One lord one faith one baptism

One lord one  faith one baptism One lord

27/05/2026

#መጽሐፍ ቅዱስ ስናገር ! ኃያል አምላክ፥ የዘላለም አባት....ተብሎ ይጠራል!! #በብሉይ ኪዳን የትንቢት መጻሕፍት ውስጥ እጅግ ጎልቶ ከሚታየውና በክርስትና እምነት ውስጥ ትልቅ ሥነ-መለኮታዊ ትርጉም ካላቸው ጥቅሶች አንዱ ነው። ጥቅሱ የሚገኘው በ**ትንቢተ ኢሳይያስ 9፥6** ላይ ሲሆን፣ ሙሉ ቃሉ እንዲህ ይላል፦ #ሕፃን ተወልዶልናልና፥ ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልና፤ አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል፤ ስሙም ድንቅ መካር፥ ኃያል አምላክ፥ የዘላለም አባት፥ የሰላም አለቃ ተብሎ ይጠራል።

#ይህ ጥቅስ ስለሚመጣው መሲሕ (ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ) የተነገረ ትንቢት ሲሆን፣ ስለ ልጁ ማንነትና ስለሚሰጡት መለኮታዊ ስሞች ሰፋ ያለ ማብራሪያ እንደሚከተለው ቀርቧል፦
1. "ሕፃን ተወልዶልናልና፥ ወንድ ልጅም ተሰጥቶናል" (የሥጋዌ ምስጢር) ነቢዩ ኢሳይያስ ትንቢቱን ሲጀምር ሁለት ነገሮችን ያጣጥማል፦ "ሕፃን መወለድ" እና "ወንድ ልጅ መሰጠት። ፦ ይህ የሚያሳየው መሲሑ ፍጹም ሰው ሆኖ፣ እንደ ማንኛውም ሕፃን ከሴት እንደሚወለድና ሰብአዊ አካልን እንደሚለብስ ነው (ሰብአዊነቱን ወይም Humanity ያሳያል)።
#ወንድ ልጅ #ተሰጥቶናል፦ይህ ደግሞ ከአምላክ ዘንድ የተሰጠ ስጦታ መሆኑንና እርሱ ቀድሞውኑ የነበረ የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑን ያመለክታል (መለኮትነቱን ወይም Divinity ያሳያል)።

2. ሰባቱ መለኮታዊ ስሞችና ማብራሪያቸው በዚህ ጥቅስ ውስጥ ለሚወለደው ልጅ የተሰጡት ስሞች ተራ መጠሪያዎች ሳይሆኑ፣ የእርሱን ማንነት፣ ባሕርይና መለኮታዊ ሥልጣን የሚገልጡ ናቸው፦
👉 ድንቅ (Wonderful) በመጽሐፍ ቅዱስ አገላለጽ "ድንቅ" የሚለው ቃል ከሰው አእምሮና ማስተዋል በላይ የሆነን መለኮታዊ ነገር ለመግለጽ ይሠራበታል። ለምሳሌ በLayout መጽሐፍ (መሳፍንት 13፥18) ላይ የአምላክ መልአክ ለማኑሄ "ስሜ ድንቅ ነውና ስለ ምን ትጠይቃለህ? እንዳለው ሁሉ። የኢየሱስ አወላለድ፣ ሕይወቱ፣ ተአምራቱና ትንሣኤው ፍጹም "ድንቅ" ነው።
👉 መካር (Counselor) እርሱ ፍጹም ጥበብና እውቀት የሞላበት፣ ሰዎችን ወደ እውነት የሚመራና በሕይወታቸው ውስጥ መለኮታዊ ምክርን የሚሰጥ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ "የጥበብና የእውቀት መዝገብ ሁሉ በእርሱ ውስጥ ተሰውሯል" ይላል ቆላስይስ 2፥3
👉 ኃያል አምላክ (Mighty God) ይህ ስም የሚወለደው ሕፃን ተራ ነቢይ ወይም መሪ ሳይሆን፣ ፍጹም አምላክ መሆኑን በግልጽ ያሳያል። እዚህ ላይ “ኃያል አምላክ” (El Gibbor) የሚለው የአምላክ መጠሪያ ለልጁ ተሰጥቷል። በአዲስ ኪዳንም ሐዋርያው ቶማስ ኢየሱስን "ጌታዬ አምላኬም" ብሎታል። (ዮሐንስ 20፥28)።
👉 የዘላለም አባት (Everlasting Father) ይህ ስም ብዙ ጊዜ ሰዎችን ግራ ሊያጋባ ይችላል (በሥላሴ አስተምህሮ ወልድ እንዴት አባት ይባላል? በሚል)። ነገር ግን በዚህ በትንቢት ክፍል ውስጥ "የዘላለም አባት" መባሉ የሥላሴ አካላትን ለማቀላቀል ሳይሆን የሚከተሉትን ነገሮች ለማሳየት ነው፦
💙 የዘላለም ምንጭ መሆኑን፦ እርሱ ፍጥረት ሁሉ ከመኖሩ በፊት የነበረ፣ የዘላለም ባለቤትና ጅማሬ የሌለው መሆኑን ለማሳየት።
💙 አባትነቱን (ባሕርዩን) ለማሳየት፦ ለሕዝቡና ለሚያምኑበት ሁሉ አባት ለልጆቹ እንደሚያደርገው ዓይነት ፍጹም ጥበቃ፣ እንክብካቤ፣ አፍቃሪነትና መጋቢነትን የሚያሳይ መሆኑን ለመግለጽ ነው።
💙 የሰላም አለቃ (Prince of Peace) በሰውና በእግዚአብሔር መካከል፣ እንዲሁም በሰውና በሰው መካከል ያለውን የጥል ግድግዳ አፍርሶ እውነተኛ ሰላምን የሚሰጥ እርሱ ነው። ኢየሱስ ራሱ *"ሰላምን እተውላችኋለሁ፥ ሰላሜን እሰጣችኋለሁ፤ እኔ የምሰጣችሁ ዓለም እንደሚሰጥ አይደለም" ብሏል (ዮሐንስ 14፥27)።
💙 አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል ይህ ደግሞ የእርሱን የዘላለም ንጉሥነትና ገዥነት ያሳያል። ምድራዊ ነገሥታት ሥልጣናቸውን በሰይፍና በኃይል በሌሎች ላይ ሲጭኑ፣ የእርሱ አለቅነትና መንግሥት ግን በራሱ ትከሻ (ጫንቃ) ላይ የተሸከመው፣ በራሱ መስዋዕትነት የመጣ የፍቅርና የጽድቅ መንግሥት ነው። መንግሥቱም አያልቅም (ሉቃስ 1፥33)።

#ማጠቃለያ ኢሳይያስ 9፥6 ላይ የተጠቀሰው "የልጁ ስም" እርሱ በሥጋ የተገለጠው፣ ሰላምን ያመጣው፣ የዘላለም አባትነት አፍቃሪ ባሕርይ ያለውና ፍጹም ኃያል አምላክ የሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ መሆኑን የሚያረጋግጥ ታላቅ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረት ነው።
#ሸር ማድረግ እንዳይረሳ ከዚህ ትምህርት ብዙ ነገር እንደተረዳችሁት አስባለሁ።

25/05/2026

Enjoy the videos and music that you love, upload original content and share it all with friends, family and the world on YouTube.

25/05/2026

✿ ራስን መግዛት ✿

በመፀሐፍ ቅዱስ እይታ ራስን መግዛት ማለት ከስጋ ሀሳብ ጋር ትግል ማድረግ ማለት ነው፡፡
እስኪ የስጋ ፍሬ የምንላቸውን እንይ
ዝሙት ፣ ርኩሰት፣ መዳራት ፣ ጣኦትን ማምለክ ፣ ምዋርት ፣ ጥል ፣ ክርክር ፣ ቁጣ ፣ አድመኝነት ፣ መለያየት ፣ መናፍቅነት ፣ ምቀኝነት ፣ መግደል ፣ ስካር ፣ ዘፋኝነት
☝️☝️☝️☝️
እነዝህ ሁሉ አንድ በአንድ ብናያቸው ራስን ባለመግዛት የሚመጡ የስጋ ፍሬዎች ናቸው፡፡ በመንፈስ ፍሬዎች ፈታኙ የትዕግል ምዕራፍ እና ፊት ለፊት ወደ ግብግብ ከስጋ ጋር ምንገጥመው ራስን የመግዛት ወቅት ነው፡፡
ይህ ግዜ አስቸጋሪው የመንፈስ ፍሬዎች ሁሉ መለኪያነው፡፡ ለዛም ነው ራስን መግዛት ለመንፈስ ፍሬዎች መጨረሻ የሆነው፡፡
የአገልግሎታችንን ልክ የትዕግስታችንን መጠን የፍቅራችንን እና የመዋደዳችን መለኪያው ራስን መግዛት ነው፡፡
በተለይም ክርስቲያን በነገሮች ራሱን ካልገዛ አደጋ ላይ ነው፡፡

ለምሳሌ፦ በቤተክርስቲያን ውስጥ ከወንድም ከእህቶች ጋር ባለን የአገልግሎት ግኑኝነቶች ላይ፡፡ በመክሊት ፣ በተለያዩ አገልግሎቶች አለመግባባቶች ቢፈጠሩ የሃሳብ ግጭት ቢፈጠር በራሳችን ችግር ከቤተክርስቲያን ብንገፀፅ ስለ ወንድሞች መጥፎ ወሬ ብንሰማ የዘር ልዩነት ቢኖር ፀባይን ከፀባይ ጋር እንዴት አድርገን በሰላም ማዋሃድ እንችላለን? በአለም ላይ የሚሰጠን ስፍራ በቤተክርስቲያን ባይሰጠንስ?

በነዚህ እና በተለያዩ ነገሮች ራሳችንን እንደ ክርስቲያን ለመምራት #ራስን መግዛት ወሳኙ ነገር ነው፡፡ በተጨማሪ በቤተክርስቲያን ከአገልግሎታችን ትጋት የተነሳ በሚሰጠን አድናቆት ሙገሳ ከተለያዩ ሰዎች በምንሰማው ትችት ባላጠፋነው ጥፋት ብንኮነን አሁንም መለኪያችን ራስን መግዛት ነው አደራ!!!!
ምን አልባት ከሰማነው ነገር እንዳንወሰድ ለእርሱ አብልጠን ልንጠነቀቅ ያስፈልጋል እንደ ቃሉ፡፡ ራስን መግዛት የክርስትናችን ህልውና ነው!!

በተለይ ለአገልጋይ ህግ አለው ለዛውም ጥብቅ ሕግ ኤጲስ ቆጲስነት ለቄሶች ብቻ ነው ካልን ተሳስተናል መንግስተ ሰማይ አንድ ነች ፡፡ ምን አልባት እነሱ በብዙ ሰዎች ሊታዩ ይችሉ ይሆናል ቅድስናቸውን መጠበቃቸው እኛስ በነገስታት ንጉስ በኢየሱስ ፊት እንታያለን ስለዚህ የተፃፈው ለትምህርታችን ተፃፈ፡፡፡

1ጢሞ 3:1
ኤጲስ ቆጲስ አገልጋይ ወይም ቢሾፕ ቄስ ማለት ሲሆን
ለመሆን የሚያስፈልግ መስፈርት👇👇👇
መልካም ስራ ይመኛል ፣ የማይነቀፍ ፣ የአንዲት ምስት ባል ፣ ልከኛ ፣ #ራሱን #የሚገዛ ፣ እንደሚገባው የሚሰራ ፣ እንግዳ ተቀባይ ፣ ለማስተማር የሚበቃ ፣ የማይሰክር ፣ የማይጨቃጨቅ ነገር ግን ገር የሆነ ፣ የማይከራከር ፣ ገንዘብን የማይወድ ፣ ልጆቹን በጭምትነት ሁሉ አየገዙ የራሱን ቤት በመልካም የሚያስተዳድር
አቤት የእግዚአብሔር ቃል ትንትን አድርጓ የሚያስረዳን ጣፋጭ እኮ ነው፡፡
ራስን መግዛት ለአገልጋይ ከላይ የተዘረዘሩትን በሙሉ ለመተግበር ወሳኝ ነው፡፡

✿ ♥✿ በንግግራችን.....
የተለያዩ ሀጢያት በማይመስሉ ቀልዶች(ፌዝ)
በአካሄዳችን ✿ በአለባበስ ✿
እንግዲህ እንደ ጥበበኞች እንደ ጥበብ እንደሌላቸው ሳይሆን እንዴት እንድትመላለሱ በጥንቃቄ ተጠበቁ

ኤፌ 5:15
ምን እንድትሰሙ ተጠበቁ ማር 4:24
አንደበትን እና ሰውነትን በሙሉ እንደ እግ/ር ቃል መምራት፡፡
ራስን መግዛት ይበጃል እንደ ክርስቲያን
ስጀምር ራስን መግዛት ከስጋ ጋር ትግል እንደሆነ አውርተን ነበረ
ለምሳሌ ከቃሉ ብናይ ሥጋዬን እየጓሰምኩ አስገዛለሁ 1ቆሮ 9:27 እየገሰምኩ አስገዛለሁ ማለቱ ነው። ስጋዬን በጥርሴ እይዛለሁ ፣ ሕይወቴን በእጄ አኖራታለሁ
ዕዮ 13:14
ራስን መግዛት ውስጥ ፈርሃ እግዛብሔር አለ
እግ/ርን መፍራት ጥበብ ነው ከሀጢያት መራቅ ማስተዋል ነው፡፡ እዮ 28:28

መጓምጀት
የሰው ሕይወት በገንዘብ ብዛት አይደለምና ተጠንቀቁ ከመጓምጀት ሁሉ ተጠበቁ አላቸው፡፡ ሉቃ 12:15

🗝🗝🗝ራስን መግዛት ማለት🔑🔑👇👇👇
✍ አለም ወይም የስጋ ሀሳብ ከሚያመጣቸው ነፍስን ከሚጎዱ ነገሮች መቆጠብ ማለት ነው፡፡
✍ ከአንደበት የሚወጣውን ቃል በሙሉ በእግዚአብሔር ቃል ቀምሞ የምያንፅ ንግግር ማውራት ማለት ነው፡፡
✍ ወንድሞችን ከሚያሰናክል ነገር የራስን ጥቅም መተው ማለት ነው፡፡
ስሜታችን ወደ ድፍረት ድፍረት ደግሞ ወደ ትዕቢት ከዛ ራሳችንን ወደማንገዛበት ከፍታ እንወጣለን፡፡ በትንሹ ያልተቀጨ አጉል ስሜት ከፍ ብሎ ከእግዚአብሔር መምሰል ይጥለናል ስለዚህ አስተዋይ ጠቢብ ሆነን እግ/ርን መፍራት ተምረን ራሳችንን እንግዛ፡፡
ኢየሱስ ሀይሉን ይስጠን !!
🙏🙏አሜን!!!🙏🙏
የመንፈስ ፍሬዎች በህይወታችን እለት እለት ያፍሩ ይብዙ እላለሁ የሱስ ይባርካቹ!!!
🍇🍇🍇🍇🍇🍇🍓🍓🍇🍇🍇
♥ፍቅር♥ደስታ♥ሰላም♥ትዕግስት♥ቸርነት♥በጎነት♥እምነት♥የዋሃት♥ራስን መግዛት!!
እነዚህን የሚከለክል ሕግ የለም ሊኖርም አይችልም

በተጨማሪ
https://t.me/jesus_is_the_savior1
https://t.me/jesus_is_the_savior1

22/05/2026
21/05/2026

1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 13:1 "በሰዎችና በመላእክት ልሳን ብናገር ፍቅር ግን ከሌለኝ እንደሚጮኽ ናስ ...

Address

Awassa

Telephone

+251916804947

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when One lord one faith one baptism posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share