19/04/2026
ዳግመ ትንሣኤን ከነዳያን ጋር
በፍኖተ ብርሃን ሰንበት ት/ቤት አዘጋጅነት ከምዕመናን አልባሳትን፣ የንጽሕና መጠበቂያ ዕቃዎችን እንዲሁም ገንዘብ በማሰባሰብ በዛሬው ዕለት ነዳያን ታስበዋል። ነዳያንን ከማሰባሰብ ጀምሮ ሰውነት በማጠብ፣ ፀጉር በማስተካከል/ በመስራት ልብስ በመቀየር በዝማሬ፣ በወንጌል እንዲሁም ማዕድ በማጋራት ዳግም ትንሣኤውን በማሰብ በደማቅ መርሃ ግብር ተካሂዷል። በዕለቱም የበገና ዝማሬ የቀረበ ሲሆን ከሰንበት ት/ቤታችን ጋር በመሆን ማኀበረ ቅዱስ ገብርኤልና የማኀበረ እስጢፋኖስ አባላት በበጎ ፍቃደኝነት አብረው በማሳተፍ የበረከቱ ተካፋይ ሆነዋል።
የዓመት ሰው ይበለን!
ፍኖተ ብርሃን ሰንበት ት/ቤት
👉 https://t.me/fenotebirhanss