የደቡብ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ምዕመናንን ኅብረት-አርባ ምንጭ

  • Home
  • Ethiopia
  • Arba Minch'
  • የደቡብ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ምዕመናንን ኅብረት-አርባ ምንጭ

የደቡብ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ምዕመናንን ኅብረት-አርባ ምንጭ Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from የደቡብ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ምዕመናንን ኅብረት-አርባ ምንጭ, Religious organisation, Sikela, Arba Minch'.

24/05/2026
Nuso፣wolaita times..በተቃውሞ ፓለቲካ  ሃይማኖት ግብ ያዘሉ*** ደቡብ ኢትዮጵያ ላይ አይናቸውን ተክለው ከሚንቀሳቀሱ በማኅበራዊ ሚዲያ የተቃውሞ  ፓለቲካ ገጾች እና ጦማርያ መካከል...
06/04/2026

Nuso፣wolaita times..በተቃውሞ ፓለቲካ ሃይማኖት ግብ ያዘሉ
***

ደቡብ ኢትዮጵያ ላይ አይናቸውን ተክለው ከሚንቀሳቀሱ በማኅበራዊ ሚዲያ የተቃውሞ ፓለቲካ ገጾች እና ጦማርያ መካከል... ኑሶ፣ወላይታ ታይምስ፣ ናትናኤል ጌጆ እና መሰል ተረፈ ገጾች ፓለቲካን ብቻ ሳይሆን የሃይማኖት ግብ ጭምር ይዘው ሚዲያው ላይ የተበተኑ ኦርቶዶክስ ጠል ብናኞች ናቸው።

በማኅበራዊ ሚዲያ የተቃውሞ እንቅስቃሴ ላይ መሰረታዊ የመልካም አስተዳደር ጥያቄ ከፊት አስቀድሞው ስውር ግባቸው (covert operation) ግን ከእነርሱ እምነት ውጪ ያለውን ሹማምንት በእምነቱ ምክንያት ነጥለው የማጥቃት አዝማሚያ ያሳያሉ።

ጎፋ ላይ በኬንቾ የመሬት ናዳ ለተጎዱ ወገኖች ተሰብስቦ በቼክ ማጭበርበር ከተፈጠረ ችግር ጋር በተያያዘ ርዕስ በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ የማብጠልጠል ዘመቻ ያካሄዱት ሃይማኖቱ ከእርሳቸው ወገን ውጪ የሆነውን አጭበርባሪውን የያዘው ምስጉን ሹማምንት ነው።

የክልል መዋቅርን የሚመሩ አካላት ፓለቲካዊ በሆነ አቋማቸው በፓርቲያቸው እንቅስቃሴ ሳይሆን በልዩነት በእምነታቸው ብቻ ተነጥለው እስኪመስል ድረስ ከሁሉም ፓለቲከኛ ተነጥለው ግለሰባዊ በሆነ ጉዳዮች ጭምር ድረስ ዘልቀው ዕለት ዕለት እንደ መደበኛ ሥራ ይብጠለጠላሉ።

ከእነርሱ ሃይማኖት ውጪ የሆነ ሰው በህዝብና መንግስት ስልጣን ላይ ከተሾመ የፓለቲካ አቋም እና ዝግጅነቱን ይልቅ ሃይማኖቱን መነሻ አድርገው ለመተቸትና ለማጥፋት ክምር ድንጋይ ይንዳሉ።

ከመኪና ተጋጨ እስከ ከንቲባዋ አጥር አፈረሰች ድረስ ያሉ ጩኸቶች ውስጥ በጉልህ የሚሰማው የእምነት ልዩነትን እንደ ጥፋት የመቁጠር ትችት እንጅ የተቃውሞ ፓለቲካ ብቻ አይደለም።

በእነዚህ አካላት የተቃውሞ መንደር ፓለቲካዊ ጽንሰ ሐሳብ ብቻ ሳይሆን ሃይማኖታዊ መለያዎች የመተቻ ርዕስ ሆኖ ያገለግላል።

በተለይ በተለይ በመንግስት እና በቤተክርስቲያን መካከል የአስተዳደራዊ ጥያቄ አለመግባባት ከተፈጠረ ለእነኝህ አካላት የሰርግና ምላሻቸው ድግሳቸው ነው።

እነ ወላይታ ታይምስ፣ኑሶ እና ናትናኤል መንግስትን የሚደግፉበት ብቸኛው ርዕሳቸው ከቤተክርስትያን ጋር ጠብ ከገጠመ ብቻ ነው። የኦቶና ማርያም ጉዳይ ምስክር ነው።

ክብረ ክህነትን አዋርደው ካህናትን ሲሳደቡ፣ቤተክርስቲያንን እያንጓጠጡ በመሬት መጎተትን በግልጽ ለማሳዬት ፍርሃት የላቸውም።

ስለዚህ እነ ናትናኤል ፣እነ ኑሶ፣እነወላይታ ታይምስ እና መሰል የተቃውሞ ገጾች ሆይ... ለሃይማኖታችሁ ተልዕኮ ወይም ለፓለቲካ ግባችሁ ታለይታችሁ ታመኑ።

ክርስቶስ ኢየሱስ የሰቃዮችሁን ጨካኝነት ሲገልጥ "በእርጥብ እንጨት እንዲህ የሚያደርጉ ከሆኑ፥ በደረቀውስ እንዴት ይሆን?
የሉቃስ ወንጌል 23:31" ሲል እንደገለጸው ... እናንተ ገና ሀገር ሳትገዙ መንግስት ስትሆኑ በማኅበራዊ ሚዲያ የተቃውሞ ዘመቻ ብቻ እንዲህ ቤተክርስቲያንን እና ልጆቿን ለማብጠልጠል ከተራሯጣችሁ መንግስት የሆናችሁ ዕለት እንዴት ልትዘነጥሉን አቅዳችዋል?

የማንም ፓርቲ የፓለቲካ እንቅስቃሴ አያገባኝም። ነገር ግን የትኛውንም አካል በእምነቱ ብቻ ነጥለህ ለማጥቃት ከዳከርክ ያኔ ጉዳዩ ይሰፋል።

በእምነት እኩልነት ዙርያ ገና ገና የምንጠይቀው እልፍ ኦርቶዶክሳውያ ጉዳዮች በታጨበት በደቡብ ኢትዮጵያ ፓለቲካ ውስጥ ያለውን ጉዳይ በጥንቃቄ መመልከት የሁሉም ምዕመናንን እና የሃይማኖት አባቶች ድርሻ ነው።

Kune Demelash kassaye -Arba Minch

እግዚአብሔር ሀገር እና መንጋውን ያለአንዳች ደግ አባት እንደማይተው ምስክር የሆኑ የጋሞ ኦርቶዶክሳውያን ያለ ልዩነት ተስማምተው የሚያከብራቸው የተለዩ አባቶች።ምንኩስና ለዓለም መሞት መሆኑን ...
16/02/2026

እግዚአብሔር ሀገር እና መንጋውን ያለአንዳች ደግ አባት እንደማይተው ምስክር የሆኑ የጋሞ ኦርቶዶክሳውያን ያለ ልዩነት ተስማምተው የሚያከብራቸው የተለዩ አባቶች።

ምንኩስና ለዓለም መሞት መሆኑን በግብር የገለጸ ለእግዚአብሔር ብቻ ማድላትን የሚያውቁ በአብነት ማማ ላይ የነገሱ የሚሳሳላቸው ድንቆች።

እግዚአብሔር እድሜን ከጤና ይስጥላቸው።

Kune Demelash Kassaye

የአ/ምንጭ ደ/ኃ/ ቅዱስ ገብርኤልና ደብረ መ/ቅ/ሚካኤል ያለሰበካ ጉባኤ ከህገ ቤተክርስቲያን ውጪ በሆነ አካሄድ በ3 ሰዎች ብቻ ለወራት እየተመራ ይገኛል።***የአርባምንጭ ደብረ ኃይል ቅዱስ ...
06/02/2026

የአ/ምንጭ ደ/ኃ/ ቅዱስ ገብርኤልና ደብረ መ/ቅ/ሚካኤል ያለሰበካ ጉባኤ ከህገ ቤተክርስቲያን ውጪ በሆነ አካሄድ በ3 ሰዎች ብቻ ለወራት እየተመራ ይገኛል።
***

የአርባምንጭ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል እና ደብረ መንክራት ቅዱስ ሚካኤል አብያተክርስቲያናት የኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስትያን ሰበካ ጉባኤ አስተዳደር ደንብ ቃለ አዋዲ ሙሉ በሙሉ ተወርውሮ እና እንዳይፈጸም ተደርጎ ከህዝብ፣ከካህናት እና ከሰንበት ትምህርት ቤት በህዝብ የተመረጡ አካላት እንዲበተን በማድረግ

በሰበካ ጉባኤ ውስጥ በቀሩ 3 ግለሰቦች ይሁንታ እና ፈቃጅነት ብቻ ያለሰበካ ጉባኤ ውሳኔ፣ውይይት እና በጀት ሳይያዝ ሐብት እንዲንቀሳቀስ፣ቅጥር እንዲፈጸም፣ግዢ እንዲከናወን ግንባታዎች እንዲፈጸሙ እየተደረገ ይገኛል። እንዲሁም ሙሉ በሙሉ የአብያተክርስቲያናቱ አስተዳደር ከሰበካ ጉባኤ ወደ ግለሰባዊ የቡድን ፈጻሚነት ተሽሮ የጥቂት ሰዎች መፈንጫ አጥቢያ ሆኗል።

እንግዲህ እስከዛሬ የቤተክርስቲያን የውስጥ ችግር በውስጥ እንዲያልቅ አብዝተን ዝምታ ብንይዝም ይህ ዝምታ ቤተክርስቲያንን በክህነት እና መዋቅር ውስጥ የተሸፈኑ አንባገነኖች እንዲፈነጩ ዕድል ስለሰጠ ህዝብ ያውቅ ዘንድ መጮኹ እንጀምራለን።

ማኅበረ ምዕመናንም ቅድስት ቤተክርስቲያን በህገ ቤተክርስቲያን ስርዓት ትመራ ዘንድ ትቆሙ የተቀበላችሁትን አደራ ትወጡ ዘንድ ሁሉን አቀፍ እንቅስቃሴ የምናደርግ ይሆናል።

ቤተክርስቲያን በግለሰቦች ፍላጎት እንድትመራ ስትተጉ የነበራችሁ እንኳን ደስ አላችሁ።

ቤተክርስቲያን ለማገልገል ፌክ አካውንት ፈጥራችሁ በስድብ፣ፎቶ በመዘቅዘቅ እና ሰው ላይ በመፍረድ ደምወዝ የምታገኙ ከጥቂት ወራት በፊት ጓደኞቻችን የነበራችሁ ባለፌክ አካውንቶች አሁን ፎቶ መዘቅዘቅ ጀምሩ።

Kune Demelash Kassaye

የአከባቢ ቋንቋ አገልግሎት እና አገልጋይነት ***የአከባቢ ቋንቋ አገልግሎት በሰው ፍቃድ ፣በመዋቅር ይሁንታ ወደ ቅድስት ቤተክርስቲያን የገባ የሰው ስሪት ሳይሆን በማርታ እና አላዛር ቤት ውስ...
23/01/2026

የአከባቢ ቋንቋ አገልግሎት እና አገልጋይነት
***

የአከባቢ ቋንቋ አገልግሎት በሰው ፍቃድ ፣በመዋቅር ይሁንታ ወደ ቅድስት ቤተክርስቲያን የገባ የሰው ስሪት ሳይሆን በማርታ እና አላዛር ቤት ውስጥ ለነበረችው የመጀመርያቱ ቤተ ክርስቲያን የተሰጣት የጰራቂሊጦስ ጸጋ ነው።

ይህንንም እውነት መጽሐፍ ቅዱስ ሲገልጸው... "በሁሉም መንፈስ ቅዱስ ሞላባቸው፥ በሌላ ልሳኖች [ቋንቋዎች] ይናገሩ ጀመር።ሐዋ ሥራ 2:4" .....ሲል ይገልጻል።

ሐዋርያቱ አብዛው የገሊላ ሰው ሆነው ሳሉ የሌሎችን ሀገራት ቋንቋ ሲናገሩ የሰሙ ሰዎች... " እኛም እያንዳንዳችን የተወለድንበትን የገዛ ቋንቋችንን እንዴት እንሰማለን?ሐዋ ሥራ 2:8"... ብለው እየተደነቁ ለቃለ እግዚአብሔር እራሳቸውን ሲያስማሙ ተስተውላል።

ቅድስት ቤተክርስቲያንም ይህን የመንፈስ ቅዱስ መንገድ ተከትላ በህገ ቤተክርስቲያን አንቀጽ 5 ንዑስ አንቀጵ 3 ላይ ...."ግእዝ፣ አማርኛ እና አገልግሎቱ በሚፈጸምበት ስፍራ የሚነገር የውጭ ሀገር ወይም የሀገር ውስጥቋንቋ በጣምራ የቤተ ክርስቲያን የትምህርትና የአምልኮ ሥርዓት ማከናወኛ ቋንቋ ሆነው ያገለግላሉ" ....ብላ በቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ ደምድማለች።

ለአገልግሎት መደብ ጭምር የሚሰየሙ አገልጋዮች አከባቢው ላይ የሚናገረው ቋንቋ መረዳት መናገር እና ማወቅ መሰረታዊ እንደሆነ ለመግለጽ በሰበካ መተዳደርያ ደንብ ቃለ አዋዲ አንቀጽ 58 ክፍል 1 ንዑስ አንቀጽ 6፤ክፍል 2 ንዑስ አንቀጽ 7 እና ክፍል 3 ንዑስ አንቀጽ 7 ላይ በግልጽ ተደንግጓል።

ይህ ጥያቄ በእዚህም በእዛም ጽንፍ ላይ ቆመው የሚጓተቱ እንጀራቸውን የሚጋግሩ አካላት አሉ። አንደኛዎቹ በአከባቢ ቋንቋ አገልግሎት ሰበብ የሥጋ ነገድ ፍላጎታቸውን ለማስፈጸም ፍቅር አልባ ሚና ላይ የሚቆም ሲሆን ሌላኛው ቡድን ደግሞ የቋንቋ አገልግሎት ከተስፋፋ የሥራ መደባቸው እንደሚያጡ በመስጋት እንቅፋት ይሆናሉ።ከእነዚህ ሁለት ቡድን ውጪ የሆነ የቋንቋ አገልግሎት ማስፋፍያ ሥራ ግን የግዴታ ውዴታ ነው።

ነገር ግን አሁን ላይ በአብዛኛውም የደቡብ ኢትዮጵያ የሚገኙ ሀገረስብከቶች ውስጥ የቋንቋ አገልግሎት እና የአከባቢ አገልጋይ እንዲስፋፋ መጠየቅ ቤተክህነቱን ለተቆጣጠሩ በጥቂት ቡድኖች አፍ "ጽንፈኛ" የሚያስብል ማሸማቀቂያ ቃል ያሰጣል። ለዓመታት ይህን ሰምተን ችለናል።

ቋንቋን ብቻ መሰረት ባደረገ ችግር ምን ያህል ቅድስት ቤተክርስቲያን መከራውን እንደምትበላ እና ስንቱ ምዕመን ከበረቱ እንደሚሰደዱ የሚያውቅ ያውቀዋል።

" አሜን አባታችን " ...የሚለው ጸሎት እንኳን በአንድ ሀገረስብከት የገጠር ምዕመናንን በቋንቋቸው ተደራሽ እንዳልሆነ ስታውቅ መከራው ምን ያህል እንደሆነ ይገብሃል።

በቋንቋ አገልግሎት ላይ የወላይታ ሀገረስብከት ሽልማት የሚያሰጠው ልምድ አለው፤ጌዲኦ፣ኮሬ እና ቡርጅ ሀገረስብከት እና ደቡብ ኦሞና አሪ ዞኖች ሀገረስብከት ጥሩ ተነሳሽነት ያለው ሥራ እየሰሩ ነው።

ነገር ግን ደቡብ ላይ ካሉ የቤተክርስቲያን መአለን።ይልቅ ጎጃም ፣ጎንደር እና ወሎ ላይ ያሉ የጉባኤ ቤት መምህራን ደቡብ ላይ ላለች ቤተክርስቲያን የአከባቢ አገልጋይ የማፍራት ዘመቻ እና ለአከባቢ ቋንቋ አገልግሎት ዋጋ እንደሚከፍሉ የምናውቀው እናውቃለን። በእውነት ለሰሜን ሊቃውንት ትልቅ ፍቅርና ክብር አለን።እናመሰግናለን።

ለማንኛውም አሁን ላይ ሁለት አማራጭ ፊት ለፊታችን ተደቅኗል።በደቡብ ያለችውን ቅድስት ቤተክርስቲያንን እጅ እግሯን ይዞ የሚጎትታትን የቋንቋ አገልግሎት ድክመት እየተጋፈጥን ማገልገል ወይም ፍረጃን ፈርተን መከራዋን እያየን ማላዘን።

ደቡብ ላይ ያለችው ቅድስት ቤተክርስቲያን ጸንታ ትሰፋ ዘንድ የአከባቢ ቋንቋ እና አገልጋይነት ላይ በእልህ ካልተሰራ እና የቤተክህነት በሮች ለእዚህ አገልግሎት ካልተከፈቱ በደል ይጸንብናል።

የቋንቋ አገልግሎት በሌላ እህት አብያተክርስቲያናት እና በአሁኒቷ መቅደስ ያለውን ፈተና በተመለከተ ተከታታይ ዘገባ እናቀርባለን።

እግዚአብሔር ይርዳን !!!

Kune Demelash kassaye -Arba Minch

የደ/ኃ/ቅ/ገብርኤል ቤተክርስቲያን አገልጋይ ዲያቆናት ሀገረ ስብከቱን ጥያቄ ጠየቁ‎***‎እኛ የደብሩ ዲያቆናት ከልጅነታችን ጀምሮ እስከ እወቀታችን ድረስ ያደግንባት እና ያሳደገችን ደብር ስት...
03/01/2026

የደ/ኃ/ቅ/ገብርኤል ቤተክርስቲያን አገልጋይ ዲያቆናት ሀገረ ስብከቱን ጥያቄ ጠየቁ
‎***

‎እኛ የደብሩ ዲያቆናት ከልጅነታችን ጀምሮ እስከ እወቀታችን ድረስ ያደግንባት እና ያሳደገችን ደብር ስትሆን አሁንም በዚችው አጥቢያ ውስጥ በአገልግሎት ላይ ያለን ልጆች ስለሆንን እንደልጅነታችን በያገባናል ስሜት የሚከተሉ ጥያቄዎችን አቅርበናል።

‎1ኛ በቀን 14/03/2018 የቀረበው የኦዲት ሪፖርት ሥርዓተ ቤተክስቲያንን በጣሰ መልኩ መቅረቡ ሳያንስ የተከሰሱ ግለሰቦች የምላሽ ሀሳብ እንዳይሰጡ ለምን አውደ ምህረት ተከለከሉ?

‎2 ኛ በገለልተኛ አካል እንዲታይ እንፈልጋለን የተባለው የኦዲት ሪፖርት ከምን ደረሰ

‎3 ኛ ቤተክርስቲያንን ብለው ስለእውነት የቆሙ ካህናት እና ዲያቆናት ጥያቄ ስለጠየቁ ብቻ ለምን ተገለሉ

‎ 4ኛ አገልጋዮች እየተመረጡ የሚጠሩ ስብሰባዎች ለምን ይደረጋሉ? እናም በዚህ አንገብጋቢ ጉዳይ አጠቃላይ አገልጋይ ካህናት እና ዲያቆናት ለምን እንዲወያዩ አልተደረገም?

‎5ኛያለሰበካ ጉባኤ ስምምነት ውሳኔ ሰጪነት እና ያለውድርር ህገ ቤተክርያንን በጣሰ መልኩ ቅጥር ለምን ይፈፀማል?

‎6ኛ ያለሰበካ ጉባኤ ውሳኔ ሰጭነት እና ስምምነት ገንዘብ በጥቂት ሰዎች ስምምነት ብቻ ከቤተክርስቲያን አካውንት ወጪ እንዲሆን ማስቻል እና ሰበካው የማያውቀውን ፣ቅጥር ፣ስንብት፣ደምወዝ ጭማሪ ለምን ተደረገ ? ይህም እየሆነ ባለበት ሁኔታ ኃላፊነቱን እየወሰደ ያለዉ ማን ነው ?

‎7ኛ የቤተክርስቲያኒቷ ህንፃ እርጅና ተጫጭኖት ጣሪያው እንደሚያፈስ ስለታወቀ በሰበካ ጉባኤ ጸድቆ በሀገረስብከቱ ይሁንታ ሰጪነት ወደ ህንፃ እድሳት የገባው የዕደሳ ክፍልን 5.6 ሚልየን ብር በ3:00 ሰዓት ውስጥ ያሰባሰበው ክፍል ባሰባሰበ በጥቂት ቀናት ልዩነት ውስጥ ራሳቸውን ለምን አገለሉ ? ሀገረ ስብከቱስ በዚህ ጉዳይ ላይ ምን ሀሳብ አለው?

‎በዚህ መሰረት እኛ የደብሩ ዲያቆናት ቃለ አዋዲ በጣሰ መልኩ የሚሰሩ ማንኛውም ሥራዎችና አገልግሎቶች
‎ውስጥ ለሚፈጠሩ ጥሰቶች ስለእውነትና ብለን ከቤተክርስቲያን ጎን እንደምንቆም እናሳውቃለን።

‎ህገ ቤተክርስቲያንን እየጣሱ እና ክፉ እየሰሩ ቤተክርስቲያንን መደበቂያ የሚያደርጉ ግለሰቦችን አጥብቀን እንቃወማለን!!

‎"እስመ ቅንዓተ ቤተከ በልዓኒ" የቤትህ ቅንአት በልታኛለችና መዝ 68፥9🙏🙏

የአ/ምንጭ ደ/ኃ/ቅ/ገብርኤልና ደ/መ/ቅ/ሚካኤል ሰበካ ጉባኤ 5 ተመራጮች በሀገረስብከቱ እየደረሳ ባለው ኢ-ህገቤተክርስቲያናዊ ጉዳይ ላይ መግለጫ በመስጠት ማኅበረ ምዕመናንን ለመፍቴሄ እንዲሰ...
03/01/2026

የአ/ምንጭ ደ/ኃ/ቅ/ገብርኤልና ደ/መ/ቅ/ሚካኤል ሰበካ ጉባኤ 5 ተመራጮች በሀገረስብከቱ እየደረሳ ባለው ኢ-ህገቤተክርስቲያናዊ ጉዳይ ላይ መግለጫ በመስጠት ማኅበረ ምዕመናንን ለመፍቴሄ እንዲሰባሰቡ ጥሪ አቅርበዋል።
***

በአርባምንጭ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል እና በደብረ መንክራት ቅዱስ ሚካኤል ሰበካ ጉባኤ የካህናት ፣የህዝብ እና የሰንበት ትምህርት ቤት ተወካይ ከሆኑ 8 አባላት መካከል በቁጥር 5 የሆኑ የካህናት ፣የሰንበት ት/ቤት እና የህዝብ ተወካዮች በደብሩ ላይ የጋሞና አከባቢ ሀገረስብከት ጽ/ቤት እያደረሰ ያለውን ኢ ህገቤተክርስቲያን በተመለከተ ማኅበረ ምዕመናንን ለመፍቴሄ እንዲሰባሰቡ መግለጫ በማውጣት ጥሪ አስተላልፈዋል።

የሰበካ ጉባኤ 5 አባላት የሆኑ አካላት በመግለጫው ከአካተቱ ነጥቦች መካከል

* ያለህገ ቤተክርስቲያን መሰረት የከተማ አድባራት በቀጥታ ለሀገረስብከት ተጠሪ እንዲሆኑ በማድረግ መዋቅር የመጣስ

*ያለሰበካ ጉባኤ ስምምነት ውሳኔ በጡረታ የተገለሉ አካላት ጭምር ቅጥር እንዲፈጸም በግድ ምደባ ማድረግ

* ያለሰበካ ጉባኤ ውሳኔ እና ስምምነት ገንዘብ በጥቂት ሰዎች ስምምነት ብቻ ከቤተክርስቲያን አካውንት ወጪ እንዲሆን ማስቻል እና ሰበካው የማያውቀውን ጨረታ፣ግዢ ፣ቅጥር፣ስንብት፣ደምወዝ ጭማሪ እየተደረገ መሆን

* ኦዲት በሚል መነሻ ግለሰቦችን ፣ክፍላትን እና ተግባርን ማሳደድ የታዬ እንደሆነ እና በኦዲት ሽፋን ስም የሀገረስብከቱ ታማኝ የተባሉ አካላትን ከሂሳብ ጉድለት ለማዳን መጣር

* እራሱን የኦዲት ኮሚቴ አካል እና ታዛቢ ነኝ የሚለው አካል ሰራተኛ በማገድ፣እራሱን ቦርድ አድርጎ በማሾም በድርብ ስልጣን መምጣት እና ሌሌች ጉዳዮች በመግለጫው ተካተዋል።

መግለጫውን ያወጡ 5 የሰበካ ጉባኤ አባላት ከማኅበረ ምዕመናንን በተወጣጣ ገለልተኛ የሂሳብ አጣሪ ኮሚቴ ወይም በውጪ ኦዲተር እንዲሁም ከጠቅላይ ቤተክህነት በሚላኩ ኦዲተሮች የደብሩ የ6 ዓመት መደበኛ ሂሳብ ፣የፓርኪንግ እና ት/ቤት ሂሳቦች እንዲጣራ እና በጉድለት ግኝት የተገኘባቸው አካላት የቅድስት ቤተክርስቲያንን ሐብት እንዲመለሱ እንዲደረግ ጠይቋል።

በነገ ታህሳስ 25 ዕለተ ሰንበት ከቅዳሴ መልስ በደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል የሰበካ ጉባኤ አባላት ከህዝብ ጋር በአውደምህረት ውይይት ለማድረግ እና እየደረሰባቸውን ያለውን ጫና ለመረጣቸው ህዝብ ማሳወቅ ስላስፈለገ ህዝቡ እንዲሰባሰብ ጥሪ ያስተላለፉ ሲሆን ይህን የተዘረጋውን መርኃግብር ለመረበሽ የሚፈልግ የትኛውም አካል ላይ መንግስት ስርዓተ ቤተክርስቲያንን ባከበረ መልኩ ጥበቃ እንዲያደርግ ጥሪ አስተላልፈዋል።

ሙሉ መግለጫው ከታች በተያያዘ 5 ገጽ የሰፈረ ሲሆን ደብሩ ላይ ከሀገረስብከቱ ጋር የተፈጠረውን አለመግባባት ሙሉ በሙሉ በሚገልጽ እና ቃለአዋዲያዊ መሰረት የተጣሰባቸውን ክፍላትን የዳሰሰ ሲሆን ሙሉውን መግለጫ ታነቡ ዘንድ እንጠይቃለን ።

Kune Demelash kassaye -Arba Minch

አርባምንጭ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን !!!የደቡብ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ምዕመናንን ኅብረት-አርባ ምንጭ
19/12/2025

አርባምንጭ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን !!!

የደቡብ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ምዕመናንን ኅብረት-አርባ ምንጭ

ግሽን ደብረ ከርቤ ***የበረከት እና የረድኤት አጸድ። ለመሳለም ያብቃችሁየደቡብ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ምዕመናንን ኅብረት-አርባ ምንጭ
06/10/2025

ግሽን ደብረ ከርቤ
***

የበረከት እና የረድኤት አጸድ።

ለመሳለም ያብቃችሁ

የደቡብ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ምዕመናንን ኅብረት-አርባ ምንጭ

230 ቆርቆሮ ለሚሰሩት የቤተክርስቲያን ጣሪያ እየተማጸኑ ነው።***እባካችሁ   ታደርግ ዘንድ እለምናችዋለው ።ይህኝ በጋሞ ዞን ብርብር ማርያም አከባቢ ካለችው ሐጋዜ በምትባል ቀበሌ የሚገኙ ኦ...
30/09/2025

230 ቆርቆሮ ለሚሰሩት የቤተክርስቲያን ጣሪያ እየተማጸኑ ነው።
***
እባካችሁ ታደርግ ዘንድ እለምናችዋለው ።

ይህኝ በጋሞ ዞን ብርብር ማርያም አከባቢ ካለችው ሐጋዜ በምትባል ቀበሌ የሚገኙ ኦርቶዶክሳውያን ናቸው።

ለዓመታት ተባርኮ በተሰጣቸው ሜዳ ላይ ከታች በፎቶ እንደምትመለከቱ መስቀል ተክለው እና ስእል አድኖ እየተሳለሙ ስርዓተ አምልኮ እየፈጸሙ ይገኛሉ።

አሁን ላይ በወልደ እግዚአብሔር ስም ቤተክርስትያን አንጸው ስርዓተ አምልኮ ለመፈጸም በአቅማቸው የመቅደስ እንጨት ከማሳ ቆርጠው አምጥተው ቢያቆሙም ከአቅም አንጻር ቤተክርስቲያኑ ጣሪያ የሚለብሰውን 230 ቆርቆሮ አጥተው ከ2 ዓመት በላይ ተቸግረዋል።

የቆመውም እንጨት በጸሀይ እና ዝናብ መፈራረቅ የተነሳ ሊፈርስ ደርሷል።እርጅናም ተጭኖታል።

በ920 ብር መግዛት የሚቻለውን ቆርቆሮ 230 ሰው ብቻ አንድ አንድ ቆርቆሮ መግዛት ከቻለ የብዙ ዓመት ድካም እና ችግራቸውን መቅረፍ እንችላለን ። ስለበዓለ ወልድ ብለን ይህን እንድንሟላ እንማጸናለን።

***
ስጦታ መቀበያ ህጋዊ የቤተክርስቲያን አካውን

1000584438286

ሐጋዜ ቅዱስ ባለ ወልድ ቤተክርስቲያን

***

ለበለጠ መረጀ በ0982341985 ቴሌግራም እና ዋስአፕ መስመር ላይ አለን ።

ያስገባችሁትን የባንክ ስሊፕ በውስጥ መስመር ላኩልን

ስለ ቅዱስ በዓለ ወልድ

Kune Demelash kassaye -Arba Minch

Address

Sikela
Arba Minch'

Telephone

+251910319059

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የደቡብ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ምዕመናንን ኅብረት-አርባ ምንጭ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Place Of Worship

Send a message to የደቡብ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ምዕመናንን ኅብረት-አርባ ምንጭ:

Share