Mahibere Kidusan - ማኅበረ ቅዱሳን አርባ ምንጭ ማእከል

Mahibere Kidusan - ማኅበረ ቅዱሳን አርባ ምንጭ ማእከል Mahibere Kidusan is set under the Ethiopian Orthodox Church. It provides spiritual services.

የሥራ ቅጥር ማስታወቂያ
11/08/2026

የሥራ ቅጥር ማስታወቂያ

አርባ ምንጭ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤልሐምሌ ፲፱/፳፻፲፰ ዓ/ም📷ደጉ
27/07/2026

አርባ ምንጭ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል
ሐምሌ ፲፱/፳፻፲፰ ዓ/ም
📷ደጉ

ማኅበረ ቅዱሳን አርባምንጭ ማዕከል ለ9 ወራት ሲያሰለጥናቸው የቆዩትን 20 የመሠንቆ ዘማርያንን አስመረቀ።ማኅበረ ቅዱሳን አርባምንጭ ማዕከል በልማት ተቋም ሥር ለ9 ወራት ሲያስተምራቸው የቆዩት...
06/07/2026

ማኅበረ ቅዱሳን አርባምንጭ ማዕከል ለ9 ወራት ሲያሰለጥናቸው የቆዩትን 20 የመሠንቆ ዘማርያንን አስመረቀ።

ማኅበረ ቅዱሳን አርባምንጭ ማዕከል በልማት ተቋም ሥር ለ9 ወራት ሲያስተምራቸው የቆዩትን 20 የመሠንቆ ዘማርያን በአርባምንጭ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ካቴድራል በቀን 28/10/2018ዓ.ም አስመረቀ።
በመርሐ ግብሩም የመሠንቆ ዝማሬ እና የማኅበረ ቅዱሳንን መልክት ለተመራቂያን የእንኳን ደስ አላችሁና የአደራ መልዕክት ቀርቧል።

የማኅበረ ቅዱሳን አርባምንጭ ማዕከል ጽ/ቤት ተወካይ በመልዕክታቸው መሠንቆ ቤተክርስቲያን ለመንፈሳዊ አገልግሎት ከምትጠቀምባቸው የዜማ መሣሪያዎች አንዱ መሆኑን ገልጸው ማኅበረ ቅዱሳን አርባምንጭ ማዕከል ላለፉት ዓመታት ከ1120 በላይ የበገናና የመሠንቆ ዘማርያንን አሰልጥኖ ለቅድስት ቤ/ክ አበርክቷል ብለዋል።
የጽ/ቤቱ ተወካዩ አክለውም አርባምንጭ ማዕከል ለአራተኛ ዙር የመሠንቆ ዘማርያንን አሰልጥኖ ያስመረቀ መሆኑን ጠቅሰው በዛሬው እለት የተመረቁ 20 የመሠንቆ መዘምራንን ጨምሮ ባለፉት ሶስት ዓመታት ብቻ ከ65 በላይ የመሠንቆ መዘምራንን አሰልጥኖ ማስመረቁና ለተመራቂዎችም የሰለጠኑትን የመሠንቆ ዜማ መሣሪያ ስልጠና ለቅድስት ቤ/ክ አገልግሎት ብቻ እንድያውሉ አመላክተዋል

15/06/2026
ማኅበረ ቅዱሳን አርባምንጭ ማዕከል ለ9 ወራት ሲያስተምራቸው የነበሩ 119 የበገና ዘማርያንን አስመረቀ።ማኅበረ ቅዱሳን አርባምንጭ ማዕከል በልማት ተቋም ሥር ለ9 ወራት ሲያስተምራቸው የቆዩትን...
01/06/2026

ማኅበረ ቅዱሳን አርባምንጭ ማዕከል ለ9 ወራት ሲያስተምራቸው የነበሩ 119 የበገና ዘማርያንን አስመረቀ።

ማኅበረ ቅዱሳን አርባምንጭ ማዕከል በልማት ተቋም ሥር ለ9 ወራት ሲያስተምራቸው የቆዩትን 119 የበገና ዘማርያን በአርባምንጭ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ቤ/ክ በቀን 23/09/2018ዓ.ም አስመረቀ።
በመርሐ ግብሩም የበገና ዝማሬ እና የማኅበረ ቅዱሳንን መልክት እና የኢንቨስትመንት ሀብት ልማት ቦርድ ቀርቧል።

የማኅበረ ቅዱሳን አርባምንጭ ማዕከል ሰብሳቢ ዲ/ን በየነ ባንዳ በመልዕክታቸው በገና የዜማ መሣሪያ ሊጠፋ የነበረው የቤ/ክ ቅርስ ለማስቀጠል ማኅበረ ቅዱሳን ትኩረት አድርጎ በመሥራቱ በመንፈሳዊ የዜማ መሣሪያዎች በማሰልጠን ላለፉት ዓመታት ከ30 ሺህ በላይ የበገናና የመሠንቆ ዘማርያንን አሰልጥኖ ማስመረቁን ጠቅሰው አርባምንጭ ማዕከልም የበኩልን ድርሻ በመወጣት በዛሬው እለት የተመረቁትን 119 የበገና ዘማርያን ጨምሮ 1100 በላይ የበገናና የመሠንቆ ዘማርያንን አስተምሮ ለቅድስት ቤ/ክ አበርክቷል ብለዋል።
ሰብሳቢው አክለውም ለበገና ተመራቂዎች የሰለጠኑትን የበገና ዜማ መሣሪያ ለቅድስት ቤ/ክ አገልግሎት ብቻ እንድያውሉ አጽንኦት በመሥጠት ተናግረው እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል።

የማኀበረ ቅዱሳን አርባምንጭ ማዕከል ኢንቨስትመንትና ሀብት ልማት ቦርድ ሰብሰቢ ጌታቸው አበበ በበኩላቸው ላለፉት ዘጠኝ ወራት የበገና ተማሪዎችን ለማስተማር ብቃት ያላቸው መምህራን እና ረዳት መምህራንን መድበው መቆየታቸውን ገልጸው የዜማ ትምህርት ቤቱ ቅርንጫፎቹን አሳድጎ ለብዙዎች ተደራሽ እንደሆነ ገልጸዋል።
የቦርዱ ሰብሳቢ አክለውም በገና ተምረው የሚመረቁ በርካታ ናችው አብረው አገልግሎት ለመጽናት ግን መንፈሳዊነትና ትጋት የሚጠይቅ መሆኑን አንሰተው ሲያስተምሩ የነበሩ መምህራንን እና የአገልግሎት ዘርፍ አስተባባሪዎችን አመስግነው በቀጣይም ልማት ተቋሙ ተጨማሪ አቅም ማሳደጊያ ስልጠናዎች ( advance) ስለሚኖሩት እንድከታተሉ አመላክተዋል።
በመጨረሻም የዜማና ኪነጥበበት አገልግሎት ዋና ክፍል ሲ/ር ሰላማዊት መኮንን እንኳን ደስ አላችሁ በማለት ከዚህ በኋላ ተመራቂዎቹን መዝሙር ክፈሉ ተረክቦ አባል ሆነው እንድያገለግሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል

29/05/2026

Address

Arba Mintch

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Mahibere Kidusan - ማኅበረ ቅዱሳን አርባ ምንጭ ማእከል posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Place Of Worship

Send a message to Mahibere Kidusan - ማኅበረ ቅዱሳን አርባ ምንጭ ማእከል:

Shortcuts

Share