የቤ/ጉ/ክ/እስ/ጉ/ከ/ም/ ቤት-المجلس العالي للشؤون الاسلامية باقليم بنى شنقول قمز

  • Home
  • Ethiopia
  • Asosa
  • የቤ/ጉ/ክ/እስ/ጉ/ከ/ም/ ቤት-المجلس العالي للشؤون الاسلامية باقليم بنى شنقول قمز

የቤ/ጉ/ክ/እስ/ጉ/ከ/ም/ ቤት-المجلس العالي للشؤون الاسلامية باقليم بنى شنقول قمز Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from የቤ/ጉ/ክ/እስ/ጉ/ከ/ም/ ቤት-المجلس العالي للشؤون الاسلامية باقليم بنى شنقول قمز, Religious organisation, asossa, Asosa.

نشر القيم الإسلامية، وتعزيز الوحدة، وخدمة المجتمع بإخلاص.
قسم الاعلام والعلاقات العامة بالمجلس العالى للشؤون الإسلامية في اقليم بني شنقول-قمز.

የእስልምና እሴቶችን ማስፋፋት፣ አንድነትን ማጠናከር፣ ማህበረሰብን በቅንነት ማገልገል።
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት የህዝብ ግኑኝነት ክፍል።

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የእስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት በ1447 አ.ሂ/2018 ዓ.ል. ከኢትዮጵያ እስልምና ጠቅላይ ምክር ቤት ሁለት ከፍተኛ የእውቅናና የሽልማት ሽልማቶችን አግኝቷል።...
30/07/2026

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የእስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት በ1447 አ.ሂ/2018 ዓ.ል. ከኢትዮጵያ እስልምና ጠቅላይ ምክር ቤት ሁለት ከፍተኛ የእውቅናና የሽልማት ሽልማቶችን አግኝቷል።
━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━
ሐምሌ 23 /2018 ዓ.ል | ሰፈር 16/1448 ዓ.ሂ| አሶሳ

بِسْمِ ٱللَّٰهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ

━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━
ይህ ዕውቅና ምክር ቤቱ በሃይማኖታዊ አገልግሎት፣ በተቋማዊ ግንባታ፣ በአስተዳደራዊ ብቃት እና ለማኅበረሰቡ በሰጠው ውጤታማ አገልግሎት የተገኘ ከፍተኛ እውቅና መሆኑን ያሳያል።

ምክር ቤቱ ወደፊትም በተመሳሳይ ቁርጠኝነትና ትጋት ለእስልምና አገልግሎት እና ለሕዝብ ጥቅም መስራቱን ይቀጥላል።
━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━
መረጃው፦ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት የሕዝብ ግንኙነት ክፍል።

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የእስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ልዑካን የኢትዮጵያ እስልምና ጠቅላይ ምክር ቤት የአስተዳደራዊ ጉዳዮችና ተቋማዊ ልህቀት ምክትል ፕሬዚዳንት ኡስታዝ ተምኪን አብዱ...
30/07/2026

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የእስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ልዑካን የኢትዮጵያ እስልምና ጠቅላይ ምክር ቤት የአስተዳደራዊ ጉዳዮችና ተቋማዊ ልህቀት ምክትል ፕሬዚዳንት ኡስታዝ ተምኪን አብዱላሂን በቢሯቸው ጎበኙ።
━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━
ሐምሌ 23 /2018 ዓ.ል | ሰፈር 16/1448 ዓ.ሂ|

አዲስ አበባ

بِسْمِ ٱللَّٰهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ

━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የእስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ምክትል ፕሬዚዳንት ሸይኽ ዑመር ሐጅ አኑር፣ የምክር ቤቱ የሐጅና ዑምራ ዘርፍ ተጠሪ ሸይኽ ጅብሪል ዩኑስ፣ እንዲሁም ሌሎች የምክር ቤቱ ኃላፊዎችና እንግዶች በቅርቡ የሥራ ጉብኝት በማድረግ የኢትዮጵያ እስልምና ጠቅላይ ምክር ቤት የአስተዳደራዊ ጉዳዮችና ተቋማዊ ልህቀት ምክትል ፕሬዚዳንት ኡስታዝ ተምኪን አብዱላሂን በቢሯቸው ጎብኝተዋል።

በጉብኝቱ ወቅት በሁለቱ ተቋማት መካከል ያለውን የሥራ ትስስር የበለጠ ለማጠናከር፣ በተቋማዊ አቅም ግንባታ፣ በአስተዳደራዊ ልህቀት እና በቀጣይ በጋራ ሊከናወኑ በሚችሉ የሥራ መርሃ ግብሮች ላይ ገንቢ ውይይት ተደርጓል።
━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━
መረጃው፦ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት የሕዝብ ግንኙነት ክፍል።

መልካም ዜና | የዕውቅና ሽልማት 🏅«በአማና የተፈጸመ አገልግሎት፤ በክብር የሚዘከር ስኬት!»━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━ሐምሌ 23 /2018 ዓ.ል | ሰፈር 16/1448 ዓ.ሂ| አዲስ ...
30/07/2026

መልካም ዜና | የዕውቅና ሽልማት 🏅

«በአማና የተፈጸመ አገልግሎት፤ በክብር የሚዘከር ስኬት!»
━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━
ሐምሌ 23 /2018 ዓ.ል | ሰፈር 16/1448 ዓ.ሂ|

አዲስ አበባ

بِسْمِ ٱللَّٰهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ

━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━
በ1447 ዓ.ሂ / 2018 ዓ.ል የሐጅ አገልግሎት አፈጻጸም ላይ ለተመዘገበው የላቀ ስኬት፣ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የእስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት የሐጅና ዑምራ ዘርፍ ከኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የሐጅና ዑምራ ዘርፍ የዕውቅና ምስክር ወረቀት በመቀበሉ ከፍተኛ ደስታና ኩራት ተሰምቶናል።

በዚህ የዕውቅና ሥነ-ሥርዓት ላይ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የእስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ምክትል ፕሬዚዳንት ሸይኽ ዑመር ሐጅ አኑር፣ የምክር ቤቱ የሐጅና ዑምራ ዘርፍ ተጠሪ ሸይኽ ጅብሪል ዩኑስ እንዲሁም ሌሎች የምክር ቤቱ ኃላፊዎችና እንግዶች በመገኘት መርሃ ግብሩ በክብር ተከናውኗል።

ይህ የዕውቅና ሽልማት በሐጅ አገልግሎት ላይ ለታየው ታማኝነት፣ ትጋት፣ ቅንነትና ከፍተኛ የአገልግሎት ጥራት የተሰጠ እውቅና ሲሆን፣ ለምክር ቤታችን እንዲሁም ለመላው የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ሙስሊም ማህበረሰብ ትልቅ ኩራት ነው።

ይህ ስኬት የአላህ (ሱ.ወ) ችሮታ፣ የአመራሩ፣ የባለሙያዎችና የሁሉም አካላት የጋራ ትጋት ፍሬ መሆኑን እየገለጽን፣ ወደፊትም የበለጠ ጥራት ያለውና በአማና የተመሰረተ የሐጅና ዑምራ አገልግሎት ለመስጠት በተመሳሳይ ቁርጠኝነት እንቀጥላለን።

እንኳን ደስ አላችሁ! አላህ (ሱ.ወ) መልካም ሥራችሁን ይቀበል፣ በመጪዎቹም ዓመታት የበለጠ ስኬትና በረከት ይወፍቃችሁ።🤲
━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━
መረጃው፦ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት የሕዝብ ግንኙነት ክፍል።

«ኢትዮጵያ አልታዘሉ ያሉ ትርክቶቿን ወደ ኋላ በመተው፣ በምክክር፣ በመግባባት እና በሰላም ወደ አዲስ ምዕራፍ እየተሻገረች ነው።»ያ አላህ! ኢትዮጵያችንን የተሻለች፣ የበለጸገች፣ ሰላሟ የተረጋ...
28/07/2026

«ኢትዮጵያ አልታዘሉ ያሉ ትርክቶቿን ወደ ኋላ በመተው፣ በምክክር፣ በመግባባት እና በሰላም ወደ አዲስ ምዕራፍ እየተሻገረች ነው።»

ያ አላህ! ኢትዮጵያችንን የተሻለች፣ የበለጸገች፣ ሰላሟ የተረጋገጠ፣ ለባርያዎችህ ምቹና የፍትሕ ሀገር አድርግልን።
🤲🇪🇹

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሸይኽ ኢብራሂም ሙሐመድ ስራጅ!

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የፋይናንስ አካታችነት ምክር ቤት፣ ግብረ ኃይል (Taskforce) እና የክልሉ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት በሶማሌ ክልል የልምድ ልውውጥ ጉብኝት አካሄዱ።━━...
25/07/2026

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የፋይናንስ አካታችነት ምክር ቤት፣ ግብረ ኃይል (Taskforce) እና የክልሉ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት በሶማሌ ክልል የልምድ ልውውጥ ጉብኝት አካሄዱ።
━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━
ሐምሌ 18 /2018 ዓ.ል | ሰፈር 09/1448 ዓ.ሂ|

ሱማሌ - ጂግጂጋ

بِسْمِ ٱللَّٰهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ

━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የፋይናንስ አካታችነት ምክር ቤት፣ ግብረ ኃይል (Taskforce) እና የክልሉ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ልዑካን በሶማሌ ክልል የልምድ ልውውጥና የሥራ ጉብኝት እያካሄዱ ይገኛሉ።

በዚህ የልምድ ልውውጥ ጉብኝት የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት የኢስላማዊ ተቋማትና የማህበራት አስተዳደር ዘርፍ ተጠሪ ሸይኽ ሐመድነላህ አብዱላሂ ኢብራሂም እና የመጅሊሱ ዋና ፀሐፊ እንዲሁም የመስጂዶችና የአውቃፍ ዘርፍ ተጠሪ ኡስታዝ አደም ሐሰን ደፍዐላህ ተሳትፈዋል።

የጉብኝቱ ዋና ዓላማ በሸሪዓን የሚያከብር (Sharia-Compliant) የፋይናንስ ሥርዓት፣ በእስላማዊ ተቋማት አስተዳደር፣ በመስጂዶች አመራር፣ በአውቃፍ አስተዳደር እና በማህበራት አደረጃጀት ዙሪያ ያሉ ልምዶችን ለመቀያየር እንዲሁም በሁለቱ ክልሎች መካከል ያለውን የተቋማት ትብብር ለማጠናከር ነው።

በቆይታቸውም በሶማሌ ክልል የሚገኙ የተለያዩ እስላማዊ ተቋማትን በመጎብኘት ተግባራዊ የሥራ ልምዶችን እየተመለከቱ ሲሆን፣ ይህ ጉብኝት በሸሪዓን የሚያከብር የፋይናንስ አገልግሎት ዕውቀትን እና ተግባራዊ ልምድን በማጠናከር እንዲሁም በሁለቱ ክልሎች መጅሊሶች መካከል ያለውን የጋራ ግንኙነትና ትብብር ይበልጥ እንደሚያጠናክር ይጠበቃል።
━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━
መረጃው፦ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት የሕዝብ ግንኙነት ክፍል።

━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━ሐምሌ 17 /2018 ዓ.ል | ሰፈር 08/1448 ዓ.ሂ| አዲስ አበባ                                   بِسْمِ ٱللَّٰهِ ٱلرَ...
24/07/2026

━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━
ሐምሌ 17 /2018 ዓ.ል | ሰፈር 08/1448 ዓ.ሂ|

አዲስ አበባ

بِسْمِ ٱللَّٰهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ

━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━
በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምክክር ኮሚሽን በተዘጋጀው የምክክር ሂደት ላይ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሸይኽ ኢብራሂም ሙሐመድ ስራጅ፣ የመጅሊሱ ምክትል ፕሬዚዳንት ሸይኽ ዑመር ሓጅ አኑር
የህዝብ ግንኙነት ክፍል ተጠሪ ሓጅ ሙሐመድ አማን ሙስጠፋ፣ የመጅሊሱ ምክትል ፕሬዚዳንት ሸይኽ ዑመር ሓጅ አኑር፣ የአሶሳ ከተማ አስተዳደር እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሸይኽ አሳዲቅ አብዱልጀሊል እንዲሁም ሌሎች የክልሉ ሙስሊም ማህበረሰብ ተወካዮች በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምክክር ሂደት ላይ በንቃት እየተሳተፉ ይገኛሉ።

ይህ ሀገራዊ ምክክር የመግባባት፣ የሰላም እና የፍትሕ መሠረት እንዲሆን፣ እንዲሁም የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ለረጅም ዓመታት ሲያነሷቸው የቆዩ ጥያቄዎች ተገቢውን ትኩረትና ፍትሐዊ ምላሽ እንዲያገኙ ተስፋችን ጽኑ ነው።

አላህ ሀገራችንን በሰላም፣ በፍትሕ እና በአንድነት ይባርክ።

━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━
መረጃው፦ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት የሕዝብ ግንኙነት ክፍል።

በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ዑለማእ ጉባዔ፣ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት እና በቡኒያን ዓለም ዓቀፍ ዩኒቨርስቲ ትብብር ለ100 ኢማሞችና ኡ...
09/07/2026

በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ዑለማእ ጉባዔ፣ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት እና በቡኒያን ዓለም ዓቀፍ ዩኒቨርስቲ ትብብር ለ100 ኢማሞችና ኡስታዞች የተሰጠው የአቅም ግንባታ ስልጠና ተጠናቀቀ።
━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━
ሐምሌ 02/2018 ዓ.ል | ሙሐረም 24/1448 ዓ.ሂ-አሶሳ

بِسْمِ ٱللَّٰهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ

━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━
በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ዑለማእ ጉባዔ፣ ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤትና ከቡኒያን ዓለም ዓቀፍ ዩኒቨርስቲ ጋር በመተባበር በአሶሳ ከተማ ለክልሉ ኢማሞችና ኡስታዞች የተዘጋጀው የአቅም ግንባታ ስልጠና ዛሬ በይፋ ተጠናቋል።
ስልጠናው ለስድስት ተከታታይ ቀናት በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ግብርና ኮሌጅ የተሰጠ ሲሆን፣ 50 ኢማሞችና 50 ኡስታዞች በድምሩ 100 የሃይማኖት አገልጋዮች ተሳትፈውበታል። በስልጠናውም ተሳታፊዎቹ በእስላማዊ እውቀት፣ በዳዕዋ፣ በሰላም ግንባታ፣ በማኅበራዊ ኃላፊነት፣ በአመራር ክህሎት እና በወቅታዊ አገራዊ ጉዳዮች ላይ ሰፊ ስልጠና አግኝተዋል።
የስልጠናው ማጠቃለያ ፕሮግራም በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሸይኽ ኢብራሂም ሙሐመድ ስራጅ፣ ምክትል ፕሬዚዳንት ሸይኽ ዑመር ሐጅ አኑር፣ ሸይኽ ሷሊህ ሙሐመድ እና ሌሎች የመጅሊሱ አመራሮች በተገኙበት ተካሂዷል።
በፕሮግራሙ ላይ አሰልጣኞች ለሰልጣኞች በስድስቱ ቀናት የቀሰሙትን እውቀት በተግባር በማዋል የሰላም፣ የአንድነት፣ የመቻቻልና የትክክለኛ እስላማዊ እሴቶች አስፋፊዎች ሆነው ማኅበረሰባቸውን በብቃት እንዲያገለግሉ አደራ ሰጥተዋል።
በማጠቃለያውም ለስልጠናው በሙሉ ተሳትፎ ላደረጉት 50 ኢማሞችና 50 ኡስታዞች በድምሩ 100 ሰልጣኞች የስልጠና ማረጋገጫ (Certificate) በክብር ተሰጥቷቸዋል።
በመጨረሻም የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሸይኽ ኢብራሂም ሙሐመድ ስራጅ ባደረጉት የመዝጊያ ንግግር፣ ሰልጣኞች የተማሩትን እውቀት በተግባር በመተርጎም በየአካባቢያቸው ለሰላም፣ ለአንድነት፣ ለመልካም ሥነ-ምግባርና ለትክክለኛ እስላማዊ እሴቶች መጠናከር የበኩላቸውን ኃላፊነት በብቃት እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል። በተጨማሪም መጅሊሱ ተመሳሳይ የአቅም ግንባታ መርሃ ግብሮችን በቀጣይነት እንደሚያጠናክር ገልጸዋል።
በመጨረሻም ለስልጠናው ስኬታማነት አስተዋፅኦ ላበረከቱ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ዑለማእ ጉባዔ፣ ለቡኒያን ዓለም ዓቀፍ ዩኒቨርስቲ፣ ለአሰልጣኞች፣ ለሰልጣኞች እና ለሁሉም የፕሮግራሙ ተባባሪዎች ምስጋና ቀርቧል።
━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━
መረጃው፦ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት የሕዝብ ግንኙነት ክፍል።

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ፕሬዚዳንትና ምክትል ፕሬዚዳንት በስልጠና ላይ የሚገኙ ኢማሞችና ኡስታዞችን ጎበኙ።        ━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━ሰኔ...
07/07/2026

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ፕሬዚዳንትና ምክትል ፕሬዚዳንት በስልጠና ላይ የሚገኙ ኢማሞችና ኡስታዞችን ጎበኙ።
━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━
ሰኔ 30/2018 ዓ.ል | ሙሐረም 21/1448 ዓ.ሂ-አሶሳ

بِسْمِ ٱللَّٰهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ

━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━
ዛሬ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሸይኽ ኢብራሂም ሙሐመድ ስራጅ እና ምክትል ፕሬዚዳንት ሸይኽ ዑመር ሓጅ አኑር ሓሚድ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ግብርና ኮሌጅ በስልጠና ላይ የሚገኙ ኢማሞችና ኡስታዞችን ጎብኝተዋል።

በኮሌጁ እየተሰጠ ያለው ስልጠና በታዋቂው ዓሊም ሸይኽ ሙሐመድ ፈረጅ እና ከኢትዮጵያ ሙስሊሞች ጠቅላይ ምክር ቤት በመጡ ሌሎች ምሁራንና ኡስታዞች እየተሰጠ ሲሆን፣ በእስልምና ትምህርት፣ በዳዕዋ ሥራ፣ በማኅበረሰብ ግንኙነት እና በወቅታዊ ማኅበራዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ መሆኑን ተገልጿል።

በጉብኝቱ ወቅት የምክር ቤቱ አመራሮች ከሰልጣኞቹ ጋር ሰፊ ውይይት በማድረግ የስልጠናውን ሂደት የተመለከቱ ሲሆን፣ ኢማሞችና ኡስታዞች በማኅበረሰቡ ውስጥ የሰላም፣ የአንድነት፣ የመልካም ሥነ-ምግባር እና የትክክለኛ እስላማዊ እሴቶችን በማጠናከር ያላቸውን ሚና የበለጠ እንዲያጠናክሩ አሳስበዋል።

በተጨማሪም ሰልጣኞቹ ከስልጠናው የሚያገኙትን እውቀትና ልምድ ወደ ማኅበረሰቡ በማውረድ ለክልሉ ዘላቂ ሰላም፣ አንድነትና ልማት የበኩላቸውን አስተዋፅኦ እንዲያበረክቱ ጥሪ ቀርቧል።
━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት
የህዝብ ግንኙነት ክፍል።

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሸይኽ ኢብራሂም ሙሐመድ ስራጅ እና ምክትል ፕሬዚዳንት ሸይኽ ዑመር ሐጅ አኑር ከክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ጋር በመሆን ከ...
07/07/2026

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሸይኽ ኢብራሂም ሙሐመድ ስራጅ እና ምክትል ፕሬዚዳንት ሸይኽ ዑመር ሐጅ አኑር ከክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ጋር በመሆን ከኢማሞችና ከኡስታዞች ጋር በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ሰፊና ጥልቅ ውይይት አካሄዱ።
━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━
ሰኔ 30/2018 ዓ.ል | ሙሐረም 21/1448 ዓ.ሂ-አሶሳ

بِسْمِ ٱللَّٰهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ

━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሸይኽ ኢብራሂም ሙሐመድ ስራጅ እና ምክትል ፕሬዚዳንት ሸይኽ ዑመር ሐጅ አኑር ከክልሉ ከፍተኛ አመራሮች፣ ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሴቶችና ህፃናት ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ምክትል ኃላፊ ወይዘሮ መርየም አብዱረህማን፣ ከክልሉ ምክር ቤት የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ወይዘሮ ሁዳ አልኽድር እንዲሁም ከክልሉ ጠቅላይ ሸርዒያ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ሸይኽ አልሐሰን አልመዕሙን ጋር በመሆን፣ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ግብርና ኮሌጅ በስልጠና ላይ ከሚገኙ ኢማሞችና ኡስታዞች ጋር በወቅታዊ አገራዊና ማኅበራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ሰፊና ጥልቅ ውይይት አካሂደዋል።

በውይይቱ ወቅት በተለይ በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ እየተስፋፉ የሚገኙ ፈሳዳዊ ይዘቶች በማኅበረሰቡ እሴት፣ አንድነትና ሰላም ላይ የሚያሳድሩት አሉታዊ ተጽዕኖ፣ እንዲሁም በጋብቻ ላይ ከአቅም በላይ የሆነ የጥሎሽና የወጪ ጫና የሚያስከትለው ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጽዕኖ ላይ ሰፊ ውይይት ተካሂዷል።

በመድረኩ ላይ ከሰልጣኞቹ የተነሱ የተለያዩ ጥያቄዎችና አስተያየቶች በመጅሊሱ አመራሮች፣ በክልሉ ከፍተኛ አመራሮች እና በተሳታፊ ተቋማት ኃላፊዎች በጋራ ምላሽ የተሰጠባቸው ሲሆን፣ ቀጣይ የሥራ አቅጣጫዎችም በግልጽ ተቀምጠዋል።

በመጨረሻም ኢማሞችና ኡስታዞች በማኅበረሰቡ ውስጥ የሰላም፣ የአንድነት፣ የመልካም ሥነ-ምግባር እና የትክክለኛ እስላማዊ እሴቶችን በማጠናከር ያላቸውን ኃላፊነት በብቃት እንዲወጡ ጥሪ ቀርቦ፣ ለክልሉና ለሀገሪቱ ዘላቂ ሰላም፣ አንድነትና ልማት የበኩላቸውን አስተዋፅኦ እንዲያጠናክሩ አፅንኦት ተሰጥቷል።

━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት የሕዝብ ግንኙነት ክፍል።

Address

Asossa
Asosa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የቤ/ጉ/ክ/እስ/ጉ/ከ/ም/ ቤት-المجلس العالي للشؤون الاسلامية باقليم بنى شنقول قمز posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share