉት አባት ዛሬ ጧት ከዝህ ዓለም ድካም አርፈዋል ። በወንጌል ስርጭት በቤተክርስቲያን ተከላ ወንጌል ባልደረሰባቸው ...
19/05/2025

ዜና ዕረፍት😭
የቤተ ክርስትያናችን አገልጋይ ጰጥሮስ(ኪዳኔ ) ኪም ወደ አገለገሉት አባት ዛሬ ጧት ከዝህ ዓለም ድካም አርፈዋል ። በወንጌል ስርጭት በቤተክርስቲያን ተከላ ወንጌል ባልደረሰባቸው አካባቢዎች ሚሽነር በመላክ ስያገለግሉ የነበሩ አገልጋይ ጰጥሮስ ኪሞ አዳዲስ ራዕይ በመፍጠር በቤተክርስቲያናችን ፈር ቀዳጅ ለአገልግሎቱ የጠራውን እግዚአብሔርንና ምዕመኑን በታማኝነት በብዙ መሰጠትና መስዋዕትነት ዘመናቸውን ሁሉ ያገለገሉ ለአካባቢያችን በረከት የነበሩ አቅመ ደካማዎችን የሚረዱ ቀና ባለራዕይ አገልጋይ በድንገት ባጋጠማቸው ህመም እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ወደ አገልግሉት ጌታ ሄድዋል ልባችሁ ያዘነ ቤተሰቦቻቸው ለጓደኞቻቸው ለወዳጅ ዘመዶቻቸው ቤተክርስቲያን ምእመናን አገልጋዮች አባላት እንዲሁም ለመላው አጎራባች አብያተክርስቲያናት አገልጋዮች ልባዊ መጽናናትን እንመኛለን።
ዋጫኖ ገነት ቤተክርስቲያን
ቀብር ነገ 12/09/2017 ዓ.ም ከቀኑ 6:30
ዋጫኖ ሚሽን መቃብር ይፈጸማል።
መልካም እረፍት 😭😭😭

👉Wachano Guenet Church✔️ግንቦት 010/2017 ዓ.ም ➯ እሁድ ማለዳ የዝማሬ ፣ የፀሎት ፣ የአምልኮ እና የቃል መልዕክት በአንድነት ተካፍለናል በዕለቱ በጌታ የተወደደ የቤተክርስ...
18/05/2025

👉Wachano Guenet Church
✔️ግንቦት 010/2017 ዓ.ም
➯ እሁድ ማለዳ የዝማሬ ፣ የፀሎት ፣ የአምልኮ እና የቃል መልዕክት በአንድነት ተካፍለናል በዕለቱ በጌታ የተወደደ የቤተክርስትያናችን አገልጋይ ብርሃኑ ፍጡራ ጋር ጌታ ድንቅ የቃል መልዕክት እና የአምልኮ ግዜ ሰጥቶናል ።
👉➯ ርዕስ:- ሕይወታችን ግንድ/መሠረት እግዚአብሔር ነው
ዮሐንስ 15፥4-12
በእኔ ኑሩ እኔም በእናንተ። ቅርንጫፍ በወይኑ ግንድ ባይኖር ከራሱ ፍሬ ሊያፈራ እንዳይቻለው፥ እንዲሁ እናንተ ደግሞ በእኔ ባትኖሩ አትችሉም።
እኔ የወይን ግንድ ነኝ እናንተም ቅርንጫፎች ናችሁ። ያለ እኔ ምንም ልታደርጉ አትችሉምና በእኔ የሚኖር እኔም በእርሱ፥ እርሱ ብዙ ፍሬ ያፈራል።
በእኔ የማይኖር ቢሆን እንደ ቅርንጫፍ ወደ ውጭ ይጣላል ይደርቅማል፤ እነርሱንም ሰብስበው ወደ እሳት ይጥሉአቸዋል፥ ያቃጥሉአቸውማል።
በእኔ ብትኖሩ ቃሎቼም በእናንተ ቢኖሩ የምትወዱትን ሁሉ ለምኑ ይሆንላችሁማል።
ብዙ ፍሬ ብታፈሩና ደቀ መዛሙርቴ ብትሆኑ በዚህ አባቴ ይከበራል።
አብ እንደ ወደደኝ እኔ ደግሞ ወደድኋችሁ፤ በፍቅሬ ኑሩ።
👉ከኢየሱስ ጋር በመኖር የሚገኝ በረከት/ትርፍ።
1.እርሱ በእኛ ይኖራል/ዋናው ኢየሱስ ነው።
“እግዚአብሔር ብርሃኔና መድኃኒቴ ነው፤ የሚያስፈራኝ ማን ነው? እግዚአብሔር የሕይወቴ መታመኛዋ ነው፤ የሚያስደነግጠኝ ማን ነው?”
መዝሙር 27፥1
2.ጌታ ካለ በፍሬያማው ህይወት ዉስጥ እንኖራለን ።
መዝሙር 91፥1
በልዑል መጠጊያ የሚኖር ሁሉን በሚችል አምላክ ጥላ ውስጥ ያድራል።
ከእርሱ ጋር በመሆን
ማቴ 7:7 ለምኑ፥ ይሰጣችሁማል፤ ፈልጉ፥ ታገኙማላችሁ፤ መዝጊያን አንኳኩ፥ ይከፈትላችሁማል።
የሚለምነው ሁሉ ይቀበላልና፥ የሚፈልገውም ያገኛል፥ መዝጊያንም ለሚያንኳኳ ይከፈትለታል።
3.እርሱ የእኛን ቃል/ድምጽ ይሰማናል
“አሁንም በእግዚአብሔር ዓይን ከብሬአለሁና፥ አምላኬም ጕልበት ሆኖኛልና ያዕቆብን ወደ እርሱ እንድመልስ እስራኤልንም ወደ እርሱ እንድሰበስብ ባሪያ እሆነው ዘንድ ከማኅፀን ጀምሮ የሠራኝ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል።”
ኢሳይያስ 49፥5
4. ከብዙ መከራ እናመልጣለን።
ኢሳይያስ 43፥1
አሁንም ያዕቆብ ሆይ፥ የፈጠረህ፥ እስራኤልም ሆይ፥ የሠራህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ተቤዥቼሃለሁና አትፍራ፤ በስምህም ጠርቼሃለሁ፥ አንተ የእኔ ነህ።
በውኃ ውስጥ ባለፍህ ጊዜ ከአንተ ጋር እሆናለሁ፥ በወንዞችም ውስጥ ባለፍህ ጊዜ አያሰጥሙህም፤ በእሳትም ውስጥ በሄድህ ጊዜ አትቃጠልም፥ ነበልባሉም አይፈጅህም።
👈እኛስ ማንን እንመስላለን
👈አካሄዳችን እንዴት ነው?
በሕይወታችን ከእግዚአብሔር እንጣበቅ።
አሜን!

👉Wachano Guenet Church🖋 ሚያዚያ 19/2017 ዓ.ም ➯ እሁድ ማለዳ የዝማሬ ፣ የፀሎት ፣ የአምልኮ እና የቃል መልዕክት በአንድነት ተካፍለናል በዕለቱ በጌታ የተወደደ የቤተክርስት...
27/04/2025

👉Wachano Guenet Church
🖋 ሚያዚያ 19/2017 ዓ.ም
➯ እሁድ ማለዳ የዝማሬ ፣ የፀሎት ፣ የአምልኮ እና የቃል መልዕክት በአንድነት ተካፍለናል በዕለቱ በጌታ የተወደደ የቤተክርስትያናችን አገልጋይ ኤርምያስ ኤዳኦ ጋር ጌታ ድንቅ የቃል መልዕክት እና የአምልኮ ግዜ ሰጥቶናል ።
👉➯ ርዕስ:- በሕይወታችን ኢየሱስ ክርስቶስን እንግለጥ/እናንጸባርቅ!
👉 የሚታመልኩት አምላክ ከእስራትና ከሞት ያስመልጣችሃል
👉ሐዋርያት 16፥16-35
ወደ ጸሎት ስፍራም ስንሄድ፥ የምዋርተኝነት መንፈስ የነበረባት ለጌቶችዋም እየጠነቈለች ብዙ ትርፍ ታመጣ የነበረች አንዲት ገረድ አገኘችን።
✔️እሳም እየተከተለች፦ ትጮኽ ነበር።
✔️ጳውሎስ ግን ተቸገረና ዘወር ብሎ መንፈሱን፦ ከእርስዋ እንድትወጣ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አዝሃለሁ አለው፤ በዚያም ሰዓት ወጣ።
✔️ጌቶችዋም የትርፋቸው ተስፋ እንደ ወጣ ባዩ ጊዜ ጳውሎስንና ሲላስን ይዘው ✔️ወደ ገበያ በሹማምት ፊት ጐተቱአቸው፤
✔️ወደ ገዢዎችም አቅርበው፦ እነዚህ ሰዎች አይሁድ ሆነው ከተማችንን እጅግ ያናውጣሉ።
🔐 በብዙም ከደበደቡአቸው በኋላ ወደ ወኅኒ ጣሉአቸው፥
✔️የወኅኒውንም ጠባቂ ተጠንቅቆ እንዲጠብቃቸው አዘዙት።
✔️እርሱም የዚህን ዓይነት ትእዛዝ ተቀብሎ
ወደ ውስጠኛው ወኅኒ ጣላቸው፥ እግራቸውንም በግንድ አጣብቆ ጠረቃቸው።
@🙏 በመንፈቀ ሌሊት ግን ጳውሎስና ሲላስ እየጸለዩ እግዚአብሔርን በዜማ ያመሰግኑ ነበር፥ እስረኞቹም ያደምጡአቸው ነበር
🔓ድንገትም የወኅኒው መሠረት እስኪናወጥ ድረስ ታላቅ የምድር መንቀጥቀጥ ሆነ፤
🔓በዚያን ጊዜም ደጆቹ ሁሉ ተከፈቱ የሁሉም እስራት ተፈታ።
🔑የወኅኒውም ጠባቂ ከእንቅልፉ ነቅቶ የወኅኒው ደጆች ተከፍተው ባየ ጊዜ፥ እስረኞቹ ያመለጡ መስሎት ራሱን ይገድል ዘንድ አስቦ ሰይፉን መዘዘ።
✔️ ጳውሎስ ግን በታላቅ ድምፅ፦ ሁላችን ከዚህ አለንና በራስህ ክፉ ነገር አታድርግ ብሎ ጮኸ።
✔️ እየተንቀጠቀጠም ከጳውሎስና ከሲላስ ፊት ተደፋ፤
✔️ወደ ውጭም አውጥቶ፦ ጌቶች ሆይ፥ እድን ዘንድ ምን ማድረግ ይገባኛል? ኣላቸው።
🙏እነርሱም፦ በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ እመን አንተና ቤተ ሰዎችህ ትድናላችሁ አሉት።
✔️ለእርሱና በቤቱም ላሉት ሁሉ የእግዚአብሔርን ቃል ተናገሩአቸው።
✔️በሌሊትም በዚያች ሰዓት ወስዶ ቍስላቸውን አጠበላቸው፥ ያን ጊዜውንም እርሱ ከቤተ ሰዎቹ ሁሉ ጋር ተጠመቀ፤
✔️ወደ ቤቱም አውጥቶ ማዕድ አቀረበላቸው፥ በእግዚአብሔርም ስላመነ ከቤተ ሰዎቹ ሁሉ ጋር ሐሤት አደረገ።
✔️በነጋም ጊዜ ገዢዎቹ፦ እነዚያን ሰዎች ፍታቸው ብለው ሎሌዎቻቸውን ላኩ።
የወኅኒውም ጠባቂ፦ ትፈቱ ዘንድ ገዢዎቹ ልከዋል፤ እንግዲህ አሁን ወጥታችሁ በሰላም ሂዱ ብሎ ይህን ቃል ለጳውሎስ ነገረው።
የእኛ ጌታ ወደ ልጆቹ ይመጣል! የመከራ፥የስቃይ፥የችግር፥የበሽታ፥የእስራትና
ሰንሰለት እግዚአብሔር ይበጣጥሰዋል።
አሜን!
ክብር ለኢየሱስ ይሁን!

👉Wachano Guenet Church🖋 መጋቢት 28/2017 ዓ.ም ➯ እሁድ ማለዳ የዝማሬ ፣ የፀሎት ፣ የአምልኮ እና የቃል መልዕክት በአንድነት ተካፍለናል በዕለቱ በጌታ የተወደደች የቤተክርስ...
06/04/2025

👉Wachano Guenet Church
🖋 መጋቢት 28/2017 ዓ.ም
➯ እሁድ ማለዳ የዝማሬ ፣ የፀሎት ፣ የአምልኮ እና የቃል መልዕክት በአንድነት ተካፍለናል በዕለቱ በጌታ የተወደደች የቤተክርስትያናችን የሴቶች አገልጋይ ወ/ሮ የሺ ሰለሞን ጋር ጌታ ድንቅ የቃል መልዕክት እና የአምልኮ ግዜ ሰጥቶናል ።
👉➯ ርዕስ:-ተስፋ ስጠፋ እግዚአብሔር
ተስፋችን ነው!

👉 ሕዝቅኤል 37፥1-14

➯ የእግዚአብሔርም እጅ በላዬ ነበረ እግዚአብሔርም በመንፈሱ አወጣኝ አጥንቶችም በሞሉባት ሸለቆ መካከል አኖረኝ።
በእነርሱም አንጻር በዙሪያቸው አሳለፈኝ፤ እነሆም፥ በሸለቆው ፊት እጅግ ብዙ ነበሩ፥ እነሆም፥ እጅግ ደርቀው ነበር።
➯ እርሱም፦ የሰው ልጅ ሆይ፥ እነዚህ አጥንቶች በሕይወት ይኖራሉን? አለኝ። እኔም፦ ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፥ አንተ ታውቃለህ አልሁ።

➯እርሱም እንዲህ አለኝ፦ በእነዚህ አጥንቶች ላይ ትንቢት ተናገር እንዲህም በላቸው፦ እናንተ የደረቃችሁ አጥንቶች ሆይ፥ የእግዚአብሔርን ቃል ሰሙ።

➯ ጌታ እግዚአብሔር ለእነዚህ አጥንቶች እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ ትንፋሽን አገባባችኋለሁ በሕይወትም ትኖራላችሁ።
ጅማትም እሰጣችኋለሁ ሥጋንም አወጣባችኋለሁ በእናንተም ላይ ቁርበትን እዘረጋለሁ ትንፋሽንም አገባባችኋለሁ በሕይወትም ትኖራላችሁ፤ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ።

➯ እንዳዘዘኝም ትንቢት ተናገርሁ፤ ስናገርም ድምፅ ሆነ፥ እነሆም፥ መናወጥ ሆነ፥ አጥንቶችም አጥንት ከአጥንት ጋር ተቀራረቡ።

➯ እኔም አየሁ፥ እነሆም፥ ጅማት ነበረባቸው ሥጋም ወጣ ቁርበትም በላያቸው ተዘረጋ፥ ትንፋሽ ግን አልነበረባቸውም።

➯ እርሱም፦ የሰው ልጅ ሆይ፥ ትንቢት ተናገር፥ ለነፋስ ትንቢት ተናገር፥ ለነፋስም፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ነፋስ ሆይ፥ ከአራቱ ነፋሳት ዘንድ ና፥ እነዚህም የተገደሉት በሕይወት ይኖሩ ዘንድ እፍ በልባቸው በል አለኝ።

➯ እንዳዘዘኝም ትንቢት ተናገርሁ፥ ትንፋሽም ገባባቸው ሕያዋንም ሆኑ፥ እጅግም ታላቅ ሠራዊት ሆነው በእግራቸው ቆሙ።

➯ እርሱም እንዲህ አለኝ፦ የሰው ልጅ ሆይ፥ እነዚህ አጥንቶች የእስራኤል ቤት ሁሉ ናቸው፤ እነሆ፦ አጥንቶቻችን ደርቀዋል ተስፋችንም ጠፍቶአል ፈጽመንም ተቈርጠናል ብለዋል።

➯ ስለዚህ ትንቢት ተናገር እንዲህም በላቸው፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ሕዝቤ ሆይ፥ እነሆ፥ መቃብራችሁን እከፍታለሁ ከመቃብራችሁም አወጣችኋለሁ፥ ወደ እስራኤልም ምድር አገባችኋለሁ።

ሕዝቤ ሆይ፥ መቃብራችሁን በከፈትሁ ጊዜ ከመቃብራችሁም ባወጣኋችሁ ጊዜ፥ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ።

➯ መንፈሴንም በውስጣችሁ አሳድራለሁ፥ እናንተም በሕይወት ትኖራላችሁ፥ በገዛ ምድራችሁም አኖራችኋለሁ፤ እኔም እግዚአብሔር እንደ ተናገርሁ እንዳደረግሁም ታውቃላችሁ፥ ይላል እግዚአብሔር። ተስፋ ስጠፋ ኢየሱስ ተስፋችን ነው
አሜን!!!

👉Wachano Guenet Church🖋 መጋቢት 21/2017 ዓ.ም ➯ እሁድ ማለዳ የዝማሬ ፣ የፀሎት ፣ የአምልኮ እና የቃል መልዕክት በአንድነት ተካፍለናል በዕለቱ በጌታ የተወደደ የቤተክርስት...
30/03/2025

👉Wachano Guenet Church
🖋 መጋቢት 21/2017 ዓ.ም
➯ እሁድ ማለዳ የዝማሬ ፣ የፀሎት ፣ የአምልኮ እና የቃል መልዕክት በአንድነት ተካፍለናል በዕለቱ በጌታ የተወደደ የቤተክርስትያናችን መሪና አገልጋይ ሚልክያስ ሽጉጤ ጋር ጌታ ድንቅ የቃል መልዕክት እና የአምልኮ ግዜ ሰጥቶናል ።
ርዕስ:-ትዕዛዝ ስለወጣ ተፈትቻለሁ።
ከታሰርንበት እስራት ብዙዎች ሳይወዱን ተገደው ተፈተናል።
ማርቆስ 11፥2-10

በፊታችሁ ወዳለችው መንደር ሂዱ፥ ወዲያውም ወደ እርስዋ ገብታችሁ ከሰው ማንም ገና ያልተቀመጠበት ውርንጫ ታስሮ ታገኛላችሁ፤ ፈትታችሁ አምጡልኝ።
ማንም፦ ስለ ምን እንዲህ ታደርጋላችሁ? ቢላችሁ፦ ለጌታ ያስፈልገዋል በሉት፥ ወዲያውም ደግሞ ወደዚህ ይሰደዋል አላቸው።
ሄዱም ውርንጫውንም በመንገድ መተላለፊያ በደጅ ውጭ ታስሮ አገኙት፥ ፈቱትም።
በዚያም ከቆሙት አንዳንዶቹ፦ ውርንጫውን የምትፈቱት ምን ልታደርጉት ነው አሉአቸው።
እነርሱም ኢየሱስ እንዳዘዘ አሉአቸው፤ ተዉአቸውም።
ውርንጫውንም ወደ ኢየሱስ አመጡት፥ ልብሳቸውንም በላዩ ጣሉ፥ ተቀመጠበትም።
ብዙ ሰዎችም ልብሳቸውን በመንገድ ላይ አነጠፉ፥ ሌሎችም ከዛፍ ቅጠሎችን እየቈረጡ ያነጥፉ ነበር።
የሚቀድሙትም የሚከተሉትም፦ ሆሣዕና፤ በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ
ነው፤
በጌታ ስም የምትመጣ የአባታችን የዳዊት መንግሥት የተባረከች ናት፤ ሆሣዕና በአርያም እያሉ ይጮኹ ነበር።

እኛን ያዳነን ኢየሱስ ነው
የስሙ ጉልበት የትኛውም እስራት፤ ቀንበርና መከራ ህዝቡን ይፈታል። አሜን
ከጌታ ዘንድ ትዕዛዝ ስወጣ ወዲያው ክብር ይጀምራል።
ከልጅነት ጀምሮ ከታሰርንበት ዛሬ ጌታን ይፍታህ።
ሉቃስ 13፥8-10
እነሆም፥ ከአሥራ ስምንት ዓመት ጀምሮ የድካም መንፈስ ያደረባት ሴት ነበረች፥ እርስዋም ጐባጣ ነበረች ቀንታም ልትቆም ከቶ አልተቻላትም።
ኢየሱስም ባያት ጊዜ ጠራትና። አንቺ ሴት፥ ከድካምሽ ተፈትተሻል አላት፥ እጁንም ጫነባት፤
ያን ጊዜም ቀጥ አለች፥ እግዚአብሔርንም አመሰገነች።
ተከራካርዎች እያሉ ነገርህን ተፈታል።
የተለያየ ችግር ያጎበጣችሁ ዛሬ መፈታት ሆኖላችሃል ።
1.የተፈታኸው ልታገለግል ነው
2. የተፈታኸው ልያከብርህ ነዉ
3. የተፈታነው ጌታ የዘላሌም ሕይወት ልሰጠን ነው። አሜን

🎄🎄🌲🎄 ለክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ  አንኳን ለጌታችንና ለመዲሐኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ልደት መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሳችሁ !! ታህሳስ 2017 ዓ.ምComing Soon !!Com...
03/01/2025

🎄🎄🌲🎄 ለክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ አንኳን ለጌታችንና ለመዲሐኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ልደት መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሳችሁ !! ታህሳስ 2017 ዓ.ም
Coming Soon !!
Coming Soon !!
ዋጫኖ ገነት ቤተክርስትያን አማኑኤል መዘምራን የእግዚአብሔር ፈቃድ ሆኖ በቅርቡ 2ኛውን ካሴት (vcd) መዝሙር ለመላው ሕዝብ ዓይንና ጆሮ ለማድረስ ዝግጅታቸውን አጠናቅቀው የቀናት ጊዜ ብቻ ይቀራል ፤ ይሄንን ዝማሬ ሰምታችሁ እንድትባረኩና ለሌሎችም እንድታደርሱ በታላቅ ትህትና እንጠይቃለን ። የጌታ ይባርካችሁ !!!
መልኳም የልደት በዓል!

👉Wachano Guenet Churchታህሳስ 20/2017 ዓ.ም ማለዳ የዝማሬ ፣ የፀሎት ፣ የአምልኮ እና የቃል መልዕክት ተካፍለናል በዕለቱ በጌታ የተወደዱና የምንወዳቸው ቀደምት የስዳማ ክልል...
03/01/2025

👉Wachano Guenet Church
ታህሳስ 20/2017 ዓ.ም ማለዳ የዝማሬ ፣ የፀሎት ፣ የአምልኮ እና የቃል መልዕክት ተካፍለናል በዕለቱ በጌታ የተወደዱና የምንወዳቸው ቀደምት የስዳማ ክልል ገነት ቤተክርስትያን ቦርድ እና ጣጤሣ ገነት ቤተክርስትያን አገልጋይ አባታችን ገረሙ ጋብሶ ጋር ጌታ ድንቅ የቃል መልዕክት ግዜ ሰጥቶናል ።
“በልባችሁ መታደስ ተለወጡ እንጂ ይህን ዓለም አትምሰሉ።”
ሮሜ 12፥2
“በዚያ ቀን የወደቀችውን የዳዊትን ድንኳን አነሣለሁ፥ የተናደውንም ቅጥርዋን እጠግናለሁ፤ የፈረሰውንም አድሳለሁ፥ እንደ ቀደመውም ዘመን እሠራታለሁ፤”
አሞጽ 9፥11
መጽሐፍ ወቅዱስ በውስጡ ሁለት ነገር ይዛል። 1.በረከት
2.መርገም
✍✍ ርዕስ :- ከእናንተ እያንዳንዱ ወንድሙን ከልቡ ይቅር ካለ፥ እንዲሁ ደግሞ የሰማዩ አባቴ ይቅር ይላችሃል።
👉ማቴ 18፥21-31
በዚያን ጊዜ ጴጥሮስ ወደ እርሱ ቀርቦ፦ ጌታ ሆይ፥ ወንድሜ ቢበድለኝ ስንት ጊዜ ልተውለት? እስከ ሰባት ጊዜን? አለው።
ኢየሱስ እንዲህ አለው፦ እስከ ሰባ ጊዜ ሰባት እንጂ እስከ ሰባት ጊዜ አልልህም።
ስለዚህ መንግሥተ ሰማያት ባሮቹን ሊቈጣጠር የወደደን ንጉሥ ትመስላለች።
መቈጣጠርም በጀመረ ጊዜ፥ እልፍ መክሊት ዕዳ ያለበትን አንድ ሰው ወደ እርሱ አመጡ።
የሚከፍለውም ቢያጣ፥ እርሱና ሚስቱ ልጆቹም ያለውም ሁሉ እንዲሸጥና ዕዳው እንዲከፈል ጌታው አዘዘ።
ስለዚህ ባሪያው ወድቆ ሰገደለትና፦ ጌታ ሆይ፥ ታገሠኝ፥ ሁሉንም እከፍልሃለሁ አለው።
የዚያም ባሪያ ጌታ አዘነለትና ለቀቀው፥ ዕዳውንም ተወለት። ነገር ግን ያ ባሪያ ወጥቶ ከባልንጀሮቹ ከባሮቹ መቶ ዲናር ዕዳ ያለበትን አንዱን አገኘና፦ ዕዳህን ክፈለኝ ብሎ ያዘና አነቀው።
ስለዚህ ባልንጀራው ባሪያ ወድቆ፦ ታገሠኝ፥ ሁሉንም እከፍልሃለሁ ብሎ ለመነው።
እርሱም አልወደደም፥ ግን ሄዶ ዕዳውን እስኪከፍል ድረስ በወኅኒ አኖረው።
ባልንጀሮቹ የሆኑ ባሮችም ያደረገውን አይተው እጅግ አዘኑ፥ መጥተውም የሆነውን ሁሉ ለጌታቸው ገለጡ።
እኔ እንደ ማርሁህ ባልንጀራህ የሆነውን ያን ባሪያ ልትምረው ለአንተስ አይገባህምን? አለው።
ጌታውም ተቈጣና ዕዳውን ሁሉ እስኪከፍለው ድረስ ለሚሣቅዩት አሳልፎ ሰጠው።
ከእናንተ እያንዳንዱ ወንድሙን ከልቡ ይቅር ካላለ፥ እንዲሁ ደግሞ የሰማዩ አባቴ ያደርግባችኋል።

👉1ኛ ዮሐንስ 3-10

እናንተ ደግሞ ከእኛ ጋር ኅብረት እንዲኖራችሁ ያየነውንና የሰማነውን ለእናንተ ደግሞ እናወራላችኋለን። ኅብረታችንም ከአባት ጋር ከልጁም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ነው።
ደስታችሁም እንዲፈጸም ይህን እንጽፍላችኋለን።
ከእርሱም የሰማናት ለእናንተም የምናወራላችሁ መልእክት፦ እግዚአብሔር ብርሃን ነው ጨለማም በእርሱ ዘንድ ከቶ የለም የምትል ይህች ናት።
ከእርሱ ጋር ኅብረት አለን ብንል በጨለማም ብንመላለስ እንዋሻለን እውነትንም አናደርግም፤
ነገር ግን እርሱ በብርሃን እንዳለ በብርሃን ብንመላለስ ለእያንዳንዳችን ኅብረት አለን፥ የልጁም የኢየሱስ ክርስቶስ ደም ከኃጢአት ሁሉ ያነጻናል።
ኃጢአት የለብንም ብንል ራሳችንን እናስታለን፥ እውነትም በእኛ ውስጥ የለም።
በኃጢአታችን ብንናዘዝ ኃጢአታችንን ይቅር ሊለን ከዓመፃም ሁሉ ሊያነጻን የታመነና ጻድቅ ነው።
ኃጢአትን አላደረግንም ብንል ሐሰተኛ እናደርገዋለን ቃሉም በእኛ ውስጥ የለም።

👉 ሮሜ 2 ፥4-12
የእግዚአብሔር ቸርነት ወደ ንስሐ እንዲመራህ ሳታውቅ የቸርነቱንና የመቻሉን የትዕግሥቱንም ባለጠግነት ትንቃለህን?
ነገር ግን እንደ ጥንካሬህና ንስሐ እንደማይገባ ልብህ የእግዚአብሔር ቅን ፍርድ በሚገለጥበት በቍጣ ቀን ቍጣን በራስህ ላይ ታከማቻለህ።
እርሱ ለእያንዳንዱ እንደ ሥራው ያስረክበዋል፤
በበጎ ሥራ በመጽናት ምስጋናንና ክብርን የማይጠፋንም ሕይወት ለሚፈልጉ የዘላለምን ሕይወት ይሰጣቸዋል፤
ለዓመፃ በሚታዘዙ እንጂ ለእውነት በማይታዘዙትና በአድመኞች ላይ ግን ቍጣና መቅሠፍት ይሆንባቸዋል።
ክፉውን በሚያደርግ ሰው ነፍስ ሁሉ መከራና ጭንቀት ይሆንበታል፥ አስቀድሞ በአይሁዳዊ ደግሞም በግሪክ ሰው፤
ነገር ግን በጎ ሥራ ለሚያደርጉ ሁሉ ምስጋናና ክብር ሰላምም ይሆንላቸዋል፥ አስቀድሞ ለአይሁዳዊ ደግሞም ለግሪክ ሰው።
👉 ኢሳይያስ 62፥1-10
ስለ ጽዮን ዝም አልልም፥ ስለኢየሩሳሌምም ጸጥ አልልም፥ ጽድቅዋ እንደ ጸዳል መዳንዋም እንደሚበራ ፋና እስኪወጣ ድረስ።
አሕዛብም ጽድቅሽን ነገሥታትም ሁሉ ክብርሽን ያያሉ፤ የእግዚአብሔርም አፍ በሚጠራበት በአዲሱ ስም ትጠሪያለሽ።
በእግዚአብሔር እጅ የክብር አክሊል፥ በአምላክሽም እጅ የመንግሥት ዘውድ ትሆኛለሽ። ከእንግዲህ ወዲህ፦ የተተወች አትባዪም፤ ምድርሽም ከእንግዲህ ወዲህ፦ ውድማ አትባልም፤ ነገር ግን እግዚአብሔር በአንቺ ደስ ብሎታልና፥ ምድርሽም ባል ታገባለችና አንቺ፦ ደስታዬ የሚኖርባት ትባያለሽ ምድርሽም፦ ባል ያገባች ትባላለች።
ጕልማሳም ድንግሊቱን እንደሚያገባ፥ እንዲሁ ልጆችሽ ያገቡሻል፤ ሙሽራም በሙሽራይቱ ደስ እንደሚለው፥ እንዲሁ አምላክሽ በአንቺ ደስ ይለዋል።
እግዚአብሔርን በመፍራት እንኑር !
አሜን!!!

Address

Awassa

Telephone

+251939169016

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Wachano Guenet Church posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share