በአፋር ሀገረ ስብከት የአይሳኢታ ደብረ ምጥማቅ ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን የመርሀ ህይወት ሰንበት ት/ቤት

  • Home
  • Ethiopia
  • Asaita
  • በአፋር ሀገረ ስብከት የአይሳኢታ ደብረ ምጥማቅ ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን የመርሀ ህይወት ሰንበት ት/ቤት

በአፋር ሀገረ ስብከት የአይሳኢታ ደብረ ምጥማቅ ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን የመርሀ ህይወት ሰንበት ት/ቤት ye ethiopia ortodox tewahdo bete kristiyan dogma Ena kenona yetebeke timhrt mestet Ena yetefu abalat mesebasebiya eruk ager lalut megenagna new

25/02/2025

ዘወረደ የመጀመሪያው ሳምንት

25/02/2025
25/02/2025

እንኳን ለታላቁ ዐብይ ፆም በሰላም አደረሰን

26/12/2023
02/05/2021

በእዚህ ጉባኤ ውስጥ ተገኝተህ " #ተነስቷል" ሲባል እንደመስማት ነፍስን ሰብቆ የሚይዝ ደስታ ከወዴት ይገኛል?
~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~

በእዚህች ቅዱስት ምሽት ከጓደኞችህ ጋር ሆነህ ጠረጴዛ ከበኸ የሆድ የሆድህን እያወጋህ አንድ ሁለት በማለትህ ..... ደስ የሚል ስሜት እንደሚሰማህ ታስብ ይሆናል

የትንሳኤው ማብሰርያ ዕለት በሆነችው ምሽት ላይ ሆነህ ከምትወዳት የሴት ጓደኛህ ጋር በሻማ በተዋቡ ምሽቶች ላይ ተሰይመህ ወደ ሌላኛው የፍቅር ዓለም ውስጥ መንጎድህ .....ልብህ አይቶ በማያውቀው የደስታ መዕበል ውስጥ እንደተዘፈቀ ታስብም ይሆናል።

ምናልባትም ለነገ የፋሲካ በዓል ማብሰሪያነት ዛሬ ላይ እየተብለጨለጩ ህሊናን በሚያናውዙ መብራቶች በተፐውዘህ አስረሽ ምችው ጨዋታ ምቾት በአንድ ናይት ክለብ ውስጥ መውረግረግህ.....የፍፁም ደስታ ግኝት ሊመስልህ ይችላል።

በተሻረችው ቅዳሜ ላይ ሆነህ በናፍቆት ተጠራርተው በአንድ ጎጆ ውስጥ ተሰብስበው በናፍቆት በተገናኙ እልፍ ቤተዘመድ መሀል የባጡን የቆጡን እያወጋህ ማምሽተም .....የደስተኝነት ጥግ ውስጥ ያስቀመጠህ ሊመስል ይችላል

ወዳጄ ..የእውነት ግን እመነኝ ።

ፀሐይ ዑደቷን ጨርሳ በሰረገችበት በእዛ እኩል ለሊት፤....ሰዎች እና ከተሞች ተኝተው በሚያንኮራፉበት በእዚህ ድቅድቅ ሰዓት .........

ካህናት በዘረጉት የምስጋና ጉባኤ ላይ ተገኝተህ፤ውዳሴ በማይነጥፍበት ማህሌት ውስጥ ቆመህ፤ የዕለት ምስባክ ሰምተህ፤በቅዱስ ወንጌሉ ቃል ሐሴት አድርገህ ፤"አሃዱ አብ ቅዱስ...እየተባለ ተጀምሮ እትሁ በሰላም ተብሎ እስኪጠናቀቅ ድረስ በተስጦ ግብረ መልስ ከቅዳሴው ጋር ህብረት አድርገህ.......... #ተነስቷል.......ሲባል እንደመስማት ነፍስን ሰብቆ የሚያዝ ደስታ ከወዴት ይገኛል?

የከበሮው ምት፤የመቋሚያው ድምድምታ፤የጽናጽኑ ድምጽ አንድ ላይ ህብረት ሰርተው የትንሳኤውን የምስራች ሲያበስሩ ስትሰማ መግደላዊት ማርያም የተገኘችበት ቦታ ላይ የቆምክ ይመስላል።

ህብስት ተነፍጎ ነገር ግን ድካም በሌለው ብርቱ ድምጽ "ትንሳኤከ ለእለ አመነ -ብርሃነከ ፈኑ ዲቤነ" የሚለውን ዝማሬ መቅደስ ውስጥ እንደመዘመር የነፍስ ህብስቷ ከወዴት ይገኛል?

ይህን ጥቅል መንፈሳዊ ሚስጢር እና ረቂቅ እውነት በእዚህች በምድር በተተከለች የሰማያዊ መንግስቱ አካል በሆነችው ጉባኤ ውስጥ ናት።

የቴሌግራም ቻናላችን ሊንክን በመስፈንጠር ቤተሰብ ይሁኑን፤

via Kune Demelash Kassaye

t.me/southethiopiaorthodoxy

Address

Asaita

Telephone

+251335550244

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when በአፋር ሀገረ ስብከት የአይሳኢታ ደብረ ምጥማቅ ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን የመርሀ ህይወት ሰንበት ት/ቤት posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Place Of Worship

Send a message to በአፋር ሀገረ ስብከት የአይሳኢታ ደብረ ምጥማቅ ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን የመርሀ ህይወት ሰንበት ት/ቤት:

Share