22/08/2023
"መዳኔ"
የመዳኖች ሁሉ መዳን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ የስቃይ ሞት ያገኘነው የህይወት መዳን ነው!
እጃችን ላይ ስለገባ መቼም የማይቀልብንን ይህንን ውድ መዳን ከየት እንደተነሳንና ከምን እንደወጣን እለት እለት እያሰብን መገረም መደነቅና ማመስገን የኛ ድርሻ ነው!
ሞት ሆይ፥ መውጊያህ የት አለ? ሲኦል ሆይ፥ ድል መንሣትህ የት አለ?"እንደሚል ቅዱስ ቃሉ በክርስቶስ ሞትና ትንሳኤ ላመንነው ሁሉ ሞትና ሲኦል ዳግም ላያስፈሩን በድል ንጉሱ ኢየሱስ ድል ተነስተዋል!ክብር ለኢየሱስ ይሁን!
"ለወደደን ከኃጢአታችንም በደሙ ላጠበን፥
መንግሥትም ለአምላኩና ለአባቱም ካህናት እንድንሆን ላደረገ፥ ለእርሱ ከዘላለም እስከ ዘላለም ድረስ ክብርና ኃይል ይሁን፤ አሜን።"
የዬሐንስ ራእይ 1:5-6
በዚህ አዲስ ዝማሬ ይህ መዳን ያልደረሳችሁ እንዲደርሳችሁ የዳናችሁ ደግሞ ስለመዳናችሁ ከልብ እንድታመሰግኑበት ፀሎቴ ነው!
ነገ ይለቀቃል!
ተባረኩ!
https://youtube.com/