Areka No.1 kale hiwot church youth officially

Areka No.1 kale hiwot church youth officially ወልድ ያለው ሕይወት አለው

በኢትዮጵያ ቃለ በአረካ ከተማ ቁ-1 ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን ለ 18ኛ ዙር የሚከበረው የእናቶች(የእህቶች) በደማቅ እየተከበረ ውሏል።
21/06/2026

በኢትዮጵያ ቃለ በአረካ ከተማ ቁ-1 ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን ለ 18ኛ ዙር የሚከበረው የእናቶች(የእህቶች) በደማቅ እየተከበረ ውሏል።

17/06/2026
ዛሬ በአረካ ከተማ ቁ-1 ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን ድንቅ የሆነ ወንጌል ሥርጭት ጊዜ ነበረን። በኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን በሚከበረው በእህቶች(እናቶች) ሳምንት እንደ ቤተክርስቲያና...
17/06/2026

ዛሬ በአረካ ከተማ ቁ-1 ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን ድንቅ የሆነ ወንጌል ሥርጭት ጊዜ ነበረን። በኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን በሚከበረው በእህቶች(እናቶች) ሳምንት እንደ ቤተክርስቲያናችን በሳምንቱ ከተያዘው መረሃ ግብር በዛሬው ቀን የወንጌል ሥርጭት ጊዜ ነበረን።
"መልካሙን የምሥራች የሚያወሩ እግሮቻቸው እንዴት ያማሩ ናቸው!" (ሮሜ 10:15) 📖✨

በሐዋርያት ሥራ 1፥20-22 እና በሌሎችም ክፍሎች ላይ የተገለጠው መለኮታዊ ሐሳብ፣ ከመጀመሪያው አንስቶ እስካሁን ድረስ ባለው ሂደት በጥልቀትና በግልጽ ተብራርቶ ቀርቦልናል። ይህ ትንታኔ መጽ...
27/05/2026

በሐዋርያት ሥራ 1፥20-22 እና በሌሎችም ክፍሎች ላይ የተገለጠው መለኮታዊ ሐሳብ፣ ከመጀመሪያው አንስቶ እስካሁን ድረስ ባለው ሂደት በጥልቀትና በግልጽ ተብራርቶ ቀርቦልናል። ይህ ትንታኔ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረቱን፣ ታሪካዊ ይዘቱንና የቤተ ክርስቲያንን መልካም ወግ ጠብቆ በሰፊው የተዘጋጀ ነው።
ውድ መሪዎቻችንና አባላቶቻችን፤ በዚህ ጉዳይ ላይ ማንኛውም ጥያቄ ካላችሁ፣ የተዘጋጀውን ትምህርት በጥሞና እንድትከታተሉት በፍቅር እንጋብዛችኋለን።
እንግዲህ ሁላችንም በእውነትና በአንድነት ሆነን በአቋማችን እንድንጸና፣ የእግዚአብሔርንም መንግሥት በጋራ ለማስፋትና ለማስከበር እንድንተጋ እግዚአብሔር ጸጋውን ያብዛልን።
👇👇👇👇👇

Enjoy the videos and music you love, upload original content, and share it all with friends, family, and the world on YouTube.

ተግባራዊ እንዲሁም ተፈጻሚ ሊደረግ የሚገባ
23/05/2026

ተግባራዊ እንዲሁም ተፈጻሚ ሊደረግ የሚገባ

19/05/2026
"መልካሙን የምሥራች የሚያወሩ እግሮቻቸው እንዴት ያማሩ ናቸው!" (ሮሜ 10:15) 📖✨የቤተክርስቲያን ቀዳሚና ዘላለማዊ ተልዕኮ በኃጢአትና በጨለማ ውስጥ ላለው ዓለም የክርስቶስን ወንጌል ማብሰ...
15/05/2026

"መልካሙን የምሥራች የሚያወሩ እግሮቻቸው እንዴት ያማሩ ናቸው!" (ሮሜ 10:15) 📖✨
የቤተክርስቲያን ቀዳሚና ዘላለማዊ ተልዕኮ በኃጢአትና በጨለማ ውስጥ ላለው ዓለም የክርስቶስን ወንጌል ማብሰር ነው!
ይህንን ታላቅ ሰማያዊ አደራ በድል ለመወጣት ደግሞ ምንጊዜም በማይናወጥ የእግዚአብሔር ቃልና በጽኑ ጸሎት መታጠቅ መሠረታዊና ቅድመ-ሁኔታ የሌለው ዝግጅት ነው። የአሕዛብን ልብ በሕያው ወንጌል ለመንካት የቀረበው መለኮታዊ ጥሪ ዛሬም ለእያንዳንዳችን ነው! 🌍🙌
🔥 ታላቅ የምሥራች! 🔥
ይህንኑ ታላቅ ሰማያዊ ዓላማ ከግብ ለማድረስ፣ የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን ከኢግልስ ኦፍ ፒስ ሚኒስትሪ (Eagles of Peace Ministry) ጋር በመተባበር ያዘጋጀችው ዓለም አቀፍ የወንጌል ሥርጭት ሥልጠና ዛሬ(07/09/18) በ ቢሾፍቱ ከተማ ቃለ ህይወት ማዕክል በይፋ ተጀምሯል።
በዚህ እጅግ ወሳኝ በሆነ መንፈሳዊ መድረክ ላይ፦
🔹 ከቀጣና እስከ አጥቢያ የሚገኙ የቤተክርስቲያን መሪዎች ተገኝተዋል
🔹 በርካታ የእግዚአብሔር መንጋዎችና መጋቢያን (ፓስተሮች) በንቃት እየተሳተፉ ነው
🔹 ለታላቁ ተልዕኮ (Great Commission) ራሳቸውን እያዘጋጁ ይገኛሉ
የጌታን የምሥራች ለመሸከምና ለወንጌል አገልግሎት ወደ ፊት የተነሱ እግሮች ሁሉ የተባረኩና የተቀደሱ ይሁኑ! አሜን። 🙏✨
#የኢትዮጵያቃለሕይወትቤተክርስቲያን #የወንጌልሥርጭት #የዓለምአቀፍሥልጠና #የክርስቶስወንጌል

የእምነት ሩጫቸውን በድል አጠናቀዋል።በወላይታ ቀጣና ቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን ቀደምት ወንጌል አገልጋዮች መካከል አንዱ የሆኑት ወንጌል በመስበክና ዝማረን በማቅረብ ለምሳሌ "ኑናራ ዲያጌ ኡ...
01/05/2026

የእምነት ሩጫቸውን በድል አጠናቀዋል።
በወላይታ ቀጣና ቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን ቀደምት ወንጌል አገልጋዮች መካከል አንዱ የሆኑት ወንጌል በመስበክና ዝማረን በማቅረብ ለምሳሌ "ኑናራ ዲያጌ ኡባ ጦንያጋ" "ጦሳይ ታማ ድርሣ ባርናቱስ" በማለት ለእግዚአብሔር ክብር በመዘመር የሚታወቁ የወንጌል አርበኛ አባባ ማርቆስ ሄቫና ወዳገለገሉት ጌታ በክብር ስለተሰበሰቡ እግዚአብሔርን እያመሰገንን ለቤተሰቦቻቸው መጽናናትን እንመኛለን ።
"መልካሙን ገድል ተጋድዬአለሁ፥ ሩጫውን ጨርሼአለሁ፥ ሃይማኖትን ጠብቄአለሁ፤" 2 ጢሞ 4:7

በሰሞኑ በቤተክርስቲያን ይዞታ ጋር በተያያዘ ከከተማው መንግሥት ጋር በነበረው አለመግባባት በዋናነት የዞኑ መንግሥት ጉዳዩን ወደ መድረክ በማምጣት በማወያየት የነበረውን አለመግባባት በሠላማዊ ...
27/04/2026

በሰሞኑ በቤተክርስቲያን ይዞታ ጋር በተያያዘ ከከተማው መንግሥት ጋር በነበረው አለመግባባት በዋናነት የዞኑ መንግሥት ጉዳዩን ወደ መድረክ በማምጣት በማወያየት የነበረውን አለመግባባት በሠላማዊ መንገድ በእርቅ ሠላም መጭረሱን እና የክስ ሁኔታና እገዳ መነሳቱን እየገለጽን የዞኑን መንግሥት እያመሰገንን በግልም ይሁን በቤተክርስቲያን ደረጃ በፀሎትም በሐሳብም እንዲሁም በተለያዩ ሚዲያ ድምፅ የሆናችሁ፥ አለኝታነታችሁን ያሳያችሁ በሙሉ ቤተክርስቲያኒቱ ታመሰግናለች።
ቀጥሎ ያለውን ህደት በቅርቡ የምናሳውቅ ይሆናል።

የእውነት ምስክርነት ከብዙ በጥቅቱ፦ ስለ አረካ ቁጥር 1 ቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን ማኅበራዊ ፋይዳቤተ ክርስቲያኒቱ ለከተማውና ለሕዝቧ ያበረከተችውን ታላቅ አስተዋጽኦ በተደጋጋሚ ስንዘግብ ቆ...
26/04/2026

የእውነት ምስክርነት ከብዙ በጥቅቱ፦ ስለ አረካ ቁጥር 1 ቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን ማኅበራዊ ፋይዳ
ቤተ ክርስቲያኒቱ ለከተማውና ለሕዝቧ ያበረከተችውን ታላቅ አስተዋጽኦ በተደጋጋሚ ስንዘግብ ቆይተናል። ይህን የምናደርገው እውነታውን እያወቁ የተኙትን ለማሳሰብ፣ ላላወቁት መረጃ ለመጠቆም፣ እንዲሁም ጉዳዩን ካላስተዋሉት ጋር ለማጋራት ነው። የከተማው መስተዳድር በዚህች ቤተ ክርስቲያን የሥራ ውጤት ምክንያት በዞንና በክልል ደረጃ በተደጋጋሚ ተሸላሚ ሲሆን ቆይቷል። ይህንንም በማስረጃ አስደግፈን በሚከተሉት ስድስት ዋና ዋና ክፍሎች አቅርበነዋል፤ ፍርዱን ደግሞ ለእናንተ ለቅን ልቦናችሁ እንተዋለን።
ይህች ቤተ ክርስቲያን ልትደነቅና ልትሸለም ይገባታል እንጂ፣ አንዳንድ በክፋት የተነሳሱ ሰዎች አማካኝነት ስም የማጥፋት ዘመቻ ሊከፈትባት አይገባም ነበር።
1. በትምህርት ዘርፍ፦
በትምህርት ዘርፍ በክልል ደረጃ አንደኛ መውጣታችን የቅርብ ጊዜ ትዝታ ነው። በተጨማሪም፣ በከተማው ከሚገኙ የመንግሥትም ሆኑ የግል ትምህርት ቤቶች በተለየ መልኩ፣ ለማኅበረሰቡ ያለምንም የሃይማኖት፣ የጾታና የዘር ልዩነት ሳይኖር ከ10 ዓመታት በላይ ነፃ የክረምት ትምህርት አገልግሎት ስንሰጥ ቆይተናል። ስለዚህ ትምህርት ቤቱ በክልል ደረጃ መሸለም የቤተክርስቲያኒቱ ብርቱ የሆነ ጥረትና ትግል ውጤት መሆኑ የገሃድ ምስጥር ነው።
2. በበጎ አድራጎት ዘርፍ፦
ለአቅመ ደካማ ወገኖች ቤት በመገንባትና በመጠገን ረገድ ለተከታታይ 10 ዓመታት አገልግለናል። እንደዚሁም አሁንም ብዙ አቅሜ ደካሞችን በልዩነት እየደገፍን እንገኛለን። በየዓመቱ መስከረም 1 ቀን በቤተ ክርስቲያኒቱ ቅጥር ግቢ ውስጥ የሚካሄደው "የማዕድ ማጋራት" መርሐ ግብር ሳይቋረጥ ቀጥሏል። ከዚህም ባሻገር ለከተማዋ ወጣቶች የሥራ ዕድል በመፍጠር ረገድ የድርሻችንን ተወጥተናል።
3. በጤና ዘርፍ፦
ከኢትዮጵያ ደም ባንክ ወላይታ ዲስትሪክት ጋር በመተባበር፣ በከተማዋ ታሪክ ከፍተኛ ቁጥር ያለው (ሪከርድ) የደም ልገሳ መርሐ ግብር በቤተ ክርስቲያኒቱ ቅጥር ግቢ ውስጥ እንዲከናወን አድርገናል። የቤተክርስቲያን መሪዎች እና ምዕመናኑም ያለ ምንም ማቅማማት ደም ልገሳ ተተግብሮአል። ቤተክርስቲያናችን አንዳንድ ጽንፊ የረገጡ ሰዎች በክፋት ተነሳስተው ስሟን በከንቱ የሚያጠፏት ዓይነት አይደለችም። ለዚህ ጉዳይ የከተማው ማሕበረሰብ በሙሉ ምስክር ናቸው።
4. በስፖርት ዘርፍ፦
የመጀመሪያውን የሴቶች የእግር ኳስ ቡድን በማቋቋም በከተማ ደረጃ ሴቶችን በማበረታታት ረገድ ቀዳሚዎች ነን። ከእነዚህም ተጫዋቾች መካከል አንዳንዶቹ አሁን ላይ ለወላይታ ዲቻ ዋና ቡድን እየተጫወቱ ይገኛሉ።
5. በአስቸጋሪ ወቅቶች (ለምሳሌ ያክል ኮቪድ-19)፦
በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ወቅት ለኅብረተሰቡ ግንዛቤ በመፍጠርና የጥንቃቄ መልእክቶችን በማድረስ ረገድ የአረካ ከተማ ቁጥር 1 ቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን ግንባር ቀደም ነበረች።
6. በከተማ ጽዳትና ውበት፦
የተለያዩ መርሐ ግብሮችን ምክንያት በማድረግ የከተማዋን ጽዳትና ውበት በመጠበቅ ረገድ ከፍተኛ ተሳትፎ ስናደርግ ቆይተናል።
በእነዚህ ሁሉ አኩሪ ሥራዎች ምክንያት የከተማዋ የትምህርት ቢሮ እንዲሁም የወጣቶችና ስፖርት መምሪያ በክልል ደረጃ በተደጋጋሚ የአንደኝነት ሽልማትን ለመቀበል በቅተዋል። ይህ ግልጽ የሆነ እውነት ነው! ለዚህ ጉዳይ ታሪክ ራሱ ምስክር ነው።
በቀን 18-08-2018 ዓ.ም. መልዕክቱ ለብዙዎች እንዲደርስ ሼር በማድረግ እንድትተባበሩ እናሳስባለን።

Address

Wolayta
Areka

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Areka No.1 kale hiwot church youth officially posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share