14/08/2026
አሳዛኝ ዜና
በአሰቦት ደብረ ወገግ ቅድስት ሥላሴና አቡነ ሳሙኤል አንድነት ገዳም ባልታወቁ ኃይሎች አንድ መነኩሴ አባት አንገታቸው ላይ በጬቤ ተወጉ ።
✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝
✍ የገዳሙ አገልጋይ በሆኑት አባ ተክለ ዮሐንስ ደረሰ በተባሉ አባት በእንጨት ለቀማ ላይ እያሉ ዛሬ ነሐሴ 8 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 5:30 አካባቢ አደጋው እንደደረሰ ለሀገረ ስብከቱ ጽ/ቤት መረጃውን ገዳሙ አድርሶናል።
✍ ታጣቂዎቹ አባ ተክለ ዮሐንስ ደረሰ የተባሉ አገልጋይ መንኩሴ አባት በአሰቃቂ ሁኔታ ጉሮሯቸውን ወግተው ለመግደል ሲሞክሩ ለማምለጥ የቻሉ ሲሆን ገዳሙም በህይወትና በሞት መካከል ያሉትን አባት ወደ ህክምና የወሰዱ መሆናቸውን ገልጸው እየደረሰባቸው ያለውን ተደጋጋሚ ጥቃት ለሚመለከታቸው አካላት መረጃውን አድርሱልን በማለት አቅርበዋል።
✍ የሀገረ ስብከቱም ጽ/ቤት በአሰቦት ደብረ ወገግ ቅድስት ሥላሴና አቡነ ሳሙኤል አንድነት ገዳም ተደጋጋሚ ጥቃቶችና ችግር እንዲቀረፍና ገዳማውያኑም በተረጋጋ ሁኔታ እንዲኖሩና ለሀገር እንዲፀልዩ የመንግስት የፀጥታ አካላት መፍትሄ እንዲሰጥና ክትትል እንዲያደርግ ለሚመለከተው የዞኑ የፀጥታ አካላት የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ እንጦንስና የሀገረ ስብከቱ ጽ/ቤት ሪፖርት በማድረግ ክትትል እያደረጉ መሆኑን ይገልጻል።
ነሐሴ 8/2018 ዓ/ም
ጭሮ - ኢትዮጵያ
መረጃው የምዕራብ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት ገጽ ነው