ወንድማችሁ ነኝ

ወንድማችሁ ነኝ Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from ወንድማችሁ ነኝ, Wolaita, Areka.
(4)

ወንድማችሁ ነኝ :- ሥራዬ የእግዚአብሔር አውነት መናገር እርሱም አንዱ እግዚአብሔር በሥጋ መገለጡ ነው።

ለሙሴ በእሳት ተገልጦ የተናገረ ለእኛ በ ልጁ ተናገረን ቃል ሥጋ በሆነው በሥጋ ተገልጦ ።

ወንጌል ዓለም ለማደረስ ማህበራዊ ሚድያ በዚህ ግዜ ወሳኝ ሆኖ ተገኝቷል ስለዚህ ከእኔ ጋር የወንጌል ሥራ ለሌሎች በማጋራት የዋጋ ተካፋይ እንድትሆኑ በክርስቶስ ፍቅር አሳስባለሁ።

በኢትዮጵያ ሐዋርያዊት ቤተክርስቲያን ደቡብ ኢትዮጵያ ሰበካ መሃል ወላይታ ቅርንጫፍ ሰበካ ላድሳ ንዑስ ሰበካ 2ኛው ዙር ወጣቶች ኮንፈረንስ በነፍሳት ትርፍ ተጠናቀቀ።ዕለት አርብ በእግር ጉዞ በ...
15/06/2026

በኢትዮጵያ ሐዋርያዊት ቤተክርስቲያን ደቡብ ኢትዮጵያ ሰበካ መሃል ወላይታ ቅርንጫፍ ሰበካ ላድሳ ንዑስ ሰበካ 2ኛው ዙር ወጣቶች ኮንፈረንስ በነፍሳት ትርፍ ተጠናቀቀ።

ዕለት አርብ በእግር ጉዞ በተጀመረው በዚህ ኮንፈረንስ ቅዳሜና እሁድ ሙሉ ቀን በላድሳ 01 አጥቢያ ቅጥር ግቢ ውስጥ የእግዚአብሔር ቃል በኃይል ተሰበከ።

በቅዳሜ ዕለት ዶክተር [ቄስ] ቸርነት ለቃ ለወጣቶች ይህን እውነት ወንጌል ሚስጥር በሚገባ አስተማሩ።

ለብዙዎች ይህ ወንጌል የተሰወረ ከመሆኑ የተነሳ በሰው አእምሮ ለመወሰን በተለያዩ ጉባኤ እየወሰኑ እንዳመጡ ታሪክ ይናገራል ለመሆኑ ለእኛ ግን ይህን የእውነት ወንጌል ሚስጥር ተገለጠልን ብዙዎች የእኛን መገለጥ ይጠበቃሉ እኛም መገለጥ እንዳለብን የእግዚአብሔር ቃል ይናገራል።

የደቡብ ኢትዮጵያ ወጣቶች ኃላፊ ቄስ አሸናፊ ሀመሎ:- ተኛችሁ ወይስ ነቅታችሁ ነው ያላችሁ ኢየሱስ ልመጣ ነው በሚል ርዕሰ ያስተማሩ ስሆን ፥የደቡብ ኢትዮጵያ ሰበካ ኃላፊ ቢሾፕ ብራሃኑ:- በፊትህ ስላለው ደስታ በዙሪያው ያለው ነውረኛ ንቄ ኢየሱስ ተመልከተህ ወደፊት ሩጥ በሚል ርዕሰ ወጣቶችን አስተማሩ።

በጉባኤ ከተገኙ የእግዚአብሔር ሰዎች መካከል የሶዶ እናት አጥቢያ ምክትል መጋቢት ቄስ አሉላ ኩሳም ለወጣቶች ገንቢ የሆኑ ትምርህት አስተማሩ እግዚአብሔር ለሁሉም ፀጋ ያብዛላችው።

በሌላው በኩል በዚህ ቀን በተደረገው የነፍሳት ጥሪ አጠቃላይ 39 ነፍሳት በሐዋርያት ትምህርት የተጨመሩ ስሆን 33 አድስ ነፍሳት እግዚአብሔር አንድ ነው ስሙም ኢየሱስ ክርስቶስ ነው በማለት አምኖ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም የተጠመቁ ስሆን 6 ነፍሳት በንስሐ ወደ አባታቸው ቤት ተመለሱ ክብር ምስጋና ለአንዱ ለእሥራኤል አምላክ ለኢየሱስ ክርስቶስ ይሁን።
አሜን

ለአሕዛብም ሁሉ ምስክር እንዲሆን ይህ የመንግሥት ወንጌል በዓለም ሁሉ ይሰበካል፥ በዚያን ጊዜም መጨረሻው ይመጣል።
ማቴዎስ 24:14
ወንድማችሁ ነኝ

14/06/2026

አምልኮ ለአንድ አምላክ እንዲሁ ነው
ኢየሱስ ይንገሥ በሰማይ በምድርም።
ወንድማችሁ ነኝ

14/06/2026

ጉሩሞ ንዑስ መዝሙራን

14/06/2026

ጉሩሞ ላድሳ ንዑስ ሰበካ ወጣቶች ኮንፈረንስ።
እሁድ ጧት ፕሮግራም
ወንድማችሁ ነኝ

ሚስጥሩ ክርስቶስ ነው ወይስ ሥላሴ ነው❓መጽሐፍ ቅዱስ "ምስጢር" ብሎ የሚጠራው ክርስቶስን ነው እንጅ ሥላሴ አይደለም።በክርስትና እምነትና ሥነ-መለኮት (Theology) መሠረት፣ መልሱ "ሁለቱ...
13/06/2026

ሚስጥሩ ክርስቶስ ነው ወይስ ሥላሴ ነው❓
መጽሐፍ ቅዱስ "ምስጢር" ብሎ የሚጠራው ክርስቶስን ነው እንጅ ሥላሴ አይደለም።

በክርስትና እምነትና ሥነ-መለኮት (Theology) መሠረት፣ መልሱ "ሁለቱም ሚስጥር ናቸው" የሚል ሃሳብ አንዳንድ የሃይማኖት ሰዎች ያነሳሉ ። ነገር ግን ሁለቱ ምስጥ መሆን አይችሉም ወይ ሥላሴ ወይ ክርስቶስ ምስጥር መሆን አለበት።

በየትኛውም ዓለም ሁለት ሚስጥር የለም ወይ ሥላሴን ወይም ክርስቶስ ሚስጥር ይሆናል። የግድ አንድ ምስጥር መምረጥ የመንፈሳዊ ግዴታ ነው፤ ስለዚህ ነገሩን ወደ አንድ ዋና ማዕከል ማጥበብና ከሁለቱ አንዱን የግድ መምረጥ ካለብን፣ በክርስትና አስተምህሮ መሠረት የመጨረሻውና ዋናው ሚስጥር "ክርስቶስ" ነው የሚል ሃሳብ በላይነት አግኝቷል ምስጢር ሥላሴ የሚለው በሰው ሃሳብ እንጂ በእግዚአብሔር ቃል የለም።

የግድ ክርስቶስን እንድንመርጥ የሚያደርጉን ሦስት ዋና ዋና ምክንያቶች አሉ፦

1ኛ. እግዚአብሔር የታየውና የተገለጠው በክርስቶስ ነው
የሰው ልጅ ረቂቁንና የማይታየውን የእግዚአብሔር ባሕርይ በምርምር ሊደርስበት አይችልም። ያ የማይደረስበት ምስጢር ግን ሥጋ ለብሶ፣ ተጨብጦና ታይቶ ለዓለም የተገለጠው በኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ስለዚህ ምስጢሩ ክርስቶስ ነው።

2ኛ. መጽሐፍ ቅዱስ "ምስጢር" ብሎ የሚጠራው ክርስቶስን ነው እንጅ ሥላሴ አይደለም።

ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በደብዳቤዎቹ ላይ "ምስጢር" የሚለውን ቃል በቀጥታ የተጠቀመው ለክርስቶስ ነው፦

ቈላስይስ 2፥2፦ "...የእግዚአብሔርን ምስጢር እርሱንም ክርስቶስን ለማወቅ..." ይላል።
ቃል በቃል ምስጢሩ ክርስቶስ እንደሆነ ይናገራል።

ቈላስይስ 1፥27፦ "...ይህም ምስጢር በእናንተ ዘንድ ያለው የክብር ተስፋ ክርስቶስ ነው።"

1ኛ ጢሞቴዎስ 3፥16፦ "እግዚአብሔር በሥጋ የተገለጠበት...
ምስጢር ያለ ጥርጥር ታላቅ ነው።"

3ኛ. የክርስትና መለያ ማዕከል ነው።

እግዚአብሔር አንድ ነው ወይም ሦስት ነው የሚሉ ሃሳቦች በሌሎች ጥንታውያን ፍልስፍናዎችና እምነቶች ውስጥ በተለያየ መንገድ ሊነሱ ይችላሉ። ነገር ግን "አምላክ በሥጋ ተገለጠ ፣ በሥጋ ሞተ፣ ተነሣ፣ ዓለምን አዳነ" የሚለው ሃሳብ በዓለም ታሪክ ውስጥ ለሰው ልጅ አእምሮ ፈጽሞ የማይታመንና ትልቁ አስደናቂ ምስጢር ነው። ይህ ምስጢር ደግሞ ክርስቶስ ብቻ ነው።

ስለዚህ ከአንድ በላይ ምስጢር የለም ከተባለና ምርጫ ከተደረገ፣ የማይታየው አምላክ የታየበት፣ የተገለጠበትና ሰውን ሁሉ ያዳነበት ዋናውና የመጨረሻው ምስጢር "ኢየሱስ ክርስቶስ" ነው።

ሚስጥሩ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው እንጂ ሥላሴ አይደለም ሚስጥሩ እርሱ ከሆነ ለእርሱ የተደበቀ ማንነት አለው ማለት ነው ይህ ደግሞ አብ መሆኑ ነው።

የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ ደግሞ ራሱ አንዱ የእሥራኤል አምላክ መሆኑን እመኑ ይህ ነው ወንጌል።
ወንድማችሁ ነኝ

13/06/2026

እየጻፋችሁ ወገን
✍️ አብ ይጣዳል
✍️ወልድ ይፈላል
✍️መንፈስ ቅዱስ ይገነፈላል።
ጥቅሱ ግን የት ነው?🤔 የሰው እውቀት ይህ ነው።
እሱን ተውና ይህን ጻፉ
የእግዚአብሔር እውቀት ደግሞ
👉ለእኛ የሚጣድ አብ የለንም የሚያድን አብ እንጂ።
👉ለእኛ ራሱን የገለጠ ወልድ አለን እንጂ የፈላ ወልድ የለንም።
👉ለእኛ የሚያጽናና የእግዚአብሔር መንፈስ አለን እንጂ የሚገነፍል የለም ።
ወንድማችሁ ነኝ

13/06/2026

#የእግር #ጉዞ
በኢትዮጵያ ሐዋርያዊት ቤተክርስቲያን ደቡብ ኢትዮጵያ ሰበካ መሃል ወላይታ ቅርንጫፍ ሰበካ ላድሳ ንዑስ ሰበካ 2ኛው ዙር ወጣቶች ኮንፈረንስ እግር ጉዞ።

በላድሳ ከተማ በ ዋዱ ገበያ የእውነት ወንጌል በኃይል ተሰበከ

ለአሕዛብም ሁሉ ምስክር እንዲሆን ይህ የመንግሥት ወንጌል በዓለም ሁሉ ይሰበካል፥ በዚያን ጊዜም መጨረሻው ይመጣል።
ማቴዎስ 24:14
ወንድማችሁ ነኝ

በሐዋርያት መሠረት ላይ ያልቆመ ሰው መንግስት ሰማይ ልገባ አይችልም።            የሐዋርያት መሠረት ምንድን ነው?በመጽሐፈ ቅዱስ እና በ ክርስትና አስተምህሮ፣ "በሐዋርያት መሠረት ላይ ...
12/06/2026

በሐዋርያት መሠረት ላይ ያልቆመ ሰው መንግስት ሰማይ ልገባ አይችልም።
የሐዋርያት መሠረት ምንድን ነው?

በመጽሐፈ ቅዱስ እና በ ክርስትና አስተምህሮ፣ "በሐዋርያት መሠረት ላይ መቆም" ማለት ሐዋርያት ኢየሱስ ክርስቶስን መሠረት አድርገው ያስተማሩትን እውነተኛ እምነት፣ የኖሩትን ሕይወት፣ እና ያስረከቧትን አንዲት፣ ቅድስትና ሐዋርያዊት ቤተክርስቲያንን ሙጥኝ ብሎ መያዝ ማለት ነው።

"በሐዋርያትና በነቢያት መሠረት ላይ ታንጻችኋል፥ የማዕዘኑም ራስ ድንጋይ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው።" (ኤፌሶን ፪፥፳)

ስለዚህ፣ መሠረቱ ራሱ ክርስቶስ ሲሆን፣ ሕንጻውና ጠባቂዎቹ ደግሞ ሐዋርያት ናቸው። ከዚህ መሠረት መውጣት ማለት ከራሱ ከክርስቶስ አካልና ትምህርት መለየት ተደርጎ ይወሰዳል።

የሐዋርያት መሠረት ደግሞ ኢየሱስ ክርሰቶስ የእግዚአብሔር ልጅም ራስ እግዚአብሔር አብ እንደሆነ ይናገራል በሌላ በኩል ኢየሱስ ክርስቶስ ራስ አባትህ ወዴት ነው ተብሎ በተጠየቀ ግዜ እነ እርሱ ነኝ እኔ እርሱ እንደሆንኩ ባታምኑ በኃጥአታችሁ ትሞታላችሁ አላችሁ። [ዮሐንስ ወንጌል 8:19_24]

የሐዋርያት ትምህርት ይህን ያመኑ ሰዎች በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተጠምቆ መዳን ያገኛሉ በማለት ያምናሉ ኢየሱስ ክርስቶስ ራሱ ያመነ የተጠመቀም ይድናል በማለት ተናገረ።
[ማርቆስ 16:16]

በቀጥታ ኢየሱስ ክርስቶስ ራሱ ባቋቋመው በቤተክርስቲያን ትምህርትና ቀኖና መሠረት ከተገመገመ፣ በሐዋርያት መሠረት (በእውነተኛዋ እምነትና ሥርዓት) ላይ ያልቆመ ሰው መንግስተ ሰማያት ለመግባት ዋስትናም ሆነ መብት የለውም፤ ምክንያቱም የድኅነት መንገዶችን (ጥምቀትን እና እውነተኛውን እምነት) ስለሚያጣ።

ነገር ግን፣ "ፍጹም አይገባም" ብሎ የመጨረሻውን በር መዝጋት በምድራዊ ድንኳን ያለው አሁን ያልሞተ ሰውን ለመኮነን ሳይሆን የእግዚአብሔርን የመፍረድና የመማር ሉዓላዊ ሥልጣን መጋፋት ስለሚሆን፣ የሰውን ልጅ የመጨረሻ ዕድል (በተለይ ባለማወቅ ያሉትን) ለባለቤቱ ለፈጣሪ ፍርድ መተውና እነርሱም ወደ እውነተኛ መንገድ በሐዋርያት መሠረት እንድቆሙ ዘውትር መትጋት አሰፈላጊ ነው።

ለክርስቲያኖች የተሰጠው አስተማማኝና ትክክለኛው መንገድ ግን በሐዋርያት መሠረት ላይ ጸንቶ መኖር ብቻ ነው።

ይህ ነው የሰማይ መንገድ ከዚህ ውጭ ወደ ሰማይ መሄጃ መንገድ የለም ኑ እና በዚህ ሕንጻ ታነፀው ኑሩ።
ወንድማችሁ ነኝ

 #እግር  #ጉዞበኢትዮጵያ ሐዋርያዊት ቤተክርስቲያን ደቡብ ኢትዮጵያ ሰበካ መሃል ወላይታ ቅርንጫፍ ሰበካ ላድሳ ንዑስ ሰበካ 2ኛው ዙር ወጣቶች ኮንፈረንስ ተጀመረ።ኮንፈረንሱ ነገ ቅዳሜና እሁድ...
12/06/2026

#እግር #ጉዞ
በኢትዮጵያ ሐዋርያዊት ቤተክርስቲያን ደቡብ ኢትዮጵያ ሰበካ መሃል ወላይታ ቅርንጫፍ ሰበካ ላድሳ ንዑስ ሰበካ 2ኛው ዙር ወጣቶች ኮንፈረንስ ተጀመረ።

ኮንፈረንሱ ነገ ቅዳሜና እሁድ ሙሉ ቀን ስለሚኖር የእግዚአብሔር ቃል ተካፋዮች እንድትሆኑ ተጋብዛችኋል።
ወንድማችሁ ነኝ

12/06/2026

ሰላም ቅዱስን የላድሳ ንዑስ ሰበካ ወጣቶች ኮንፈረንስ ዛሬ በእግር ጉዞ ስለሚጀምር በዚህ ቀጥታ ስርጭት እንድትከታተሉ እናሳውቃለን።
ወንድማችሁ ነኝ

Address

Wolaita
Areka

Telephone

+251916996769

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ወንድማችሁ ነኝ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Place Of Worship

Send a message to ወንድማችሁ ነኝ:

Share