Shibiru Meseret

Shibiru Meseret This page primierelly aims about promotion Evangelism at the same time page appriciates positive thinkings

18/05/2026
https://www.facebook.com/share/19KHiwYH2M/
01/04/2025

https://www.facebook.com/share/19KHiwYH2M/

የመፅሐፍ ቅዱስ ስሞች እና ትርጓሜ

1 ሩሐማ፦ምሕረት ማለት ነው።
2 ዮዳሔ፦እግዚአብሔር ያውቃል ማለት ነው።
3 ቴዎፍሎስ፦የእግዚአብሔር ወዳጅ ማለት ነው።
4 ኑኃሚን፦ደስታየ ማለት ነው።
5 ናትናኤል፦የእግዚአብሔር ስጦታ ማለት ነው።
6 አዛሄል፦እግዚአብሔር ያያል ማለት ነው።
7 ኢዮስያስ፦እግዚአብሔር ይደግፋል ማለት ነው
8 ኢዩኤል፦እግዚአብሔር አምላክ ነው ማለት ነው።
9 በርናባስ፦የመጽናናት ልጅ ማለት ነው።
10 ሶፎንያስ፦እግዚአብሔር ሰውሯል/ጠብቋል ማለት ነው።
11 ሕዝቅኤል፦እግዚአብሔር ብርታትን ይሰጣል ማለት ነው።
12 ኬልቅያስ፦እድል ፈንታየ እግዚአብሔር ማለት ነው
13 ሳሙኤል፦እግዚአብሔር ሰማኝ ማለት ነው።
14 ሚኪያስ፦ እንደ እግዚአብሔር ያለ ማን ነው! ማለት ነው።
15 ሆሴዕ፦እግዚአብሔር ያድናል ማለት ነው።
16 ሔዋን፦የሕያዋን ሁሉ እናት ማለት ነው።
17 ሕዝቅያስ፦እግዚአብሔር ኃይሌ ነው ማለት ነው።
18 መልከጼዴቅ፦የሰላም ንጉሥ ማለት ነው።
19 ሚልኪያስ፦መልእክተኛየ ማለት ነው።
20 ሣራ፦ልዕልት ማለት ነው።
21 ስምዖን፦ሰማ ማለት ነው።
22 ብንያም፦የቀኝ እጄ ልጅ ማለት ነው።
23 ናሆም፦መጽናናት ማለት ነው።
24 ናታን፦ እግዚአብሔር ሰጥቷል ማለት ነው።
25 አልዓዛር፦እግዚአብሔር ረድቷል ማለት ነው።
26 አስቴር፦ኮከብ ማለት ነው፣
27 አቤሜሌክ፦የንጉሥ አገልጋይ ማለት ነው።
28 አቤሴሎም፦አባቴ ሰላም ነው ማለት ነው።
29 አብድዩ፦የእግዚአብሔር አገልጋይ ማለት ነው።
30 አብራም፦ታላቅ አባት ማለት ነው።
31 አብርሃም፦የብዙዎች አባት ማለት ነው
32 አኪያ፦እግዚአብሔር ወንድሜ ነው ማለት ነው።
33 አክዐብ፦የአባት ወንድም ማለት ነው።
34 ባሮክ፦ቡሩክ ማለት ነው።
35 አዳም፦መልካሙ ማለት ነው።
36 ኢሳይያስ፦ እግዚአብሔር ደኅንነት ነው ማለት ነው።
37 ባርቅ፦መብረቅ ማለት ነው።
38 ኢያሱ፦እግዚአብሔር አዳኝ ነው ማለት ነው።
39 ኢዮሳፍጥ፦እግዚአብሔር ፈርዷል ማለት ነው።
40 ኢዮራም፦እግዚአብሔር ከፍ ከፍ አለ ማለት ነው።
41 ኢዮርብዓም፦ሕዝቡ እየበዛ ይሄዳል ማለት ነው።
42 ቤተልሔም፦የእንጀራ ቤት ማለት ነው።
43 ኢዮአስ፦እግዚአብሔር ሰጥቷል ማለት ነው።
44 ኢዮአቄም፦እግዚአብሔር አቆመ ማለት ነው።
45 ኢዮአብ፦እግዚአብሔር አባት ነው ማለት ነው።
46 ኢዮአታም፦እግዚአብሔር ፍጹም ነው ማለት ነው።
47 ኢዮአካዝ፦እግዚአብሔር ይዟል ማለት ነው።
48 ኤልሳዕ፦እግዚአብሔር ደኅንነት ነው ማለት ነው።
49 ኤልያስ፦እግዚአብሔር አምላክ ነው ማለት ነው።
50 ኤልያቄም፦እግዚአብሔር ያስነሳል ማለት ነው።
51 ኤዶም፦ቀይ ማለት ነው
52 እስራኤል፦ከእግዚአብሔር ጋር ይታገላል ያሸንፍማል ማለት ነው።
53 ኤልሳቤጥ፦እግዚአብሔር መሐላየ ነው ማለት ነው።
54 ኤልሻዳይ፦ሁሉን ቻይ አምላክ ማለት ነው።
55 ሀሌሉያ፦እግዚአብሔርን አመስግኑ ማለት ነው።
56 ሰሎሞን፦ሰላማዊ ማለት ነው።
57 ኬብሮን፦ኅብረት ማለት ነው
58 አዛርያስ፦እግዚአብሔር ረድቷል ማለት ነው።
59 ኤደን፦ደስታ ማለት ነው።
60 ዖዝያን፦እግዚአብሔር ኃይሌ ነው ማለት ነው።
61 ዘካርያስ፦እግዚአብሔር ያስታውሳል ማለት ነው።
62 ይሳኮር፦ ዋጋዬ ማለት ነው
63 ይዲድያ፦በእግዚአብሔር የተወደደ ማለት ነው።
64 ዮሐናን፦እግዚአብሔር ጸጋ ሰጪ ነው ማለት ነው።
65 ዮሐንስ፦እግዚአብሔር ጸጋ ነው ማለት ነው።
66 ዮሴፍ፦ይጨምር ማለት ነው።
67 ዮናስ፦ርግብ ማለት ነው።
68 ዮናታን፦እግዚአብሔር ሰጥቷል ማለት ነው።
69 ዮአኪን፦እግዚአብሔር ያቆማል ማለት ነው።
70 ዮካብድ፦እግዚአብሔር ክብር ነው ማለት ነው።
71 ምናሴ፦ማስረሻ ማለት ነው።
72 ዮፍታሔ፦እግዚአብሔር ይከፍታል ማለት ነው።
73 ዲቦራ፦ንብ ማለት ነው።
74 ዳንኤል፦እግዚአብሔር ፈራጅ ነው ማለት ነው።
75 ጎዶልያስ፦እግዚአብሔር ታላቅ ነው ማለት ነው።
76 ጽዮን፦አምባ ማለት ነው።
77 ጳውሎስ፦ብርሃን ማለት ነው።
78 ሴት፦ምትክ ማለት ነው።
79 ጴጥሮስ፦አለት ማለት ነው።
80 ሄኖክ፦ታደሰ ማለት ነው።
81 ኄራኒ፦ሰላም እና ፍቅር ማለት ነው።


1 ሐና፦ጸጋ ወይም ስጦታ ማለት ነው።
2 ሮቤል፦እነሆ ወንድ ልጅ ማለት ነው።
3 ኤርምያስ፦እግዚአብሔር ከፍ ያደርጋል ማለት ነው።
4 ሮብዓም፦ሕዝብ ይብዛ ማለት ነው።
5 ማራናታ፦ጌታ ሆይ ና ማለት ነው።
6 ቤቴል፦የእግዚአብሔር ቤት ማለት ነው።
7 ቄርሎስ፦የተመረጠ ምርጥ ማለት ነው።
8 እስጢፋኖስ፦አክሊል ማለት ነው።
9 ሳውል/ሳኦል፦ከእግዚአብሔር የተለመነ ማለት ነው።
10 ሴዴቅያስ፦የእግዚአብሔር ጽድቅ ማለት ነው።
11 ፊቅጦር፦ኀዘኔን አራቀልኝ ማለት ነው።
12 ንፍታሌም፦ታጋይ የሚታገል ማለት ነው።
13 ዮርዳኖስ፦ወራጅ ውሃ ማለት ነው።
14 ዮአስ፦እግዚአብሔር ሰጥቷል ማለት ነው።
15 ገነት፦የአትክልት ስፍራ ማለት ነው።
16 ፊልድልፍያ፦የወንድማማች ፍቅር ማለት ነው።
17 ዲና፦ፈረደ ማለት ነው።
18 ማኑሄ፦እረፍት ማለት ነው።
19 መልሕቅ፦ከብረት የተሠራ የመርከብ ማቆሚያ
20 ራማ፦ከፍታ ማለት ነው።
21ቴዎድሮስ፦የእግዚአብሔር ስጦታ ማለት ነው።
22 ፊላታዎስ፦የአምላክ ወዳጅ ማለት ነው።
23 ሕርያቆስ፦ኅሩይ ምርጥ ማለት ነው።
24 ፊልጶስ፦ወንድም ወዳጅ ማለት ነው።
25 ቶማስ፦ፀሐይ ማለት ነው።
26 ታዴዎስ፦እሸቱ ማለት ነው።(ግብራዊ ትርጓሜ)
27 ማትያስ፦ፀሐይ ወይም ምትክ ማለት ነው።
28 ቀሌምንጦስ፦ግንብ ማለት ነው።
29 አቤል፦በግ ወይም ደመና ማለት ነው።
30 ኖኅ፦ደስታ ማለት ነው።
31 ሴም፦ተሾመ ማለት ነው።
32 ይሥሐቅ፦ደስታ አንድም ይሳቅ ማለት ነው።
33 ሙሴ፦የውሃ ልጅ ማለት ነው
34 አሮን፦የእግዚአብሔር ተራራ ማለት ነው።
35 ጌዴዎን፦እግዚአብሔር ኃያል ነው ማለት ነው።
36 እሴይ፦ዋጋየ ማለት ነው።
37 አሚናዳብ፦መንፈስቅዱስ ማለት ነው።
38 ዳዊት፦የተወደደ ልበ አምላክ ማለት ነው፣
39 ዕንባቆም፦ጠቢብ አዋቂ አስተዋይ ማለት ነው።
40 ሄኤሜን፦ምኞቴን አገኘሁ ማለት ነው።
41 አሞጽ፦እግዚአብሔር ጽኑ ነው ማለት ነው፣
42 ዮናስ፦ርግብ ማለት ነው።
43 ሐጌ፦የእግዚአብሔር መልእክተኛ ማለት ነው።
44 ራኄል፦በግዕት ማለት ነው።
45 ዕዝራ፦ረዳቴ ማለት ነው።
46 ሔርሜላ፦ከክብር ዘመድ የተገኘች ማለት ነው።
47 መርቆሬዎስ፦የአባት ወዳጅ ማለት ነው።
48 ኤጲፋንዮስ፦ምስጢር ገላጭ ማለት ነው።
49 ሜሮን፦የተባረከ ሽቱ ማለት ነው።
50 ሱላማጢስ፦ሰላማዊት ማለት ነው።
51 ሶምሶን፦ፀሐይ ማለት ነው።
52 ብንያም፦የቀኝ እጄ ልጅ ማለት ነው።
53 ማርታ፦እመቤት ማለት ነው።
54 ሊዲያ፦ፈራሂተ እግዚአብሔር ማለት ነው።
55 ኤፍሬም፦ፍሬያማ ፍሬው ማለት ነው።
56 ኤፍራታ፦ክብርት የተከበረች ማለት ነው።
57 ታዴዎስ፦ተወዳጅ ወይም ፍቁር ማለት
58 ኢየሩሳሌም፦የሰላም ሀገር ማለት ነው።
59 ሄኖስ፦ሰው ማለት ነው።
60 ሰሎሜ፦ሰላም ማለት ነው።
ማስታወሻ፦ከላይ ከጻፍኳቸው ውስጥ አንዳንድ ስሞች ከ81ዱ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የማይገኙ ከሌሎች የታሪክ እና የገድል መጻሕፍት ውስጥ የሚገኙ ስሞች መሆናቸውን ማሳወቅ እፈልጋለሁ።
ምንጭ፦የመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት፣ የአራቱ ጉባኤያት ትርጓሜ መጻሕፍት
1ማዕዶት፦መሻገሪያ ማለት ነው
2 ኖላዊ፦ጠባቂ ማለት ነው።
3 ማኅቶት፦ብርሃን ማለት ነው
4 ኂሩት፦በጎነት ማለት ነው።
5 ሜላት፦የሐር ግምጃ ማለት ነው።
6 ኅሩይ፦ምርጥ የተመረጠ ማለት ነው።ለሴት ኅሪት
7 ሮዛ፦ጽጌረዳ ማለት ነው።
8 ቀጸላ፦አክሊል ማለት ነው።
9 አስካል፦ፍሬ ማለት ነው።
10 በጽሐ፦ደረሰ ማለት ነው።
11 መሐሪ፦ይቅር ባይ ማለት ነው።
12 መንክር፦ልዩ ማለት ነው።
13 ሥሙር፦የተወደደ ማለት ነው።
14 ሐመልማል፦ለምለም ማለት ነው።
15 ነጸረ፦አየ ተመለከተ ማለት ነው።
16 ቅድስት፦ልዩ ምስጉን ማለት ነው።ቅዱስ ለወንድ ነው።
17 ይኄይስ፦ይሻላል ማለት ነው።
18 ጥዑም፦ጣፋጭ ማለት ነው
19 ግሩም፦የተፈራ ማለት ነው።
20 ተቅዋም፦መቅረዝ ማለት ነው።
21 ጸገየ፦አበበ ማለት ነው
22 ደምፀ፦ተሰማ ማለት ነው።
23 ጎሐጽባሕ፦የንጋት ኮከብ ማለት ነው።
24 ሐዋዝ፦መልካሙ ማለት ነው።
25 ሠናይ፦መልካሙ ማለት ነው።ሰናይት ለሴት ነው።
26 ፈታሒ፦ፈራጁ ማለት ነው።
27 መዓዛ፦ጥሩ ሽታ ማለት ነው።
28 መራሒ፦መሪ ማለት ነው።
29 ነጋሢ/ንጉሥ፦የነገሠ ማለት ነው።
30 ስቡሕ፦የተመሰገነ ማለት ነው።
31 ስብሐት፦ምስጋና ማለት ነው።
32 ብሩህ፦የበራ ማለት ነው።
33 ብርሃን፦ያው በቁሙ ብርሃን ማለት ነው።
34 ትጉህ፦የተጋ ማለት ነው።
35 አምኃ፦እጅ መንሻ ማለት ነው።
36 ልዑል፦ከፍ ያለው ማለት ነው።
37 ከሀሊ፦የሚችል ማለት ነው።
38 ዳግም፦ዳግመኛ ማለት ነው።
39 ማዕረር፦አዝመራ ማለት ነው።
40 ክቡር፦የተከበረ ማለት ነው።
41 አዕምሮ፦እውቀት ማለት ነው።
42 ደብሩ፦ተራራው ማለት ነው።
43 ምሥራቅ፦የፀሐይ መውጫ ማለት ነው።
44 ይባቤ፦እልልታ ማለት ነው።
45 ጥበቡ፦ብልሀተኛው ማለት ነው።
46 ሃይማኖት፦ሃይማኖት ማለት ነው።
47 ትሕትና፦ትሕትና ማለት ነው።
48 ተከሥተ፦ተገለጠ ማለት ነው።
49 በየነ፦ፈረደ ማለት ነው።
50 መኮንን፦ገዢ ማለት ነው።
51 ሐዳስ፦አዲሱ ማለት ነው።
52 ትንሣኤ፦መነሳት ማለት ነው።
53 ሢራክ፦ብልሀተኛ ማለት ነው።
54 ቡሩክ፦ምስጉን የተመሰገነ ማለት ነው።
55 ህላዌ፦መኖር ማለት ነው።
56 ማኅደር፦መኖሪያ ማለት ነው።
57 ሕይወት፦መኖር ማለት ነው።
58 ቤዛ፦መድኃኒት ማለት ነው። ቤዛዊት ለሴት ነው።
59 ኄራን፦ደጋጎች ማለት ነው።
60 መርዓዊ፦ሙሽራ ማለት ነው። መርዓዊት ለሴት ነው።
61 ተስፋ፦ተስፋ ማለት ነው።
62 ዜናዊ፦ነጋሪ ማለት ነው።
63 ጸዐዳ፦ነጭ ማለት ነው።
64 ጸጋ፦ስጦታ ማለት ነው።
65 ብሥራት፦የምሥራች ማለት ነው።
66 ኅሊና፦ማሰቢያ፥ሀሳብ እውቀት ማለት ነው።
67 ማህሌት፦ምስጋና ማለት ነው።
68 ሐሴት፦ደስታ ማለት ነው።
69 ፍሥሓ፦ደስታ ማለት ነው።
70 ትርሲት፦ሽልማት ማለት ነው። በተጨማሪ ስርጉት ማለት የተሸለመች ያጌጠች ማለት ነው።
71 ምዕራፍ፦ማረፊያ ማለት ነው።
72 መቅደስ፦ማመስገኛ፥ መመስገኛ ማለት ነው።
73 ዋካ፦ብርሃን ማለት ነው።
74 ረድኤት፦ እርዳታ ማለት ነው።
75 ጽጌ፦አበባ ማለት ነው።
76 ሠረገላ፦መኪና ማለት ነው።
77 አማን፦እውነት ማለት ነው።
78 አሜን፦ይሁንልኝ ይደረግልኝ ማለት ነው።
79 ተንከተም፦ድልድይ ማለት ነው።
80 ጸዳሉ፦ብርሃኑ ማለት ነው።

18/10/2022

ከጋብቻ ፍቺ በኋላ የባልና ሚስትን ሀብት ስለማጣራት የፍቺ ውጤት ስለመወሰን
==========================
1. #የባልና ሚስትን ሀብት በስምምነት ስለማጣራት
በዚህ ሕግ ስለካሣ ክፍያ የተደነገጉት እንደተጠበቁ ሆነው ጋብቻው በዚህ ሕግ ድንጋጌዎች መሠረት የፈረሰ እንደሆነ ባልና ሚስቱ የጋብቻቸው መፍረስ በንብረት በኩል የሚያስከትለውን ውጤት አስመልክተው በሚያደርጉት ስምምነት ወይም በጋብቻ ውላቸው መሠረት ይጣራል፡፡
ከዚህ በላይ የተመለከተው የጋብቻ ውል ወይም ስምምነት የሌለ ወይም በሕግ ፊት የማይፀና ሆኖ የተገኘ እንደሆነ የባልና ሚስት ሀብት በሚከተሉት ድንጋጌዎች መሠረት ይጣራል፡፡
2. #የግል ሀብትን መልሶ ስለመውሰድ
ባል ወይም ሚስት የግሉ መሆኑን በማስረዳት የግል ሀብቱ የሆነውን ንብረቱን መልሶ የመውሰድ መብት ይኖረዋል፡፡
ከባልና ሚስቱ አንደኛው የግል ሀብቱ የሆነ ማናቸውም ንብረት ለሌላ ሰው የተላለፈ መሆኑንና ከዚሁ ግብይት የተገኘውም ገንዘብ ከጋራ ሀብታቸው ጋር የተቀላቀለ መሆኑን ያስረዳ እንደሆነ ከዚህ ንብረት ጋር ተመጣጣኝ የሆነ ገንዘብ ወይም ንብረት ከጋራ ሀብታቸው በቅድሚያ የማንሳት መብት ይኖረዋል፡፡ ባልና ሚስት የየግል ሀብታቸውን የሚያነሱበት ሁኔታ ሲኖር ሁለቱም በመጨረሻ ከተገኘው የንብረት መጠን እንደየአስተዋጽኦዋቸው ሊደርሳቸው የሚችለውን ያህል የማንሳት መብት ይኖራቸዋል፡፡
3. #ስለካሳ
በዚህ ሕግ መሠረት የጋራ ንብረቱን ወይም የሌላኛውን ተጋቢ ንብረት በብቸኝነት እንዲያስተዳድር ሥልጣን የተሰጠው ተጋቢ ከተሰጠው ሥልጣን ውጪ በፈፀማቸው ድርጊቶች ምክንያት ወይም ከብልሹ አስተዳደር የተነሳ ወይም የካሳ ጠያቂውን መብት በማታለል ድርጊቱ የጎዳ እንደሆነ፣ ፍርድ ቤቱ በተበዳዩ ጥያቄ ሲቀርብለት ተገቢ የጉዳት ካሳ እንዲከፈለው ሊያዝ ይችላል፡፡
ከዚህ በላይ በተመለከተ መሠረት የሚቀርብ የካሳ ጥያቄ ተፈፀመ የተባለው ድርጊት ጋብቻው ከመፍረሱ ከአምስት ዓመት በፊት የሆነ እንደሆነ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
4. #ያለአግባብ ስለመበልጸግ
ባልና ሚስት ተቃራኒ ስምምነት ካላደረጉ በስተቀር ከባልና ሚስት የአንደኛው የግል ሀብት ከሆነ ንብረት የሌላኛው የግል ሀብት ወይም የጋራ ሀብታቸው ያለአግባብ መበልጸጉን ያስረዳ እንደሆነ ፍርድ ቤቱ ተገቢ ካሳ እንዲከፈለው ሊያዝ ይችላል፡፡
5. #የዕዳ ጠያቂዎችን መብት ስለማክበር
ከባልና ሚስት አንደኛው ወይም ሁለቱም በጋራ በፍርድ የተረጋገጠባቸው ወይም ሁለቱም ያመኑት ዕዳ መኖሩ የታወቀ እንደሆነ ይኸው ዕዳ የባልና ሚስት ሀብት ከመከፋፈሉ በፊት ተቀንሶ የሚከፈል ይሆናል፡፡
6. #የጋራ ሀብትን ስለማከፋፈል
ከዚህ በላይ የተመለከቱትና የባልና ሚስት ሀብትን በስምምነት ስለማከፋፈል የተደነገጉት እንደተጠበቁ ሆነው የባልና ሚስት የጋራ ሀብት ለሁለቱም እኩል የሚከፋፈል ይሆናል፡፡
7. #የባልና ሚስት ሀብት በዓይነት የሚከፋፈል ስለመሆኑ
በመሠረቱ፣ እያንዳንዱ ተጋቢ ከጋራ ሀብቱ የተወሰነ ንብረት እንዲደርሰው በማድረግ የጋራ ሀብቱ በዓይነት እንዲከፋፈል ይደረጋል፡፡
ከዚህ በላይ በተመለከተው አኳኋን እኩል ለማከፋፈል የማይቻል ሆኖ የተገኘ እንደሆነ፣ ልዩነቱ በገንዘብ እንዲካካስ ይደረጋል፡፡ የሀብት ክፍፍሉ በሚደረግበት ጊዜ እያንዳንዱ ተጋቢ ይበልጥ ጠቃሚነት ያላቸውን ንብረቶች እንዲያገኝ ለማድረግ ጥረት መደረግ ይኖርበታል፡፡
8. #ለማከፋፈል አዳጋች ስለሆኑ ንብረቶች
ንብረቱ ለክፍፍል የማያመች ወይም ለማከፋፈል የማይቻል ሆኖ የተገኘ እንደሆነና ባልና ሚስቱን ንብረቱ ከሁለቱ ለአንዳቸው እንዲሰጥ ለማስማማት ሳይቻል የቀረ እንደሆነ ንብረቱ ተሸጦ የተገኘውን ገንዘብ እንዲከፋፈሉ ይደረጋል፡፡
ስለአሻሻጡ ሁኔታ ባልና ሚስቱ ሳይስማሙ ቀርተው አንደኛው ጥያቄ ያቀረበ እንደሆነ ሽያጩ የሚደረገው በጨረታ ይሆናል፡፡
9. #ጋብቻው ከፈረሰ በኋላ ከባልና ሚስት ስለሚጠየቅ ዕዳ
ጋብቻው ከፈረሰና የባልና ሚስት ሀብት ከተከፋፈለ በኋላ የሚጠየቅ ዕዳ በጋራ መከፈል የነበረበት በሆነ ጊዜ፣ ስለዕዳው አከፋፈል ሁለቱም በየድርሻቸው መጠን ተጠያቂ ይሆናሉ፡፡ ዕዳው የሚመለከተው አንደኛውን ተጋቢ በሆነ ጊዜ፣ የዕዳው ክፍያ ሊጠየቅ የሚችለው ባለዕዳ ከሆነው ተጋቢ ብቻ ይሆናል፡፡

24/10/2021

ጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤትና ፍትሕ ሚኒስቴርን ጨምሮ በአምስት የመንግሥት ተቋማት ላይ ክስ ተመሠረተ

~ ከ9 ነጥብ 8 ሚሊዮን ብር በላይ የካሳ ጥያቄም ቀርቧል፣


በጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) የሚመራው አመራር ከመምጣቱ አንድ ዓመት በፊት ተፈጽሟል ከተባለ ከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ጋር በተያያዘ፣ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት፣ የቀድሞ ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ (ፍትሕ ሚኒስቴር)፣ የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ዳኞች አስተዳደር ጉባዔ፣ የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽንና የፌዴራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር ላይ የፍትሐ ብሔር ክስ ተመሠረተ፡፡

ክሱ የተመሠረተባቸው መንግሥታዊ ተቋማት፣ ኢትዮጵያ ፈርማ የተቀበለቻቸውና በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 9(4) ላይ የሕጓ አካል ያደረገቻቸውን ዓለም አቀፍ የፀረ-ስቃይ ስምምነት (Convention Against Torture and Other Cruel Inhuman or Degrading Treatment or Punishment) አንቀጽ 1 እና 2(1)፣ የዓለም አቀፍ የሲቪልና የፖለቲካ መብቶች (ICCPR) አንቀጽ (7) እና የአፍሪካ ሕዝቦችና ሰዎች መብት ሰነድ (Africa (Banjul) charter on Human and Peoples Rights) አንቀጽ (5) እና (6)ን ድንጋጌዎች በመተላለፍ መሆኑን ክሱ ያብራራል፡፡

የሰብዓዊ መብት ጥሰት የተፈጸመባቸውና በተቋማቱ ላይ ክስ የመሠረቱት አቶ ዮናስ ጋሻው ደመቀ የተባሉ ተበዳይ ሲሆኑ፣ የሰብዓዊ መብት ጥሰት የተፈጸመባቸው፣ ‹‹በወንጀል ድርጊት ተጠርጥረሃል›› ተብለው በቁጥጥር ሥር ከዋሉበት ጥር 5 ቀን 2009 ዓ.ም. እስከ ሰኔ 15 ቀን 2010 ዓ.ም. ድረስ መሆኑም በክሱ ተጠቁሟል፡፡

የጥቃቱ ሰለባ የሆኑት ከሳሽ ከላይ የተጠቀሱት ዓለም አቀፍ የስምምነት ድንጋጌዎች ተጥሰው ሰቅሎ (አንጠልጥሎ) በጎማ ዱላና ኤሌክትሪክ ገመድ ግርፋት፣ በሰውነት ላይ የኤሌክትሪክ ኃይል መልቀቅ (Electric Shocking) እንደተፈጸመባቸውም በክሱ ተገልጿል፡፡ በመሆኑም ከሳሽ በአሁኑ ጊዜ ሙሉ በሙሉ መራመድ እንደማይችሉ፣ ለአዕምሮ ችግርና ለከፍተኛ የሥነ ልቦናዊ ቀውስ መዳረጋቸውንና መቶ በመቶ ቋሚ የአካል ጉዳት እንደደረሰባቸው፣ በሙያቸው ሠርተው ያገኙት የነበረው ገቢ የባለቤታቸውን ጨምሮ መቋረጡንና ሌሎች አካላዊና የሥነ ልቦና ችግር እንደደረሰባቸውም ክሱ ያብራራል፡፡

የጉዳቱ ሰለባ የሆኑት ከሳሽ የተጠቀሱት ቋሚ ጉዳቶች የደረሱባቸው፣ በወንጀል ጉዳይ እንደሚፈለጉ በቁጥጥር ሥር ያዋላቸው ፌዴራል ፖሊስ በወቅቱ በሥራ ላይ የነበረውን የፀረ ሽብር አዋጅ ቁጥር 652/2001 ድንጋጌን በመተላፍ፣ ያለምንም የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ከአንድ ወር በላይ ታስረው እንዲቆዩ በማድረጉና ያልፈጸሙትን ወንጀል ‹‹ፈጽሜያለሁ›› ብለው እንደሚያምኑ፣ በተለያዩ የፖሊስ አባላት ተሰቅለው በመገረፋቸው፣ የኤሌክትሪክ ኃይል እንዲለቀቅባቸው በመደረጉና ከሰኔ 15 ቀን 2009 ዓ.ም. ጀምሮ ክስ ተመሥርቶባቸው ቅሊንጦ የቀጠሮ እስረኞች ማቆያ ከተወሰዱ በኋላም የደረሰባቸውን አካላዊ ጉዳት እንዳይታከሙ በመከልከላቸው መሆኑን ክሱ ያስረዳል፡፡ በጊዜ ቀጠሮ ለአራት ወራት ፍርድ ቤት ከተመላለሱ በኋላ ለጥርጣሬ የሚያበቃ ማስረጃ በመታጣቱ በነፃ ወይም በዋስ መለቀቅ ሲኖርባቸው፣ ፍርድ ቤቱ ምንም ሳይል መዝገቡን ዘግቶ ለስድስት ወራት ያህል በማዕከላዊ ሲገረፉና ሲደበደቡ ቆይተው፣ ክስ ከተመሠረተባቸው በኋላም የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት አቤቱታቸውን እያሰማ ምንም ዓይነት ትዕዛዝ ባለመስጠቱ ጉዳቱ እየባሰ መምጣቱን ክሱ ይጠቁማል፡፡

በአጠቃላይ ከሳሽ የተያዙበት ሁኔታ ሕገወጥ መሆኑን ቢያመለክቱም እንዳልተመረመረላቸው፣ ንፁህ ሆኖ የመገመት መብታቸው አለመከበሩን፣ የተፋጠነ ፍትሕ የማግኘት መብት (ፍትሐዊ ዳኝነት) አለማግኘታቸውን ክሱ አብራርቶ፣ ከሕግ ውጭ መያዛቸው፣ በሕግ ከተፈቀደው ውጭ በምርመራ ክፍል ታስረው መቆየታቸው፣ የስቃይ ድርጊት ተፈጽሞባቸው ሳለ የማረሚያ ቤቱ አስተዳደር ሕክምና እንዳያገኙ መከልከሉና በፍርድ ቤቶቹም ፍትሐዊ ዳኝነት ባለማግኘታቸው፣ የሚቆጣጠራቸው መንግሥት (የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት) እና ተቋማቱ ተጠያቂ እንዲሆኑ ክሱ መቅረቡን የክስ ሰነዱ ያብራራል፡፡

ተከሳሹ ባቀረቡት ክስ መሠረት ተከሳሽ ተቋማት በአጠቃላይ ለደረሰባቸው አዕምሯዊና አካላዊ ጉዳት 9,821,339 ብር የካሳ ክፍያ እንዲከፈላቸው ጠይቀዋል፡፡

በተጨማሪም ከሳሽ ለደረሰባቸው የሰብዓዊ መብት ጥሰት ሁሉም ተቋማት ባልተነጣጠለ ሁኔታ ሙሉ ኃላፊነት አለባቸው ተብሎ እንዲወሰንላቸው፣ የተፈጸመባቸው ድብደባና ስቃይ፣ ኢትዮጵያ ተቀብላ የሕገ መንግሥቱ አካል ያደረገቻቸውን ዓለም አቀፍ ድንጋጌዎች የጣሰ ነው እንዲባልላቸው፣ ተቋማቱ ሥልጣን ባለው አካል ትዕዛዝ በመስጠት የሰብዓዊ መብት ጥሰት እንዲፈጽሙ በታዘዙ የፌዴራል ፖሊስና ማረሚያ ቤት ሠራተኞችና ኃላፊዎች ላይ የወንጀል ክስ እንዲያቀርቡ እንዲታዘዝላቸው ዳኝነት ጠይቀዋል፡፡ በማናቸውም ሁኔታ የታሰሩ ሰዎች አያያዝና የሰብዓዊ መብት ጥሰት የስቃይ ተግባር (Torture) እንዳይፈጸምና ሥውር እስር (Incommunicado Detention) እንዲቀር ትዕዛዝ እንዲሰጥና ሌሎችም ትዛዝ እንዲሰጥላቸው በጠበቆቻቸው አማካይነት ባቀረቡት የፍትሐ ብሔር ክስ ዳኝነት ጠይቀዋል፡፡
(ታምሩ ፅጌ ~ ሪፖርተር)

21/10/2021

10 የአገልጋይ አመራር መርሆዎች (እና ለምን የእኛ ተወዳጅ ዘይቤ ነው) /Principles of Servant Leadership (and Why It’s Our Favorite Style)
========================
የአገልጋይ አመራር ምንድነው?
የአገልጋይ አመራር ከድርጅቱ ወይም ከመሪው ፍላጎቶች በላይ ለቡድኑ ዕድገትና ደህንነት ቅድሚያ የሚሰጥ የአስተዳደር ዘይቤ ነው። አገልጋይ መሪ ከባህላዊ መሪዎች በተለየ መልኩ የድርጅቱን ዓላማ ማሳካት ብቻ ሳይሆን ግለሰቦችን በማሰልጠን እና በማልማት ላይ ያተኩራል።

የአገልጋይ አመራር መነሻው ሮበርት ግሪንሊፍ ነው። በ 1970 “አገልጋዩ እንደ መሪ” ድርሰቱ ፣ የአገልጋይ አመራርን እንዲህ ሲል ገልጾታል።

“አገልጋይ-መሪ መጀመሪያ አገልጋይ ነው… የሚጀምረው አንድ ሰው ማገልገል በሚፈልግ ተፈጥሯዊ ስሜት ነው።
ብዙ ኩባንያዎች ድርጅቱን ግቦቹን ለማሳደግ ብቻ የሚሠሩ ሠራተኞችን እንደ ጎማ ጎማ አድርገው ይመለከታሉ። መሪዎች በሰዓቱ እስካልደረሰ ድረስ ሥልጣናቸውን የሚጥሱ እና ሥራ እንዴት እንደሚከናወን ግድ የማይሰጣቸው የሥራ አስኪያጆች ሆነው ያገለግላሉ። አገልጋይ አመራር ሰዎችን ከስልጣን በማስቀደም የተለመደውን የአመራር ስክሪፕት ይገለብጣል።

የአገልጋይ አመራር 10 ቁልፍ መርሆዎች
ስለዚህ የአገልጋይ መሪ ለመሆን ምን ያስፈልጋል? የአገልጋይ መሪዎች የጋራ ዋና ዋና ባህሪያትን ይጋራሉ። ከቡድንዎ ጋር እንዲሠራ የአገልጋይ አመራርን ለማስቀመጥ እነዚህን 10 መርሆዎች ይከተሉ።

1. ማዳመጥ
ማዳመጥ በአገልጋይ አመራር ልብ ውስጥ ነው። አንድ የቡድን አባል እያወራ ከሆነ ፣ ሙሉ ትኩረትዎን እና ትኩረትዎን ይስጧቸው - ምንም መቋረጥ አይፈቀድም! እርስዎ እንደሚያስቡዎት እንዲያውቁ ቡድንዎ ዋጋ እንዳለው እንዲሰማቸው ለማድረግ ቀላል መንገድ ነው።

2. ርኅራኄ
ብዙ ወደ ርህራሄ ይሄዳል ፣ ግን ወደ አገልጋይ አመራር ሲመጣ በመሠረቱ ቡድንዎን ለማወቅ ይወርዳል። የሚያንኳኳቸው ምን እንደሆነ ይወቁ እና ጥንካሬያቸውን እና ድክመቶቻቸውን ይማሩ። በዚህ መንገድ የቡድንዎ አባላት እንዲያበሩ እና ምናልባትም ድክመቶቻቸውን ወደ ጥንካሬዎች እንዲለውጡ ሊረዷቸው ይችላሉ።

3. ፈውስ
አንዳንድ የቡድን አባላት በእርግጥ መርዛማ የሥራ አካባቢ ካለው ከቀድሞው ሥራ ወደ እርስዎ ሊመጡ ይችላሉ - እናም እነሱ እንዲፈውሱ የመርዳት መብት አለዎት።

አይጨነቁ: እንደሚመስለው ከባድ አይደለም። ፈውስ ጤናማ የሥራ አካባቢን እንደመፍጠር ቀላል ነው። እሱ እንደ ሰዎች ዋጋ ያለው የቡድን አባል እንዲሰማቸው ለስኬታማነት የሚያስፈልጉ መሣሪያዎችን ለሰዎች መስጠት ነው።

4. ራስን ማወቅ
የቡድንዎን ጥንካሬ እና ድክመቶች የመረዳትን አስፈላጊነት አስቀድሜ ጠቅሻለሁ። ግን የእራስዎን ትንሽ የራስ-ነፀብራቅ ማድረግ እንዲሁ አስፈላጊ ነው።

የእራስዎን ጥንካሬዎች እና ድክመቶች ዝርዝር ይያዙ እና ከጠቅላላው ቡድን ጋር እንዴት እንደሚስማሙ ይወቁ። ከዚያ ለቡድኑ እና ለኩባንያው በሚጠቅሙ መንገዶች እራስዎን ይጠቀሙ። የእራስዎን ገደቦች ማወቅ የቡድንዎን ጥንካሬዎች የበለጠ በግልፅ ለመጠቀም እድሎችን እንዲያዩ ይረዳዎታል።

የተሻለ መሪ ለመሆን ያቅዱ
ሥራ ወደየት እያመራ እንደሆነ ትልቁን ምስል ማየት ሲችሉ እንደ መሪ ማገልገል በጣም ቀላል ነው። TeamGantt በልበ ሙሉነት ለመምራት መሳሪያዎችን ይሰጥዎታል።

5. ማሳመን
ማሳመንን በሚያስቡበት ጊዜ ተንሸራታች የሽያጭ ዘዴዎች ወደ አእምሮዎ ሊመጡ ይችላሉ። ግን እዚህ የምንናገረው ይህ አይደለም።

የአገልጋይ መሪዎች መግባባትን ለመገንባት እና ከቡድናቸው ግዢን ለማሳመን ማሳመንን ይጠቀማሉ። በዚህ መንገድ ሁሉም በቡድኑ ስኬት ውስጥ ድርሻ እንዳላቸው ይሰማቸዋል።

6. ጽንሰ -ሀሳብ
እንደ መሪ እና ኩባንያ የት እንደሚሄዱ ማወቅ አለብዎት። ደግሞስ ፣ ለቡድንዎ አዎንታዊ መንገድን ሌላ እንዴት ይቀረጹታል?

TeamGantt በዕለት ተዕለት ላይ ትኩረትን ሳያጡ ትልቁን ምስል በአዕምሮዎ ውስጥ እንዲያስቀምጡ ያስችልዎታል። ለምሳሌ ፣ የፕሮጀክቱ ጤና ሪፖርት ሁሉም ፕሮጄክቶችዎ እንዴት እየተከታተሉ እንደሆኑ ለማየት ቀላል ያደርገዋል ፣ የሥራ ጫነዎች ግን በቡድንዎ ምት ላይ ጣት እንዲይዙ ያስችልዎታል።

7. አርቆ ማሰብ
ሌላው የአገልጋይ አመራር ቁልፍ ባህሪ እርስዎ እና ቡድንዎ ማደጉን እንዲቀጥሉ ከዚህ ቀደም የተማሩትን ዕውቀት ወስደው ለወደፊቱ ተግባራዊ ማድረግ ነው።

ከእያንዳንዱ ፕሮጀክት ጋር ሂደትዎን ማረም እንዲችሉ የፕሮጀክት ድህረ-ሙታሞች ወይም የኋላ ተመልካቾች ምን እንደሰራ-እና ምን እንዳልሆነ ለማወቅ ጥሩ መሣሪያ ነው። እንዲሁም የመጀመሪያውን ዕቅድዎን ከእውነተኛው የጊዜ መስመር እና ለማሻሻል እድሎችን ለማነፃፀር የ TeamGantt መሰረታዊ መስመሮችን ባህሪ መጠቀም ይችላሉ።

8. መጋቢነት
መጋቢነት በቀላሉ በምሳሌነት ይመራል። ለቡድንዎ ቃና ማዘጋጀት የእርስዎ ተግባር ነው ፣ ስለሆነም ሰዎች እርስዎ እራስዎ የማይሰሩትን እንዲያደርጉ አይጠይቁ።

በ TeamGantt እኔ የልማት ቡድኑን እመራለሁ። ይህንን በተግባር የምሠራበት አንዱ መንገድ ለጠዋቱ 2 00 ሰዓት ማሰማራት የመጀመሪያው ሰው በመሆን ነው። የሆነ ችግር ከተፈጠረ ሙቀቱን እወስዳለሁ። ይህ መተማመንን ለመገንባት ረጅም መንገድ ይሄዳል-ለማንኛውም በደንብ ለሚሠራ ቡድን ግዴታ ነው።

9. ለሰዎች እድገት ቁርጠኝነት
ቡድንዎ እንዲያድግ ከፈለጉ በሰዎች ላይ መዋዕለ ንዋይ ማፍሰስ አለብዎት። ይህን የምናደርግበት አንድ ቀላል መንገድ የቡድን አባላት በሚኖራቸው ሚና እንዲበለጽጉ የሚያስፈልጋቸውን ክህሎት እንዲያሳድጉ ዓመታዊ የኮንፈረንስ በጀት በማቅረብ ነው።

እኛ በየዓመቱ 360 የአፈጻጸም ግምገማዎችን እናካሂዳለን። እንደ መሪ ፣ እርስዎ ብቻ ብዙ ማየት ይችላሉ። የ 360 ዲግሪ ግምገማ የበለጠ የአፈፃፀም ስዕል እንዲኖርዎት እና ለእድገቱ ትርጉም ያላቸው ዕድሎችን መለየት እንዲችሉ የአቻ እና ቀጥታ የሪፖርት ግብረመልስን ወደ ሂደቱ ያመጣል።

10. ማህበረሰብ መገንባት
እርስ በእርስ የሚተማመኑ ቡድኖች የበለጠ ለመስራት አብረው ይሰራሉ። ለዚህም ነው በቡድንዎ መካከል ግንኙነቶችን ማዳበር አስፈላጊ የሆነው።

እንደ ሙሉ የርቀት ቡድን ፣ ስለዚህ ጉዳይ ከመጠን በላይ ሆን ብለን መሆን አለብን። ለዓመታዊ የቡድን ስብሰባችን በዓመት አንድ ጊዜ መላውን ቡድን አንድ ላይ እናመጣለን ፣ ትናንሽ ቡድኖች ደግሞ ብዙ ጊዜ ይሰበሰባሉ። መተማመን ለማደግ ቦታ እንዲኖረው በንግድ ስትራቴጂ መካከል ለመዝናናት በጊዜ መገንባቱን እናረጋግጣለን። ኢንቨስትመንቱ ዋጋ አለው!

Address

Hawasa
Awassa

Telephone

+251916042054

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Shibiru Meseret posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Place Of Worship

Send a message to Shibiru Meseret:

Share