ኦርቶዶክሳዊ አገልግሎት

ኦርቶዶክሳዊ አገልግሎት አገልግሎታችንን እንታደግ

23/03/2026

አንቶኒ ኮኒያሪስ የሚባሉ አንድ ጸሐፊ ይህን አስገራሚ ታሪክ እንዲህ ሲሉ ያካፍሉናል:-

ዓይነ ስውር ለነበረ አንድ ሰው በፈቃደኝነት ቤቱ እየመጡ መጽሐፍ ቅዱስን የሚያነቡለት ሁለት ወጣት ልጆች ነበሩ። ወጣቶቹ ንባባቸውን የጀመሩት ከማቴዎስ ወንጌል ነው። ታዲያ በቀዳሚ ምዕራፍ ያለውን ክርስቶስ በሥጋ የመጣበትን የዘር ሐረግ የሚዘረዝረውን እና በአስቸጋሪ (ለንባብ) የዕብራይስጥ ስሞች የተሞላውን ክፍል ማንበብ እንደ ጀመሩ ወዲያው “ይበቃናል፥ እነዚህንስ ስሞች ብንዘላቸው ይሻላል” አሉ። ዓይነ ስውሩ ግን “በፍጹም አይዘለሉ። እባካችሁ እናንብበው” አላቸው። ወጣቶቹም ጥያቄውን በእሺታ ተቀብለው ለአፋቸው እንግዳ ከሆኑት የዕብራስጥ ስሞች ጋር እየታገሉ ማንበባቸውን ቀጠሉ።

የስም ዝርዝሮቹን አንብበው እንደጨረሱም ከመጽሐፉ ላይ ቀና ብለው ዓይነ ስውሩን ሰው ሲመለከቱት ጉንጮቹ በእንባ ርሰዋል። “ምነው? አሁን ይህ የስሞች ዝርዝር እንዴት ስሜታዊ ያደርጋል?” ሲሉ ጠየቁት። ያም ነው “ልጆቼ፣ እግዚአብሔር በደለኞችን ሁሉንም ያውቃቸዋል። ያውም በስማቸው ያውቃቸዋል። ይህ ደግሞ እግዚአብሔር እኔን ኃጢአተኛውንም ከነስሜ እንደሚያውቀኝ እንድረዳ አደረገኝ። በዚህም ምክንያት የተፈላጊነት ስሜት ተሰማኝ” ብሎ መለሰላቸው።

“ሴሰነች” የተባለችው ትዕማርን፣ ከነናዊቷን ዘማ ረዓብን፣ የተገፋችውን ሞዓባዊት ሩትን ያልረሳ ጌታ እኛን አይረሳንም። “ለጌታ እናስፈልገዋለን!”

ዲያቆን አቤል ካሣሁን
መጋቢት 14- 2018 ዓ. ም.

https://t.me/Dnabel

Address

Adis

Telephone

+251969022076

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ኦርቶዶክሳዊ አገልግሎት posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Place Of Worship

Send a message to ኦርቶዶክሳዊ አገልግሎት:

Share