Grace Media

Grace Media “ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አለው፦ ከትእዛዛቱ ሁሉ ፊተኛይቱ፦ እስራኤል ሆይ፥ ስማ፤ ጌታ አምላካችን አንድ ጌታ ነው፥”
— ማርቆስ 12፥29

 በዋራ ጉባዔ መሪያችን ቢሾፕ ደጉ እስካበሰሩን ሰዓት ድረስ 12,296 ሰዎች ድነው የነበሩ ቢሆንም ከሪፖርቱ በኋላ በተጨመሩ አዳዲስ ሰዎች ምክንያት እስከ ጉባዔ መዝጊያ ድረስ አጠቃላይ የዳኑ...
22/03/2026


በዋራ ጉባዔ መሪያችን ቢሾፕ ደጉ እስካበሰሩን ሰዓት ድረስ 12,296 ሰዎች ድነው የነበሩ ቢሆንም ከሪፖርቱ በኋላ በተጨመሩ አዳዲስ ሰዎች ምክንያት እስከ ጉባዔ መዝጊያ ድረስ አጠቃላይ የዳኑት ሰዎች ቁጥር #12,409 ሰዎች በመድረስ ጉባዔው ተጠናቅቋል።

ደንቅ አምልኮ በ35ኛዉ ዋራ ቤቴል
17/03/2026

ደንቅ አምልኮ በ35ኛዉ ዋራ ቤቴል

35th wara bethel Amazing Worship

ታሪካዊው የ  #ዋራቤቴል 2018 ጉባኤ በበዓለ ሃምሳ ዕለት በኢየሱስ ስም ከተጠመቁት በአራት እጥፍ ከ12 ሺህ በላይ ነፍሳት በኢየሱስ ስም በማስጠመቅ ተጠናቀቀለአራት ተከታታይ ቀናት በሲዳማ ...
16/03/2026

ታሪካዊው የ #ዋራቤቴል 2018 ጉባኤ በበዓለ ሃምሳ ዕለት በኢየሱስ ስም ከተጠመቁት በአራት እጥፍ ከ12 ሺህ በላይ ነፍሳት በኢየሱስ ስም በማስጠመቅ ተጠናቀቀ

ለአራት ተከታታይ ቀናት በሲዳማ ክልል ዋራ ሜዳ ላይ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ምዕመናን ሲሳተፉበት የነበረው 35ኛው የአለም አቀፍ ሐዋሪያዊት ቤተክርስቲያን ታላቅ ዓመታዊ ኮንፈረንስ ( #ዋራቤቴል) በዛሬው ዕለት በታላቅ መንፈሳዊ ስኬትና በሰላም ተጠናቋል።

ከባለፈው ሐሙስ ጀምሮ እስከ ዛሬው የማጠቃለያ ዕለት ድረስ በነበረው መንፈሳዊ አገልግሎት፣ 12,296 (አሥራ ሁለት ሺህ ሁለት መቶ ዘጠና ስድስት) ነፍሳት ብቻውን አምላክ የሆነውን ኢየሱስ ክርስቶስን በማመንና ለኃጢአታቸው ስርየት በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም መጠመቃቸው ታውቋል።

ይህ ቁጥር በመጽሐፍ ቅዱስ በሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ ሁለት ላይ፣ በበዓለ ሃምሳ ዕለት በኢየሱስ ስም ከተጠመቁት ሦስት ሺህ ሰዎች በላይ በመሆኑ፣ ጉባኤው በዘመናችን የታየ ታላቅ ተአምርና መንፈሳዊ መነቃቃት ተደርጎ ተወስዷል።

በዋራ ሜዳ ላይ የተከናወነውን ይህን ታላቅ መንፈሳዊ ድልና ተአምራት ተከትሎ፣ ከአንድ ሚሊዮን በላይ የሚቆጠሩ ምዕመናን ለፈጣሪያቸው ታላቅ ምስጋና አቅርበዋል።

በደዌና በአጋንንት እስራት የነበሩ መፈታታቸውንና በንስሐ ወደ አምላካቸው የተመለሱት ቁጥር እጅግ ከፍተኛ መሆኑ ጉባኤውን ልዩ ያደርገዋል።

ይህ ጉባኤ በኢትዮጵያም ሆነ በዓለም ደረጃ ይህን ያህል ቁጥር ያለው ሕዝብ ያለ ምንም የዘርና የነገድ ልዩነት ከየአቅጣጫው በአንድነት የሚሰበሰብበት ብቸኛ ቦታ ነው ማለት ይቻላል።

ያለ ምንም የዘርና የነገድ ልዩነት ከዓለም ዙሪያ የመጡ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች በአንድ ልብ አምላካቸውን ያመሰገኑበት ይህ ጉባኤ፣ ለሲዳማ ክልልም ሆነ ለኢትዮጵያ የሰላምና የመቻቻል ትልቅ ማሳያ ሆኖ አልፏል።

ከሃይማኖታዊ ፋይዳው ባሻገር፣ ክልሉን ለዓለም በማስተዋወቅና የቱሪዝም አቅምን በማሳደግ ረገድም ጉልህ ሚና ተጫውቷል።

የአለም አቀፍ ሐዋሪያዊት ቤተክርስቲያን አመታዊ ኮንፈረንስ በዛሬው ዕለት በሰላም መጠናቀቁን ተከትሎ፣ ምዕመናን ወደየመጡበት አካባቢ በመመለስ ላይ ይገኛሉ።


#ዋራቤቴል #ኢትዮጵያ

35th Wara Bethel On pics
14/03/2026

35th Wara Bethel On pics

13/03/2026

35th wara bethel

11/03/2026

09/03/2026

Amesginewalew

Ameeen.....
09/03/2026

Ameeen.....

ሰላም ለቅዱሳን በሙሉ!የኢትዮጵያ ሐዋርያዊት ቤተክርስቲያን ኦዲዮቪዥዋልና ስነ-ጽሑፍ ክፍል በዘማሪት ኢየሩሳሌም መዝገቡ የተዘጋጀውንና “እንደገና ታነሳለህ” የተሰኘውን የዝማሬ ሰንዱቅ ሲያቀርብ...
28/02/2026

ሰላም ለቅዱሳን በሙሉ!

የኢትዮጵያ ሐዋርያዊት ቤተክርስቲያን ኦዲዮቪዥዋልና ስነ-ጽሑፍ ክፍል በዘማሪት ኢየሩሳሌም መዝገቡ የተዘጋጀውንና “እንደገና ታነሳለህ” የተሰኘውን የዝማሬ ሰንዱቅ ሲያቀርብላችሁ በታላቅ ደስታ ነው።

የበጎ ስጦታ ፍጹምም በረከት ባለቤት የሆነው እግዚአብሔር በቤተክርስቲያን በኩል ለራሱ ክብር እና ለቅዱሳን መታነጽ በሚሆኑ የዝማሬ ስጦታ እየባረከ ስላለ እናመሰግነዋለን። ዝማሬዎቹንም በታላቅ መስዋእትነት የሚያዘጋጁትንም ቅዱሳን እንባርካለን።

በዚህ አድካሚ የዝማሬ አልበም መዝሙሮቹን በመቀበል በስጦታ ለቤተክርስቲያን ያበረከተችውን እህት ኢየሩሳሌምን ጨምሮ በተለያየ መንገድ የተሳተፉትን ሁሉ የቤተክርስቲያን አምላክ ኢየሱስ በማያልቀው በረከት እንዲባርክ ጸሎታችንም ምኞታችንም ነው።

አልበሙ በቅርብ ቀናት ውስጥ በApostolic Songs መተግበሪያ ላይ ዝግጁ የሚሆን ሲሆን ቅዱሳን ሁሉ ዝማሬዎቹን በተለያዩ የግዢ አማራጮች በማውረድ ጸጋውን፣ ቤተክርስቲያንን እና አገልግሎቱን ትደግፉ ዘንድ በኢየሱስ ፍቅር እናስታውሳለን።

የኢትዮጵያ ሐዋርያዊት ቤተክርስቲያን
ኦዲዮቪዥዋልና ስነ-ጽሑፍ ክፍል
የካቲት 2018 ዓ.ም

Address

Areka

Telephone

+251920579415

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Grace Media posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share