21/03/2026
እንኳን አደረሳችሁ ለቅዱስ ሚካኤል ወርሐዊ ባእል 252494944 አቢሲኒያ ባንክ።
Abebaw kasahun & Apraim Abebe
ይህ ቤተክርስቲያን እደምታዮት እድሣት ይፈልጋል እና የበርከት ተሳታፊ እድትሆኑ በቅዱስ ሚካኤል ስም አንጠይቃለን🤲🤲🤲የሠራዊት ጌታ የልዑል እግዚአብሔር አገልጋይ ሊቀ መላዕክት ቅዱስ ሚካኤል 🙏
የስሙ ትርጓሜ “እንደ እግዚአብሔር ያለ ማን ነው” ማለት ነው። ከእግዚአብሔር ዙፋን ትዕዛዝ ሲወጣ ኪሩቤልና ሱራፌል ለሚካኤል ያስተላልፋሉ፡፡ ሚካኤል ትዕዛዙን ይፈጽሙ ዘንድ መላዕክትን ያዛቸዋል፤ ኪሩቤልና ሱራፌል መላዕክቱም ሁሉ አቤቱ የእጅህን ስራ አታጥፋ እያሉ ቀንና ማታ ይለምናሉ። ድርሳነ ሩፋኤል ላይ ተጽፎ እደምናገኘው 7 ሊቃነ መላዕክት ሲኖሩ አለቃቸው ቅዱስ ሚካኤል ነው፡፡ የመላዕክቱን ስም የመጨረሻውን ፊደል ስናይ ኤል ብሎ ይጨርሳል፡፡ ሚካ-ኤል ገብር-ኤል ኡራ-ኤል፤ ይህም “ስሜ በሱ ላይ ነውና” እንደሚል የእግዚአብሔር የምህረት ስም በክንፎቻቸው ስለተጻፈ መላዕክቱ ይጠብቁናል። አይሁድ ጌታን ሲሰቅሉት መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል በቁጣ ሰይፉን አወጣ፤ ቅዱስ ሚካኤል ግን በአይሁድ ስራ አዝኖ፣ የፈጣሪን የትዕግስቱንና የፍቅሩን ብዛት እያደነቀ በአርምሞ አያቸው ይላል ድርሳኑ።
መላዕክቱ በክንፋቸው የእግዚአብሔር ስም ተጽፎበታል፡፡ “በመንገድህ ሁሉ ይጠብቁህ ዘንድ መላእክቱን ስለአንተ ያዛቸዋል፤ እግርህም በድንጋይ እንዳይሰናከል በእጆቻቸው ያነሱሃል” ተብሎም በመዝሙር 90÷11 ተጽፋልና አህዛብን ጭምር ያለጊዜያቸው እንዳይሞቱ መላዕክት ይጠብቋቸዋል፡፡ ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት በመዝሙር 33÷7 “የእግዚአብሔር መልአክ በሚፈሩት ሰዎች ዙሪያ ይሰፍራል ያድናቸውማል” ይለናል፡፡ በትንቢተ ዳንኤል 10÷13 እና 10÷21 ነብዩ ቅዱስ ዳንኤልም ስለ ቅዱስ ሚካኤል እንዲህ ሲናገር ከዋነኞቹ አለቆች አንዱ ሚካኤል ሊረዳኝ መጣ፣ በተዘጋ ጉድጓድ ሲያጽናናው ደግሞ “ከሚካኤል በቀር የሚያጽናናኝ የለም” አለ፡፡