ገ/ሚካኤል ረታ

ገ/ሚካኤል ረታ አንድ ጌታ አንድ ሃይማኖት አንዲት ጥምቀት ኤፌ ፬ ፥ ፭ እኔ እ?

09/05/2022

👏 የ #ሐና የ #ኢያቄም የእምነታቸው ፍሬ 👏
🍂 በእግዚአብሔር ፈቃድ ተወለደች ዛሬ 🍂

የኢያቄም ስዕለቱ የሐና እምነት 👏
ለምኝልን ለኛ ኪዳነ ምሕረት 👏




+ + + + +



አማኑኤል የማይተረጎም የሥጋን ልብስነት
ከአንቺ የለበሳት መሥሪያ ነሽ።
ዝሐውን ከአዳም ጥንተ ሥጋ አደረገ ማጉም የአንቺ ሥጋ ነው። መወርወሪያውም ቃል እርሱ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።

መሕኑም ከልዕልና የወረደ የልዑል እግዚአብሔር አምሳል ነው።
ሠሪውም መንፈስ ቅዱስ ነው።

ወዮ ይህ ነገር እጹብ ድንቅ ነው።
የቀደሙ አባቶች ከሞት ወደ ሕይወት የተሸጋገሩብሽ ድልድይ ሆይ ከምድር እስከ ሰማይ የምትደርሺ መሰላል ሆይ የፍጥረት ሁሉ መጀመሪያ በአንቺ ታደሰ ።

🙏ከገነት #በተሰደደ ጊዜ የአዳም ተስፋው አንቺ ነሽ ።🙏


/ ቅዳሴ ማርያም ቁ.29 - 31/

👏 እንኳን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም 👏
የልደት በዓል መታሰቢያ በሰላም አደረሳችሁ
የእመቤታችንን ፍቅሯን በልባችኝ
ጣዕሟን በአንደበታችን ያኑርልን
🙏

ሰዐሊ ቀሲስ አማረ ክብረት እንደሣሉት

ዲ/ን ጌታባለው አማረ
/ የቅዱሳት ሥዕላት ሰዐሊ /
t.me/deacongetabalewamare

21/04/2022

ሥጋዬን የሚበላ
ደሜንም የሚጠጣ
በእኔ ይኖራል
እኔም በርሱ እኖራለኹ።
ዮሐንስ 6:56

21/04/2022

የጸሎተ ሐሙስ ትውፊት
#ጉልባን

* ጉልባን ከባቄላ ክክ፣ ከስንዴ ወይንም ከተፈተገ ገብስ ጋር አንድ ላይ ተቀቅሎ የሚዘጋጅና የጸሎተ ሐሙስ ዕለት የሚባላ ንፍሮ ነው፡፡

* የጉልባን ትውፊት እስራኤላውያን ከግብፅ ተሰደው በሚወጡበት ጊዜ በችኮላ ስለነበር፤ አቡክተው ጋግረው መብላት ያለመቻላቸውን ሁኔታ ያመለክታል፡፡

*ያን ጊዜ ያልቦካውን ሊጥ እየጋገሩ ቂጣ መብላት፤ ንፍሮም ቀቅለው ስንቅ መያዝ ተግባራቸው ነበርና ይህን ለማሰብ በሰሙነ ሕማማት ቂጣና ጉልባን በማዘጋጀት በዓሉ ይታሰባል፡፡

*በጸሎተ ሐሙስ ይህንን መሠረት በማድረግ የሚዘጋጀው ጉልባን አንዲህም ቂጣ ጨው በዛ ተደርጎ ይጨመርበታል፡፡

*ጨው ውኃ የሚያስጠማ በመሆኑ የጌታን መጠማት ያስታውሳል፡፡

*ይህ ትውፊታዊ ሥርዓት ከእስራኤላውያን የመጣ ሲሆን በኢትዮጵያም አብዛኛዎቹ የትውፊት ክንዋኔዎች የብሉይ ኪዳን መነሻ ስላላቸው ሥርዓቱ ዛሬም ይከበራል፡፡

ምንጭ፦ ስምዐ ጽድቅ ልዩ እትም ዘሰሙነ ሕማማት መጋቢት 2002

17/04/2022

✥✥✥ በሰሙነ ሕማማት የሚፈጸሙ እና የማይፈጽሙ ሥርዓቶች ✥✥✥

አዘጋጅ በለጠ ከበደ(የጣፈጡ ልጅ)አላቲኖስ✍

1.ስግደት:-በሰሙነ ሕማማት 41 ጊዜ ኪርያላይሶን 12 ጊዜ አቡነ ዘበሰማያት እየተዜመ እጅግ አብዝቶ ይሰገዳል::

2. ጸሎት:- በሰሙነ ሕማማት ከ24 ሰዓት ውስጥ 10 የጸሎትና የንባብ ሰዓታት ይገኛሉ እነዚህም

✥ ከጠዋቱ 1 ሰዓት; 3ሰዓት; 6ሰዓት; 9ሰዓት; 11ሰዓት ናቸው

✥ በምሽቱ ሰዓት 1 ሰዓት; 3ሰዓት; 6ሰዓት; 9ሰዓት; 11ሰዓት ናቸው::
በነዚህም ሰዓታት የጌታን ስቃይ ለማዘከር መዝሙረ ዳዊትና ግብረ ሕማማት ድርሳነ ማኅያዊ አብዝተው ይጸለያሉ::

3.ጾም:-በሰሙነ ሕማማት ብዙ አዝማደ መባልዕት /አዘውትረን የምንመገባቸው ምግቦች/ አይበሉም:: በዚህም ሳምንት እስከ ምሽቱ አንድ ሰዓት እንድንጾም; ይኸውም ቆሎ;ዳቦ;ወኃና ጨው ብቻ እንደታዘዙ በግብረ ሕማማት ላይ ተጽፎ ይገኛል::

4.አለመሳሳም:-አይሁድ ጌታችንን ለመስቀል እየተንሾካሾኩ ስለተመካከሩና ይሁዳ ጌታችንን በመሳም አሳልፎ ስለሰጠው መሳሳም አይፈቀድም::

ማማተብ : - በሰሞነ ሕማማት አባቶች ካህናት መስቀል አያሳልሙም ምዕመናን አናማትብም በጠቅላላ በሰሞነ ሕማማት የመስቀል አገልግሎት በቤተክርስቲያናችን የመስቀል አገልግሎት አይሰጥ ምክንያቱም መስቀልም በዘመነ ኦሪት የወንጀለኛ መቅጫ የእርግማን ምልክት ስለ ነበር ጌታችን በክቡር ደሙ ቀድሶ የድል አርማ እስኪያደርግልን ድረስ አንሳለምም ገላ. 3:13 ማቴ.10:38 ማቴ. 26:29 ሞትን በመስቀል ላይ ሞቶ ሽሮት ትንሳኤ ገልጦ ለሚያምኑት ጠላት ዲያቢሎስን የሚሳፍሩበትን መሰቀል ምልክት ሰጣቸው እንዳለ ልብ አምልክ ቅዱስ ዳዊት በትንሳኤ ጊዜ እንሳለማዋለን ጠላትን እናርቀበታለን ።

5.አክፍሎት:-እመቤታችን; ያዕቆብና ዮሐንስ የጌታችን ትንሳኤ ሳናይ እህልና ውኃ አንቀምስም ብለው እስከ ትንሳኤው መቆየታቸውን በማሰብ የሚጾም ነው::

6.ጉልባን:-ከባቄላ ከስንዴ ከገብስ የሚዘጋጅ በጸሎተ ሐሙስ ዕለት የሚበላ ንፍሮ ሲሆን ትውፊቱም የስቅለቱ ሐዘን መግለጫ ነው::

7.ጥብጠባ:-ይህ ምዕመናን በሰሙነ ሕማማት የፈጸሟቸውን ኃጢአቶች ለካህን እየተናዘዙ በወይራ ቅጠል ቸብቸብ እየተደረጉ ስግደት የሚቀበሉበት ነው:: ይህም የጌታ ምሳሌ ነው::

8.ቄጠማ:-ጌታችን ብርሃነ ትንሳኤዉን እንደገለጠልን የምናስብበት ሲሆን የእሾህ አክሊል በመድፋቱ ምሳሌም በራሳችን ላይ እናስረዋለን::

እንበለ ደዌ ወሕማም እንበለ ጻማ ወድካም
ያብጽሐነ ያብጽሕክሙ ለብርሃነ ትንሳኤሁ እግዚአብሔር በፍስሐ ወበሰላም::

አዘጋጅ በለጠ ከበደ(የጣፈጡ ልጅ) #አላቲኖስ ✍

[email protected]

ጥቅምት 2009 የተጻፈው ድጋሚ 2012ዓ.ም
አዲስ አበባ(ጣፎ)ተለፈ✍

╔​✞═┉✽🌹✥🌹✽┉═✞╗
❀ ❀
╚✞═┉✽🌹✥🌹✽┉═✞╝አላቲኖስ

የተሣተውን ፤ የተረሳው፤ የተገደፈውን፤ የነጠፈውን በቀና መንፈስ አቃንታቹ አንብቡት🙏🙏🙏

በቴሌ ግራም
👉 " መዝገበ ሃይማኖት" t.me/mezgebehaymanot

በ Facebook " መዝገበ ሃይማኖት" ወይም ከዚህ እታች ያለውን በመጫን ፔጁን ይቀላቀላሉ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇... ...... 👉አስተማሪ ጹሁች ለማግኝት ከስር ያለውን በመጫን ላይክ 👍 ይቀላቀላሉ https://www.facebook.com/%E1%88%98%E1%8B%9D%E1%8C%88%E1%89%A0-%E1%88%83%E1%8B%AD%E1%88%9B%E1%8A%96%E1%89%B5-232318137666445/
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆

ወስብሐት ወለመስቀሉ
ወወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ

16/04/2022
16/04/2022

" ልብሳቸውን በመንገድ ላይ አነጠፉ " ( ማቴ ፳፩ ፥ ፰ )

" ስንኳን ለአንተ ለተቀመጥኽባት አህያ መሬት መርገጥ አይገባትም ሲሉ " ( ትርጓሜ ወንጌል )

ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በአህያ ጀርባ ላይ ሆኖ ወደ ኢየሩሳሌም ሲገባ የሚበዙት ሕዝብ ልብሳቸውን በጎዳና አነጠፉለት ይላል ። ይህንንም እንኳን ለአንተ ለተቀመጥኽባት አህያ መሬት መርገጥ አይገባትም ሲሉ ልብሳቸውን አነጠፉለት ብለው አባቶቻችን ይተረጉሙታል ።

ጌታችን ወደ ኢየሩሳሌም ሊገባ በቀረበ ጊዜ ደብረዘይት አጠገብ ከምትሆን ከቤተ ፋጌ ደረሰ ። ደቀ ከመዛሙርቱ ሁለቱን ጠርቶ በፊታችሁ ወዳለ ሀገር ሂዱ ። አህያ ከውርጫይቱ ጋር ታስራ ታገኛላችሁ " " " "ፍትሕዎን ወአምጽእዎን ሊተ ፤ ፈታችሁ አምጡልኝ " ( ማቴ ፳፩፥፪ ) አላቸው ። ሰው ሁሉ ከማእሰረ ኃጢአት የሚፈታበት ጊዜ እንደደረሰ ለማጠየቅ ነው ፈታችሁ አምጡልኝ ያለው ። ምን ታደርጋላችሁ የሚላችሁ ሰው ቢኖር “በሉ እግዚኦሙ ይፈቅዶሙ ጌታቸው ይሻቸዋል “ በሉ አላቸው ። በተፈጥሮ ለእነዚህ አህዮች ጌታቸው ነውና ይህን አለ ።

የሆሣዕና አህያ መረሳት መዘንጋት ታስሮ መተውን ገንዘብ አድርጋ ነበር ። በተፈጥሮ ጌታዋ የሚሆን የሚፈቷትን ልኮ ነጻ እስኪያደርጋት በሥራ ተጠምዳ ፣ እየተደበደበች እየታሰረች ትኖር ነበር ። አስታዋሽ የሌላት ለሸክም ካልሆነ ማንም የማያስታውሳት ነበረች ። የፈጠራት ሲመጣ ግን አስታወሳት ፣ ደቀ መዛሙርቱን ልኮ አስፈታት ። ወደ እርሱ አቀረባት ። ይህም ሰይጣን ከፈጣሪያቸው አርቆ ፣ በኃጢአት ገመድ አስሮ ፣ ከመንፈሳዊ ሕይወት ለይቶ በዚህ ዓለም ሸሽጎ ለሚያኖራቸው የሰው ልጆች ሕይወትን የሚያስታውሰን ነው ። እርሱ ደቀመዛሙርቱን እስኪልክላቸው በኃጢአት ገመድ ታስረው ይቆያሉ ። የድኅነታቸው ቀን ሲደርስ ግን ከታሰሩበት ተፈትተው ወደ ባለቤቱ ይቀርባሉ ። የፈጠራቸው ይሻቸዋልና ከእርሱ ጋር ሊኖሩ ከእስራታቸው ይፈታሉ ።

ጌታችን በአህያ ላይ ተቀምጦ ወደ ኢየሩሳሌም የገባው የባሕርይ አምላክ የዋህ ኃዳጌ በቀል ንጉሥሽ በዕዋል በዕድግት (በአህያዋና በአህያይቱ ግልገል በውርንጫይቱ ) ተቀምጦ ይመጣል ብላችሁ ለጽዮን ልጅ ንገሯት ብሎ ነቢዩ የተናገረው ይደርስ ይፈጸም ዘንድ ነው ( ትን . ዘካ ፱ ፥ ፱ ) ። ደቀመዛሙርቱ ሄደው እንደአዘዛቸው አደረጉ ። አህያዋን ከውርንጫይቱ ጋር አመጡለት ። ልብሳቸውን በአህያዋ ላይ ጎዘጎዙለት (ኮርቻ በማድረግ ፈንታ ልብሳቸውን እንዲጎዘጉዝላት ያደረገው ልብስ አይቆረቁርምና የማትቆረቁር ሕግ ሠራሁላችሁ ሲለን ነው) ። እንዲሁም ልብስ በአካል ያለውን ነውር ይሰውራል አንተም ከባቴ አበሳ ነህ ሲሉ ልብስ ጎዘጎዙለት ።

በአህያይቱ እና በውርንጫይቱ ላይ በተአምራት ተቀመጠባቸው ። አንድም ከኢየሩሳሌም እስከ ቤተመቅደስ አስራ ስድስት ምዕራፍ ነው ። አስራ አራቱን በእግሩ ተጓዘ ። የቀረውን ሁለት ምዕራፍ በአህያዋ ላይ ተጉዞ ከቤተ መቅደስ ደረስ ፡፡ ቤተ መቅደሱን ሦስት ጊዜ በውርልንጭላዋ ላይ ተቀምጦ ዞረ ። በአህያ ላይ መቀመጡ ለምንድ ነው ቢሉ ትንቢቱ ምሳሌው ሊፈጸም ። ትንቢት ፦” አጠፍእ ሠረገላ እምኤፍሬም ወአፍራሰ እምይሁዳ “ ተብሎ ተነግሯል ።ምሳሌ ፦ በቀደመው ዘመን አባቶች ነቢያት ዘመነ ጸብእ (የጦርነተ ዘመን )የሆነ እንደሆነ በፈረስ ተቀምጠው ዘገር ነጥቀው ይታያሉ ። ዘመነ ሰላም የሆነ እንደሆነ በአህያ ተቀምጠው መነሳንስ ይዘው ይታያሉና ዘመነ ሰላም ደረሰ ሲል ጌታችን በአህያ ተቀምጦ ወደ ኢየሩሳሌም ገባ ። ምስጢሩ በአህያ የተቀመጠ ሸሽቶ አያመልጥም አሳዶም አይዝም ፡፡ እርሱም ካልሹኝ አልገኝም ከሹኝም አልታጣም ሲል በአህያ ላይ ተቀምጦ ወደ ኢየሩሳሌም ገብቷል ።

ለሆሣዕና አህያ በጀርባዋ ልብሳቸውን ጎዘጎዙላት ። በመንበረ መንግሥት ለቅዱሳኑ በወደደ ጊዜ በክብር የሚታያችው ፣ በኪሩቤል ጀርባ የሚቀመጥ ፣ መላእክት የሚንቀጠቀጡለት እርሱ በጀርባዋ ላይ ተቀመጦ ወደ ኢየሩሳሌም ገባ ። አስቀድሞ በሸክም ብዛት የተጎዳ ጀርባዋ ላይ ልብስ ተነጠፎ ። የፈጠራትን እርሱን ተሸክማ ወደኢየሩሳሌም ገባች ። አየህ ወዳጄ አየህ እርሱ አምላክህ ስትቀርበው እንዲህ ያደርግልሃል፡፡ እንደ ሆሣዕና አህያ ከታሰርህበት አስፈትቶ ሜዳ ላይ አይተውህም ። በጀርባህ ኮርቻ ሳይሆን ልብስ ያስነጥፍለሃል ። በዚህ ዓለም ሸክም የጎበጠ የቆሰለ ጀርባህን ይፈውስልሃል ። የህሊናህን ሸክም አስወግዶ ጸጋውን ያለብስሃል ። ማደሪያው ዙፋኑ ያደርግሃል ። አይተህም አስበህም የማታውቀውን በረከት የሞላበት አዲስ ሕይወት ያድልሃል ።

"ወዘይበዝኁ ሕዝብ ነጸፉ አልባሲሆሙ ውስተ ፍኖት " ። እንኳን ለአንተ ለተቀመጥኽባት አህያ መሬት መርገጥ አይገባትም ሲሉ " ልብሳቸዉን በመንገዱም ላይ አነጠፉለት " ( ማቴ ፳፩ ፥ ፰ ) ። ሌሎችም ቅጠል እየቆረጡ ከመንገድ ያነጥፉ ነበር ። ሰሌን ነው ቢሉ አብረሃም ይስሐቅን ፣ ይስሐቅ ያዕቆብን በወለዱ ጊዜ እስራኤል ከግብጽ በወጡ ሰሌን ቆርጠው ይዘው አመስግነዋልና በዚያ ልማድ ሰሌን አንጥፈዋል ። ሰሌን እሾሀማ ነው ። ትእምርተ ኃይል ትእምርተ መዊእ አለህ ሲሉ ። እሾህ እሳት አይበላውም ለብልቦ ይተወዋል ። አንተም ባሕርይ አይመረመርም ሲሉ ሰሌን አንጥፈውለታል ፡፡

የሆሣዕና አህያ ጌታችን ደቀ መዛሙርቱን ልኮ እስከሚያስፈታት ድረስ እንኳን የሚያነጥፍላት የሚያስታውሳትም አልነበረም ። ከነውርንጫይቱ ተረስታ ትኖር ነበር ። እርሱ ከታሰረችበት አስፈትቶ ሲያስመጣት በጀርባዋም ተቀምጦ ወደ ኢየሩሳሌም ሲገባ ግን የማያውቃት ሕዝብ አወቃት ፣ የረሳት ሕዝብ አስታወሳት ። ጌታዋ በጀርባዋ ተቀምጧልና አይታ የማታውቀውን ክብር አሳያት ። መደብደቡ መገፋቱ ፣ አህያ ተብሎ መሰደቡ ቀርቶ በምትሄድበት መንገድ ልብስ ፣ ዘንባባ ተነጠፈላት ።

የአህያዋ ታሪክ እርሱ ጌታችን ወደ ሕይወታችን ሲቀርብ የእኛም ሕይወት እንዲሁ መለወጡን ያሳየናል ። አየህ ወዳጄ ዓለም ብቻህን ስታገኝህ ትጎዳሃለች ። በተለያየ ሱስ ጠምዳ ፣ በኃጢአት አስራ ታሰቃይሃለች ። ከሰው ለይታ ተስፋ አስቆርጣ ትጥልሃለች ። ወደ ፈጠረህ መቅረብ ስትጀምር ሰውነትህ የእርሱ ማደሪያ ማድረግ ስትጀምር ግን የናቁህ ፣ ያቃለሉህ ያከብሩሃል ። ለአንተ ሳይሆን አብሮህ ላለው አምላክ ልባቸውን ሲያነጥፉለት ታያለህ ። ስምህ ይቀየራል ሌባ ፣ ወንበዴ መባልህ ይቀርና መንፈሳዊ ፣ የእግዚአብሔር ሰው የሚል አዲስ ስም ይሰጥሃል ። የእግዚአብሔር በመሆንህ በከተማው በየቤቱ ሰዎች ሁሉ ስትናገር ይሰሙሃል ። ከአንተ ጋር ጥቂት ጊዜ ማሳለፍ መታደል መመረጥ እንደሆነ እያነሱ ይነግሩሃል ። አንተ በዚህ ጊዜ እንዳትታበይ ተጠንቀቅ ። ይልቁንስ እኔ እንደሆሣዕና አህያ ነኝ ። ይህ ክብር እና መወደድ ሁሉ የመጣው ከአንተ የተነሣ ነው ብለህ ፈጣሪህን የበለጠ አክብረው ።

በፊት በኋላ ያሉ ሕዝቡም " ሆሣዕና ለወልደ ዳዊት ለዳዊት ልጅ መድኀኒት መባል ይገባዋል " አሉ ። አዕሩግ እየተከተሉ ሕጻናት እየመሩ (ሐዋርያት እየመሩ ነቢያት በፊቱ እና በኋላው ሆነው ። ጻድቃን በቀኙ ተነሳሕያን በግራው ሆነው ) እኒህ ሁሉ መድኀኒት መባል ለዳዊት ልጅ ይገባዋል አሉ ። ወደ ኢየሩሳሌምም በገባ ጊዜ ኢየሩሳሌም ታወከች ። የፊቱን ብርሃን ፀሐይን ሲበዘብዛት አይታ የሕጻናቱን ድምጽ ሰምታ ታወከች ። ጌታችን ወደ ቤተ መቅደስ ገብቶ በቤተ መቅደስ የሚሸጡትን ሁሉ አስወጣቸው ። ብሩን ለወርቅ ወርቁን ለብር የሚለውጡበትን ስፍራ አፈረሰባቸው ። ርግብ የሚሸጡትንም ወንበራቸውን ገለበጠ ። " ቤትየሰ ቤተ ጸሎት ትሰመይ ወአንትሙሰ ረሰይምዎ በአተ ፈያት ወሰረቀት " አላቸው ። " ቤቴ ቤተ መቅደስ የጸሎት ቤት ይባላል ተጽፏል ። እናንተ ግን የሌባ ዋሻ የወንበዴ ጋሻ አደረጋችሁት " ( ማቴ ፳፩ ፥ ፲፫ ) አላቸው ። ገበያ ከሆነ የተሰረቀውን የተቀማውን ይሸጡበታል ይለውጡበታልና እንዲህ አለ ።

ቤተ መቅደሱ የኦሪት መስዋዕት ሲሰዋበት ቆይቷል ። አሁን ግን የሐዲስ ኪዳን መስዋዕት የጌታችን እና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋና ደም ሊፈተትበት ነው ። ጥላው አልፎ አካሉ ሊገለጥ ነው ። ስለዚህ በሐዲስ ኪዳን ቤተ መቅደሱን ከሻጮች ከለዋጮች አጽድቶ ሰጥቶናል ። ቤቴ የጸሎት ቤት ይባላል ብሎ ገና በሐዲስ ኪዳንም የጸሎት ቤት ሆኖ እንደሚቀጥል ። የሐዲስ ኪዳን መስዋዕት እንደሚሰዋበት ነግሮናል ።

ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ እንዲህ ይላል " " የሙሴን ሕግ የናቀ ሰው ሁለት ወይም ሦስት ቢመሰክሩበት ያለ ርህራሄ ይሞታል ። የእግዚአብሔርንም ልጅ የካደ ያንንም የተቀደሰበትን የኪዳኑን ደም እንደ ርኩስ ነገር የቆጠረ ( ያሳደፈ ) ( እርሱስ አያድፍም ደሙን ሳይበቃ የተቀበለ ማለት ነው ) አንድም እንደ እሩቅ ብእሲ ደም እንደ ፍጡር ደም አድርጎ የቆጠረ እንዴት ይልቅ የሚብስ ቅጣት የሚገባው ይመስላችኋል ( ዕብ ፲ ፥ ፳፰ ) ይላል ። እግዚአብሔር ስለቤተ መቅደሱ በብሉይ ኪዳንም ዘመን እንዲህ ብሎ ነበር " አሁንም በዚህ ሥፍራ ለሚጸለይ ጸሎት ዐይኖቼ ይገለጣሉ ፥ ጆሮቼም ያደምጣሉ ። አሁንም ስሜ ለዘላለም በዚያ ይኖር ዘንድ ይህን ቤት መርጫለሁ ቀድሻለሁም ፤ ዐይኖቼና ልቤም ዘወትር በዚያ ይሆናሉ ። " ( ፪ ዜና . መዋ ፯ ፥ ፲፭ ) ። ቤተ መቅደሱ የእግዚአብሔር የክብሩ መገለጫ እንደሆነ ለአንድ ዘመን ብቻ ሳይሆን ስሙ ለዘላለም እንዲጠራበት ቤቱን እንዳከበረ በዚህ ቃል እንረዳለን ። በዚህም መሠረት የቤተ መቅደስ አገልግሎት በሐዲስ ኪዳንም ሳይቋረጥ ቀጥሏል ።

የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋና ደም እየተፈተተበት ፣ የሥጋ ነውር የሚወገድበት ብቻ ሳይሆን ለነፍስም የኃጢአት ሥርየት የሚሰጥበት ሆኗል ። ስለዚህ ቤተ መቅደሱ አበው የሠሩልን ሥርዓት እያከበርን ፣ በጥንቃቄ እየተመላለስን ቃለ እግዚአብሔር የምንማማርበት ፣ ንስሐ የምንገባበት ፣ ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን የምንቀበልበት ሊሆን ይገባል ። በልማድ በመመላለስ ፣ ዘመድ ማፍሪያ ፣ ከባልንጀራ መጠያየቂያ ፣ ከምድራዊ ችግር መላቀቂያ ብቻ ልናደርገው አይገባም ። ቤተ ክርስቲያን የሰማይ ደጅ ናትና በእርሷ ስንገኝ የሰማዩን ልናስብ ። ለዘላለማዊው ቤታችን አብልጠን ልንሠራ ይገባናል ።

አንዳንዶች ቤተ መቅደሱን የኦሪት ቤተ መቅደስ እንደሆነ የሚናገሩ የሚፈተተውን የጌታ ሥጋ እና ደም የሚያቃልሉ ። ቤተ ክርስቲያን በምትሰዋው መስዋዕት በምትቀድሰው ቅዳሴ በአገልግሎቷ ሁሉ የሚቀልዱ አሉ ። እነዚህም መናፍቃን እና የተሐድሶ እምነት አራማጆች ናቸው ። ቅዱስ ጳውሎስ እንደተናገረው ካልተመለሱ የበለጠውን ፍርድ ያገኛቸዋል ። የሚያቃልሉት የሙሴን ሕግ ሳይሆን እርሱ ወልደ እግዚአብሔር ወርዶ ተወልዶ የሠራውን ሕግ ነውና የበለጠውን ቅጣት እንዳያገኛቸው አውቀው በንስሐ ሊመለሱ ይገባል ።

ወዳጄ በመንገድህ በጉዞህ ሁሉ እንዲቀናህ ለእርሱ ለአምላክህ ልቡናህን ክፈት ። እንኳን ለእርሱ ለተቀመጠባት አህያ መሬት መርገጥ አይገባትምና እርሱ ከአንተ ጋር ሲሆን እሾህ አይወጋህም ጥፋት አያገኝህም ። ስለዚህ አምላክህን መውጣቴና እና መግባቴን ጠብቅ ሁልጊዜም ከእኔ አትለይ በለው ። ያን ጊዜ ሁሉ የአንተ ይሆናል ። ልብህ በተስፋ ይሞላል ።

በእንተ ሆሣዕና ከብዙ በጥቂቱ !

የተጨነቁ የሚጽናኑበት የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይዳረስ ዘንድ

16/04/2022

ሆሣዕና ምን ማለት ነው? የወይራ ዛፍና የዘንባባ ዝንጣፊ ምስጢራዊ ትርጓሜ ምንድነው ?
ጌታ በአህያ የመቀመጡን ምክንያቱን ለማወቅ 👇 👇 👇ያንብቡ ።

አዘጋጅ በለጠ ከበደ(የጣፈጡ ልጅ)አላቲኖስ✍

ሆሣዕና ማለት መድኀኒት ማለት ነው
ሆሣዕና የጌታችን የአምላካችን በዓል ነው
ከጌታችን ከዘጠኙ ዓበይት በዓላት አንዱ ነው።

✥ ሆሳዕና ክፍል 1✥

በዕለተ ሆሳዕና እስራኤላውያን ለምን የዘንባባ ዝንጣፊ ፤ የቴምር ዛፍ ዝንጣፊ እና የወይራ ዛፍ ዝንጣፊ ይዘው ዘመሩ? (ማቴ. 21÷1-17፣ ማር. 11÷ 1-10፣ ሉቃ. 19÷29-38፣ ዮሐ. 12÷12-15

የዘንባባ ዝንጣፊ፡-
☞ይስሃቅ በተወለደ ጊዜ አብርሃም ደስ ብሎት ዘንባባ ይዞ እግዚአብሄርን አመስግኖበታል የደስታ መግለጫ በመሆኑ አነተ ደሰታ የምታስገኝ ሃዘናችንንም የምታርቅ አምላክ ነህ ሲሉ ነው፡፡
☞ ዘንባባ ደርቆ እንደገና ህይወት ይዘራል የደረቀ ሕይወታችንን የምታለመልም አምላክ ነህ ሲሉ ነው
☞ ዘንባባ የሰላም ምልክት ነው የሰላም አምልክ ነህ ሲሉ ነው
☞ ዘንባባ እሾሃማ ነው አንተ ህያው አሸናፊ አምላክ ነህ ሲሉ ነው
☞ ዘንባባ እሳት አይበላውም ለብልቦ ይተወዋል እንጅ ጌታም አንተ ባህርይህ የማይመረመር ነው ሲሉ ነው
☞ ዘንባባ የነፃነት ምልክት ነው ከባርነት ነፃ የምታወጣን አንተነህ ሲሉ ነው አኛም ይህን በማሰብ ዘንባባ ይዘን ሆሳእና በአርያም እያልን እለቱን እናስባለን፡፡

የቴምር ዛፍ ዝንጣፊ፡-
☞ የቴምር ዛፍ ፍሬ ጣፋጭ ነው፦ በሃጥያት የመረረውን ሂወታችን የምታጣፍጥልን አምላክ ነህ ሲሉ ነው።
☞ የቴምር ፍሬ የሚገኘው ከዛፉ ከፍታ ላይ ነው አንተ አምላካችን ልዑለ ባህሪ ነህ ከፍ ከፍ ያልክ አምላክ ነህ ሲሉ ነው።
☞ የቴምር ዛፍ ፍሬ በውስጡ ያለው ፍሬ አንድ ነው አንድ አካል አንድ ባህሪ ነህ ሲሉ ነው።
☞ የቴምር ፍሬ በእሾህ የተከበበ ነው ይህም የአንት ባህሪ የማይመረመር በእሳት የተከበበ ነው ሲሉ ነው።

የወይራ ዛፍ ዝንጣፊ፡-
☞ የወይራ ቅጠል የሰላም ማብሰሪያ ነው ሰላማችንን የምታበስርልን የምታስገኝልን አንተ ነህ ሲሉ ነው፡፡
☞ የወይራ ቅጠል ከእንጨት ሁሉ ጽኑ ነው አንተም ጽኑ ሃያል አምላክ ነህ ሲሉ ነው።
☞ ወይራ ለመብራት ያገለግላል ፍሬው ዘይት ያወጣል ከወይራ የሚገኝ ዘይት ጨለማን አሸንፎ ብርሃን እንደሚሰጥ ሁሉ አንተም ጨለማ ህይወታችንን የምታስወግድልን አምላክ ነህ ሲሉ ነው።
☞ በኦሪት ግዜ የወይራ ዘይት ለመስዋአትነት ይቀርብ ነበር አንተም እንደ ዘይቱ ለመተላለፋችን መስዋዕት ሆነህ የምትቀርብ አምላክ ነህ ሲሉ ነው። በመስቀል ላይ መስዋዕት ሆኗልና።

❖ ጌታችን አምላካችን ደቀ መዛሙርቱን ወደ ፊታችው ባለው ሀገር ሂዱና አህያ ከውርጭላዋ ጋራ ታስራ ታገኛላችው ፈታችው እምጡልኝ ምን ታደርጋላችው? የሚላቸው ሰው ካለ ጌታቸው ይፈልጋቸዋል በሉ ብሎ ላካቸው

ከዚህ በኋላ ደቀ መዛሙርቱ እንዳዘዛቸው ሂደው ፈተው አመጡለት
በዚያም የተሰበሰቡት ሁሉ በአህዮች ላይ ልብሳቸውን ጎዘጎዙለት ጌታችንም በሁለቱ አህዮች ላይ ተቀመጠ

👉ከሌሎቹ እንስሳት አህዮችን መርጦ በአህዮች ተቀምጧል
አህዮች በመጽሐፍ ቅዱስ ብዙ ታሪክ አላቸውና።

❖የበልአም አህያ የመልአኩን ክብር ለመግለጥ አፍ አውጥታ ተናግራለች ዘሁል22÷28

❖ ጌታችን በተወለደ ጊዜ አህዮች ከከብቶች ጋር
በበረት እስትፋሳቸውን አሟሙቀውታል ቅዳሴ ማርያም

❖ የሰላም ንጉሥ መሆኑን ለመግጽ

ምሳሌ- ቀድሞ ነቢያት ዘመነ ጸብእ ከሆነ በፈረስ ተቀምጠው ዘገር ነጥቀው ይታያሉ ዘመነ ሰላም ከሆነ
በአህያ ተቀምጠው መነሳንስ ይዘው ይታዩ ነበርና ጌታችንም ዘመነ ሰላም ነው ሲል በአህያ ተቀምጦ መጥቷል።

❖ ትንቢቱን ለመፈጸም
ትንቢት- አንቺ የጽዮን ልጅ ሆይ እጅግ ደስ ይበልሽ አንቺ የኢየሩሳሌም ልጅ ሆይ እልል በዪ እነሆ ንጉሥሽ ጻድቅና አዳኝ ነው
ትሁትም ሁኖ በእህያም በውርንጭላቱ ላይ ተቀምጦ ወደ አንቺ ይመጣል ሰረገላውንም ከኤፍሬም ፈረሱንም ከኢየሩሳሌም ያጠፋል ብሎ ዘካርያስ ትንቢት ተናግሮ ነበርና ለመፈጸም ነው ዘካ 9÷1

❖ምሥጢሩን ለመግለጽ
ምሥጢር- በአህያ የተቀመጠ ሸሽቶ አያመልጥም አሳዶም አይዝም እሱም ካልፈለጋችሁኝ አልገኝም ከፈለጋችሁኝ አልታጣም ሲል በአህያ ተቀምጦ መጥቷል ይህ እና ሌሎች ምስጢራትን ለመግለፅ ትንቢት ለመፈጸም አምላካችን በአህ።

❖ በዓለ በሆሳዕና ጊዜ የጌታችን ትህትና የምናስብበት እኔ ምሰሉ ስላለ በትህትና እራሳችንን የምናኖርበት ። በእላይ በሰማይ ኪሩቤል በፍርሃት መንበሩን የሚሸከሙት ቅዱሳን መላእክት ያለማቋረጥ የሚመሰግኑት በትህትና በአህያ ጀርባ የተቀመጠ በሕፃናት አንደበት የተመሰገን ቢታንያ ድንጋዮች የዘመሩለት የአምላካችን የጌታችን ክብረ በዓል በምናከብረበት ጊዜ የአምላካችን ትህትናውን በልባችን እያሰብ በተግባር እየገለጥ እንድንኖር አምላካችን ይርዳን ።

❤️በዓሉን በዓለ ክብር በዓለ ፍስሐ ያድርግልን ሰላም ፍቅርን አንድነት አምላካችን ይስጠን ፡፡❤️

በድጋሚ ተለጠፈ

አዘጋጅ በለጠ ከበደ(የጣፈጡ ልጅ) #አላቲኖስ ✍

╔​✞═┉✽🌹✥🌹✽┉═✞╗
❀ ❀
╚✞═┉✽🌹✥🌹✽┉═✞╝አላቲኖስ

የተሣተውን ፤ የተረሳው፤ የተገደፈውን፤ የነጠፈውን በቀና መንፈስ አቃንታቹ አንብቡት🙏🙏🙏

በቴሌ ግራም
👉 " መዝገበ ሃይማኖት" t.me/mezgebehaymanot

በ Facebook " መዝገበ ሃይማኖት" ወይም ከዚህ እታች ያለውን በመጫን ፔጁን ይቀላቀላሉ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇... ...... 👉አስተማሪ ጹሁች ለማግኝት ከስር ያለውን በመጫን ላይክ 👍 ይቀላቀላሉ https://www.facebook.com/%E1%88%98%E1%8B%9D%E1%8C%88%E1%89%A0-%E1%88%83%E1%8B%AD%E1%88%9B%E1%8A%96%E1%89%B5-232318137666445/
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆

ወስብሐት ወለመስቀሉ
ወወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ

16/04/2022

እንኳን ለበዓለ ሆሣዕና አደረሰን አደረሳችሁ!!
"የሚቀድሙትም ሕዝብ የሚከተሉትም ሆሣዕና ለዳዊት ልጅ በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው ሆሳዕና በአርያም እያሉ ይጮኹ ነበር "ማቴ 21_9


ወእንዘ ሰሙን በዓለ ፋሲካ ቀርቡ አርዳኢሁ ለአምላከ ጽድቅ ኀበ ደብረ ዘይት ሙራደ አቀብ ሀገረ እግዚአብሔር ወተቀበልዎ ሕዝብ ብዙኃን አዕሩግ ወሕፃናት ነሢኦሙ አዕፁቀ በቀልት እንዘ ይብሉ ሆሣዕና በአርያም ተፅዒኖ ዲበ ዕዋል ቦአ ሀገረ ኢየሩሳሌም በትፍሥሕት ወበሐሤት ይሁቦሙ ኃይለ ወሥልጣነ

ትርጉም፦

የፋሲካ በዓል ሰሞን ሲሆን ደቀ መዛሙርቱ በእግዚአብሔር ሀገር በደብረ ዘይት በአቀበቱ መውረጃ ወደ እውነተኛ አምላክ ቀረቡ ብዙ ወገኖች ሽማግሌዎችና ሕፃናት የዘንባባ ቅጠሎችን ይዘው ሆሣዕና በአርያም እያሉ ተቀበሉት በአህያይቱ ግልገል ላይ ተቀምጦ በደስታና በሐሤት ወደ ኢየሩሳሌም ገባ ኃይልና ሥልጣንን ይሰጣቸዋል

ምስባክ፦
ቡሩክ ዘይመጽእ በስመ እግዚአብሔር
ባረክናክሙ እምቤተ እግዚአብሔር
እግዚአብሔር እግዚእ አስተርአየ ለነ

በምዕዋድ ጊዜ የሚባሉ አቡኖችና ምስባኮች


ተፈሣሕኩ እስመ ይቤሉኒ ቤተ እግዚአብሔር ነሐውር
ወቆማ እገሪነ ውስተ አዕፃድኪ ኢየሩሳሌም
ኢየሩሳሌምሰ ሕንጽት ከመ ሀገር

አቡን፦ በ፪ አርእዩነ ፍኖቶ ወንሑር ቤቶ እስመ እምጽዮን ይወጽእ ሕግ ወቃለ እግዚአብሔር እምኢየሩሳሌም ንሳለማ ለመድኃኒትነ በትፍሥሕት ተቀበልዋ ለታቦት እስመ ዋካ ይእቲ ወብርሃን

ምልጣን፦ ንሳለማ በል
ምዕዋድ፦ እስመ ዋካ ይእቲ ወብርሃን ዋካ ይእቲ ወብርሃን

፪ ንፍሑ ቀርነ በዕለተ ሠርቅ
በዕምርት ዕለት በዓልነ
እስመ ሥርዓቱ ለእስራኤል ውእቱ

አቡን፦ በ፮ ሰመያ አብርሃም ወይቤላ ዛቲ ዕለት በዓለ እግዚአብሔር ንፍሑ ቀርነ በዕለተ ሠርቅ በዕምርት ዕለት በዓልነ ሶበ ተዘከርናሃ ለጽዮን

ምልጣን፦ ንፍሑ ቀር በል
ምዕዋድ፦ ሶበ ተዘከርናሃ ለጽዮን ሶበ ተዘከርናሃ ለጽዮን

፫ እምአፈ ደቂቅ ወሕፃናት አስተዳሎከ ስብሐተ
በእንተ ጸላኢ
ከመ ትንሥቶ ለጸላኢ ወለገፋዒ

አቡን፦ በ፮ ወትቤ ጽዮን አርኅዉ ሊተ አናቅጸ ይባኡ ሕዝብ ብዙኃን ወያዕትቱ ዕብነ እምፍኖት ለንጉሥ ለወልደ ዳዊት ንጉሦሙ ለእስራኤል ውእቱ ይብሉ ሆሣዕና በአርያም

ምልጣን፦ ወያዕትቱ በል
ምዕዋድ፦ ይብሉ ሆሣዕና በአርያም

፬ እምሥራቀ ፀሐይ እስከነዓረብ
ወእምጽዮን ሥነ ስብሐቲሁ
እግዚአብሔርሰ ገሃደ ይመጽእ

አቡን፦ በ፮ ባረኮ ያዕቆብ ለይሁዳ ወልዱ ወይቤሎ ሀሎ ንጉሥ ዘይወጽእ እምኔከ ዘየሐፅብ በወይን ልብሶ ወበደመ አስካል ሰንዱኖ ንጉሦሙ ለእስራኤል ውእቱ ይብሉ ሆሣዕና በአርያም

ምልጣን፦ ዘየሐፅብ በል
ምዕዋድ፦ ይብሉ ሆሣዕና በአርያም

፭ ትሴብሖ ኢየሩሳሌም ለእግዚአብሔር
ወሰብሒዮ ለአምላክኪ ጽዮን
እስመ አጽንዐ መናሥግተ ኆኃትኪ

በ፪ ባኡ ውስተ ሀገር ወበዊአክሙ ትረክቡ ዕዋለ ዕሡረ ፍትሕዎ ወአምጽእዎ ሊተ

ምልጣን፦ ፍትሕዎ ወአምጽእዎ ሊተ

ሰላም በ፩ አልጺቆ ኢየሱስ ኢየሩሳሌም ርእያ ለሀገር ወይቤላ ሶበ ተአምሪ ጽዮን ነዋ ንገሥኪ በጽሐ ብርሃንኪ ዮም ሰላምኪ

ምልጣን፦ ወይቤላ ሶበ ተአምሪ ጽዮን ነዋ ንጉሥኪ በጽሐ ብርሃንኪ፤ ተፈሥሒ በሕዝብኪ፤ ይትሐፈሩ ጸላእትኪ፤ ሰላምኪ ሰላምኪ ዮም ሰላምኪ

ዘምሩ ለእግዚአብሔር ዘየኀድር ውስተ ጽዮን
ወንግርዎሙ ለአሕዛብ ምግባሮ
እስመ ተዘከረ ዘይትሐሠሥ ደሞሙ
መልካም በዓል!!
ይቆየን!
7/08/2014 አ.ም
አዲስአበባ

Address

Gofa/Sawla
Arba Minch'

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ገ/ሚካኤል ረታ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Place Of Worship

Send a message to ገ/ሚካኤል ረታ:

Share