28/07/2026
፡- በቀድሞው የደቡብ ብ/ብ/ክ መንግስት የከተማ ልማት እና ቤቶች ቢሮ ባወጣው መመሪያ መሰረት ( የደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መመሪያ ቁ 17/2008 አንቀፅ 8(7) መሰረት) "ነባር ቤተክርስቲያን ባለበት አካባቢ አዲስ ሌላ የእምነት ተቋም ሲገነባ ርቀት በመሃከላቸው ሊኖር ይገባል ይህ ሳይጠበቅ የተገነባ የቤተክርስቲያን ህንፃ ሊፈርስ ይገባል።" ይላል ። አሁን በተሻሻለው በአዲሱ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መመሪያ መሰረት በነበሩ ቤተእምነት እና በአዲሱ ሌላ እምነት ተቋም መሐከል ሊኖር የሚገባው ርቀት ከ600 እስከ #1000ሜትር (1ኪ.ሜ) መሆን እንዳለበት ይደነግጋል። እኛ የምንፈልገው ይሄ ህግ እንዲከበርልን ብቻ ነው!!! መብታችን ይከበርልን፤ እኛ ከማንም ጋር ግጭት አንፈልግም! በዚሁ አጋጣሚ እነዚህ የሌላ እምነት ተቋም አባላት #100ሜትር እንኳን በማይሞላ ርቀት ውስጥ ያለውን መሬት ለመቃብር ቦታ/ለችግኝ ተከላ ፈልገን ነው ብለው ገዝተው መጠጋታቸው ሳያንስ ትዕግሥታችንን እንደ አለማወቅ በመቁጠር ድምጽ ማጉያ በመጠቀም እየረበሹን የአምልኮ ሥርዓታችንን እና መብታችንን ጭምር መጋፋት መጀመራቸው እንዲታወቅልን እንፈልጋለን። ህግ የሰጠንን መብት እስከ መጨረሻው ድረስ በመሄድ በሰላማዊ መንገድ መብታችንን የምናስከብር መሆናችንን በዚሁ አጋጣሚ ግልጽ ለማድረግ እንወዳለን። አሁንም የሚመለከታቸው አካላት ፍትህ እንዲሰጡን እና ህግ እንዲያስከብሩልን በታላቅ ትህትና በድጋሚ ለመጠየቅ እንወዳለን።