Hawassa Kale Heywet Local Churches Hibret Youth Ministry

Hawassa Kale Heywet Local Churches Hibret Youth Ministry ይህ ገፅ የሀ/ቃ/ሕ/አ/ቤተ/ክናት ኅብረት የወጣቶች አገልግሎት ነው።

29/04/2024
የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን 63ኛ ጠቅላላ ጉባኤከመጋቢት 24-27/2016 ዓ.ም በኩሪፍቱ ማዕከል።
05/04/2024

የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን 63ኛ ጠቅላላ ጉባኤ
ከመጋቢት 24-27/2016 ዓ.ም በኩሪፍቱ ማዕከል።

በኩሪፍቱ ማዕከል ላይ የተቃጣው ምንድር ነው?1. ማዕከሉ ህጋዊ የቃለ ሕይወት ይዞታ ነው። ካርታ፣ ፕላን አለው። በህጋዊ መንገድ የቦታ ግብር ይከፈልበታል። 2. ማዕከሉን በተሻለ ሁኔታ ለማልማ...
02/01/2024

በኩሪፍቱ ማዕከል ላይ የተቃጣው ምንድር ነው?

1. ማዕከሉ ህጋዊ የቃለ ሕይወት ይዞታ ነው። ካርታ፣ ፕላን አለው። በህጋዊ መንገድ የቦታ ግብር ይከፈልበታል።

2. ማዕከሉን በተሻለ ሁኔታ ለማልማት የግንባታ ፈቃድ በህጋዊ መንገድ ተሰጥቶ የባንክ ብድር ተፈቅዶ እየለማ ይገኛል።

3. የቢሾፍቱ ከንቲባ ጽ/ቤት ግንባታውን በሃይል እርምጃ አስቁሞአል። በዚህ ጊዜ አጥር ር ፈርሶ ስለነበር የማዕከሉ የምዕራብ አቅጣጫ አሁን አጥር የለውም።

4. የሁከት ይወገድልኝ ትዕዛዝ፣ የፍርድ ቤት ውሳኔን በመጣስ በድጋሚ ሠራተኞችን ጭምር በማሰርና በማስፈራራት ሥራው እንዲቆም ተደርጓል።

5. ይህ ሁሉ የሚሆነው ከማዕከሉ ዋነኛና ለግንባታ አመቺ የሆነውን ከ3 - 5 ሄክታር መሬት ለአንድ ግለሰብ ሆቴል እንዲሠራበት ቆርጦ ለመስጠት ነው።

ስለዚህ ሁላችን ይህን ድርጊት ልንቃወም ይገባል። ከየትኛውም የእምነት ተቋም ይዞታ ለሆቴል ተቆርጦ አይሰጥም። ይህ በቤተ ክርስቲያኒቱ ላይ የተቃጣ ጥቃት ነው። ሥፍራው የ12 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ንብረት ነው። ከአንድ ግለሰብ በላይ፣ ለትውልድ ትርፍና ጥቅም ያለው ነገር መገንባት እንችላለን።

💐💐የጌታ ፀጋ እና ሰላም ይብዛላችሁ! 💐💐👉 ለመላው የአ/ቤ/ክ/ህብረት የወ/አ ስራ አስፈፃሚዎች፣ የአጥቢያ ወጣት መሪዎች፣ አስተባባሪዎች እና ወጣቶች በሙሉ እንኳን ለ13ኛው የኢ/ቃ/ሕ/ቤ/ክ...
11/12/2023

💐💐የጌታ ፀጋ እና ሰላም ይብዛላችሁ! 💐💐
👉 ለመላው የአ/ቤ/ክ/ህብረት የወ/አ ስራ አስፈፃሚዎች፣ የአጥቢያ ወጣት መሪዎች፣ አስተባባሪዎች እና ወጣቶች በሙሉ እንኳን ለ13ኛው የኢ/ቃ/ሕ/ቤ/ክ የወጣቶች ሳምንት ክብረበዓል በሰላም አደረሳችሁ።
👉 በበዓሉ እና በቀጣይነትም ለተሃድሱ እንቅስቃሴዎች ወጣቶችን በማንቃት፣ በማስተማር፣ በመጸለይ እና በመመካከር የአስተምህሮ፣ የኑሮ፣ የስራ፣ የአገልግሎት... ተሃድሶ በቤተክርስቲያናችን እንዲሁም በሀገራችን የሚመጣበት ዘመን እንዲሆን ታላቅ ምኞቴ ጸሎቴም ነው።
መልካም በዓል ይሁንላችሁ!
አማኑኤል መ. የመሀል ደቡብ ቀጠና
የወጣቶች አገልግሎት ሰብሳቢ

ታላቅ የፆም ጸሎት ጥሪ"ዘመቻ ናቡቴ" 1ኛ ነገ 20፥1- 10
05/12/2023

ታላቅ የፆም ጸሎት ጥሪ
"ዘመቻ ናቡቴ" 1ኛ ነገ 20፥1- 10

ሻሎም!በጌታ የተወደዳችሁ በሐዋሳ ታቦር ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን ከጥር 30  ማለትም ከማክሰኞ ምሽት ጀምሮ እስከ የካቲት 5 ቀን 2015ዓ.ም ድረስ ልዩ መንፈሳዊ ኮንፍረንስ የተዘጋጀ ሲሆን...
02/02/2023

ሻሎም!በጌታ የተወደዳችሁ በሐዋሳ ታቦር ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን ከጥር 30 ማለትም ከማክሰኞ ምሽት ጀምሮ እስከ የካቲት 5 ቀን 2015ዓ.ም ድረስ ልዩ መንፈሳዊ ኮንፍረንስ የተዘጋጀ ሲሆን በተለይም የካቲት 1 እና 2 (ረቡዕና ሐሙስ ጠዋት ከ2:30--6:00 ) በሐዋሳና በዙሪያዋ በሚገኙ አብያተክርስቲያናት ለሚገኙ መጋቢያን ፣ወንጌላውያን ፣ መሪዎችና በተለያዩ የአገልግሎት ዘርፍ ለተሰማሩ ሁሉ የትምህርት ጊዜ ስለተዘጋጀ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት በቦታው በመገኘት የበረከቱ ተካፋይ እንድትሆኑ ተጋብዛችኋል።

Address

Selasi
Awassa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Hawassa Kale Heywet Local Churches Hibret Youth Ministry posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Place Of Worship

Send a message to Hawassa Kale Heywet Local Churches Hibret Youth Ministry:

Share