አባቶችህን ጠይቅ ይነግሩህማል?

አባቶችህን ጠይቅ ይነግሩህማል? Hello Friends, this page will deals with spiritual Orthodox Tewahdo Church question and answer page.

06/09/2025

ዘመኑን መቀደስ

ክፍል አንድ

(በመምህር የኔታ ገብረ መድኅን እንየው )

✍️ያለ ዘመን በባሕርዩ ጸንቶ ይኖር የነበር፤አሁንም ያለ፤ ለዘለዓለሙም የሚኖር እግዚአብሔር ብቻ ነው።

ሌሎች ፍጡራን ግን የጊዜ መነሻና መዳረሻ አላቸው።ለሕያዋን ፍጡራንም መኖሪያቸው እግዚአብሔር ነው።

✍️ፍጡራን እኛ የምንመላለስበት የአሁን ጊዜ ግን በዘለዓለማዊነት መካከል ጣልቃ የገባ ስፍረ ዘመን ነው።ከዚህ ጊዜያዊ ዘመን በኋላ የማይለካ ዘለዓለማዊነትን እንወርስ ዘንድ ተስፋ እናደርጋለን።

በዚህ አሁናዊ ስፍረ ዘመንም ዕድሜያችን እና ሥራችን ሲለካበት ይኖራል። በቀኝም ሆነ በግራ የምንቆመው በዚህ ጊዜ ባስመዘገብነው ውጤት ነው።ነጻ ፈቃዳችንን በነጻነት ጊዜ ተጠቅመን ስንሠራ ወይ ለፍትሀ እግዚአብሔር ወይም ለምሕረተ እግዚአብሔር የተገባን እንሆናለን።

✍️ያለፈው ዓመት ከተሰጠን ከዕድሜያችን አንዱ ዓመት ሲሆን የሚመጣውም ዓመትም ከቀሪ ዕድሜያችን አንዱ ዓመት ነው።ስለዚህ ዕድሜን ማበላሸት ራስን ከመብላት ይቆጠራል ጊዜን በግድየለሽነት መግደል ራስን ከማጥፋት ይቆጠራል።

እያንዳንዷ ሰከንድ፣ሰዓት፣ቀን ፣ዕለት፣ዓመት..የምትውለው ከዕድሜያችን እየተቀነሰች ስለሆነ የትኛውም ጊዜ ድኅነታችንን የምንፈጽምበት የተወደደ ጸጋ ነው።"በተወደደ ሰዓት ሰማሁህ በመዳንም ቀንረዳሁህ ይላልና እንሆ የተወደደው ሰዓት አሁን
ነው፤እንሆ የመዳን ቀን አሁን ነው።"፪.ቆሮ.፮፥፪ እንዳል።

✍️በዚህች ፈጣን ጊዜ፦ትናንትን ተቀባይ፤ዛሬን ጠባቂ፤ነገን ለተተኪው ትውልድ አቀባይ የሆኑ ክርስቲያኖች ጊዜያቸውን በአግባብ ተጠቅመው በሁለገብ ኦርቶዶክሳዊት ዕይታና በነባራዊ ሁነት ላይ በቂ ግንዛቤ ኑሯቸው ባለቸው የክህሎት አቅም ሁሉ ዕድሜያቸውን ሳያባክኑ በጊዜው ሁሉ የቤተ ክርስቲያንን ሐዋርያዊነት ማስቀጠል ግዴታ አለባቸው።

✍️ሰው ከእግዚአብሔር ጋራ፣ሰው ከሰው ጋራ፣ሰው ከሥነ ፍጥረታት ጋራ ያለው መስተጋብር የሚወሰነው በፈጣሪና በፍጡር መካከል ያለውን ግንኙነት በጊዜው ሁሉ መጠበቅ ሲቻል ነው።

✍️ከተግባር ሁሉ ትልቁ ስኬት ተፈጥሮን እና መዳረሻዋን መረዳት ነው።መረዳት የሌለው ሕይወት ግን ጽኑዕ ሸክም ነው፡፡ኦርቶዶክሳዊ ደግሞ ምሉዕነት ነው።ክርስቲያናዊ መረዳት ፍጡራዊ ድንበር የለውም።ድንበሩ ወሰኑ ህላዌ እግዚአብሔር ነው።

✍️ከአቅም ሁሉ ከተግባር ሁሉ የሚበልጠው የአስተሳስብ ብልጫ ነው።በዚህ ዘመን ያለን አማኞች ዋናው ክፍተታችን የአስተሳስብ ጉድለት ነው።የወሬ ክምችት ዕውቀት አይሆንምና በኦርቶዶክሳዊ አስተሳስብ ቅኝት ውስጥ ጊዜውን መዋጀት እንዳለብን ጊዜው ራሱ ግድ ይለናል።"ዘመኑን ዋጁ።"ኤፌ.፭፥፲፮እን.

✍️ዘመኑን ዋጁ ማለት ዘመኑን ምሰሉ ማለት አይደለም።
ዘመኑን መቀደስ ቻሉ ዘመኑን አስከትሉት እንጂ ዘመን የወለደውን ንጉሥ የወደደውን እያላችሁ አትከተሉ ማለቱ ነው።
ሃይማኖት፣ቀኖና፣ትውፊት እንደ አባቶቻችን አሠራር ግን እንደ ዘመናችን ሲሆን ዘመኑን መዋጀት ይባላል።

✍️በሥሁት እሳቤ እየተመሩ ዘመኑን ከመከተል በርቱዕ እሳቤ እየተቃኙ ዘመኑን ማስከተል እጅግ ይበልጣል።

✍️ከላይ እንዳየነው ጊዜ ማለት ራሱ በሂደታዊ ድኅነት ውስጥ ያለ ሰው ነው። (ጧት፣ቀን፣ማታ፣ሌሊት- ህፃንነት፣ወጣትነት፣ጉልምስና፣ ሽምግልና፣ ሞት ወጣኒነት፣ማዕከላዊነት፣ፍጹምነት፣) ስለዚህ ጊዜን ማባከን ጸረ ራስነት ነው።ወይም ነገረ ድኅነትን ማማሰን ነው።

✍️ጊዜ ከቅጽበት ቢጀምርም ምልዓቱ ሂደታዊነት ነው።ምሥጢረ ድኅነትም ከቅጽበት ቢጀምርም አፈጻጽሙ ሂደታዊነት ነው።"የራሳችሁን መዳን ፈጽሙ"ፊል.፪፥፲፪ እን.

15/08/2025

ክፍል አንድ

👉 ቅዳሴ ማለት ምን ማለት ነው???
👉 በቅዳሴ ጊዜ 5ቱ ምሥዋዕቶች ምን ምን ናቸው?
👉 14ቱ ፍሬ ቅዳሴያት እነማን ይሆኑ?
👉 ካህናት በቅዳሴ ወቅት 2: 3: 4: 5: 7: 12: ወይም 24: ሆነው ከቀደሱ ምሳሌነቱ ምን ምን ይሆን?
👉 እኛ ክርስቲያኖች ቅዳሴን ባስቀደስን ቁጥር 4 ነገሮች እናገኛለን ምን ይሆኑ?
👉 አምስቱ የስሜት ሕዋሳት በፀሎተ ቅዳሴ ጊዜ ያስቀድሳሉ እንዴት?

አውቀነው እንጠቀምበት ዘንድ ይነበብ .... ለሌሎች ሰማያዊ ምሥጢርን አካፍለን የተሰጠንን መክሊት እናተርፍበት ዘንድ እንትጋ!

ቅዳሴ ማለት ምንም ማለት ነው???

ቅዳሴ በሥርዓተ ቤተክርስቲያናችን ሥርዓት መሠረት በኅብረት የሚጸለይ የኅብረት ጸሎት ነው፡፡ ከፀሎቶች ሁሉ የላቀ የፀሎት ክፍል ነው፡፡ በቅዳሴ ጊዜ ፭ቱ ምሥዋዕቶች ተሞልተው ይገኙበታል እዚህንም ፭ቱን መሥዋዕቶች ማንኛውም ክርስተያን ለፈጣሪው የሚያቀርበው ነው፡፡

፩. የቁርባን መስዋዕት፡- በፀሎተ ቅዳሴ ጊዜ ውስጥ ኅብስቱ ተለውጦ ሥጋ መለኮት ወይኑ ተለውጦ ደመ መለኮት የሚሆነው በቅዳሴው ፀሎት ነው ሳናስቀድስ አንቆርብምና የቁርባን መስዋዕት የሚፈጸመው በሥርዓተ ቅዳሴ ብቻ ነው፡፡

መስዋዕቱም በቤተልሔም ይዘጋጃል በቤተክርስቲያን ውስጥ በቤተ-መቅደስ ውስጥ ደግሞ ይቀርባል ወይም ይታደላል፡፡ ጌታችን ሲወለደ በቤተልሔም
ተወልዶ ቀራንዮ ለዓለም ሁሉ መስዋዕት ሆኗልና ቀራንዮ በተባለች በቤተክርስቲያን ቅዱሱ መስዋዕት ለሕዝብ ይታደላል፡፡

፪. የከንፈር መስዋዕት፡- ካህኑ፣ ዲያቆኑና ሕዝቡ በመቀባበል በአንድነት ምስጋና ለፈጣሪያቸው የሚያቀርቡበት
የከንፈራችን ፍሬ የሚሰዋበት የፀሎት ክፍል ፀሎተ ቅዳሴ ነው፡፡

፫. የመብራት መስዋዕት፡- በቅዳሴ ጊዜ የሚበራው ጧፍ ለእግዚአብሔር የሚቀርብ የሚሰጥ የመብራት መስዋዕት ነው፡፡

ምሳሌነቱም የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ምሳሌ ነው ይህውም ጌታችን ጨላመ ለሆነ ዓለም ብርሃን ሆኖ ብርሃንን ሊያበራ ወደ ዓለም መቷልና ነው፡፡

፬. የዕጣን መስዋዕት፡- የዕጣን ፀሎት ካህኑ ብቻ የሚያጥነው ሲሆን ይህውም በማዕጠንቱ አማካኝነት ቅዱሱን እጣን በመንበሩ፣ በቅዱሳን ስዕላቱ፣ በሕዝቡ መካከል ያጥናል ይህውም የሕዝቡን ፀሎት ወደላይ በደሥላሴ መንበር ይዞ ይወጣል በሰማይም ያሉ ቅዱሳን መላእክት ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እያሉ የሥላሴን መንበር እንደሚያጥኑ ሁሉ በምድርም ያለው ካህን የሰማያዊው ምሳሌ ነውና በምድር ያውን መንበር በማጠን ለእግዚአብሔር የዕጣን መስዋዕት ያቀርባል፡፡

፭. የሰውነት መስዋዕትነት፡- በቅዳሴ ጊዜ አብዛኛውን ሰዓት ሙሉውን ማለት ይቻላል በመቆም የሚፀለይ የፀሎት ክፍል ነው፡፡ በመሐል 2 ጊዜያት ብቻ የስገዱ ትዕዛዝ ሲተላለፍ ሕዝቡ ሁሉ ፊቱን ወደ ፈጣሪው አዞሮ እራሱን አዋርዶ ይሰግዳል በእግዚአብሔር ፊት መቆምም ሆነ መስገድ ለእግዚአብሔር የሚሰጥ የሰውነት መሥዋዕት ነው።

19/04/2025

ይሁዳን አገኘሁት!
ክፍል ሦስት

ዕቅዱን ሁሉ በየቤተ ክርስቲያኑ እየዞራችሁ ብትመረምሩ ስንት ገቢ እናስገባለን፣ ስንት ወጪ እናወጣለን አይነት ነው እንጅ ድኅነተ ምዕመናንን ታሳቢ ያደረገ ዕቅድ ብዙም አታገኙም። ፈርታችሁ ካልሆነ እናንተም ይሁዳን አግኝታችሁት ታውቃላችሁ።

በአጥቢያችሁ በዓመት ለምን ያኽል ጊዜ ታቦት ይወጣል? ስንት ድርብ ታቦት አለ? ለክርስቶስ ተብሎ የመጣውን ሽቶ ሽጦ መክበር የሚፈልጉ ሰዎች ክርስቶስን የሚያገለግሉት የሽቶው ብር ተሽጦ ገቢ እስከተደረገ ድረስ ብቻ ነው። ካልሆነ ጉባኤው ክርስቶስን መስማቱን ትቶ “ይህ ገንዘብ ተሽጦ ለድሆች ሊሰጥ ይገባ ነበር” በሚል የእንጉርጉሮ ቃል እንዲሞላ ለማድረግ ፈጣኖች ናቸው።

ከላይ ስትመለከቱት ለቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ካላቸው ፍቅር የተነሣ የሚመስል ውስጡ ግን የራሳቸውን ጥቅም ለማስከበር የተፈጠረ አጀንዳ መቅረጽ የሚችሉ ይሁዳዎች በእኛ ዘንድ ብዙ አሉ።

የተነሡት አለቆች፣ ጳጳሳት እና ሌሎችም አገልጋዮች ሁሉም ሥራ አበላሽተው ቤተ ክርስቲያንን በድለው ይመስላችኋል? ምናልባትም የሴቲቱን ዕንባ እንጅ የያዘችውን የአልባስጥሮስ ሽቶ ስለማይመለከቱ በከረጢት ያዦች ዘንድ ነገራቸው ስላልተወደደ ይሆናል ዮሐ. 12፥6።

ይሁዳ ይኼውላችሁ ከሚፈሰው እንባችን ይልቅ የሚፈሰው ሽቶ የሚያስቆጨው ከዳኑ ነፍሳት ይልቅ ከነሱ የሚያገኘውን ጥቅም የሚያስቀድም ሰው ካገኛችሁ ይሁዳ እሱ ነው።

ይሁዳ በሌላም ቦታ አለላችሁ። ይሁዳ ክርስቶስን ሸጠ፤ ጸጋውን ሽጦ መኖር የሚፈልግ ስንት ይሁዳ አለ መሰላችሁ? መጽሐፍ እንደነገረን ክርስቶስ ጸጋ ሆኖ ተሰጥቶናል ዮሐ. 1፥18 ይህንን ጸጋ ምዕመናንን ከመጥቀም በቀር ለሌላ ጥቅም ማዋል ይሁዳነት ነው።

ለሚያስተምር መምህር የሚገባውን ዋጋ መክፈል ምዕመናን የታዘዙት ትዕዛዝ ነው። ሐዋርያው እንደነገረን በገዛ ገንዘቡ በወታደርነት የሚያገለግል የለምና።

ወይን ተክሎ ፍሬውን የማይበላም አይገኝም። መምህራንም መንፈሳዊውን ዘርተው ሥጋዊውን እንዲበሉ ተፈቅዶላቸዋል። ነገር ግን ከአሥራ አንዱ ደቀ መዛሙርት የተለየ መቀበል ከይሁዳ በቀር ማንም የማያደርገው ነውረኛ ገንዘብ dirty money ነው።

ቤተ ክርስቲያን በየቀኑ “ለይሁዳ ወልዱ ወውሉደ ውሉዱ ይደምሰስ” እያለች ብትረግመውም ይሁዳ ግን ዛሬም አለ። የሄው በእኔ ውስጥ፣ በእናንተም አጠገብ ይሁዳን አገኘሁት።

እስኪ የእናንተን ሀሳብ ልስማ? ይሁዳ አለ ወይስ ሞቷል?

©️ስምዐኮነ መልአከ

19/04/2025

ይሁዳን አገኘሁት!
ክፍል ሁለት

ይሁዳ ዓለማዊ ሳለ ያልታወቀች ኃጢአቱን ሊናዘዝ ወደ ሊቀ ካህናቱ ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ ቀረበ፤ መንፈሳዊ ከሆነ በኋላ ግን የተገለጠች ኃጢአቱን በማስመሰል ሊሰውር ፈለገ።
በልቡ ያሰባትን ኃጢአት ገልጾ መናገሩ ተመልሶ እንዲተዋትና ወደ መዳን እንዲመጣ ነበር እሱ ግን አላደረገውም እንዲያውም ከወንድሞቹ ጋር አብሮ “እኔ እሆንን?” ማለት ጀመረ ማቴ. 26፥25 ድሮ ዓለማዊ ሳሉ ሰዎችን ሲዋሹ ይደነግጡ የነበሩት ሰዎች ዛሬ ፈጣሪአቸውን መዋሸትን እንደ ቀላል ነገር ቆጥረዋታል።

ከመቅደስ ወጥተን በገሀነም እንዳንጣል እግዚአብሔር የሰጠንን ዕድል ካለመጠቀም በላይ ይሁዳነት አለ? በዓለም ከሠራነው በላይ ኃጢአትን አብዝተን በመንፈሳዊነት ሰበብ ከመሥራት የሚበልጥ ይሁዳነትስ የት ይገኛል? መጠጥ ቤት ገብቶ ማመንዘር ምናልባትም ወደ ዝሙት የሚገፋፋ መብልና መጠጥ ስላለ ሊሆን ይችላል፤ ቤተ መቅደስ ገብቶ ማመንዘር ግን በምን ሊተረጎም ይችላል? መጠጥ ቤት ያሉ ሰዎች ፈልገውት የመጡ ሊሆኑ ይችላሉ፤ ቤተ መቅደስ ያሉት ግን ሴቶችም ሆነ ወንዶች ይህንን አስበው የመጡ አይደሉም።
ታዲያ መንፈሳዊ አገልግሎትን ጥግ አድርጎ ነውር መሥራት ይሁዳነት አይደለም?

ይሁዳ በሌላም ቦታ ዘወር ዘወር ብትሉ ታገኙታላችሁ። በክርስቶስ ጉባኤ ብዙ ዕዳ ያለባት ሴት ቀርባ እግሩን ይዛ እያለቀሰች ይቅርታ ጠየቀች፤ ክርስቶስም ብዙ ኃጢአቷን ተወላት። ይሁዳ እንደ አገልጋይነቱ ብዙ ኃጢአቷ በተተወላት ሴት ደስ ሊሰኝ ሲገባው ይዛው የመጣችው ሽቶ ተሽጦ ለድሆች ባለመሰጠቱ ማንጎራጎር ጀመረ።

ወደ ቤተ መቅደስ መጥተው ንስሓ የሚገቡ ነፍሳትን ሳይሆን የሚያመጡትን ሳንቲም የሚጠባበቁ ሰዎችን ባየሁ ጊዜ ይሁዳን በዘመናችን ባለችው ቤተ መቅደስ መኖሩን አረጋግጣለሁ። “ነፍሴ ወደ ሕያው አምላክ ተጠማች፤ መቼ እደርሳለሁ የአምላኬንስ ፊት መቼ አያለሁ?” መዝ. 42፥2 እያሉ በናፍቆት የመጡ ምዕመናንን ማሰናከል እግዚአብሔርን እንዴት እንደሚያሳዝነው ብናስብ እኮ እንዴት ያስፈራል መሰላችሁ!

ለገንዘብ ማስቀመጫዎቻችን የምንጠነቀቀውን ያክል ለምዕመናን ነፍሳት አለመጨነቃችንን ሳስብ ከዚህ በላይ ይሁዳነት አለ? ብየ ከራሴ ጋር እሟገታለሁ።

አንድ የገንዘብ ሳጥን {ሙዳየ ምጽዋት} ቢጠፋ በዕለቱ ይታወቃል አንድ ምዕመን ቢጠፋ ግን በዓመቱም ላናውቀው እንችላለን። ገንዘብ ተቀባዩን በብዙ ሰነድ አስፈርመን ብዙ ማንነቱን የሚገልጡ ሰነዶች ተቀብለን እንቀጥረዋለን፤ በምዕመናን ላይ የምንሾመውን ካህንስ ካላችሁኝ የትምህርት ችሎታው አያስጨንቀን፣ የምዕመናን አባት አብነት መሆን ይችላል ወይ ብለን አንጠይቅ፣ በእጁ ስላሉ ምዕመናን መረጃ አይጠየቅ እንዲሁ ይዟቸው ወይም ይዘውት ይኖራል።

አንዳንድ ምዕመናን እኮ ለአባቶቻቸው አባት ሆነው እየኖሩ ነው እኛ ይህ ሁሉ አያስጨንቀንም። ከቤታቸው እኩል ለንስሐ አባቶቻቸው ዕዳ የወደቀባቸው ምዕመናን ብዙ ሆነው እንመለከታለን።

በክርስቶስ ያሳመንናቸው የፈረሰ ቤታችንን እንዲሠሩልን ነው? የተጣመመ ኑሯችንን እንዲያቃኑልን ነው? ለዚያውም አንዳች ቃለ እግዚአብሔር ያልነገርናቸው በክርስቶስና በገብርኤል መካከል ያለውን ልዩነት እንኳን ያላስተማርናቸው የዋሆችን ክርስቶስን በማወቅ ነው እንጅ የኛን ቤት በመሥራት ገነት ይገቡ ይመስል ገንዘባቸውን እንጅ ልባቸውን ያልሰበሰብናቸው ብዙ ናቸው።

አንዳንድ ምዕመናንም የሰበካ ጉባኤ አባል ሆነው ሲመረጡ ልማት የሚመስላቸው ሕንጻ መሥራት ግቢ ማጽዳት ነው እንጅ ምን ያክል ምዕመን ሠርክ ጉባኤ ይከታተላል፣ ስንት ሰው ልጆቹን ኦርቶዶክሳዊ ትምህርት ያስተምራል፣ ከተመዘገበው ምዕመን ስንቱ ይቆርባል ብለው አያስቡም።

ይቀጥላል

19/04/2025

ይሁዳን አገኘሁት!
ክፍል አንድ

ይሁዳን ስናነሣ በተቀደሰ መንገድ አገልግሎታቸውን ፈጽመው ያረፉ ቅዱሳን ሰዎች መኖራቸውንም መርሳት የለብንም።

አንዳንድ ሰዎች ሌላ ይሁዳ ያለ ስለማይመስላቸው መልዕክት የጻፈልንን ሐዋርያ ጌታን ከሸጠው ይሁዳ ጋር ሲያምታቱ ይሰማሉ።
“የተረገመ ነበር አንድ ምዕራፍ ያላት መልዕክት ጽፎ ቀረ” ብለው ፈገግ የሚያደርጉን አንዳንድ ሰባኪዎችም ሳናይ ሳንሰማ አልቀረንም።

ለማንኛውም እኔ ለዛሬ ልጽፍላችሁ ወደ ምፈልገው መልዕክት ልመለስና ይሁዳን የት እንዳገኘሁት ልንገራችሁ።

ተመሳስሎብህ እንዳይሆን ካላችሁኝ የለም ራሱ ይሁዳ ነው ብየ በእርግጠኝነት እነግራችኋለሁ። ከሁለት ሺህ ዓመት በኋላ የት አገኘኸው? የሚል ጥያቄ ከልባችሁ ሲወጣ ይታየኛል።

እኔንም ያስገረመኝ እሱ ነበር ግን እናንተም ብትገረሙ ነው የሚሻላችሁ ይሁዳ ዛሬም አለ።
ኃጢአት ከብዶት ወደ ክርስቶስ የመጣው ይሁዳ “እናንት ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ፥ ወደ እኔ ኑ እኔም አሳርፋችኋለሁ” ማቴ. 11፥28 የሚለውን ጥሪ ሰምቶ የመጣ ቃለ እግዚአብሔር ገብቶት በራሱ ተነሳሽነት የተመለሰ ሰው ነው።

አምላከ መምህራን ኢየሱስ ክርስቶስ እንደ ጴጥሮስና እንደ ዮሐንስ ባለበት ቦታ ሂዶ ጠርቶ አላመጣውም፤ ራሱ ከኃጢአት ለመሸሽ የመጣ ሰው ነው።

በጽድቁ ስፍራ ኃጢአት ያገኘኛል ብሎ መች አሰበና እንዲሁ መጥቶ በጌታ ፊት ሰገደ ኃጢአቱ ተተወችለት።

ከመጣ በኋላ የተለወጠችው መንገዱ ይሁዳ ቀድሞ ያሰባትና የጠበቃት አልነበረችም። ይሁዳ ከኃጢአት ከመፈታት በቀር ሌላ ምኞት አልነበረውም። ግን እንዳሰበው መቀጠል አልቻለም። ከኃጢአት ሸሽቶ የመጣው ይሁዳን ኃጢአት በዚህም ስፍራ ጠበቀችው። ለካ ወደ መንፈሳዊ ስፍራ ገብቶ መቆም ብቻ ሳይሆን ልብን መንፈሳዊ ማድረግ ግዴታ ነው።

ካህኑ ቅዳሴ ከመጀመሩ በፊት “ኦ እኁየ ሀሉ በዝንቱ መካን እንዘ ትሔሊ ኃጣውኢከ፤ ወንድሜ ሆይ በዚህ ቦታ ኃጢአትህን እያሰብህ ኑር” ብሎ የሚያውጀው በመንፈሳዊ ቦታ መቆማችን ብቻ ሳይሆን መንፈሳዊ ነገር በማሰብ ጸንተን አለመኖራችን በመንፈሳዊ ቦታ ሥጋዊ ሥራ ሊያሠራን ስለሚችል ነው።

ዛሬም ዓለማዊነት ሰልችቷቸው፣ መንፈስ ቅዱስ ከዕለታት በአንዱ ቀን በልባቸው አድሮ ዕለተ ሞታቸውን አሳስቧቸው ከታሰሩበት ልማድ ሊፈቱ የሚመጡ ብዙዎች ናቸው።

መብላት መጠጣት፣ ማግባት መፍታት፣ መስረቅ መቀማት፣ ጉቦ መብላት ፍርድ ማድላት፣ መተኛት መነሣት ሆኖባቸው ሕይወት ግራ የምታጋባ ሆናባቸው ደግመው ላይመለሱ ምለው ከዓለም የተመለሱ ሰዎች ዛሬ ንስሐ ገብተው ቢያገኛቸው “ይህ ልጄ ሞቶ ነበርና ደግሞም ሕያው ሆኗል፤ ጠፍቶም ነበር ተገኝቷል” ሉቃ. 15፥24 ብሎ ክርስቶስ የተቀበላቸው ናቸው።
ጠልተዋት የመጧት ኃጢአት መልሳ በሌላ መንገድ ወረሰቻቸው። ያንጊዜ ከሰሩት ይልቅ የከፋ በደልን ወደ መሥራት ተሸጋግረዋል።

ይሁዳ ከጸሐፍት እና ከፈሪሳውያን አንዱ ስንኳ ያልደፈረውን ኃጢአት እንደሠራ እነዚህም በዓለም ሳሉ ከሠሩት ይልቅ ወደ መቅደሱ ከመጡ በኋላ የሠሩት ኃጢአት ይበልጣል።

ከጸሐፍት ከፈሪሳውያን መካከል ክርስቶስን ለመግደል እንጅ ለመሸጥ ያሰበ አልነበረም ይሁዳ ግን ሊሸጠው እየመከረ ነው ማቴ. 26፥15።

ይቀጥላል

19/04/2025



በተለምዶ ቅዳም ሹር ትባላለች። የቀናው አነጋገር ቀዳም ስዑር ነው። ስዑር ማለት የተሻረች ማለት ሲኾን ሹር የሚለው ያንን ያመለክታል። መሻሯም ጌታ በከርሰ መቃብር ስላደረባትና ጦም ስለሚዋልባት ነው። የበዓል እንጅ የሥራ ቀን አይደለችም።

ገብረ ሰላም በመባልም ትታወቃለች። ቅዱስ ጳውሎስ ገብረ ሰላመ በደመ መስቀሉ - በመስቀሉ ደም ሰላምን አደረገ ማለቱን መሠረት ያደርጋል። ቆላ ፩:፳።

ጌታ ተመረመረ ዲያብሎስ ታሰረ እያሉ ካህናት ለምለም ቀጤማ ያድላሉ። ልምላሜ የብሥራት ነውና። የሲኦልን መበርበር የዲያብሎስን መታሰር ስለሚያበሥሩባት ነው።

እንኳን አደረሳችሁ!!!
መልካም በዓል።

19/04/2025

++በእጅህ መካከል ያለው ቁስል ምንድርነው? ++

በዕለተ ፍጥረት እግዚአብሔር በሰማያት ያሉትን ፍጥረታት በዝምታ ብቻ ከፈጠረ ቡኋላ አንዳች ባልነበረባት ምድርየፈጠራቸውን ፍጥረታት የሚዘረዝረው ኦሪት ዘፍጥረት"እግዚአብሔር አለ ይሁን"እግዚአብሔር አለ ይከፈል"እግዚአብሔር አለ ታስገኝ በማለት እግዚአብሔር በቃሉ"ይሁን ይሁን እያለየፈጠራቸውንየፍጥረታትወገኖችይዘረዝራል።እግዚአብሔር በዝምታውና በቃሉፍጥረታትን ሁሉፈጥሮ ከጨረሰ ቡኋላበመጨረሻሁሉን ያሰናዳትንናበአምሳሉ ሊፈጥር ወደደ ይህንን ክቡርፍጥረት ግንእንደ ሰማያዋን ፍጥረቱ በዝምታ ምድርን እንደሞሉት ፍጥረታቱ ደግሞ በቃሉ ሊፈጠረው አልፈለገም ስለዚህበአምላካዊ እጆቹ ከምድር አፈር ንጉሥ አንስቶበእጆቹ አበጀውሔዋንንም ከአዳምጎን አሥቶ በእጆቹሠራት።ቅዳሲያችን የሰውን ልጅ ስለማክበርጭቃ ይዞ ታየ እንደሚለው ልዑል
እግዚአብሔር የሰውን ልጅ ከፍጥረታቱ ሁሉ አክብሮ በእጆቹ ፈጠረው። እግዚአብሔር ከፍጥረታት ሁሉ እንደሰው ያከበረው የለምየሁንና ከፍጥረታትም ሁሉእንደ ሰው እግዚአብሔር ን ያቃለለ የለም ያከበረውን አምላክ በኃጢአት አቃለለ በዕለተ አርብ የሆነው ደግሞ የባሰ ነው ከፍጥረታት ሁሉ አክብሮ አፈር ከምድር አንስቶ የፈጠረበትን የእግዚአብሔር እጅ የሰው ልጅ በምስማር ቸነከረው።
"አዳምን የፈጠሩ እጆች በመስቀል ችንካሮች ተቸነከሩ።"የጠፋውን አዳም ፍለጋ አዳም ሆይ ወዴት ነህ እያሉበገነት የተመላለሱት አምላካዊ እግሮች "በመስቀል ችንካር ተቸነከሩ "ሰውን ወዳጁ አምላክበወዳጆቹበሰው ልጆች መካከል ሰው ሆኖ ቢገለጥም እጆቹ በችንካርቆሰሉነብዩ ዘካርያስ "ሰውም በእጅህ መካከል ያለ ቁስል ምንድር ነው ይለዋል እርሱም በወዳጆቼ ቤት የቆሰልሁት ቁስል ነውይላል። "የተባለው ትንቢትተፈጸመ (ዘካ፲፫፥፮)
++++++++++++++++++
የሰው ልጅ ዕፀበለስንሊቀጥፍ እጁን በመስደዱ ምክንያትእግዚአብሔር ሰው ሆኖ እጆቹን ለሕማምዘረጋ። ይሕም ነብዩ ዳዊት በመዝሙሩአስቀድሞ "እጆቼንና እግሮቼን ቸነከሩኝ"ብሎ በትንቢት የተናገረው ቃል ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ መሆኑን የሚያሳይ ነው።(መዝ፳፩፥፲፮}ሰማዕቱ ዮስጢኖስ በኢየሱስ ክርሰቶስ ከማያምን አንድ አይሁዳዊ ጋር ባደረገው ምልልስ ላይ....... *
* እጆቼንና እግሮቼን ቸነከሩኝ የሚለውን የዳዊት ትንቢት ስለክርስቶስ የተነገረ አይደለም ትላላችሁ ከክርስቶስ በቀርእጆቹና እግሮቹን የተቸነከረ ማነው? (ንጉስ ዳዊት ነውን?)
ይኽንን እንዴት አታስተውሉም? ብሎታል። *
ጌታችን ከተገረፈው ግርፋትና ከተንገላታበት የቀራንዮ መንገድ በኋላ ከመስቀሉ ዕንጨት ጋር በረዣዥም ምስማሮች መቸንከሩ እጅግ የማይነገር ስቃይ የሚያስከትል ነበር ሮማውያኑ ይህንን ስቃይ ጠንቅቀው ስለሚያቁም የሚሰቀለውን ሰው ከመቸንከራቸው በፊት የወይን ጠጅ እንዲጠጣ ያደርጉት ነበር ሮማውያኑ ይህንን ስቃይ ጠንቅቀው ስለሚያውቁም የሚሠቀለውን ሰው ከመቸንከራቸው በፊት የወይን ጠጅ እንዲጠጣ ያደርጉት ነበር ይህንን የሚያደርጉበት የመጀመሪያ ምክንያት ለቀኖት (ለችንካር) እንዲያዝልላቸው "ጠጁ ከከርቤና ሐሞት ጋር ተቀላቅሎ ሲጠጣ የማፍዘዝ የማደንገዝ ኃይል ስላለው የሚቸነከረው ሰው እየተወራጨና እየጮህኸ እዳያስቸግራ ቸውና እጆቹና እግሮቹ በድካም ዝለው እንዲቸነከሩ ለማድረግ ነው።

ዲያቆን ሄኖክ ሃይሌ

19/08/2023

ደብር ርጉአ ወደብር ጥሉል ለምንት ይትነስኡ አድባር ርጉአን ደብር ዘሰምሮ ይሃድር ውስቴቱ እግዚአብሔር አማን ተሰብሃ በደብረታቦር

19/08/2020

[ደብረ ታቦር]
♥❖ ይኽ በዓል ከጌታችን 9ኙ ዐበይት በዓላት አንደኛው ሲኾን በዓሉ በየዓመቱ ነሐሴ 13 ላይ በታላቅ ድምቀት ይከበራል፡፡ ታሪኩ በ3ቱ ወንጌላት ላይ የተጻፈ ሲኾን ጌታችን አምላችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሌሎቹን ሐዋርያትን ከእግረ ደብር (ከተራራው ሥር) ትቶ የምስጢር ደቀ መዛሙርት የሚባሉት ሦስቱን (ጴጥሮን፣ ያዕቆብን፣ ዮሐንስን) ይዟቸው ወደ ታቦር ተራራ በመውጣት የሞተውን ሙሴን ከ1644 ዓመታት በኋላ አስነሥቶ፤ የተሰወረውን ኤልያስንም ከብሔረ ሕያዋን አምጥቶ የሕያዋን አምላክና የሙታን አሥነሺያቸው ርሱ መኾኑን የገለጸበት ታላቅ ምስጢር የተከናወነበት ነው፡፡ (ማቴ 17፡1-9)።

♥❖ ጌታ 8ቱን ሐዋርያት ይዟቸው ያልወጣበት በይሁዳ ምክንያት ነው ምክያቱም ከምሥጢረ መንግሥቱ ቢለየኝ ከሞቱ ገባኹበት ባለ ነበርና ነው፤ ነገር ግን በተራራው ላይ ለ3ቱ የተገለጸው ምስጢር ከተራራው ሥር ላሉት ከይሁዳ በስተቀር ተገልጾላቸዋል፤ ለእኛም እንደ ሐዋርያት ምስጢሩን ጥበቡን ይግለጽልን፡፡

♥❖ ብዙ ተራሮች ሳሉ የታቦር ተራራን የመረጠበት
1)አስቀድሞ የጌትነት ክብሩ በዚያ ተራራ ላይ እንደሚገልጽ ነቢዩ ዳዊት በመዝ 88፡12 ላይ “ታቦር ወአርሞንኤም በስመ ዚኣከ ይትፌሥሑ” (ታቦርና አርሞንኤም በስምህ ይደሰታሉ) በማለት ጌታ በዚያ ተራራ ላይ ብርሃኑን ሲገልጽ የብርሃኑ ነጸብራቅ እስከ አርሞንኤም ተራራ ድረስ እንደሚታይ የተናገረውን ትንቢት ለመፈጸም ነው፡፡

♥❖ ሌላው ታቦር በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ 12 ጊዜያት ሲጠቀስ በተለይ በመሳ 4 እና 5 ላይ እንደተጻፈው አስቀድሞ በብሉይ ኪዳን የእስራኤል ጠላት የነበረው ሲሳራን መስፍኑ ባርቅ በተራራው ላይ ድል ነሥቶበት ነቢይቱ ዲቦራም በተራራው ላይ በደስታ አመስግናበታለች ዘምራበታለች፤ በተመሳሳይ መልኩ የእስራኤል ዘነፍስ የክርስቲያኖችን ጠላት የኾነውን ዲያብሎስን የኹላችን ፈጣሪ ንጉሠ ነገሥት ኢየሱስ ክርስቶስ አምላክነቱን ገልጦ ድል ስለነሣው ነቢያት ሐዋርያት ምእመናን የሚያመሰግኑት ስለኾነ ለምሳሌነቱ ተስማሚነት ያለውን የታቦርን ተራራን መርጦታል፡፡

♥❖ ለምን ሙሴንና ኤልያስን ከነቢያት መኻከል መረጠ? ቢሉ
ሀ) በማቴ 16፡13 ላይ ሐዋርያትን ስለማንነቱ እንደጠያቃቸው እንደመለሱለት ኹሉ በእውነት ጌታችን የሙሴና የኤልያስ ፈጣሪ መኾኑን ሲገልጽላቸው ነው።

ለ) በዘፀ 33፡17-23 ላይ ሊቀ ነቢያት ሙሴ ከእግዚአብሔር ጋር ካለው ጥልቅ ግንኙነት የተነሣ “እባክኽ ክብርኽን አሳየኝ” ብሎ ልመናን አቀረበ፤ እግዚአብሔርም "ወአነብረከ ውስተ ስቊረተ ኰኲሕ ወእከድን እዴየ በላዕሌከ እስከ አኃልፍ" (በሰንጣቃው ዐለት አኖርሃለኍ፤ እስካልፍ ድረስ እጄን በላይኽ እጋርዳለኍ፤ ካለፍኍ በኋላ እጄን አንሥቼልኽ ጀርባዬን ታያለኽ፤ ፊቴ ግን አይታይም) ብሎታል (ዘፀ ፴፫፥፲፯-፳፫)፡፡

♥❖ ይኸውም ጀርባ በስተኋላ እንደሚገኝ ኹሉ በኋላ ዘመን አካላዊ ቃል ከቅድስት ድንግል ማርያም ተወልዶ በታቦር ተራራ ላይ እንደሚገለጽለት ሲያመለክተው ነው።

♥❖ ሊቁ ቅዱስ ያዕቆብም ስለ ታቦር በሚተነትነው መጽሐፉ ሙሴ በቃዴስ ባለው በመሪባ ውሃ ከእስራኤል ጋር በበደለው በደል ምክንያት ምድረ ርስት ኢየሩሳሌም እንዳይገባ አይቷት ብቻ በናባው ተራራ ላይ እንዲያርፍ ኾኗል (ዘፀ ፴፪፥፶፪፤ ዘፀ ፴፬፥፩-፰)፡፡

♥❖ ይኽ ለሙሴ አሳዛኝ ቢኾንም በኋላ ዘመን አካላዊ ቃል ክርስቶስ ከቅድስት ድንግል ማርያም ተወልዶ ሙሴ በፊት በሩቁ ያያት ግን ያልገባባት በምድረ ርስት በኢየሩሳሌም ያለች ታቦር ተራራ ላይ አምጥቶት በዘመነ ብሉይ በአካለ ሥጋ ያልገባባትን ርስት እንዲገባባት አድርጎታል፤ ይኸውም አዳምና ልጆቹ በአካለ ሥጋ ያጡትን ርስታቸው ገነትን በአካለ ነፍሳቸው ዳግመኛ ሊያገባቸው እንደመጣ የሚያመለክት መኾኑን በስፋት አስተምሯል፡፡

♥❖ ጌታችን በብሉይ ኪዳን ከነበሩት ከነቢያት ሙሴንና ኤልያስን በሐዲስ ኪዳን ከነበሩት ከሐዋርያት ሦስቱን በታቦር ተራራ ላይ ማውጣቱ፦

1) የታቦር ተራራ የቤተ ክርስቲያን ምሳሌ በመኾኗ ሲኾን በቤተ ክርስቲያናችን ብሉይ ኪዳንና ሐዲስ ኪዳን እንደሚነገሩ ለማመልከት

2) በተራራ በተመሰለች በጉባኤ ቤት ብሉይና ሐዲስ እንደሚነገሩ ለመግለጽ፡፡

3) ሌላው የታቦር ተራራ የመንግሥተ ሰማያት ምሳሌ ስትኾን ይኸውም ጌታ ነቢያትንና ሐዋርያትን በተራራዋ ላይ መሰብሰቡ መንግሥተ ሰማያትን ነቢያትም ሐዋርያትም እንደሚወርሷን ለማመልከት

4) ሙሴ ያገባ ሲኾን ኤልያስ ድንግል ነውና መንግሥተ ሰማያትን ደናግልም ያገቡም እንደሚወርሷት ለማጠየቅ ነው፡፡

5) እንደ ያዕቆብ ዘሥሩግ ትርጓሜ ሙሴ ኦሪት ዘፍጥረትን ሲጽፍ “በመጀመሪያ እግዚአብሔር ሰማይንና ምድርን ፈጠረ” (ዘፍ 1፡1) እንዳለ፤ ዮሐንስም “በመጀመሪያ ቃል ነበር” (ዮሐ 1፡1) ብሎ እንደ ሙሴ አምላክነቱን የሚመሰክር ነውና ሙሴ አስቀድሞ የጻፈልኝ፤ አኹንም ዮሐንስ አምላክነቴን የሚጽፍልኝ እኔ ነኝ ሲል ነው፡፡

6) ሙሴና ኤልያስ ይመሳሰላሉ፤ ይኸውም በሲና ተራራ 40 ቀንና ሌሊት እንደጾመ ኤልያስም በደብረ ኮሬብ 40 ቀንና ሌሊት የጾመ ነውና፨

7) ሙሴ ንጉሡ ፈርዖንን የገሠፀ እንደነበር ኤልያስም ንጉሡ አክዐብን የገሠፀ ነውና፨

8) ሙሴ ከንጉሡ ፈርዖን ፊት ሸሽቶ እንደሄደ ኤልያስም ከንግሥቲቱ ኤልዛቤል ፊት ሸሽቶ ሄዶ ነበር።

9) ዳግመኛም ሰማይኑን ዝናብ እንዳያዘንም በተሰጠው ሥልጣን ባሰረውና ከ3 ዓመት ከ6ወር ቆይታ በኋላ እንዲዘንብ በፈታው ኤልያስን እንዳመጣ ኹሉ የማሰር የመፍታት ሥልጣን ሥልጣነ ተሰጥቶት “እኔም እልሃለሁ፥ አንተ ጴጥሮስ ነህ፥ በዚችም ዓለት ላይ ቤተ ክርስቲያኔን እሠራለሁ፥ የገሃነም ደጆችም አይችሉአትም የመንግሥተ ሰማያትንም መክፈቻዎች እሰጥሃለሁ፤ በምድር የምታስረው ሁሉ በሰማያት የታሰረ ይሆናል፥ በምድርም የምትፈታው ሁሉ በሰማያት የተፈታ ይሆናል” (ማቴ 16፡18-19) ላለው ለጴጥሮስን ታላቅ ሰማያዊ ሥልጣን መስጠቱን ለማመልከት አምጥቷቸዋል፡፡

♥❖ በቤተ ክርስቲያንና በሀገራችን ያለው መንፈሳዊ አከባበር ደማቅ ነው፤ ይኽ በዓል በቤተ ክርስቲያን በማሕሌት በቅዳሴ በትምህርት የሚከበር በዓል ሲኾን በሀገርኛ የቡሄ በዓል ይባላል፤ ቡሔ ማለት ሊቁ ደስታ ተክለ ወልድ በመዝገበ ቃላት ላይ ሲገልጹት ቧ ብሎ በደብረ ታቦር የተገለጠው የጌታችንን የፊቱን ብርሃን ጸዳል የልብሱን እንደ በረዶ ነጭ መኾን ያስረዳል ስለዚኽ የብርሃን፣ ብርሃናዊ ማለት ነው፡፡

♥❖ በዚህ በዓል በታቦር የታየው የብርሃኑ ምሳሌ የሚሆን ችቦ ይበራል፤ ሌላው በዚኽ በዓል ሰሞን በገጠር ከተራራ ላይ እረኞች ሕጻናት ዥራፍ እየገመዱ ማስጮኻቸው ጌታ በተራራ ላይ ብርሃኑን በገለጸ ጊዜ አብ በደመና ኾኖ “እርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው፤ እርሱን ስሙት” ባለ ጊዜ ሐዋርያት በድምፁ ደንግጸው መውደቃቸውን ለማመለክት ነው፡፡

♥❖ ሌላው ሙሉሙሉ ዳቦ መጋገሩ በትውፊት እንደምንረዳው ጌታ ብርሃኑን ሲገልጽ ብርሃኑ እስከ አርሞንኤም ተራራ ድረስ ያበራ ስለነበር እረኞች ሌሊቱ ኹሉ ቀን መስሏቸው እዛው ስለዋሉ ቤተሰቦቻቸው “ኅብስት” ይዘውላቸው ሄደዋልና የዚያ ምሳሌ እንደኾነ ይነገራል፡፡

[በደብረ ታቦር ላይ ብርሃኑን የገለጠው አምላካችን ክርስቶስ ምስጋና ይግባው]፡፡
[መልካም በዓል]
✍ መጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ

የእመቤታችን 120 ስሞች !==================ብቸኛዋ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያንየእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም 120 ስሞችን እንዲህ በማለት ትጠራታለች።1. ...
27/06/2020

የእመቤታችን 120 ስሞች !
==================
ብቸኛዋ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን
የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም 120 ስሞችን እንዲህ በማለት ትጠራታለች።
1. ሰአሊተ ምሕረት
2. ድንግል
3. እመ ብዙሃን
4. አቁራሪተ መዓት
5. የገብርኤል ብስራት
6. ንፅህተ ንጹሐን
7. ሃገረ እግዚአብሔር
8. ቅድስተ ቅዱሳን
9. ማህደረ ሰላም
10. መዓርገ ሕይወት
11. ማኅደረ ስብሐት
12. ማኅደረ ትፍስሕት
13. ቤተ ሃይማኖት
14. ብጽዕት
15. ሕሪት
16. ክብርት
17. ልእልት
18. ውድስት
19. የሰማዕታት እናት
20. የመላዕክት እህት
21. የነቢያት ትንቢት
22. የሐዋርያት ሞገስ
23. እመ ብርሃን
24. ርሕርሕተ ልብ
25. እመ አምላክ
26. የሲና እፀ ጳጦስ
27. የአዳም ተስፋ
28. የአብል ይውሕና
29. የሴት ቸርነት
30. የሔኖክ ደግነት
31. ሙጻአ ፀሐይ
32. ታቦት ዘዶር
33. እግዝትነ ማርያም
34. የቅዱስ ኤፍሬም ባራኪ
35. ምልዕተ ውዳሴ
36. ቡርክት
37. የደስታ መገኛ
38. ምእራግ
39. አዳም ቆማ
40. ጽርሕ ንጽሕት
41. ማሕደረ መለኮት
42. እሕቱ ለሙሴ
43. ገራሕቱ ለአብርሃም
44. ወለቱ ለዳዊት
45. እሙ ለአማኑኤል
46. ነያ ሰናይት
47. እምነ ጽዮን
48. መዝገበ ብርሃን
49. ጽጌ ሃይማኖት
50. ደብተራ ፍጽምት
51. ማርያም ቅድስት
52. አክሊለ ንጹሐን
53. ብርሃነ ቅዱሳን
54. ወለተ ሐና ወኢያቄም
55. መድኃኒተ ይእቲ
56. ሐመልማለ ገነት
57. ሙዳዬ መና
58. ርግበ ጸአዳ
59. ሐመልማላዊት
60. መንፈሳዊት ሃገር
61. የኖህ መርከብ
62. የሴም ምርቃቱ
63. የሴም እድል ፈንታዉ
64. የአብርሃም ዘመድ
65. ሶልያና
66. እሙ ለፀሐይ ጽድቅ
67. ምስራቀ ምስራቃት
68. በትረ አሮን
69. የገነት ኮል
70. የይስሐቅ ሽቱ
71. የያዕቆብ መሰላል
72. የዮሴፍ አረጋጊ
73. ቤዛዊተ ዓለም
74. የእሴይ ሥር
75. ወለተ ዳዊት
76. የሙሴ ጽላት
77. የአሮን ካህን ጸናጽል
78. የኢያሱ የምስክር ሐውልት
79. የጌዴዎን ጸምር
80. የሳሙኤል ሽቱ
81. የአሚናዳብ ሰረገላ
82. የዳዊት መሰንቆ
83. የሰሎሞን ቀለበት
84. የኤልያስ መሶበወርቅ
85. የኤልሳዕ ልሕኩት
86. የኢሳይያስ ትንቢት
87. የሕዝቅኤል አዳራሽ
88. ዕፀ ሕይወት
89. የሚኪያስ ኤፍራታ
90. የናሆም ፈዋሽ
91. የዘካርያስ ደስታ
92. ወለተ ጽዮን
93. ንጽሕት ጸምር
94. ደብተራ ዘትዕይንት
95. ሀገረ ክርስቶስ
96. ኪዳነ ምሕረት
97. በአታ
98. መሰረተ ሕይወት
99. ናዛዚተ ሕዙናን
100. እሕትነ ነያ
101. አንቀጸ አድሕኖ
102. መዓዛ እረፍት
103. ርግብየ ሠናይት
104. ሐረገወይን
105. አንቀጸ ብርሃን
106. ተቅዋም ዘወርቅ
107. መቅደስ
108. ሐመልማለ ወርቅ
109. ብርሃነ ሕይወት
110. ሆሕተ ምስራቅ
111. መዝገቡ ለቃል
112. ፍኖተ ሕይወት
113. ምስጢረ ስብሐት
114. መዝገበ ብርሃን
115. ምልእተ ክብር
116. ምልእተ ፍስሐ
117. ምልእተ ፀጋ
118. ጽላተ ኪዳን
119. ጽላተ ሕግ
120. ዳግሚት ሰማይ

አማላጅነት በመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል አንድ ከተሰኘው መጽሐፌ ገጽ 72 ላይ የተወሰደ

22/05/2020

“የክርስቶስን ሕግ ፈጽሙ” (ገላ. ፮፥፪)

የክርስቶስ ሕግ ፍጻሜ ፍቅር ነው። ፍቅር አንድ ሰው ከሌላው ጋር በየዕለቱ የሚያደርገው ግንኙነት፣ በመተሳሰብ ላይ የተመሠረተ ልባዊ መዋደድና ጥልቅ መንፈሳዊ ጸጋ ነው።በሰዎች መካከል በሚኖረው መልካም ግንኙነት የተነሳ አንዱ ለሌላው የሚያደርገው መልካም ነገር ሁሉ ፍቅር ነው።

ለሌላው የምናደርገው ይህ መልካም የሆነ ፍቅር በልዑል እግዚአብሔር ዘንድ ትልቅ ዋጋ አለው፡፡ በዚህም በዕለት ተዕለት ግኑኝነት ለተራበ ማብላት፣ ለተጠማ ማጠጣት፣ ለተቸገረ መርዳት፣ ያዘነን ማጽናናት፤ ይህን የመሰለውን መልካም ምግባር ሁሉ ሰው ለሰው ካለው ፍቅር የተነሳ የሚያደርገው ነው።

በዚህ መሰል ተግባር ለሌሎች መልካም ያደረጉትን ሁሉ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለፍርድ በሚመጣ ጊዜ “የአባቴ በሩካን ኑ ዓለም ከተፈጠረበት ጊዜ ጀምሮ የተዘጋጀላችሁን መንግሥት ውረሱ። ከሁሉ የሚያንሱ ከእነዚህ ወንድሞቼ ለአንዱ እንኳ ያደረጋችሁት ለእኔ አደረጋችሁት” በማለት የከበረ ዋጋ እንደሚሰጠን በወንጌል ተናግሯል። (ማቴ.፳፭፥፭፤፴፭-፴፮)

ሰውን መውደድና መርዳት ፍቅር ነውና ከፍቅር አምላክ ከእግዚአብሔር ዘንድ ሰማያዊ ዋጋን ያስገኛል። ቅዱስ ጳውሎስ “እንግዲያስ ጊዜ ካገኘን ዘንድ ለሰው ሁሉ መልካም እናድርግ” ያለው በፍቅር የሚደረግ መልካም ነገር ሁሉ የሚያስገኘውን መንፈሳዊ ዋጋ በሚገባ ስለተረዳ ነው። (ገላ. ፮፥፲)

ይህ ፍቅር የተባለው ለሰው መልካም መሥራት፣ የሰውን ድካሙን ሳይቀር በመሸፈን መገለጥ የሚገባው ተግባር ነው። ቅዱስ ጳውሎስ ይህን በተመለከተ “ከእናንተ እያንዳንዱ የአንዱን ሸክም ይሸከም፤ እንዲህም የክርስቶስን ሕግ ፈጽሙ” ብሏል፡፡ ስለዚህ የክርስቶስ ሕግ የተባለው ፍቅር ነው፤ ይህም በተግባር መገለጥ ያለበት አስተምህሮ ነው። (ገላ.፮፥፪)

መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከጽኑ ፍቅሩ የተነሳ የሰው ልጆችን ሸክም ተሸክሞ ሞት የማይስማማው ሲሆን መዋቲ ሥጋን ተዋሕዶ ሞትን ድል እንዳደረገልን ሁሉ የሰውን ጉድለት በመታገስ ወደ ድኅነት የሰው ልጅ እንዲደርስ ማድረግ ፍቅርን በተግባር መግለጥ ነው።

ፍቅር በመላእክት ልሳን ከመናገር በላይ የከበረ ነው። ፍቅር ከዕውቀትና ከልግሥና ሁሉ ይበልጣልና። ቅዱስ ጳውሎስም በፍቅር ያልተቀመመ እና ያልጣፈጠ ሥራ (ገድል) ሁሉ የማይጠቅም መሆኑን ነግሮናል፤ “ፍቅር ይታገሳል፣ ፍቅር ያስተዛዝናል፣ ፍቅር አያስመካም፤ ፍቅር ብቻዬን ይድላኝ አያሰኝም፤ ፍቅር ክፉ ነገርን አያሳስብም፤ ፍቅር ከእውነት ጋር ሁሌ ደስ ይለዋል፤ ፍቅር ሁሉን ያምናል እንዲሁም ፍቅር ዘወትር አይወድቅም” በማለት አስተምሮናል። (፩ኛ ቆሮንቶስ ፲፫፥፩-፲)

በዚህ መሠረት ፍቅር ለሚወደውና ለሚያፈቅረው ቸርነትን ያደርጋል፤ ይታገሳልም። ስለዚህ የራሱን ሳይቀር ይተውለታል፤ ይሰጠዋልም። የሚወደውን ሰው እንዳያጣው በትሕትና፤ በየዋህነትና በትዕግስት ያፈቅረዋል። ሰው ሁሉ ለሚወደው ቸርና ርኅሩኅ ነው ካለው ሁሉ በልግስና ያካፍለዋል፤ በማንኛውም ነገር ቢሆን አይጨክንበትም። (ኤፌ. ፬፥፪፤፴፪)

በእግዚአብሔር የሚታመን ክርስቲያን ሁሉ በፍቅር መኖር ይጠበቅበታል። በመስቀል ላይ ለቤዛ ዓለም የተሰቀለው መድኃኔዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ ያስተማረው ሰውን ሁሉ መውደድ እንደሚገባን ነው።

አማናዊው ክርስትና እምነትና ትምህርትም በዚህ ፍቅር መገለጥ አለበት። ቅዱስ ጳውሎስ “በክርስቶስ ኢየሱስ ሆኖ በፍቅር የሚሠራ እምነት እንጂ መገረዝ ወይም አለመገረዝ አይጠቅምም” ብሎ አስተምሮናል። ይህም እምነትን የሚያንቀሳቅሰውና በምግባር እንዲገለጥ ሥራም እንዲሰራ የሚያደርገው ዋናው ፍቅር ነው። (ገላ. ፭፥፮)

ከዚህ ሌላ ለመንፈሳዊ ነጻነት ከተጠራንበት የክርስትና እምነታችን በተለያዩ የሥጋ ፈቃድና ፈተናዎች እንዳንሰናከል እና ፍሬ አልባ እንዳንሆን ሲያስጠነቅቀን “ወንድሞች ሆይ እናንተ ለአርነት ተጠርታችኃልና፤ ብቻ አርነታችሁ ለሥጋ ምክንያት አይስጥ፤ ነገር ግን በፍቅር እርስ በርሳችሁ እንደ ባሪያዎች ሁኑ” በማለት እንድንጠነቀቅ ነግሮናል። (ገላ. ፭፥፲፫)

ሃይማኖትን በምግባር ለመግለጥ ፍቅር እጅግ አስፈላጊ ነው። ይሁንና በመጽሐፍ ቅዱስ “ነገር ግን እርስ በርሳችሁ ብትነካከሱና ብትበላሉ፤ እርስ በርሳችሁ እንዳትጠፋፉ ተጠንቀቁ’’ ተብሏል፡፡ ከዚህ በመነሳት ፍቅር የእምነት ተግባራዊ የሥራ መገለጫ መሆኑን እንረዳለን። (ገላ. ፬፥፲፬)

በእኛ መካከል ፍቅር አለ ማለት በመካከላችን ፍጹም የሆነ አንድነትና መግባባት አለ ማለት ነው። ይህ ከሆነ ደግሞ ሰዎች በአንድ ፍቅር ይኖራሉ፤ አንድ ነገር ያስባሉ፤ በአንድ መንገድ ይጓዛሉ፤ እንዲሁም አንድ ልብ ይሆናሉ። በአንድ ወንጌል ለአንድ ሰማያዊ አገልግሎት የተጠሩ መሆናቸውን ይረዳሉ፡፡ “በአንድ ልብ ሆነው ይተጉ ነበር” (የሐዋ. ሥራ ፩፥፲፬)

ቅዱስ ጴጥሮስ “በመጨረሻው ሁላችሁ በአንድ ልብ ሁኑ፤ የሌላው መከራ ለእናንተ እንደሚሆን አድርጉ፤ እንደ ወንድሞች ተዋደዱ፤” በማለት እንዳስተማረን እኛም ስለፍቅር ስንል የሚዋደዱትን ሰዎች በመምሰል የእግዚአብሔር ማደሪያ የእውነተኛ ፍቅር ምንጭ እንሁን፡፡ ለዚህ ነው ቅዱስ ጳውሎስ “በፍቅር ተመላለሱ፤ ፍቅርን ተከታተሉ” ያለን። ሽንገላ የሌለበት ፍጹም ፍቅር የኃጢአት ጠላትና እንቅፋት መሆኑን እንወቅ። ፍቅር በእኛ መካከል ያለውን ክፋት የሚያስወግድ መንፈሳዊ መሳሪያ ነውና። ዛሬ የምንኖረው ኑሮም በፍቅር ካልጣፈጠ ትርጉም አይነረውም፤ የፍቅር ሰው መሆን በፍቅርም መኖር ተገቢ ነው። (፩ኛ ጴጥ. ፫፥፰፤ኤፌ. ፭፥፪)

ቅዱስ ዳዊት “ወንድሞች በኅብረት ቢቀመጡ እነሆ ያማረ ነው” በማለት ቃል ከፍቅር የሚመነጭ መተሳሰብ፣ መረዳዳት፣ መተዛዘን በጠቅላላው የልብ አንድነት ሊኖር እንደሚገባ ነግሮናል። (መዝ. ፻፴፪፥፪)

እንዲሁም “ማንም እግዚአብሔርን እወዳለሁ እያለ ወንድሙን ቢጠላ ሐሰተኛ ነው። ያየውን ወንድሙን የማይወድ ያላየውን እግዚአብሔርን ሊወደው እንዴት ይችላል እግዚአብሔርን የሚወድ ወንድሙን ደግሞ እንዲወድ ይህች ትእዛዝ ከእርሱ አለችን?” እንደተባለው ይህ የእግዚአብሔር ትእዛዝ መሆኑን እንወቅ። (፩ኛ ዮሐንስ ፬፥፳-፳፩)

የእርስ በርሳችን መዋደድ ከእግዚአብሔር የተሰጠን ስጦታ ነው። በጽኑ የክርስትና እምነት መሠረት ላይ የታነጽን ሁሉ በዚህ ፍጹም ፍቅር ልንዋደድ ይገባል። ፍቅር የእግዚአብሔርን ትእዛዛት በመፈጸም የፈጣሪ ታማኝ አገልጋይና ወዳጅ የመሆን ማረጋገጫ ነው።

ቅዱስ ጴጥሮስም ”ለእውነት እየታዘዛችሁ ግብዝነት የሌለበት ለወንድማማች መዋደድ ነፍሳችሁን አንጽታችሁ እርስ በርሳችሁ ከልባችሁ ተዋደዱ” በማለት አስተምሮናል። (፩ኛ ፩፥፳፪-፳፫)

ቅዱስ ጳውሎስ “አገልግሎታችንም እንዳይነቀፍ በአንዳች ነገር ማሰናከያ አንሰጥም። ነገር ግን በሁሉ እንደ እግዚአብሔር አገልጋዮች (ግብዝነት በሌለው ፍቅር) ራሳችን እናማጥናለን” በማለት እውነተኛ ፍጹም ፍቅር ከግብዝነት የነጻ መሆኑን አስረድቶናል። (፪ኛ ቆሮንቶስ ፮፥፫)

በወንድሞች መካከል የሚኖረው የእርስ በርስ ፍቅር በተወሰነ ጊዜ ታይቶ የሚጠፋ በአንድ ወቅት ፈክቶ በሌላ ጊዜ እንደሚጠወልግ አበባ መሆን የለበትም። ከዚህ ይልቅ በጽኑ እምነት ላይ በቅሎ በጊዜው ሁሉ እያበበ መንፈሳዊ በረከትንና ረድኤተ እግዚአብሔር እያፈራ የሚኖር ዘላቂ መሆን ይገባዋል። ለዚህ ነው ቅዱስ ጳውሎስ በመልእክቱ ”እኛ ደግሞ ለእናንተ እንደምንሆን ጌታ እርስ በርሳችሁ ያላችሁን ለሁሉም የሚሆን ፍቅራችሁን ያብዛ ይጨምርም” በማለት የጸለየልን። (፩ኛ ተሰ. ፫፥፲፫)

አባቶቻችን እንዳደረጉት ሁሉ ፍቅር እንዲጸናና አድጎም ፍሬ እንዲያፈራ በጸሎት የታጠረና በጥንቃቄ የሚጠበቅ እንደሆነ መረዳት ያስፈልጋል። ቅዱስ ጴጥሮሰ “ስለዚህም ምክንያት ትጋትን ሁሉ እያሳያችሁ እግዚአብሔርን በመምሰል የወንድማማችን መዋደድ፣ በወንድማማችም መዋደድ ፍቅርን ጨምሩ” ብሏል፡፡ ፍጹም ሰማያዊ ፍቅር ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ ሊጓዝ የሚገባ የክርስትና ሕይወት ማጣፈጫ እንደሆነ በመረዳት ፍቅራችን ከግብዝነትና ከወረት ነጻ ሆኖ ሕግጋትን በመፈጸምና በማክበር በተግባር የሚገለጥ እንዲሆን መጸለይ አለብን። (፪ኛ ጴጥ. ፩፥፯)

የለመኑትን የማይነሣ የነገሩትን የማይረሳ ልዑል እግዚአብሔር ለቀደሙት አበው እንደተለመነ ሁሉ እኛን እንዲለመነን፣ የፍቅር ሰዎች እንዲያደርገን፣ በፍቅሩ በመጽናትም መንግሥቱን ለመውረስ እንዲያበቃን ቅዱስ ፈቃዱ ይሁንልን፤ አሜን፡፡

ዲያቆን ዮሴፍ በቀለ

እንኳን አደረሳችሁ !!!እንጠግብ ዘንድ እንጠራሻለን።ከርሃበ ጽድቅ ፣ ከድርቀተ ሕይወት ታድኚን ዘንድ ምግብ የሆነ ስምሽን ማርያም ማርያም እንላለን፤በዓለም የጠወለገች ነፍሳችንን ታረሰርሻት ዘ...
27/10/2019

እንኳን አደረሳችሁ !!!

እንጠግብ ዘንድ እንጠራሻለን።
ከርሃበ ጽድቅ ፣ ከድርቀተ ሕይወት ታድኚን ዘንድ ምግብ የሆነ ስምሽን ማርያም ማርያም እንላለን፤
በዓለም የጠወለገች ነፍሳችንን ታረሰርሻት ዘንድ ማርያም ማርያም እንላለን፤
በዲያቢሎስ ፈተና የደነዘዘች መንፈሳችንን ስንቅ ትሆኚያት ዘንድ ማርያም ማርያም እንላለን፤
በመናፍቃን ድንፋታ የኮሰመነች ብርታታችን ትመለስ ዘንድ ማርያም ማርያም እንላለን፤
በዘረኝነት ብርድ የሚንሰፈሰፈው ሰብእናችን የሰማያዊ ዜግነት ፀሐይን ይሞቅ ዘንድ ማርያም ማርያም እንላለን፤
በበሽታ የወደቀ አካላችን ይፈወስ ዘንድ ማርያም ማርያም እንላለን፤
በብቸኝነት የፈራ ማንነታችን በአዕላፋት አንድነት ውስጥ እንዳለ ይረዳ ዘንድ ማርያም ማርያም እንላለን፤
የልጅሽን መድኃኒትነት እንሳተፍ ዘንድ ማርያም ማርያም እንላለን፤
ብቻ ምግባችን ነውና ፣ ስንቃችን ነውና... በነገራችን ሁሉ ማርያም ማርያም እንላለን።

Address

Adwa

Telephone

+251994053870

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when አባቶችህን ጠይቅ ይነግሩህማል? posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Place Of Worship

Send a message to አባቶችህን ጠይቅ ይነግሩህማል?:

Share