ነቅዐ ጽድቅ የጋሞና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሚዲያ

ነቅዐ ጽድቅ  የጋሞና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሚዲያ Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from ነቅዐ ጽድቅ የጋሞና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሚዲያ, Religious Center, Arba Minch, Arba Minch'.
(3)

"ነዋ ወንጌለ መንግሥት"

▶️ቴሌ ግራም
https://t.me/nekeatsidkmedia
▶️ፌስ ቡክ
https://www.facebook.com/profile.php?id=1
▶️ዩቱብ
https://www.youtube.com/
▶️ኢንታግራም
https://www.instagram.com/gamoha
▶️ቲክ ቶክ
tiktok.com/

በአርባ ምንጭ እድገት በር ደብረ አእላፍ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን የጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት የዕረፍታቸው መታሰቢያ ዓመታዊ ክብረ በዓል የማኅሌት አገልግሎት በፎቶነቅዐ ጽድቅ ...
30/08/2026

በአርባ ምንጭ እድገት በር ደብረ አእላፍ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን የጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት የዕረፍታቸው መታሰቢያ ዓመታዊ ክብረ በዓል የማኅሌት አገልግሎት በፎቶ
ነቅዐ ጽድቅ የጋሞና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሚዲያ

30/08/2026

ቀጥታ ስርጭት ▶️ ከአርባ ምንጭ ደብረ አእላፍ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን የጻድቁ አቡነ ተክለ ...

30/08/2026

ቀጥታ ስርጭት ▶️ ከአርባ ምንጭ ደብረ አእላፍ አቡነ ተክለ ሃይማኖት የጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት በዓለ ...

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በጋሞና አካባቢው ዞኖች ሀገረ ስብከት፣ በኧሌ ዞን ወረዳ ቤተ ክህነት ስር በሚገኘው በቶሾ ጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን የጻድቁ ዓ...
29/08/2026

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በጋሞና አካባቢው ዞኖች ሀገረ ስብከት፣ በኧሌ ዞን ወረዳ ቤተ ክህነት ስር በሚገኘው በቶሾ ጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን የጻድቁ ዓመታዊ የእረፍት በዓላቸው መታሰቢያ የዋዜማ ሥነ- ሥርዓት በፎቶ

📷የኧሌ ዞን ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ሚዲያ
ነቅዐ ጽድቅ የጋሞና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሚዲያ

ማኅበረ ቅዱሳን ማስተር ፕላንን ጨምሮ 76 የቤተ ክርስቲያንና የአገልግሎት ሕንጻ ዲዛይኖችን በመሥራት ከ97.1 ሚሊዮን ብር በላይ ወጭዎችን ማስቀረት መቻሉን አስታወቀ።፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠...
29/08/2026

ማኅበረ ቅዱሳን ማስተር ፕላንን ጨምሮ 76 የቤተ ክርስቲያንና የአገልግሎት ሕንጻ ዲዛይኖችን በመሥራት ከ97.1 ሚሊዮን ብር በላይ ወጭዎችን ማስቀረት መቻሉን አስታወቀ።
፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠
ነሐሴ ፳፫ ቀን ፳፻፲፰ ዓ.ም.| ነቅዐ ጽድቅ ሚዲያ

17ኛ ዓለም አቀፍ ጠቅላላ ጉባኤውን እያደረገ ያለው ማኅበሩ ይህን የገለጸው በሰብሳቢው አቶ ካሳሁን ኃ/ማርያም ነው።

ማኅበሩ ኦርቶዶክሳዊ ቤተሰብን ለማጠናከር እና ማኅበራዊ ቀውሶች በምእመናን ላይ እየፈጠሩት ያለውን ሥነ ልቦናዊና ሥነ አእምሯዊ ችግሮችን ለማቃለል ለሚሰማሩ 664 ካህናትና ባለሙያዎች የአመካካሪነት ሥልጠናዎች በተለያዩ አካባቢዎች ሰጥቷል።

ማስተር ፕላንን ጨምሮ 76 የቤተ ክርስቲያንና የአገልግሎት ሕንጻ ዲዛይኖችን እንዲሁም 18 የፕሮጀክት ጥናቶችና ቢዝነስ ፕላኖችን ሠርቶ ለጠየቁ አካላት አስረክቧል፤ በዚህም ከ97.1 ሚሊዮን ብር በላይ ወጭዎችን ማስቀረት ተችሏል።

ነጻ የህግ ምክርና የጥብቅና አገልግሎት ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው 40 አብያተ ክርስቲያናትና ኦርቶዶክሳዊያን ድጋፍ ተደርጓል፡፡

በልዩ ልዩ ማኅበራዊ ቀውሶች ለተጎዱ በ11 ሀገረ ስብከቶች ማለትም በሰቆጣ፣ በወልድያ፣ በደሴ፣ በግልገል በለስ፣ በነቀምት፣ በወላይታ ሶዶ፣ በጂንካ፣ በሻሸመኔ፣ በፍቼ፣ በደብረ ብርሃንና ለሚገኙ 3,962 ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ ተደርጓል።

በትግራይ ክልል በመቐለ ከተማ ሰባ ካሬ፣ ሰሜን ምዕራብ ዞን ሕጻፅና ማይድሙ፣ በሽሬ ከተማና ዙሪያው፣ በአክሱም ከተማ በሚገኙ ጊዜያዊ መጠለያ ጣቢያዎች ለሚገኙ ተፈናቃዮች እና በአካባቢው ለሚገኙ 5 ገዳማትና ጉባኤ ቤቶችም የምግብ ግብዓቶች ድጋፍ አድርጓል።

በተለያዩ የሀገራችን ቦታዎች በሃይማኖት ተኮር ጥቃቶች አሳዳጊዎቻቸውን ላጡ 67 አዳጊዎች ቋሚ ወርኃዊ ድጋፎችን በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡

መረጃው፦ የማህበረ ቅዱሳን ዋናው ማዕከል የፌስ ቡክ ገጽ ነው።EOTCMK
ነቅዐ ጽድቅ የጋሞና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሚዲያ

የምስራች ፲፩ ከፕሮቴስታንት ፩ ከእስልምና በድምሩ ፲፪ አዳዲስ የሌላ ሃይማኖት ተከታዮች ትምህርተ ሃይማኖት ተከታክለው የሥላሴን ልጅነት አገኙ፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠...
29/08/2026

የምስራች

፲፩ ከፕሮቴስታንት ፩ ከእስልምና በድምሩ ፲፪ አዳዲስ የሌላ ሃይማኖት ተከታዮች ትምህርተ ሃይማኖት ተከታክለው የሥላሴን ልጅነት አገኙ
፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠
ነሐሴ ፳፫ ቀን ፳፻፲፰ ዓ.ም.| ነቅዐ ጽድቅ ሚዲያ

«እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው።»ማቴ ፳፰፡፲፱

በአርባ ምንጭ ደብረ መድኃኒት መድኃኔ ዓለም ካቴድራል ለተከታታይ ቀናት ሲሰጥ የቆየውን የኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ትምህርተ ሃይማኖት ሲከታተሉ የቆዩ ፲፪ አዳዲስ ምዕመናን ጥምቀተ ክርስትና በመቀበል ወደ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ተቀላቀሉ።

ትምህርቱን ተከታትለው የሥላሴን ልጅነት ከተቀበሉት መካከል ፲፩ዱ ከፕሮቴስታንት እምነት፣ ፩ዱ ደግሞ ከእስልምና እምነት የመጡ ሲሆን፤ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም በማመንና በማወቅ የክርስትና ጥምቀትን ተቀብለዋል። ይህ የተቀደሰ ተግባር ሀገረ ስብከቱ ያቀደው የ፲ ዓመቱ መሪ እቅድ አንዱ አካል ሆኖ እየተከናወነ እንደሚገኝ ተመልክቷል።

እነዚህን ነፍሳት ወደ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በመመለሱና በማስተማሩ ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረከቱት በአርባ ምንጭ ደብረ መድኃኒት መድኃኔ ዓለም ካቴድራል እና በደብረ ኢዮር ቅዱስ ሩፋኤል አብያተ ክርስቲያናት የስብከተ ወንጌል ክፍል ኃላፊ ቀሲስ ተስፋዬ ከተማ ናቸው። ቀሲስ ተስፋዬ ሌሎች አገልጋዮችን በማስተባበር በተለይም በገጠሪቱ ቤተ ክርስቲያን ጋሞኛን ጨምሮ በተለያዩ ቋንቋዎች ሰፊ የወንጌል አገልግሎት በመስጠትና በርካቶችን ከጠፉበት ወደ እውነት መንገድ በመመለስ የሚታወቁ የቤተ ክርስቲያን አገልጋይ የጀርባ አጥንት ናቸው።

ይህ በሀገረ ስብከቱ የ፲ ዓመት መሪ እቅድ መሠረት የተከናወነው የወንጌል ትምህርት በሀገረ ስብከቱ በሚገኙ በሁሉም ወረዳ ቤተ ክህነቶች ገዳማትና አድባራት ወደፊትም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ታውቋል።

መረጃውን ያደረሰን፦የሁለቱ አብያተ ክርስቲያናት ስብከተ ወንጌል ክፍል ነው።

ነቅዐ ጽድቅ የጋሞና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሚዲያ
ግናይ ሚዲያ የአርባ ምንጭ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል እና ደብረ መንክራት ቅዱስ ሚካኤል አብያተ ክርስቲያናት ሚዲያ በጋሞና አካባቢው ዞኖች ሀገረ ስብከት የዳራማሎ ወረዳ ቤተ ክህነት ሚዲያ በጋሞ እና አከባቢው ዞኖች ሀገረ ስብከት የምዕራብ ዓባያ ወረዳ ቤተክነት ሚዲያ ኖላዊ-የአርባ ምንጭ ደ/መ/መድኃኔ ዓለም ካቴድራል እና ደ/ኢ/ቅ/ሩፋኤል አብያተክርስቲያናት ሚዲያ ዜና ሥላሴ በአርባ ምንጭ የደብረ ልዑል ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን ሚዲያ በጽሐ ሠናይ - የአርባ ምንጭ ዙሪያና ጋጮ ባባ ወረዳዎች ቤተ ክህነት ሚዲያ Mahibere Kidusan - ማኅበረ ቅዱሳን አርባ ምንጭ ማዕከል ጋሞና አከባቢው ዞኖች ሀገረስብከት ካምባና ጋርዳ ማርታ ወረዳዎች ቤተክህነት ሚዲያ የኧሌ ዞን ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ሚዲያ የኮንሶ ዞን ወረዳዎች ቤተ-ክህነት አርባምንጭ ደብረ መንክራት ቅዱስ ሚካኤል Abo media - አቦ ሚዲያ የኢኦተቤ መገናኛ ብዙኀን አገልግሎት ሥርጭት ድርጅት/ EOTC Broadcasting Service Agency/ ገረሴ መጥምቄ መሌኮት ቅዱሥ ዬሐንስ ስለ ታምራቱ ና ወደ ቦታው ለምመጡ መሬጃ እንሰጣለን ። በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በጋርዱላ ዞን ዲራሼ ወረዳ ቤተክህነትና የጊዶሌ ፬ቱ አጥቢያ ሚዲያ ፔጅ አቡቀለምሲስ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ሚዲያ የ/ኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያን ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ/Department of Public Relation,EOTC የጋሞ እና አካባቢው ዞኖች ሀገረ ሰብከት በደራማሎ ወረዳ ቤተ ክህነት መነና ቅ/ሚ/ቤ/ክ/ማ ገጽ እጬጌ የወላይታ ሀገረ ስብከት ሚዲያ ሰገን ዙርያ ወረዳ ቤቴ ክህነት Gamo ArbaMinch የቅዱስ ጳውሎስ መልዕክት

የማኅበረ ቅዱሳን ፲፯ ኛውን ዓለም አቀፍ ጠቅላላ ጉብኤ ተሳታፊዎች እየገቡ ይገኛሉ።፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠ነሐሴ ፳፪ ቀን ፳፻፲፰ ዓ.ም.| ነቅዐ ጽድቅ ሚ...
28/08/2026

የማኅበረ ቅዱሳን ፲፯ ኛውን ዓለም አቀፍ ጠቅላላ ጉብኤ ተሳታፊዎች እየገቡ ይገኛሉ።
፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠
ነሐሴ ፳፪ ቀን ፳፻፲፰ ዓ.ም.| ነቅዐ ጽድቅ ሚዲያ

ጠቅላላ ጉባኤው በነገው ዕለት የሚጀመር መሆኑን የገለጸው ማህበሩ በጉባኤው የማኅበሩ የሁለት ዓመታት የአገልግሎት አፈጻጸም ሪፖርት ላይ ተወያይቶ ቀጣይ አቅጣጫ እንደሚሰጥ ገልጿል።

በዚህ ጉባኤ ከ700 በላይ በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገራት ያሉ የማእከላትና ግቢ ጉባኤ አመራሮች በተወካዮቻቸው አማካኝነት እንዲሁም ተጋባዥ እንግዶች በአካልና በኦላይን ይሳተፋሉ። በአሁኑ ሰዓትም አቀባበል እየተደረገላቸው እና እግር አጠባ እየተካሄደ መሆኑን ማህበረ ቅዱሳን ዋናው ማዕከል በይፋዊ የፌስ ቡክ ገጹ አሳውቋል።

EOTCMK
ነቅዐ ጽድቅ የጋሞና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሚዲያ

ታላቅ የንግስ በዓል ጥሪ ለአርባ ምንጭና አካባቢዋ ምዕመናን በሙሉ። “ጻድቅስ እንደ ዘንባባ ያብባል፥ እንደ ሊባኖስ ዝግባም ያድጋል።”መዝሙር ፺፪፥፲፪በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ በጋሞና አካባቢው ዞኖች ...
28/08/2026

ታላቅ የንግስ በዓል ጥሪ ለአርባ ምንጭና አካባቢዋ ምዕመናን በሙሉ።

“ጻድቅስ እንደ ዘንባባ ያብባል፥ እንደ ሊባኖስ ዝግባም ያድጋል።”
መዝሙር ፺፪፥፲፪

በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ በጋሞና አካባቢው ዞኖች ሀገረ ስብከት በአርባ ምንጭና በዙሪያዋ የምትገኙ ኦርቶዶክሳውያን ምዕመናን በሙሉ፤ የጻድቁ አባታችን የአቡነ ተክለ ሃይማኖት የእረፍት በዓላቸው መታሰቢያ በየዓመቱ ነሐሴ ፳፬ ቀን በቤተ ክርስቲያናችን በታላቅ ድምቀት ይከበራል።

የዘንድሮው የ፳፻፲፰ ዓ.ም በዓለ እረፍታቸው በአርባ ምንጭ እድገት በር ደብረ አእላፍ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ብፁዕ አቡነ ኤልያስ የጋሞና አካባቢው ጎፋና ባስኬቶ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ፣የሀገረ ስብከቱ ከፍተኛ የሥራ ክፍል ኃላፊዎች ፣ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን በተገኙበት በልዩ መንፈሳዊ ሥነ-ሥርዓት፣ በዝማሬና በታላቅ ድምቀት ይከበራል።

በቅዱሳን አምላክ ፊት ቆመን በጸሎታቸው ለመባረክ፣ ከጻድቁ በረከት ለመሳተፍና የበዓሉ ተካፋይ ለመሆን ሁላችሁም የክርስቶስ ቤተሰቦች ተጋብዛችኋል።

በእለተ እሁድ ነሐሴ 🗓፳፬ ቀን ፳፻፲፰ ዓ.ም በአርባ ምንጭ እድገት በር ደብረ አእላፍ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ከዋዜማው ጀምሮ ማኅሌት፣ ቅዳሴ፣ መንፈሳዊ ስብከቶች በታላቅ መንፈሳዊ ድምቀት ይከናወናል።

የጻድቁ አባታችን ጸሎትና ምልጃ፣ የበአለ እረፍታቸው በረከትና ረድኤት ከሁላችን ጋር ይሁን!

የአርባ ምንጭ ደ/አ/አ/ተ/ሃ/ቤ/ክ/ጽ/ቤት
ነቅዐ ጽድቅ የጋሞና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሚዲያ

ግናይ ሚዲያ የአርባ ምንጭ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል እና ደብረ መንክራት ቅዱስ ሚካኤል አብያተ ክርስቲያናት ሚዲያ በጋሞ እና አከባቢው ዞኖች ሀገረ ስብከት የምዕራብ ዓባያ ወረዳ ቤተክነት ሚዲያ የኮንሶ ዞን ወረዳዎች ቤተ-ክህነት ጋሞና አከባቢው ዞኖች ሀገረስብከት ካምባና ጋርዳ ማርታ ወረዳዎች ቤተክህነት ሚዲያ በጋሞና አካባቢው ዞኖች ሀገረ ስብከት የዳራማሎ ወረዳ ቤተ ክህነት ሚዲያ በጽሐ ሠናይ - የአርባ ምንጭ ዙሪያና ጋጮ ባባ ወረዳዎች ቤተ ክህነት ሚዲያ ዜና ሥላሴ በአርባ ምንጭ የደብረ ልዑል ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን ሚዲያ የኧሌ ዞን ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ሚዲያ ገረሴ መጥምቄ መሌኮት ቅዱሥ ዬሐንስ ስለ ታምራቱ ና ወደ ቦታው ለምመጡ መሬጃ እንሰጣለን ። የጋሞ እና አካባቢው ዞኖች ሀገረ ሰብከት በደራማሎ ወረዳ ቤተ ክህነት መነና ቅ/ሚ/ቤ/ክ/ማ ገጽ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በጋርዱላ ዞን ዲራሼ ወረዳ ቤተክህነትና የጊዶሌ ፬ቱ አጥቢያ ሚዲያ ፔጅ Abo media - አቦ ሚዲያ የኢኦተቤ መገናኛ ብዙኀን አገልግሎት ሥርጭት ድርጅት/ EOTC Broadcasting Service Agency/ አቡቀለምሲስ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ሚዲያ የ/ኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያን ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ/Department of Public Relation,EOTC ኖላዊ-የአርባ ምንጭ ደ/መ/መድኃኔ ዓለም ካቴድራል እና ደ/ኢ/ቅ/ሩፋኤል አብያተክርስቲያናት ሚዲያ Mahibere Kidusan - ማኅበረ ቅዱሳን አርባ ምንጭ ማዕከል አርባምንጭ ደብረ መንክራት ቅዱስ ሚካኤል

የቆጎታ ወረዳ ከጨንቻ ወረዳ ቤተ ክህነት ተለይቶ ራሱን የቻለ ወረዳ ቤተ ክህነት ሆኖ በመዋቅር ደረጃ እንዲደራጅና እንዲወጣ ሙሉ ስምምነት ላይ ተደረሰ።፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠...
28/08/2026

የቆጎታ ወረዳ ከጨንቻ ወረዳ ቤተ ክህነት ተለይቶ ራሱን የቻለ ወረዳ ቤተ ክህነት ሆኖ በመዋቅር ደረጃ እንዲደራጅና እንዲወጣ ሙሉ ስምምነት ላይ ተደረሰ።
፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠
ነሐሴ ፳፪ ቀን ፳፻፲፰ ዓ.ም.| ነቅዐ ጽድቅ ሚዲያ

በጋሞና አካባቢው ዞኖች ሀገረ ስብከት በቆጎታ ወረዳ ቤተ ክህነት ምስረታ ሂደት ላይ ያተኮረ ታላቅና ታሪካዊ ጉባኤ በተሳካ ሁኔታ የተካሄደ ሲሆን በዚሁ ታሪካዊ ስብሰባ ላይ የጋሞና አካባቢው ዞኖች ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ ሊቀ ኅሩያን ገሪማ ጌታነህ፣ የሀገረ ስብከቱ ዋና ጸሐፊ መጋቤ ሠናያት ያዕቆብ ደስታ፣ የሀገረ ስብከቱ የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ኃላፊ መምህር አባይነህ ፀጋዬ፣ የጨንቻ ዙሪያና ቆጎታ ወረዳዎች ቤተ ክህነት ሥራ አስኪያጅ ሊቀ ብርሃናት ዳዊት መርዕድ እና የቤተ ክህነቱ ዋና ጸሐፊ መልአከ ፀሐይ ፈቀደ ዓምደ ማርያም ተኝተዋል። በተጨማሪም የአጥቢ አብያተክርስቲያናት ካህናት፣ የሰበካ ጉባኤ አባላት፣ የሰንበት ትምህርት ቤት ተወካዮች በቦታው ተገኝተዋል።

አዲሱ መዋቅር ሥራውን በይፋ የሚጀምረው በብፁነታቸው በሚመራው የሀገረ ስብከቱ አስተዳደር ጉባኤ ለውይይት ከቀረበ በኋላ በብፁዕነታቸው ቡራኬና አባታዊ የሥራ መመሪያ ሲሰጥ ከመስከረም ወር ፳፻፲፱ ዓ.ም. ጀምሮ እንደሆነ ተገልጿል። በመቀጠልም ጽ/ቤቱን በሁለንተናዊ መልኩ የሚያደራጅ ፯ አባላት ያሉት የመዋቅር አዘጋጅ ኮሚቴ ተመርጧል።

የተመረጡት የኮሚቴ አባላት በቅን ልቦናና በትሕትና እንዲሠሩ ጸሎት የተደረገላቸው ሲሆን፣ በክቡር ሥራ አስኪያጅ ሊቀ ኅሩያን ገሪማ ጌታነህ አማካኝነት የሥራ መመሪያ ከተሰጣቸው በኋላ ቃለ መሐላ መፈጸማቸው ተገልጿል።

ሙሉው ጉባኤ በአንድነትና በተረጋጋ መንፈስ ተከናውኖ የተደረሱት ውሳኔዎች በቃለ ጉባኤ ተመዝግበው ጉባኤው አጽድቋል። ይህ ታሪካዊና ቅዱስ ዓላማ ያለው መርሃ ግብር በሊቀ ኅሩያን ገሪማ ጌታነህ አባታዊ ቡራኬና መልእክት በጸሎት ተጠናቋል።

ነቅዐ ጽድቅ የጋሞና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሚዲያ

▶️ቴሌ ግራም
https://t.me/nekeatsidkmedia

▶️ፌስ ቡክ
https://www.facebook.com/profile.php?id=1

▶️ዩቱብ
https://www.youtube.co m/

▶️ኢንታግራም
https://www.instagram.com/nekeatsidkemedia?igsh=MWsycDFxaW0yaWxyaQ==

▶️ቲክ ቶክ
tiktok.com/

26/08/2026

ታላቅ የንግስ በዓል ጥሪ ለአርባ ምንጭና አካባቢዋ ምዕመናን በሙሉ።

“ጻድቅስ እንደ ዘንባባ ያብባል፥ እንደ ሊባኖስ ዝግባም ያድጋል።”
መዝሙር ፺፪፥፲፪

በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ በጋሞና አካባቢው ዞኖች ሀገረ ስብከት በአርባ ምንጭና በዙሪያዋ የምትገኙ ኦርቶዶክሳውያን ምዕመናን በሙሉ፤ የጻድቁ አባታችን የአቡነ ተክለ ሃይማኖት የእረፍት በዓላቸው መታሰቢያ በየዓመቱ ነሐሴ ፳፬ ቀን በቤተ ክርስቲያናችን በታላቅ ድምቀት ይከበራል።

የዘንድሮው የ፳፻፲፰ ዓ.ም በዓለ እረፍታቸው በአርባ ምንጭ እድገት በር ደብረ አእላፍ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ብፁዕ አቡነ ኤልያስ የጋሞና አካባቢው ጎፋና ባስኬቶ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ፣የሀገረ ስብከቱ ከፍተኛ የሥራ ክፍል ኃላፊዎች ፣ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን በተገኙበት በልዩ መንፈሳዊ ሥነ-ሥርዓት፣ በዝማሬና በታላቅ ድምቀት ይከበራል።

በቅዱሳን አምላክ ፊት ቆመን በጸሎታቸው ለመባረክ፣ ከጻድቁ በረከት ለመሳተፍና የበዓሉ ተካፋይ ለመሆን ሁላችሁም የክርስቶስ ቤተሰቦች ተጋብዛችኋል።

በእለተ እሁድ ነሐሴ 🗓፳፬ ቀን ፳፻፲፰ ዓ.ም በአርባ ምንጭ እድገት በር ደብረ አእላፍ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ከዋዜማው ጀምሮ ማኅሌት፣ ቅዳሴ፣ መንፈሳዊ ስብከቶች በታላቅ መንፈሳዊ ድምቀት ይከናወናል።

የጻድቁ አባታችን ጸሎትና ምልጃ፣ የበአለ እረፍታቸው በረከትና ረድኤት ከሁላችን ጋር ይሁን!

የአርባ ምንጭ ደ/አ/አ/ተ/ሃ/ቤ/ክ/ጽ/ቤት
ነቅዐ ጽድቅ የጋሞና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሚዲያ
ግናይ ሚዲያ የአርባ ምንጭ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል እና ደብረ መንክራት ቅዱስ ሚካኤል አብያተ ክርስቲያናት ሚዲያበጋሞ እና አከባቢው ዞኖች ሀገረ ስብከት የምዕራብ ዓባያ ወረዳ ቤተክነት ሚዲያጋሞና አከባቢው ዞኖች ሀገረስብከት ካምባና ጋርዳ ማርታ ወረዳዎች ቤተክህነት ሚዲያየጋሞ እና አካባቢው ዞኖች ሀገረ ሰብከት በደራማሎ ወረዳ ቤተ ክህነት መነና ቅ/ሚ/ቤ/ክ/ማ ገጽገረሴ መጥምቄ መሌኮት ቅዱሥ ዬሐንስ ስለ ታምራቱ ና ወደ ቦታው ለምመጡ መሬጃ እንሰጣለን ።የኮንሶ ዞን ወረዳዎች ቤተ-ክህነትየኧሌ ዞን ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ሚዲያየ/ኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያን ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ/Department of Public Relation,EOTCየኢኦተቤ መገናኛ ብዙኀን አገልግሎት ሥርጭት ድርጅት/ EOTC Broadcasting Service Agency/

Address

Arba Minch
Arba Minch'

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ነቅዐ ጽድቅ የጋሞና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሚዲያ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share