Areka Central Kale Hiwot Church Youth Official

Areka Central Kale Hiwot Church Youth Official የእግዚአብሔር ቃል በሙላት ይኑርባችሁ፤ በጥበብ ሁሉ እርስ በርሳችሁ አስተምሩና ገሥጹ፤ በመዝሙርና በዝማሬ በመንፈሳዊም ቅኔ በጸጋው በልባችሁ ለእግዚአብሔር ዘምሩ

 አገልጋይ የሚያገለግለው እግዚአብሔርንና ቤተክርስቲያንን እንደመሆኑ መጠን ወደ ላይ እግዚአብሔርን ወደ ጎን ሰዎችን እንዳያሳዝን፤ ለእግዚአብሔር ክብር፣ ለቤተክርስቲያን መታነጽ የሚበቃ አገልግ...
25/08/2026



አገልጋይ የሚያገለግለው እግዚአብሔርንና ቤተክርስቲያንን እንደመሆኑ መጠን ወደ ላይ እግዚአብሔርን ወደ ጎን ሰዎችን እንዳያሳዝን፤ ለእግዚአብሔር ክብር፣ ለቤተክርስቲያን መታነጽ የሚበቃ አገልግሎት እንዲኖረን የእግዚአብሔር ቃል ምክር የሚከተሉትን ይመስላል

1. የጸሎት ሰው ሁን፦

ጸሎት የምንወጣው የሆነ ግዴታ ሳይሆን ግንኙነት ነው። የፀሎት ሰው ስትሆን ከእግዚአብሔር ጋር ያለህ ግንኙነት ጤናማ ይሆናል። ኃይል ትቀበላለህ። ሞገስን ታገኛለህ። ጥበቃው ይበዛልሀል። ለበረከት ትሆናለህ። ስለዚህ ሁሌም ጸልይ። (ፊልጵ.4:6-7/1ጢሞ.2:1-4)

2. መጽሐፍ ቅዱሳዊ ሁን፦

ቃሉን ስበክ፤ ቃሉን አጥና፤ ቃሉን አስጠና፤ ቃሉን በአግባቡ አቅርብ፤ ቃሉን አሰላስል። (2ጢሞ.2:15/2ጢሞ.4:2)

3. በፍጹም ነፍስህ እግዚአብሔርን ውደድ፦

አገልግሎት መተዳደሪያ ሳይሆን ለእግዚአብሔር የምናቀርበው የፍቅር ስጦታ ነው። የአገልጋይ የመጀመሪያ ሥራው እግዚአብሔርን ከሁሉም በላይ መውደድ ነው። ከአገልግሎታችንም በላይ የምናገለግለውን እግዚአብሔርን መውደድ ዋናው ተልእኮ ነው። (ማቴ.22:35-38)

4. ተቀደስ፦

በንግግርህ፣ በአካሄድህ፣ በአዋዋልህ፣ በአገልግሎትህ፣ በኑሮህ ቅድስናን ተለማመለድ። (ዘሌዋ.19:2/1ጢሞ.4:7-8)

5. ከሌሎች አገልጋዮች ተማር፦

ከአሰባበካቸው፣ ከስኬታቸው፣ ከውድቀታቸው፣ ከአመራራቸው፣ ሰው አያያዛቸውን ተማር።

6. ራስህን ዝቅ አድርግ፦

ስለ ራስህ የወረደ ግምት አይኑርህ። ነገር ግን ራስህን ዝቅ አድርግ። የምትሰጠው የተቀበልከውን ነው። ካንተ የሆነ ምንም ነገር የለም። የጠራህን ለማስከበር እንጂ ክብር ለማግኘት አታገልግል (1ጴጥ.5:5-6/ፊልጵ.2:2:5-11)

7. ውደድ፦

ቸርችህን፣ የምታገለግላቸውን፣ አገልግሎትህን፣ የሚጠሉህን፣ የሚተቹህን፣ የሚደግፉህን ወዘተ ውደድ። ከፍቅር አትጉደል። (1ጴጥ.4:8)

8. ትጋትን አሳይ፦

አገልግሎት ለሰነፎችና የሰነፎች አይደለም። ለማንበብ፣ ለመምከር፣ ለመገሰጽ፣ ለማስተማር፣ ለመጸለይ፣ ደቀመዝሙር ለማፍራት ትጋትን አሳይ። (2ጢሞ.4:2/ 2ጴጥ.1:10)

9. ታጋሽ ሁን፦

ሁሉም ነገር ሥርዐትና ሂደት አለው። ቶሎ ለውጥ ካላየሁ አትበል። በፈተና ጽና። የዘራነው ሁሉ ቶሎ አይበቅልም። የኛ ድርሻ ለዘሩ መጠንቀቅና ታምኖ መዝራት ብቻ ነው። መቼ ይበቅላል? አናውቅም። እንታገስ። (2ጢሞ.4:2)

10. ራስህን ሁን፦

በተሰጠህ ጸጋ አገልግል እንጂ ገበያ ተኮር አትሁን። መጋቢ ሆነህ ተጠርተህ ነቢይ ልሁን አትበል። ትንቢት ለማምጣት፣ የታመመ ለመፈወስ አትጋጋጥ። ባልተጠራህበት አትድከም። ጥሪህንና ራስህን አክብር። እንደ እገሌ አትስበክ፤ ባንተ ሁኔታ፣ ባንተ ድምፅ ስበክ።(1ቆሮ.12:4-11)

11. ለቤተሰብህ ቅድሚያ ስጥ፦

ለሚስትህ፣ ለልጆችህ ቅድሚያ ስጥ። ተገኝላቸው። የሰው ቤት እያገለገልክ ቤትህን አትርሳ። (1ጢሞ.3:1-7)

12. የሚሰሙህን አክብር፦

ትምህርትና ስብከትህን በአግባቡ አደራጅ፤ በአግባቡ ዝግጅት አድርግ። ተቀመጡና ተነሡ፣ አሜን በሉ እያልክ ሕዝቡን አታድክም። እንድትሰብክ ተጠርተህ፤ ስለ ራስህ አውርተህ፤ ጉራህን ነዝተህ አትምጣ። የዝግጅት እጥረትህን መንፈስ ርእስ አስቀየረኝ፣ ጸልይ አለኝ እያልክ ሰበብ አታብዛ። ከሚሰሙህ ጉባኤ ውስጥ የሚበልጡህ አሉ። ክብርን አሳይ። ቅዱሳንን አክብር።(1ጢሞ.4:16)

Demissie Daniel ✍️

‎  ‎በአረካ መሐል ከተማ ቃ/ሕ/ቤ/ያን አመታዊ የምስጋና እና የ'A' ኳይር መዝሙር አልበም ምረቃ ኮምፍራንስ የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ክቡር ረ/ፕ ሳሙኤል ተሰማ፣ የከተማው ከንቲባ ክቡር ኢ/ር...
18/08/2026


‎በአረካ መሐል ከተማ ቃ/ሕ/ቤ/ያን አመታዊ የምስጋና እና የ'A' ኳይር መዝሙር አልበም ምረቃ ኮምፍራንስ
የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ክቡር ረ/ፕ ሳሙኤል ተሰማ፣ የከተማው ከንቲባ ክቡር ኢ/ር ጥበቡ ሳሙኤል፣የአረካ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዘለቀ ዛራን ጨምሮ የከተማው አስተባባሪ አካላት እንድሁም ለአገልግሎት የተጠሩት መጋቢ ዶ/ር ዮሐንስ ባሣና ፣ዘማሪ አስፋው መለሰ እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በድምቀት ተካሂዷል!
።። ክብር ሁሉ ለእግዚአብሔር ይሁን 2018 ዓ.ም::

17/08/2026

ከአባትም በላይ ነህ

አመታዊ የምስጋና እና የመዝሙር አልበም ምረቃ ኮምፍራንስ በአረካ መሐል ከተማ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን በድምቀት እየተካሄደ ይገኛል::
16/08/2026

አመታዊ የምስጋና እና የመዝሙር አልበም ምረቃ ኮምፍራንስ በአረካ መሐል ከተማ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን በድምቀት እየተካሄደ ይገኛል::

14/08/2026

የአረካ መሃል ከተማ ቃለ ሕይወተ ቤ/ክ 'A' ኳይር የመዝሙር አልበም ሰርቶ ጨርሰዋል ሙሉ ቪድዮ እሁድ 8:00 ሰዓት Wolayta Mazamurya tube ላይ ይለቀቃል ። ሰምታችሁ ተባረኩበት! Share adrgu!

11/08/2026

የአረካ መሐል ከተማ ቃ/ሕ/ቤ/ያን ወጣቶች አገልግሎት ዘርፍ

አመታዊ ምስጋና እና የመዝሙር አልበም ምረቃ ኮምፍራንስነሐሴ 8-10አረብ 10:00 ይጀምራልቅዳሜ እና እሁድ ሙሉ ቀንአረካ መሐል ከተማ ቃለ ሕይወት ቤ/ክ
09/08/2026

አመታዊ ምስጋና እና የመዝሙር አልበም ምረቃ ኮምፍራንስ
ነሐሴ 8-10
አረብ 10:00 ይጀምራል
ቅዳሜ እና እሁድ ሙሉ ቀን
አረካ መሐል ከተማ ቃለ ሕይወት ቤ/ክ

ስለ ሁሉ እግዚአብሔር ይመስገን የወጣቶች ሳምንት ክብረ በዓል በደማቅ ሁኔታ ተከብሯል-Fasting and prayer/ጾም እና ጸሎት -Song Worship/የመዝሙር አምልኮ -evangelism/...
06/08/2026

ስለ ሁሉ እግዚአብሔር ይመስገን
የወጣቶች ሳምንት ክብረ በዓል በደማቅ ሁኔታ ተከብሯል
-Fasting and prayer/ጾም እና ጸሎት
-Song Worship/የመዝሙር አምልኮ
-evangelism/ወንጌል ስርጭት
-compassion/በጎ ሥራ
-Education and Training/ትምህርት እና ስልጠና
-song concert/መዝሙር ኮንስርትዩ
ተደርጎ ።
አረካ መሐል ከተማ ቃለ-ሕይወት ቤ/ክ

part  #2በአረካ መሐል ከተማ ቃለ ሕይወት ቤ/ክ የወጣቶች ሳምንት ክብሬ በዓል በደማቅ ሁኔታ ተከብሯል፣   ክብር ሁሉ ለእግዚአብሔር ይሁን።
05/08/2026

part #2
በአረካ መሐል ከተማ ቃለ ሕይወት ቤ/ክ የወጣቶች ሳምንት ክብሬ በዓል በደማቅ ሁኔታ ተከብሯል፣
ክብር ሁሉ ለእግዚአብሔር ይሁን።

part  #1በአረካ መሐል ከተማ ቃለ ሕይወት ቤ/ክ የወጣቶች ሳምንት ክብሬ በዓል በደማቅ ሁኔታ ተከብሯል፣   ክብር ሁሉ ለእግዚአብሔር ይሁን።
04/08/2026

part #1
በአረካ መሐል ከተማ ቃለ ሕይወት ቤ/ክ የወጣቶች ሳምንት ክብሬ በዓል በደማቅ ሁኔታ ተከብሯል፣
ክብር ሁሉ ለእግዚአብሔር ይሁን።

Address

Areka

Telephone

+251908279351

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Areka Central Kale Hiwot Church Youth Official posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Place Of Worship

Send a message to Areka Central Kale Hiwot Church Youth Official:

Shortcuts

Share