አሰላ ደብረ ምፅላል ቅድስት ማርያም ሰንበት ትምህርት ቤት

  • Home
  • Ethiopia
  • Assela
  • አሰላ ደብረ ምፅላል ቅድስት ማርያም ሰንበት ትምህርት ቤት

አሰላ ደብረ ምፅላል ቅድስት ማርያም ሰንበት ትምህርት ቤት Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from አሰላ ደብረ ምፅላል ቅድስት ማርያም ሰንበት ትምህርት ቤት, Religious Center, asella, Assela.

13/05/2024
https://youtu.be/8AuoYWE8f40?si=Er2hUNocTFjelPbC
01/12/2023

https://youtu.be/8AuoYWE8f40?si=Er2hUNocTFjelPbC

ደግሞ ላመስግንሽዘማሪ ዳንኤል ጥበበሥላሴግጥም: ዲያቆን ከሣቴብርሃን ገብረኢየሱስ (ዶ/ር )ዜማ : ዘማሪ ዳንኤል ጥበበሥላሴድምጽ ቀርጻ: ዲ/ን ዘላለም ታከለ (ዘጎላ ሪከርድስ ) አዳዲስ ዝማሬ...

https://youtu.be/BZSXLB9jeks
29/04/2023

https://youtu.be/BZSXLB9jeks

አዲስ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ዝማሬዘማሪ ዳንኤል ጥበበሥላሴ ጉባኤያችን ማርያም-------ሰብስክራይብ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑን

https://youtu.be/k7ddP6JqWyo
04/03/2023

https://youtu.be/k7ddP6JqWyo

ምነው ሥጋውን ሳትበላው ፟ዘማሪ ዳንኤል ጥበበሥላሴ አዲስ ዘለሰኛ መዝሙር ፡፡ሌሎችም የመዝሙር ሥራዎች እንዲደርስዎት ሰብስክራይብ ያድርጉመልካም የጾም ወቅት

04/03/2023

🥰🥰🥰

ሰበር ዜና - ፓትርያርኩ ከሓላፊነታቸው ለመልቀቅ በቃል ጠየቁ፤ ጫና ለማሳደር የታሰበ ስልት መኾኑ ተጠቆመ• ከሥልጣን የመገለል ስጋት ባይኖራቸውም፣ ተገቢነታቸው ብርቱ ጥያቄ እየተነሣበት ነው፤...
20/10/2017

ሰበር ዜና - ፓትርያርኩ ከሓላፊነታቸው ለመልቀቅ በቃል ጠየቁ፤ ጫና ለማሳደር የታሰበ ስልት መኾኑ ተጠቆመ
• ከሥልጣን የመገለል ስጋት ባይኖራቸውም፣ ተገቢነታቸው ብርቱ ጥያቄ እየተነሣበት ነው፤
• “በአቅም ማነስ ያጡትን ተቀባይነት ለመመለስ፣ ከአማካሪዎቻቸው ጋራ የወጠኑት ነው፤”
• ለብፁዕ አቡነ ፋኑኤል ምክር የሰጡት ምላሽ፣ ብዙዎችን ቢያሳዝንም ሊያግዷቸውም ዛቱ፤
• የተወነጀሉት ብፁዕነታቸው፣ በምልአተ ጉባኤ እና በሕግም እንደሚጠይቋቸው ተጠቆመ፤
• በሀ/ስብከታቸው ተቀባይነት ያጡት ብፁዕ አባ ማርቆስ፣በቦታቸው ለመተካት እየሠሩ ነው፤
†††
ታማኝነታቸውና መንፈሳዊ አባትነታቸው ተቀባይነት እያጣ መምጣቱ በብርቱ አሳስቧቸዋል የተባሉት፣ ፓትርያርክ ብፁዕ
ወቅዱስ አቡነ ማትያስ፣ “መሥራት አልቻልኩም፤” ሲሉ ከሓላፊነታቸው ለመልቀቅ፣ ለመንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣናት
በቃል ጥያቄ ማቅረባቸው ተሰማ፡፡
ፓትርያርኩ ጥያቄውን ያቀረቡት፣ ከቤተ ክርስቲያኒቱ ሕግ አውጭና ወሳኝ አካል ከኾነው ቅዱስ ሲኖዶስ እና ከሥራ
አስፈጻሚው የጠቅላይ ቤተ ክህነት አስተዳደራዊ አካል ጋራ ያላቸው ግንኙነት ከፍተኛ ውጥረት ውስጥ እንደገባ እየታየ
ባለበት ወቅታዊ ኹኔታ ውስጥ ነው፡፡
“መፍትሔ ሊሰጠኝ ይገባል፤” በማለት በሓላፊነታቸው ለመቀጠል እንደተቸገሩ በቃል ለከፍተኛ የመንግሥት
ባለሥልጣናት መናገራቸውንና በቅርቡም በጽሑፍ እንደሚያሳውቁ ነው፣ ምንጮች የጠቆሙት፡፡
በሕገ ቤተ ክርስቲያኑ የፓትርያርኩ ሢመትና ርደት ጉዳይ የሚወስነው ቅዱስ ሲኖዶስ ኾኖ ሳለ፣ ጥያቄያቸውን
ለባለሥልጣናት ማቅረባቸው፣ በቅዱስ ሲኖዶስና በጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ዘንድ በአስከፊ ኹኔታ እያጡ የመጡትን
ተደማጭነትና ተቀባይነት በተጽዕኖ ለመመለስ፣ ከአማካሪዎቻቸው ጋራ የወጠኑት መኾኑን እንደሚያሳይ ተነግሯል፡፡
የቅዱስ ሲኖዶሱ፣ የመጀመሪያ ዓመታዊ የምልአተ ጉባኤ ስብሰባ፣ ከነገ በስቲያ፣ ጥቅምት 12 ቀን እንደሚጀመር እያወቁ፣
ከሓላፊነት ለመልቀቅ ጠይቀዋል፤ መባሉ ይህንኑ ጫና የማሳደር ስልታዊነቱን እንደሚያረጋግጥ ነው የተገለጸው፡፡
ከማኅበረ ቅዱሳን ጋራ በተያያዘ የሚያቀርቡት የእግድ አጀንዳ፣ በቅዱስ ሲኖዶሱ አካላት(ቋሚ ሲኖዶስ እና ምልአተ ጉባኤ)
ውድቅ መደረጉ፤ ቡድን ፈጥረው እየመከሩ ለጠቅላይ ጽ/ቤቱ የሚያስተላልፉት መመሪያ መሸራረፉ ሕመም እንደኾነባቸው
ነው የተስተዋለው፡፡
የማኅበሩ የቴሌቭዥን ፕሮግራም ሥርጭት፣ ከቋሚ ሲኖዶሱ ውሳኔ ውጭ እንዲታገድ ያስተላለፉት መመሪያ ተፈጻሚነት
ሲያጣ፣ ከአጠቃላይ ጉባኤው 36ኛ ዓመታዊ ስብሰባ ተሳትፎ እንዲታገድ ወደ ማዘዝ ቢሸጋገሩም፣ እንዳሰቡት
ሳይሳካላቸው ቀርቶ፣ በተፃራሪው፣ የማኅበሩ የማዕከልና የአህጉረ ስብከት ሥራዎች በጉልሕ እንዲስተጋቡ ምክንያት
ኾኗል፡፡
በአጠቃላይ ጉባኤው መክፈቻ ምሽት፣ የማኅበሩ ተወካዮች እንዳይሳተፉ በማድረጋቸው፣ “የእኛን ሥልጣን ማወቅ
አለባቸው፤ ሥልጣናችንን መረዳት አለባቸው፤” በማለት ከእነብፁዕ አባ ሩፋኤል፣ ብፁዕ አባ ማርቆስ እና ብፁዕ አባ ቶማስ
ጋራ ውሎውን የገመገሙ ቢኾንም፤ በቀጣዩ ቀን፣ ማኅበሩ ከአህጉረ ስብከት ጋራ በመቀናጀት ያከናወናቸው ተግባራት
በድምቀት እየተነገሩ በመዋላቸው፣ በጋራ መግለጫውና ቃለ ጉባኤው ላይ፣ የቴሌቭዥን ሥርጭቱ ሕገ ወጥ እንደኾነና
እንዲዘጋ የሚጠይቅ አንቀጽ በጣልቃ እንዲገባ አርቃቂዎቹን አዝዘዋል፡፡ ሐሳቡን የተቃወሙ የአርቃቂ ኮሚቴው ሦስት
አባላት፣ “የማኅበር ተላላኪዎች” ተብለው በሰብሳቢው የተዘለፉ ሲኾን፣ ሥርዋጹም በግድ እንዲገባና በድፍረት
እንዲነበብ ተደርጓል፡፡
በአጠቃላይ ጉባኤው ያልተነሣ ጉዳይ በቃለ ጉባኤው የውሳኔ ሐሳብ ተብሎ መስፈሩ አግባብነት እንደሌለው ወዲያውኑ
ከጉባኤተኛ

18/10/2017

በአህጉረ ስብከት የ2009 ዓ.ም. ጥምቀተ ክርስትና፡ ከ73 ሺሕ በላይ ሐዲሳን አማንያን ወደ
ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ተጨመሩ
ከ23ሺሕ በላይ ፣ ከ ማኅበረ ቅዱሳን የስብከተ ወንጌል ማስፋፊያ ፕሮግራም ጋራ በመቀናጀት
የተጠመቁ ናቸው፤
በርካታ አህጉረ ስብከት፣ ከማኅበረ ቅዱሳን ጋራ በመቀናጀት ያከናወኑትን አገልግሎት በአጽንዖትና
በቃለ አጋኖ አቀረቡ፤
“ ይህን ኹሉ ሥራ የሠራነው፥ የቤተ ክርስቲያን ክንድ፣ የቤተ ክርስቲያን ዐይንና የቤተ ክርስቲያን የጀርባ
አጥንት በኾነው በማኅበረ ቅዱሳን ነው፤ ማኅበሩን አመስግኑልኝ፤”- የወላይታ ኮንታ ሀገረ ስብከት
ሥራ አስኪያጅ፤
ስለ “ ምእመናን ፍልሰት ”፣ ያለበቂ ዳታና ያለጥንቃቄ የሚተላለፈው መልእክት ሊጤን ይገባዋል፤
“ በኖላዊ ቁርጠኝነትና የተግባር እንቅስቃሴ ካልተደገፈ ሙሾ ነው፤ ያስጠቃናል !”
ከ50 አህጉረ ስብከት፣ የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ የ35 በመቶ( የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት 65 ከመቶ) ፈሰስ፣
ከ220 ሚሊዮን ብር በላይ ጠቅላላ ገቢ ተመዘገበ፤
ብፁዕ አባ ማርቆስ የተጠበቁበትን የ”ጩኸቴን ቀሙኝ” ውንጃላ በ ማኅበረ ቅዱሳን ላይ አሰሙ፤
ጉባኤተኛው በሣቅና ሥላቅ ሸኛቸው፤ የአዊው ብፁዕ አባ ቶማስም ተከተሏቸው፤
†††
ትላንት፣ ሰኞ፣ ጥቅምት 6 ቀን የተጀመረው የመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ 36ኛ ዓመታዊ
ስብሰባ ዛሬም ቀጥሎ ውሏል፡፡ እስከ ቀትር ባለው የጉባኤው ክፍለ ጊዜ፣ 28 አህጉረ ስብከት በሥራ አስኪያጆቻቸው
አማካይነት ሪፖርታቸውን አቅርበው አሰምተዋል፡፡
በብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ሐዋርያዊ ጉዞዎች፤ በስብከተ ወንጌል እና ትምህርተ ወንጌል መስፋፋት፤ በአብያተ ክርስቲያናት፣
አገልጋዮችና ምእመናን ምዝገባ፤ በፀረ ፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ የዕቅበተ እምነት ጉባኤያት፣ በመልካም አስተዳደር
መስፈን፤ በመንፈሳዊና ዘመናዊ ትምህርት ቤቶች መስፋፋትና መጠናከር፤ የአብነት ተማሪዎችንና መምህራንን ፍልሰት
መግታት፤ በሰንበት ት/ቤቶች አያያዝና በወጣቱ ትውልድ አጠባበቅ፤ በገዳማትና ቅርሳቅርስ አጠባበቅ፤ በገንዘብና
ንብረት አጠባበቅ፣ አያያዝና ቁጥጥር ሥርዓት፤ በሰበካ ጉባኤ ማጠናከርና በፐርሰንት ድርሻ አፈጻጸም፤ በልማት
እንቅስቃሴና በገቢ ምንጭ ፈጠራ፣ በዐዲስ አብያተ ክርስቲያን ግንባታ፣ በምግባረ ሠናይ(በጎ አድራጎት) መጠነ ሰፊ
ሥራዎች መሠራታቸው ተገልጿል፤ የተገኙ ውጤቶችና ያጋጠሙ ችግሮች ተጠቅሰዋል፤ ዕቅዶችም ተመላክተዋል፡፡
በጉባኤው መክፈቻ በቀረበው የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ አቡነ ዲዮስቆሮስ
አጠቃላይ ዓመታዊ ሪፖርት እንደተሰማው፣ ከኃምሳው አህጉረ ስብከት፣ ብር 220ሚሊዮን 154ሺሕ 825 ከ55
ሳንቲም አጠቃላይ ገቢ በበጀት ዘመኑ ተመዝግቧል፤ ይህም ከአምናው ገቢ ሲነጻጸር የብር 52ሚሊዮን 556ሺሕ 902
ከ96 ሳንቲም ብላጭ አሳይቷል፡፡
በበጀት ዓመቱ፣ ከ49ኙ አህጉረ ስብከት የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ 35 በመቶ ፈሰስ ብር 88ሚሊዮን 656ሺሕ 839
ከ70 ሳንቲም ተገኝቷል፤ ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋራ ሲነጻጸርም፣ የብር 17ሚሊዮን 452ሺሕ 623 ከ52 ሳንቲም
ብልጫ አስመዝግቧል፡፡ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ለጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ያስገባው የ65 በመቶ ፈሰስ ብር 131
ሚሊዮን 497ሺሕ 985 ከ85 ሳንቲም ነው ፡፡ ከአምናው ተመሳሳይ የገቢ ዘመን ጋራ ሲነጻጸር፣ የብር 35 ሚሊዮን
104ሺሕ 279 ከ44 ሳንቲም ብልጫ አስመዝግቧል፡፡
ቤተ ክርስቲያናችን በበጀት ዓመቱ ካስመዘገበችው አጠቃላይ ገቢ ውስጥም ብር 8 ሚሊዮን 956ሺሕ 298 ከ96
ሳንቲም ከልማት ገቢ የተደረገ ሲኾን፤ ከአምናው ገቢ አንጻር የብር 2ሚሊየን 229ሺሕ 304 ከ44 ሳንቲም ልዩነት የታየ
ቢኾንም፣ በዘርፉ ጠንክሮ በመሥራት የተለየ ትኩረትና ክትትል ማድረግ ብፁዕ ዋና ሥራ አስኪያጁ አሳስበዋል፡፡
ብዙዎቹ አህጉረ ስብከት፣ በፋይናንስ አያያዝና አመዘጋገብ ወቅቱ በሚጠይቀው የደብል ኢንትሪ ሲስተም
ሠራተኞቻቸውን የአቅም ግንባታ ሥልጠናዎች እንዳሠለጠኑ አስታውቀዋል፡፡ በበጀት ዘመኑ፣ በጠቅላይ ቤተ ክህነትም
ኾነ በአህጉረ ስብከት ደረጃ የተመዘገበው አጠቃላይ የመልካም ሥራ ውጤትና የገቢ ዕድገት፣ ከብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት
ጀምሮ በየደረጃው ባሉ ሓላፊዎች ብርቱ ጥረት፣ በካህናትና ምእመናን ከፍተኛ አስተዋፅኦ የተገኘ በመኾኑ፣ “ሊመሰገን
የሚገባው ነው፤” ብለዋል ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ፡፡
የአህጉረ ስብከቱ የመልካም ሥራ ውጤት ግን በገንዘብ ገቢ ዕድገት ብቻ ሳይኾን፣ ያሉትን ምእመናነ ክርስቶስ
በስብከተ ወንጌል በማጽናት፣ ከበረት ቤተ ክርስቲያን የኮበለሉትን አሳምኖ በመመለስና ሐዲሳን አማንያንን
በጥምቀተ ክርስትና ለአሚነ ሥላሴ በማብቃትም እንደሚገለጽ ከሪፖርታቸው ለመረዳት ተችሏል፡፡ በ2009 ዓ.ም.
የአህጉረ ስብከቱ የጥምቀተ ክርስትና መርሐ ግብር ፣ 73ሺሕ 322 ሐዲሳን አማንያን ወደ ቀደመች አሐቲ
ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ሃይማኖት ተመልሰዋል፤ ከእኒህም ውስጥ 23ሺሕ 156 ጥሙቃን ማለትም 31 ነጥብ 5
በመቶው፣ አህጉረ ስብከቱ ከማኅበረ ቅዱሳን የስብከተ ወንጌል ማስፋፊያ መርሐ ግብር ጋራ በመቀናጀት ያስገኟቸው
እንደኾኑ ተገልጿል፡፡
በ2009 ዓ.ም. የጥቅምተ ክርስትና መርሐ ግብር ወደ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የተጨመሩ
ሐዲሳን አማንያን ብዛት፤
ሰሜን ወሎ – 1ሺሕ 129
ማይጨው – 221
ዓዲ ግራት – 3
ምሥራቅ ጎጃም – 10
መተከል – 15ሺሕ 656
ሲዳማ – 1ሺሕ 060
ደቡብ ኦሞ – 4ሺሕ 109
ምዕራብ ሐረርጌ – 390
ባሕር ዳር – 17
ምዕራብ ጎጃም – 1ሺሕ 522
ጋምቤላ – 262
ምሥራቅ ሐረርጌ – 38
ደቡብ ምዕራብ ሸዋ – 809
ካፋ – 5ሺሕ 645
ሸካ ቤንች ማጂ ዞን – 3ሺሕ 800
ጉጂ ቦረና – 3ሺሕ
ኢሉ አባቦራ – 840
ሶማሌ – 926
ሰሜን ምዕራብ ሸዋ/ሰላሌ – 146
ጋሞጎፋ – 19ሺሕ 862
ወላይታ – 140
ሃዲያና ስልጤ – 488
ምሥራቅ ወለጋ – 122
ምዕራብ ሸዋ – 11ሺሕ 896
ከምባታ ጠምባሮና ሀላባ – 1ሺሕ 231፣ በድምሩ 73ሺሕ 322 ጥሙቃን ወደ እናት ቤተ ክርስቲያን
ተጨምረዋል፡፡

08/05/2017
ሊቀ መዘምራን ይልማ ሀይሉ***********የሚጠብቀኝ አይተኛምየሚጠብቀኝ አይተኛምአያንቀላፋም+ +ቤት ባይኖረኝም ደጅ ብተኛምቀንና ሌሊት ከእኔ አይርቅምድምፅህ አራዊት የሌሊት ግርማወደ እኔ አ...
25/02/2017

ሊቀ መዘምራን ይልማ ሀይሉ
***********
የሚጠብቀኝ አይተኛም
የሚጠብቀኝ አይተኛም
አያንቀላፋም
+ +
ቤት ባይኖረኝም ደጅ ብተኛም
ቀንና ሌሊት ከእኔ አይርቅም
ድምፅህ አራዊት የሌሊት ግርማ
ወደ እኔ አይቀርቡም ድምፅህ ሲሰማ
+ + +
መሰናከልን ለእግሮቼ አይሰጥም
ይሰውረኛል በቀኙ ሰላም
ፀሃይም በቀን አይተኩሰኝም
የአካል አያስፈራኝም
+ + +
ነፍሴን ጠበቃት ከጠላት ወጥመድ
ጌታዬ መራኝ በጽድቅ መንገድ
መውጣት መግባቴን እየጠበቀ
ለእዚህ አበቃኝ እርሱ ባወቀ
+ + +
የሰማዩን ጠዕል እታገሳለሁ
ሰው ከጨከነ ምን እሆናልሁ
ለሌሊት በድብቅ ለሚጎበኙኝ
ለፃድቃኑ ግን አምላክ ይስጥልኝ
+ + +
እንቅልፍ ውብ አድርጌ የሰጠኝ ጌታ
በአለም ሃሳብ ሳልገላታ
ለእለት ምግቤንም ለአልነሳኝ ፍፁም
ምስጋና ላቅርብ እስከ ዘላለም

ተነሳ ህዝቤ ተነሳተነሳ ወገን ተነሳየጥንቱ እንዳይረሳየቀድሞው እንዳይረሳበሀገርም በውጪም በየትም ያላችሁየተዋህዶ ፍቅር ያለ በልባችሁበሉና ተነሱ ታሪካችሁ ይብቃምድረ ተሃድሶ ምድረ ሐራጥቃተነሳ...
07/02/2017

ተነሳ ህዝቤ ተነሳ
ተነሳ ወገን ተነሳ
የጥንቱ እንዳይረሳ
የቀድሞው እንዳይረሳ
በሀገርም በውጪም በየትም ያላችሁ
የተዋህዶ ፍቅር ያለ በልባችሁ
በሉና ተነሱ ታሪካችሁ ይብቃ
ምድረ ተሃድሶ ምድረ ሐራጥቃ
ተነሳ ወገን ተነሳ
ተነሳ ክርስቲያን ተነሳ
ዶግማችን እንዳይረሳ
ቀኖናው እንዳይረሳ
መቷል በኢየሱስ ስም ትጥቅህን ሊያስፈታ
በልና መልሰው የለም አዲስ ጌታ
አንዲት ጥምቀትና አንዲት ሃይማኖት
አለች ተዋህዶ የተረከብናት
ተነሳ ህዝቤ ተነሳ
ተነሳ ወገን ተነሳ
የጥንቱ እንዳይረሳ
የቀድሞው እንዳይረሳ
በነዮዲት ጉዲት በግራኝ አህመድ
ገዳም ሲፈርስ አየው ካህን ሲታረድ
ትናንት የሆነብን ሳይወጣ ቁጭቱ
ዳግም ተነሱባት ጡቷን የጠቡት
ተነሳ ወገን ተነሳ
ተነሳ ክርስቲያን ተነሳ
ዶግማችን እንዳይረሳ
ቀኖናው እምዳይረሳ
በእርግጥ ቢያስገርመን የኤሊ ዝምታ
እውነትን ለመግለጥ አንደበት ቢገታ
የእውነት ሰይፍ ይዞ የሚፈርድልን
እውነተኛው ዳኛ ይምጣ ሶሎሞን
ተነሳ ህዝቤ ተነሳ
ተነሳ ወገን ተነሳ
የጥንቱ እንዳይረሳ
የቀድሞው እንዳይረሳ
ከኛ የሚመስሉ ግን ከኛ ያልሆኑ
አሉ በጥፋት ላይ የሚሰለጥኑ
መክረን አስተምረን እንበል ተመለስ
እንቢ ካለወጉስ ከመአርዮስ
ተነሳ ወገን ተነሳ
ተነሳ ክርስቲያን ተነሳ
ዶግማችን እንዳይረሳ
ቀኖናው እንዳይረሳ
መዝሙሩ የመምህር ምርተአብ አሰፋና
የዘማሪ ኤርሚያስ አሰፋ ነው።
ለወንድሞቻችን አጥንት የሚያለመል
ዝማሬ መልዕክት ያስማልን

http://www.zemaretube.com/new-ethiopian-orthodox-gospel-song-by-memihr-mihretabe-asefa-and-zemari-ermiya-asefa_849cfd32f.html

New Ethiopian Orthodox Gospel Song By Memihr Mihretabe Asefa and Zemari Ermiya Asefa...

14/10/2016

1 #ተጠራጣሪው ደቀ መዝሙር ማነው ?
2 #የመጀመርያው አቢዮተኛስ ?

Address

Asella
Assela

Telephone

+251923323403

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when አሰላ ደብረ ምፅላል ቅድስት ማርያም ሰንበት ትምህርት ቤት posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Place Of Worship

Send a message to አሰላ ደብረ ምፅላል ቅድስት ማርያም ሰንበት ትምህርት ቤት:

Share