Arbegona Hiwot Birhan church

Arbegona Hiwot Birhan church እኛ ግን የተሰቀለውን ክርስቶስን እንሰብካለን
1ኛ ቆሮ1 : 23

በስሜ የተጠሩት ሕዝቤ ሰውነታቸውን አዋርደው ቢጸልዩ፥ ፊቴንም ቢፈልጉ፥ ከክፉ መንገዳቸውም ቢመለሱ፥ በሰማይ ሆኜ እሰማለሁ፥ ኃጢአታቸውንም ይቅር እላለሁ፥ ምድራቸውንም እፈውሳለሁ። 2ኛ ዜና 7...
24/08/2026

በስሜ የተጠሩት ሕዝቤ ሰውነታቸውን አዋርደው ቢጸልዩ፥ ፊቴንም ቢፈልጉ፥ ከክፉ መንገዳቸውም ቢመለሱ፥ በሰማይ ሆኜ እሰማለሁ፥ ኃጢአታቸውንም ይቅር እላለሁ፥ ምድራቸውንም እፈውሳለሁ። 2ኛ ዜና 7:14
​በአርቤጎና ያዬ ከተማ የአብያተ ክርስቲያናት ህብረት አስተባባሪነት በከተማዋ እምብርት በሚገኘው አደባባይ ታላቅ የጋራ የጸሎት፣ የንስሐና የምልጃ መርሃ-ግብር ተካሂዷል።
​የከተማዋ አብያተ ክርስቲያናትና ምእመናን በአንድነት ወደ አደባባይ በመውጣት፣ በፈጣሪ ፊት በመንበርከክና ንስሐ በመግባት ምድራቸው እንዲፈወስ ፀልየዋል።
- በመሃል አደባባይ በአፈር ላይ ተንበርክከው፣ በእግዚአብሔር ፊት በእንባና በምሬት አልቅሰዋል። ስለራሳቸው፣ ስለከተማቸው እንዲሁም ስለአባቶች በደል ንስሐ በመግባት የእግዚአብሔርን ምህረት ጠይቀዋል።
- ለበርካታ ባለስልጣናትና ለሚመለከታቸው አካላት የመንገድ ችግራቸውን አብራርተውና አመልክተው ምንም ዓይነት ዘላቂ መፍትሔ ማግኘት አልቻሉም። በመሆኑም ሕዝቡ መፍትሔውን ከሰዎች ሳይሆን ከሰማዩ አባት በመጠበቅ በለቅሶ ወደ አምላኩ ፀልዩአል።
- የዚህን መንገድ ሥራ የሚያስተጓጉል፣ የሚያዘገይና እንቅፋት የሆነ ማንኛውም ሰው ሰራሽም ሆነ መንፈሳዊ ከልካይ ኃይል በፈጣሪ እጅ እንዲወገድና መንገዱ እንዲከፈት በጽኑ ተጸልያል።
የያዬ ከተማ ሕዝብ በእንባና በጸሎት የዘራነዉን የፈውስና የልማት ፍሬ አምላክ በጊዜው እንደሚምመልስልን ሙሉ እምነት አለን!

ቀን_04_08_2018_ዓ.ምየትንሳኤ_በዓል_ፕሮግራም
14/04/2026

ቀን_04_08_2018_ዓ.ም
የትንሳኤ_በዓል_ፕሮግራም

  01/08/2018 ዓ.ም የደህንነት ትምህርት ስከታተተሉ የቆዩትን 26 ነብሳት የውሃ ጥምቀት ፈፅመዋል።ማቴዎስ ወንጌል 28:19-20 እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ...
11/04/2026

01/08/2018 ዓ.ም የደህንነት ትምህርት ስከታተተሉ የቆዩትን 26 ነብሳት የውሃ ጥምቀት ፈፅመዋል።
ማቴዎስ ወንጌል 28:19-20
እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው፥ ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው፤ እነሆም እኔ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ።

የምስራች ለአርቤጎና እና ለአካባቢው ነዋሪዎች በሙሉ! 📢እንኳን ለዓመታዊው ለአርቤጎና ክልል የሕይወት ብርሃን ቤተክርስቲያን ኮንፍራንስ በሰላም አደረሳችሁ!"እግዚአብሔር ለዘላለምና እስከ ዘላለ...
28/01/2026

የምስራች ለአርቤጎና እና ለአካባቢው ነዋሪዎች በሙሉ! 📢
እንኳን ለዓመታዊው ለአርቤጎና ክልል የሕይወት ብርሃን ቤተክርስቲያን ኮንፍራንስ በሰላም አደረሳችሁ!

"እግዚአብሔር ለዘላለምና እስከ ዘላለም ይነግሣል።" (ዘጸአት 15:18)

የአርቤጎና ክልል የህይወት ብርሃን ቤተክርስቲያን ልዩ የሆነ መንፈሳዊ የቃልና የአምልኮ ኮንፈረንስ አዘጋጅቶ ይጠብቃችኋል።
የጌታ ክብር የሚገለጥበት፣ የታሰሩ የሚፈቱበት ድንቅ ጊዜ ይሆንልናል።

📍 ቦታ፦ በአርቤጎና ያዬ ሁለገብ ስታዲየም
📅 ቀን፦ ከየካቲት 12 እስከ 16 /2018 ዓ.ም

በዚህ ታላቅ ጉባኤ ላይ፦

የጌታ አገልጋዮች (ሰባኪያን) 📖

ዘማሪዎች 🎶 በአንድነት በመሆን በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ያገለግሉናል።

ኑ! አብረን እንባረክ። የእግዚአብሔር መንግሥት በኃይል ስትገለጥ እንመልከት።
ንጉሡ ለዘላለም ይነግሣል!

በፀሎት እንዘጋጅ

#አርቤጎና #የህይወትብርሃን #መንፈሳዊጉባኤ

09/01/2026
 #ታህሳስ 29/04/2018 ዓ.ም_አርቤጎና_ያዬ_የህይወት_ብርሃን_ቤተክርስቲያንሉቃስ 29 እነሆም፥ የጌታ መልአክ ወደ እነርሱ ቀረበ የጌታ ክብርም በዙሪያቸው አበራ፥ ታላቅ ፍርሃትም ፈሩ።10...
08/01/2026

#ታህሳስ 29/04/2018 ዓ.ም_አርቤጎና_ያዬ_የህይወት_ብርሃን_ቤተክርስቲያን
ሉቃስ 2
9 እነሆም፥ የጌታ መልአክ ወደ እነርሱ ቀረበ የጌታ ክብርም በዙሪያቸው አበራ፥ ታላቅ ፍርሃትም ፈሩ።
10 መልአኩም እንዲህ አላቸው፡— እነሆ፥ ለሕዝቡ ሁሉ የሚሆን ታላቅ ደስታ የምሥራች እነግራችኋለሁና አትፍሩ፤
11 ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኃኒት እርሱም ክርስቶስ ጌታ የሆነ ተወልዶላችኋልና።

Address

Arbe Gona

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Arbegona Hiwot Birhan church posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share