EECMY Referal Congregation Hawassa

EECMY Referal Congregation Hawassa ለወንጌል የምትኖር ቤተ-ክርስቲያን!!

ሰላም ይብዛላችሁ የጌታ ብሩካን! በቀን ነሐሴ 22/2018 ዓ ም ከቀኑ 11:00 ሰዓት ጀምሮ ከአጋፔ መዘመራን ጋር ልዩ የአምልኮ ምሽት የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን መካነ ኢየሱስ ሪፈ...
26/08/2026

ሰላም ይብዛላችሁ የጌታ ብሩካን! በቀን ነሐሴ 22/2018 ዓ ም ከቀኑ 11:00 ሰዓት ጀምሮ ከአጋፔ መዘመራን ጋር ልዩ የአምልኮ ምሽት የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን መካነ ኢየሱስ ሪፈራል ማህበር ምዕመናን ሀዋሳ በወጣቶች ፕሮግራም ላይ ተዘጋጅቶልናል።

ሁላችንም በጊዜ ተገኝተን ጌታንችን በአምልኮ እንድናወድሰው በጌታ በፍቅር ተጋብዛችኋል።

‎👉ሁልጊዜ አዳዲስና ትምህርታዊ, አስተማሪና ቁምነገር ያለውን መንፈሳዊ መረጃዎችን ለማግኘት ይህንን ( Page Like Follow share ) እያደረጋችሁ ተከታተሉን !!

የማህበር ምዕመናን ዲጂታል የወንጌል አገልግሎት ዘርፍ
👇
ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ከታች ያለው Page Follow በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ
https://tr.ee/VcHXkRfRGI
‎Facebook
https://www.facebook.com/share/1BX2xBEgrx/
‎YouTube
https://www.youtube.com/
‎Telegram
https://t.me/EECMYR70

ዉድ የጌታ ቤተሰቦች ነሐሴ 24/2018 ዓ ም የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን መካነ ኢየሱስ ሪፈራል ማህበር ምዕመናን ሀዋሳ የቤተክርስቲያናችን አገልጋይ የሆነው ዘማሪ ሻምበል እምባቆም ካ...
25/08/2026

ዉድ የጌታ ቤተሰቦች ነሐሴ 24/2018 ዓ ም
የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን መካነ ኢየሱስ ሪፈራል ማህበር ምዕመናን ሀዋሳ የቤተክርስቲያናችን አገልጋይ የሆነው ዘማሪ ሻምበል እምባቆም ካሴት ምረቃና የማህበር ምዕመናኗ የሚስዮን ቀን ምክንያት በማድረግ ልዩ የአምልኮና ቃል ጊዜ ተዘጋጅቷል።

በዕለቱ የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን መካነ ኢየሱስ ልደታ ማህበር ምዕመናን አዲስ አበባ በቃል ቄስ እንዳሻው ተፈረደኝ እና በዝማሬ " ሀ" መዘምራን ያገለግሉናል።

በዕለቱ :- የእግዚአብሔር ቃል ይሰበካል
:- በዝማሬ ጌታ ይወደሳል
:- የሚስዮን ቀን ይከበራል ለወንጌል ማህበሪተኝነት ድጋፍ ይደረጋል።
በጌታ የተወደዳችሁ ቅዱሳን ኑ አበረን ጌታችን እናመልክ ሁላችሁንም ተጋብዛችኋል።

‎👉ሁልጊዜ አዳዲስና ትምህርታዊ, አስተማሪና ቁምነገር ያለውን መንፈሳዊ መረጃዎችን ለማግኘት ይህንን ( Page Like Follow share ) እያደረጋችሁ ተከታተሉን !!

የማህበር ምዕመናን ዲጂታል የወንጌል አገልግሎት ዘርፍ
👇
ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ከታች ያለው Page Follow በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ
https://tr.ee/VcHXkRfRGI
‎Facebook
https://www.facebook.com/share/1BX2xBEgrx/
‎YouTube
https://www.youtube.com/
‎Telegram
https://t.me/EECMYR70

የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ 22ኛው መደበኛ የካውንስል ስብሰባ ከዚህ በታች በተዘረዘሩት የአገልግሎት መደቦች መሪዎችን በመምረጥ በስኬት ተጠናቋል። 1. ቄስ ታምራት ታ...
22/08/2026

የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ 22ኛው መደበኛ የካውንስል ስብሰባ ከዚህ በታች በተዘረዘሩት የአገልግሎት መደቦች መሪዎችን በመምረጥ በስኬት ተጠናቋል።

1. ቄስ ታምራት ታደለ የቤተ ክርስቲያኒቱ ጠቅላይ ጸሐፊ፤
2. ቄስ ወንድማገኝ ኡዴሳ የምሥራች ድምጽ ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ዳይሬክተር፤
3.ቄስ ታገሰች ዳኘው የሴቶች አገልግሎት መምሪያ ዳይሬክተር፤
4. አቶ ጋሉንዴ ዋኬታ የእስቲዋርድሽፕና ቸርች ኤኮኖሚ መምሪያ ዳይሬክተር፤
5. ወጣት ኤፍሬም ታሪኩ የልጆችና ወጣቶች መምሪያ ዳይሬክተር፤ በመሆን ለቀጣይ አራት አመታት ቤተ ክርስቲያኒቱን የሚያገለግሉ ይሆናል።

የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ ለተመረጡት መሪዎች መልካም ምኞቷን እየገለጸች ለአገልግሎታቸው ስኬት ትጸልያለች!

የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ ፕሬዚዳንት ቄስ ዶ/ር ዮናስ ይገዙ ለ22ኛው የቤተ ክርስቲያኒቱ ካውንስል የመክፈቻ መርሐ ንግግር (Keynote Address) አቅርበዋል። ...
19/08/2026

የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ ፕሬዚዳንት ቄስ ዶ/ር ዮናስ ይገዙ ለ22ኛው የቤተ ክርስቲያኒቱ ካውንስል የመክፈቻ መርሐ ንግግር (Keynote Address) አቅርበዋል።
*** *** ***
ባሳለፍነው አንድ አመት እግዚአብሔር ያደረገልንን ምህረት ከ13 ሚልየን በላይ ከሚሆኑ ምዕመናን ጋር መለስ ብለን በምስጋና እናስባለን በማለት ፕሬዚዳንቱ አመስግነዋል። ይችም ከዓለም ሉተራዊያን አብያተ ክርስቲያናት በሁሉም ረገድ በቀዳሚነት የምትጠቀሰው ቤተ ክርስቲያናችን ለሌሎች ምሳሌ በምትሆንበት እና ተጽዕኖ መፍጠር በምትችለበት ቁመና ላይ እንደምትገኝ ገልጸዋል።

በአሁኑም ጊዜ ቤተ ክርስቲያኒቱ ከቆመችበት እውነት ያፈነገጡ ትምህርቶችና ልምምዶች የሚስተዋሉበት ከመሆኑ ጋር ተያይዞ፤ እነዚህን ጉዳዮች ለመከላከል እና ለማስቆም የሚያስችል የሥነ ቤተ ክርስቲያን አሰራሮች እንዲቀየሱ ጠቁመዋል።

ፕሬዚዳንቱም በሁለት ቋንቋዎች ባቀረቡት ሰፊ መርሐ ንግግር ባለፉት አስር ዓመታት የታየውን የቤተ ክርስቲያኒቱን ፈጣን እድገት አስቀምጠዋል። በዚህም መሰረት ባለፉት 10 ዓመታት ከ5 ሚሊየን በላይ ምዕመናን የተጨመሩ ሲሆን ከ4 ሺህ በላይ ማኅበራነ ምዕመናን ተተክለዋል። ከዚህም በተጨማሪ 19 ተጨማሪ ሲኖዶሶች ተመሥርተው የአገልግሎት ተደራሽነት ዕድገት በቤተ ክርስቲያኒቷ በጉልህ ተመዝግቧል። ለዚህም ስኬት ከሁሉ በላይ እግዚአብሔርን፤ በመቀጠል የቤተ ክርስቲያኒቱን መሪዎችና አገልጋዮችን በሙሉ ያመሰገኑ ሲሆን፤ እድገቱ በሁሉም አቅጣጫ የተማከለ እንዲሆን በትኩረት ሊሰራበት እንደሚገባ አሳስበዋል።

ከዚህም ጋር በተያያዘ ለዘብተኝነት (ሊብራሊዝም) ሃይማኖታዊ ሥርዓቶችን እንዲሁም ዶግማዎችን የሚገዳደሩበት ጊዜ ላይ ስላለን፤ በቤተ ክርስቲያኒቱ የሉተራዊነት ማዕቀፍ ውስጥ ቤተ ክርስቲያን ራስዋን ለተቀረው አለም የምትገልጽበት እና ያላት ሥነ መለኮታዊ ማንነቷን በምርመራዊ ጥናት መሠረት እንዲሰራ ምክረ ሀሳብ ለግሰዋል።

በቀጣይ ዘመናትም ቤተ ክርስቲያኒቱ ሁለንተናዊ አገልግሎትን በስፋት ለመስጠት የሚያስችሏትና የቤተ ክርስቲያኒቱን ነባራዊ ሁኔታ ያገናዘበ የደንብ ማሻሻያ እንዲደረግ፤ በቤተ/ክን ደረጃ ሀገራዊ የሰላም ግንባታ ሥራ በኮምሽን መልክ ተጠናክሮ እንዲቀጥል አቅርበዋል። አክለውም የቤተ ክርስቲያኒቱን ኢኮኖሚ ለማሳደግ የሚጠቅሙ ረቂቅ ሀሳቦች ተጠንተው ሊተገበሩ በሚችሉበት ይዘት በምክረ ሃሳብ መልክ ጠቁመዋል።

በዚሁም መሰረት መርሐ ንግግሩን ያደመጠው ካውንስል በሰፊው ከመከረ እና ውሳኔዎችን ካስተላለፈ በኋላ በሙሉ ድምጽ በምስጋና ተቀብሏል።

የቤተ ክርስቲያኒቱ የቀድሞ የክብር ፕሬዚዳንት ቄስ ኢተፋ ጎበና እና የቀድሞ ጠቅላይ ​ጸሐፊ ቄስ ዶ/ር መገርሳ ጉታ ለተከበረው የ22ኛው የቤተ ክርስቲያኒቱ ካውንል ሰላምታ አቅርበዋል። ቄስ ኢ...
18/08/2026

የቤተ ክርስቲያኒቱ የቀድሞ የክብር ፕሬዚዳንት ቄስ ኢተፋ ጎበና እና የቀድሞ ጠቅላይ ​ጸሐፊ ቄስ ዶ/ር መገርሳ ጉታ ለተከበረው የ22ኛው የቤተ ክርስቲያኒቱ ካውንል ሰላምታ አቅርበዋል።

ቄስ ኢተፋም በሰላታ ንግግራቸው መካነ ኢየሱስ እጅግ እያደገች እንደሆነ የገለጹ ሲሆን በዚህ መብዛቱ ከቤተ ክርስቲያን ብዙ እንደሚጠበቅ አሳስበዋል። ካውንስሉ መልካም እና ውጤታማ እንዲሆን መልካም ምኞታቸውን አስተላልፋዋል።

ቤተ ክርስቲያን አገልግሎትዋን የምትመራው በመጽሐፍ ቅዱስ እና በቤተ ክርቲያኒቱ መተዳደሪያ ደንብ እንደሆነ የገለጹት ቄስ ዶ/ር መገርሳ፤ የመሰረተ እምነትና የደንብ ጉዳይ የዚህ ካውንስል አጀንዳ እንዲሆን አሳስበዋል። ቤተ ክርስቲያንም በታሪክ አጋጣሚ ለብዙዎች ምሳሌ የሚሆን አሰራር እና መመሪያን ከትውልድ ወደ ትውልድ ማሸጋገሯን አስታውሰዋል።

‎👉ሁልጊዜ አዳዲስና ትምህርታዊ, አስተማሪና ቁምነገር ያለውን መንፈሳዊ መረጃዎችን ለማግኘት ይህንን ( Page Like Follow share ) እያደረጋችሁ ተከታተሉን !!

የማህበር ምዕመናን ዲጂታል የወንጌል አገልግሎት ዘርፍ
👇
ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ከታች ያለው Page Follow በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ
https://tr.ee/VcHXkRfRGI
‎Facebook
https://www.facebook.com/share/1BX2xBEgrx/
‎YouTube
https://www.youtube.com/
‎Telegram
https://t.me/EECMYR70

የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ጠቅላይ ጸሐፊ ፓስተር ዶ/ር ጌትነት ለማ የመካነ ኢየሱስ ቤተ ክርስቲያን ትልቅ ተፅዕኖ ያሳረፉ ውሳኔዎችን በማሳለፍ የታወቀች አንጋፋ ...
18/08/2026

የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ጠቅላይ ጸሐፊ ፓስተር ዶ/ር ጌትነት ለማ የመካነ ኢየሱስ ቤተ ክርስቲያን ትልቅ ተፅዕኖ ያሳረፉ ውሳኔዎችን በማሳለፍ የታወቀች አንጋፋ ቤተ እምነት ናት በማለት ተናገሩ።

ነሐሴ8 ቀን 2018 ዓ.ም በኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ 22ኛ የካውንስል ስብሰባ አካሄዷል። በስብሰባዉ ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ጠቅላይ ጸሐፊ ፓስተር ዶ/ር ጌትነት ለማ መልእክት ያስተላለፋ ሲሆን በመልክታቸዉም የመካነ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን በረጅም የአገልግሎት ዘመኗ በአገርና በዓለም አቀፍ ደረጃ ትልቅ ተፅዕኖ ያሳረፉ ውሳኔዎችን በማሳለፍ የታወቀች አንጋፋ ቤተ እምነት ናት። ለዛሬው ሁለንተናዊ እድገት የቀደሙ መሪዎች ያበረከቱት አስተዋጽዖ ከፍተኛ ነበር። ያሉት ጠቅላይ ፀሐፊዉ ዛሬም ቢሆን ከትውልድ፣ ከአገርና ከሁሉ በላይ ከእግዚአብሔር የተሰጣትን ታላቅ መለኮታዊ አደራ በታማኝነት መወጣት ይጠበቅባታል። ብለዋል የዛሬዎቹ መሪዎች ትላንትን በማስታወስ፣ ዛሬን በታማኝነት በማገልገል እና ነገን መሠረት በሚጥል ራዕይ በመመልከት ዋናውን ነገር ዋና አድርገው መቀጠል አለባቸውም በማለት አክለዋል።

ለኢቫንጀሊካል ዜና ሩት ዋቅጅራ

የኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካውንስል
የወንጌል አማኞች ድምፅ

የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ 22ኛው መደበኛ የካውንስል ስብሰባ ዛሬ ማለዳ በጸሎት መርሃግብር ተጀምሯል።***  ***  ***በትንቢተ ኤርሚያስ 6፥16 “የቀደመችውንም ...
18/08/2026

የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ 22ኛው መደበኛ የካውንስል ስብሰባ ዛሬ ማለዳ በጸሎት መርሃግብር ተጀምሯል።
*** *** ***
በትንቢተ ኤርሚያስ 6፥16 “የቀደመችውንም መንገድ ፈልጉ” የሚለውን ጥቅስ መሪ ቃል ያደረገው የቤተ ክርስቲያንቱ 22ኛ መደበኛ የካውንስል ስብሰባ፤ ዛሬ በጉዲና ቱምሳ ሁለገብ የስልጠና ማዕከል ጅማሬውን አድርጓል። ስብሰባውም ለቀጣይ ዓራት ቀናት እስከ ነሐሴ 16 ቀን 2018 ዓ.ም የሚቀጥል ሲሆን በርካታ ጉዳዮችን እንደሚዳስስ ይታመናል።

በማለዳውም የጸሎት መርሃገብር፤ በመሪ ጥቅሱ መሰረት የእግዚአብሔር ቃል ትምህርት፤ በካየር አገልግሎትም ዝማሬዎች የቀረቡ ሲሆን፤ ከቤተ ክርስቲያኒቱ ሲኖዶሶች በተነሱ የጸሎት ጥያቄዎች ዙሪያ በጋራ ተጸልዬአል። በጸሎቱም የቤተ ክርስቲያንን አንድነት፤ የሀገራችንን ሰላም፤ በመካሄድ ላይ የሚገኘውን አገራዊ የምክክር ጉባኤው፤ በወንጌል ማዳረስ አገልግሎት እና ሌሎች ተጨማሪ አርዕስቶች ዙሪያ ጸሎት ተደርጓል።

በመደበኛ የስብሰባ ጊዜውም ካውንስሉ ባለፉት 12 ወራት የተከናወኑ ተግባራትንና ያጋጠሙ ተግዳሮቶችን ከሚቀርበው መርሃ ንግግርና ሪፖርቶች አድምጦ የሚመክር እና ውሳኔዎችን የሚያስተላልፍ ይሆናል።

የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን መካነ ኢየሱስ ሪፈራል ማህበር ምዕመናን ሀዋሳ   ================================== ነሐሴ 6/2018 ዓ.ም  የሪፈራል መካነ ኢየሱስ ...
18/08/2026

የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን መካነ ኢየሱስ ሪፈራል ማህበር ምዕመናን ሀዋሳ
==================================
ነሐሴ 6/2018 ዓ.ም የሪፈራል መካነ ኢየሱስ ማህበረ ምዕመናን ሀዋሳ

ርዕሰ ወደ ሰማያዊ ርስታችን በታላቅ ናፍቆትና በጽናት እንጓዝ! በሚል ርዕሰ የሪፈራል መካነ ኢየሱስ ማህበረ ምዕመናን ሀዋሳ
አገልጋይ ወንድም ዳዊት ኩሲያ በመዝ 84:1-7 ላይ ያለዉን የእግዚአብሔር ቃል መሰረት አድርጎ አስተምሯል ።

ወደ እግዚአብሔር ቤተመቅደስ/ወደጽዮን የሚደረግ ጉዞን በተመለከተ በዋሽንት የተዘመረ የቆሬ ልጆች መዝሙር ነው፡፡

መዝሙሩ የጽዮን ተጓዦች ለጉዞ ከመነሳታቸው በፊት በውስጣቸው ያለው ናፍቆት እና ከፍተኛ ገጉት፣ ጉዞ ከጀመሩ በኋላ በመንገዳቸው የሚያጋጥማቸው አስቸጋሪ ሁኔታ እና በመጨረሻ ወደ እግዚአብሔር ቤት ሲደርሱ የሚያገኙት ደስታ እና የነፍስ እርካታ ምን እንደሚመስል ይገልፃል፡፡

በጽዮን ወደሚገኘው ቤተመቅደስ ከሚወስዱ መንገዶች መካከል ዋነኛው እና አብዛኛው መንገደኞች የሚጠቀሙት "ባካ ሸለቆ" (ለቅሶ ሸለቆ) ተብሎ በሚጠራው ሥፍራ ውስጥ የሚያልፈውን መንገድ ነው፡፡
መንገዱ እጅግ አስቸጋሪ በሆነ መልክዓ ምድር የሚያልፍ በመሆኑ፣ ውሃ የሌለበት እና ደረቅ ቦታ በመሆኑ ከነበረው ከባድ ሁኔታ የተነሳ ተጓዦች የሚጓዙት በብዙ ፈተና እና ለቅሶ ነው፡፡
የዮሐንስ ወንጌል 3፡3፣ 1ኛ ጴጥ 1፡3-5፣ 1ኛ ጴጥ 2፡25
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ሞቶ እኛን አዳነን፡፡ እኛ በስሙ አምነን በመንፈስ ዳግመኛ የተወለድን የእግዚአብሔር ልጆች ነን፡፡

በክርስቶስ አምነን ለዳንን እና የእግዚአብሔር ልጆች የማይጠፋ ርስት/የዘላለም መኖሪያ በሰማይ ተይዞልናል/inheritance that doesn''t fade away, reserved in Heaven for you/.
ነፍሳችን ከነበረችበት የመቅበዝበዝ መንገድ ተመልሳ እና አዳኟን/እረኛዋን አውቃ ዕረፍትን አግኝታለች፡፡
አማኞች በክርስቶስ ሞት እና ትንሣኤ የተዘጋጀላቸውን የክብር ርስት ለመውረስ የተጠሩ እና ወደዚያ ክብር በጉዞ ላይ ያሉ ሰዎች ናቸው፡፡

መዝ 84፡6፣ መዝ 23፡ 1-6
እግዚአብሔር/እረኛችን ለምን በሸለቆ መንገድ ይመራናል?
1ኛ) ሊያስተምረን፤ ሊቀርፀን እና በመንፈሳዊ ሕይወታችን እንድንጠነክር ወዶ ነው፡፡
መዝ 84፡6፣ መዝ 119፡71፣ ኢዮብ 36፡22
ጌታ እግዚአብሔር ልጆቹን ለማስተማር እና በእምነታቸው ጠንካራ እንዲሆኑ ከመፈለግ ውጪ ሆን ብሎ ለመጣል ወይም ለማሳዘን ብሎ በሸለቆ መንገድ አይመራም ወይም አያስጨንቅም፡፡ የእርሱ ዓላማ ሳይገባን ቀርቶ ብናዝን እንኳ እንደገና ይራራልናል፡፡

2ኛ) በእርሱ እንድንታመን እና እንድንደገፍ
መዝ 84፡5
በሕይወት መንገድ ስንጓዝ ችግርን እና ስቃይን፣ ህመምን፣ መገፋትን እና መውደቅን ፈጽሞ እንዳናይ ሳይሆን በእነዚህ አስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ ስናልፍ እግዚአብሔር ብቸኛ ረዳታችን እረኛችን እንደሆነ አውቀን ወደ እርሱ እንድንመለከትና በእርሱ እንድንታመን ፈቅዶ ነው።

3ኛ) ሊባርከን እና ወደ ደስታው ሊያስገባን ሲፈልግ
መዝ 84፡6፣ 2ኛ ነገ 3፡16-17
ሸለቆ የመከራ፣ የሃዘን እና የለቅሶ ቦታ ብቻ አይደለም፡፡ የበረከት ቦታ እንዲሁም ወደ ቀጣዩ የበረከት እና ክብር ስፍራ የምናልፍበት ቦታ ነው፡፡

ዮሴፍ በገዛ ወንደሞቹ ጉድጓድ ውስጥ ሲጣል እና በጳጥፌራ ሚስት በሃሰት ተከሶ ወህኒ ሲጣል ወደ ፌርዖን ቤተመንግስት መሄጃ መንገድ ሆኖለት ነበር፡፡ ዳንኤልም የተጣለበት ጉድጓድ መጥፊያው ሳይሆን ወደ ፋርስ እና ቂሮስ መንግስት ከፍታ ሥፍራ መውጫ መንገድ ሆኖለት ነበር፡፡

መንገዱን እንዴት እንጓዝ?
1ኛ) በታላቅ ጉጉት እና ናፍቆት
መዝ 84፡ 1-2፣ መዝ 42፡1-3፣ ኢዮብ 19፡ 25-27
በእግዚአብሔር መገኛ ቦታ መሆን እጅግ ያጓጓል፡፡
ይህች ምድር መኖሪያችን አይደለችም፡፡ እኛ እንግዶች/«የሰው አገር ሰው»/ ነን፡፡ እውነተኛው ሰማያዊ አገራችን ሁልጊዜ ሊናፍቀን ይገባል፡፡

የምንጠብቃት አዲስቱ ኢየሩሣሌም አልኖርንባትም፡፡ ነገር ግን በእምነት አይተናታል፡፡ (ራዕይ ምዕ 21 እና 22) በእምነት ስለምናውቃት ዘወትር ትናፍቀናለች፡፡
ዕብ 13፡14፣ ፊልጵ 3፡20፣ 2ኛ ጴጥ 3፡8፣ ያዕ 4፡14
ምድር ላይ የምንኖረው ጊዜ በጣም ጥቂት ነው፡፡ እንግዶች ስለሆንን ዘላለማዊ ቤታችን ይናፍቀናል፡፡
እንግድነት ካልተሰማን እና የዓለም ሰዎች አኗኗር እና አካባቢያቸውን ለምደን ምቾት ከሰጠን ራሳችንን መጠየቅ አለብን፡፡ ከየትኛው አገር ነኝ?

2ኛ) ሁልጊዜ በማሰብ
መዝ 84፡5፣ ቆላ 3፤2
በልቡ ወደ ጽዮን የሚወስደውን መንገድ የሚያስብ ሰው የተባረከና የተመሰገነ ነው።
ዘወትር ሊያሳስበን የሚገባው የማይሞላው የዚህ ምድር ኑሮ፣ ቁሳዊ ፍላጎቶች እና የጊዜያዊ ደስታ ማግኛ መንገዶች ሳይሆኑ የሰማዩ መንግስት ሊሆን ይገባል፡፡

3ኛ) እስከመጨረሻው በጽናት
መዝ 84፡ 7፣ ምሳሌ 4፡18፣ ዳንኤል 12፥13. ዕብ 10:38-39፣ ራዕ 21፡7
ክርስቲና ወደፊት የመሄድ/የመጓዝ ሕይወት ነው፡፡ ጉዞው ከቆመ ወይም ወደኋላ ከሆነ አደጋ አለው! ጉዞውን ከሌሎች ጉዞዎች ለየት የሚያደርገው ወደፊት በተራመድን ቁጥር እየደከምን ሳይሆን ሃይልን እያገኘን መሄዳችን ነው፡፡

አማኝ እረኛውን ተከትሎ እስከመጨረሻው ይጓዛል፡፡ በሸለቆ ርዝመትና ጥልቀት አይፈራም፤ እረኛውን ተጠራጥሮ ወደኋላ አይመለስም፡፡ ካፈገፈገ/ወደኋላው ከተመለሰ ከሚጠፉት አንዱ ይሆናል፡፡

በመጨረሻ
መዝ 84፡7፣ ራዕ 21፡4
በጉዞአችን መጨረሻ የምንገባባት ቅድስቲቱ ከተማ፣ በአዲሲቱ አየሩሳሌም በመንገዳችን የገጠመን ስቃይ፣ ሃዘን፣ መከራ፣ ለቅሶ እና የሞት ፍርሃት ሁሉ ዳግም የማናይባት፣ ሁሉም ዓይነት እንባችን ከሁሉም ፊት ዳግም ላይታይ ለመጨረሻ ጊዜ የሚታበስበት ርስታችን ነች፡፡

ወደፊት የሚያራምደን የእርሱ ሃይል ነው፡፡ የመንገዱ ርዝመትና አስቸጋሪነት ቢያስለቅሰንም ቢያደክመንም ወደ ዕረፍት የሚያደርሰን በቂ ሃይል እና ፀጋ አለው፡፡ የእርሱን ሃይል በድካማችን እየገለፀ ብርታቱን እየጨመረልን ወደፊት ያስኬደናል፡፡
የምንጓዘው ወደ ዘላለም ዕረፍት፣ ደስታ እና ክብር ነው፡፡

‎👉ሁልጊዜ አዳዲስና ትምህርታዊ, አስተማሪና ቁምነገር ያለውን መንፈሳዊ መረጃዎችን ለማግኘት ይህንን ( Page Like Follow share ) እያደረጋችሁ ተከታተሉን !!

የማህበር ምዕመናን ዲጂታል የወንጌል አገልግሎት ዘርፍ
👇
ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ከታች ያለው Page Follow በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ
https://tr.ee/VcHXkRfRGI
‎Facebook
https://www.facebook.com/share/1BX2xBEgrx/
‎YouTube
https://www.youtube.com/
‎Telegram
https://t.me/EECMYR70

የኢ/ወ/ቤ/ክ/መካነ ኢየሱስ የልጆች በዓል ሳምንትነሐሴ 11-17/2018ዓ.ም መሪ ጥቅስ: ''ልጅን በሚሄድበት መንገድ ምራው፥ በሸመገለም ጊዜ ከእርሱ ፈቀቅ አይልም።'' ምሳሌ 22:6ርዕስ: ...
17/08/2026

የኢ/ወ/ቤ/ክ/መካነ ኢየሱስ የልጆች በዓል ሳምንት
ነሐሴ 11-17/2018ዓ.ም

መሪ ጥቅስ: ''ልጅን በሚሄድበት መንገድ ምራው፥ በሸመገለም ጊዜ ከእርሱ ፈቀቅ አይልም።'' ምሳሌ 22:6

ርዕስ: ''ጠንካራ ቤተሰብ: ስኬታማ ትውልድ''

በሁሉም ማኀበራነ ምዕመናን
*

የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ ለ15 አገልጋዮች የቅስና ሃላፊነት ሰጠች።*** የቤተ ክርስቲያኒቱን የቃል እና የቅዱሳት ሚስጥራት አገልግሎት እንዲያግዝ ለ15 አገልጋዮች ...
17/08/2026

የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ ለ15 አገልጋዮች የቅስና ሃላፊነት ሰጠች።
***
የቤተ ክርስቲያኒቱን የቃል እና የቅዱሳት ሚስጥራት አገልግሎት እንዲያግዝ ለ15 አገልጋዮች የቅስና ሀላፊነት የመስጠት ሥነ ሥርዓት በጀሞ ቤቴል ማህበረ ምዕመናን በትላንትናው ዕለት ተካሂዷል።

እጩ ቀሳውስቱም ከማዕከላዊ ደቡብ ኢትዮጵያ፣ኢሉባቦር ቤቴል፣ ከደቡብ፣ ከጅማ ቤቴል፣ ከአዲስ አበባ እና ከፊንፊኔና አከባቢው እጩ ቤቴል ሲኖዶሶች የመጡ ናቸው።

ቅስና የመስጠት ሥነ ሥርዓቱን የቤተ ክርስቲያኒቱ ፕሬዚዳንት ቄስ ዶ/ር ዮናስ ይገዙ የመሩና ሀላፊነቱንም ሰጡ ሲሆን፤ የቤተ ክርስቲያኒቱ ምክትል ፕሬዚዳንት ቄስ ዶ/ር ታሪኩ ቶሎሳን ጨምሮ በመርሃግብሩ እጩ ቀሳውስትን የላኩ ሲኖዶስ ፕሬዚዳንቶች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

በዚህም መልክ በርካታ ሲኖዶሶች ቀሳውስትን በጋራ የማቀሰስ የቀድሞ ልማድን ያስታወሰ ሥነ ሥርዓት እንደነበር የተገለፀ ሲሆን በጋራ አገልጋዮችን የማሰማራት ምሳሌ ሆኖ የተስተዋለት የማቀሰስ መርሃግብር ነበር።

ለእረኝነት አገልግሎቱ አገልጋዮችን የጨመረልን የእግዚአብሔር ስም ብሩክ ይሁን!

Address

Referal Mekanyesus
Awassa
REFERALMEKANYESUS

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when EECMY Referal Congregation Hawassa posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Place Of Worship

Send a message to EECMY Referal Congregation Hawassa:

Shortcuts

Share