Bethel International Prayer Ministry

Bethel International Prayer Ministry The minstry pray for the generation,for the healthy grouth of churches ,for the development of the country and good governance
.

19/12/2024

ዘፍጥረት 28:15፤
እነሆም እኔ ከአንተ ጋር ነኝ፥ በምትሄድባትም መንገድ ሁሉ እጠብቅሃለሁ፥ ወደዚችም ምድር እመልስሃለሁ፤ የነገርሁህን ሁሉ እስካደርግልህ ድረስ አልተውህምና።”

26/11/2024

ኢያሱ 1:5፤
በሕይወትህ ዕድሜ ሁሉ ማንም አይቋቋምህም፤ ከሙሴ ጋር እንደ ሆንሁ እንዲሁ ከአንተ ጋር እሆናለሁ፤ አልጥልህም፥ አልተውህም።

17/11/2024

ዘዳግም 32:4፤
እርሱ አምላክ ነው፤ ሥራውም ፍጹም ነው፤ መንገዱም ሁሉ የቀና ነው፤ የታመነ አምላክ፥ ክፋትም የሌለበት፥ እርሱ እውነተኛና ቅን ነው።

01/01/2023

ሮሜ3፣23 ሁሉ ኃጢአትን ሠርተዋልና የእግዚአብሔርም ክብር ጎድሎአቸዋል
24 በኢየሱስ ክርስቶስም በሆነው ቤዛነት በኩል እንዲያው በጸጋው ይጸድቃሉ።

01/01/2023

21 አሁን ግን በሕግና በነቢያት የተመሰከረለት የእግዚአብሔር ጽድቅ ያለ ሕግ ተገልጦአል፥

22 እርሱም፥ ለሚያምኑ ሁሉ የሆነ፥ በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን የሚገኘው የእግዚአብሔር ጽድቅ ነው፤ ልዩነት የለምና፤

11/07/2021

2 የሰው ልጅ ሆይ፥ ፊትህን በግብፅ ንጉሥ በፈርዖን ላይ አድርግ፥ በእርሱና በግብፅ ሁሉ ላይም ትንቢት ተናገር፥

3 እንዲህም በል፡— ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፡— በወንዞች መካከል የምትተኛና፡— ወንዙ የእኔ ነው ለራሴም ሠርቼዋለሁ የምትል ታላቅ አዞ፥ የግብፅ ንጉሥ ፈርዖን ሆይ፥ እነሆ፥ በአንተ ላይ ነኝ።

4 በመንጋጋህ መቃጥን አገባብሃለሁ፥ የወንዞችህንም ዓሦች ወደ ቅርፊትህ አጣብቃለሁ፤ ከወንዞችህም መካከል አወጣሃለሁ፥ የወንዞችህም ዓሦች ሁሉ ወደ ቅርፊትህ ይጣበቃሉ።

5 አንተንና የወንዞችህን ዓሦች ሁሉ ወደ ምድረ በዳ እጥላለሁ፥ በምድርም ፊት ላይ ትወድቃለህ እንጂ አትከማችም አትሰበሰብም መብልም አድርጌ ለምድር አራዊትና ለሰማይ ወፎች ሰጥቼሃለሁ።

15/01/2021

ጽኑ፥ አይዞአችሁ፤ ከእኛም ጋር ያለው ከእርሱ ጋር ካለው ይበልጣልና ከአሦር ንጉሥና ከእርሱ ጋር ካለው ጭፍራ ሁሉ አትፍሩ፥ አትደንግጡም።

ከእርሱ ጋር የሥጋ ክንድ ነው፤ ከእኛ ጋር ያለው ግን የሚረዳንና የሚዋጋልን አምላካችን እግዚአብሔር ነው።
2ዜና32፤7-8

15/01/2021

7 ጽኑ፥ አይዞአችሁ፤ ከእኛም ጋር ያለው ከእርሱ ጋር ካለው ይበልጣልና ከአሦር ንጉሥና ከእርሱ ጋር ካለው ጭፍራ ሁሉ አትፍሩ፥ አትደንግጡም።

8 ከእርሱ ጋር የሥጋ ክንድ ነው፤ ከእኛ ጋር ያለው ግን የሚረዳንና የሚዋጋልን አምላካችን እግዚአብሔር ነው ብሎ አጸናናቸው። ሕዝቡም በይሁዳ ንጉሥ በሕዝቅያስ ቃል ተጽናና።

11/11/2020

አጥፊው በባቢሎን ላይ ወጥቶባታልና ኃያላኖቿ ተያዙ፣ቀስታቸው ተሰባበረ ።እግዚአብሔር ፍዳን የሚከፍል አምላክ ነውና ፣ፍዳንም በእርግጥ ይከፍላል።ኤር 51፣56

11/11/2020
25/03/2020

ለውድ በጌታወንድሞቼና እህቶቼ
ባላችሁበት ሰላም ይብዛላችሁ።
አጭር ነገር ላካፍላችሁ አሰብኩና እኔ በተጽናናሁበት እናንተም እነድትጽናኑ ጽፌላችኈለሁ።
አይዟቸሁ

ከምንሰማው ከምናየው ነገሮች በላይ እግዚአብሔር ትልቅ ነው።

ሐዋ 27፣ 22
አሁንም አይዟችሁ ብዬ እመክራችኋለህ ይህ መርከብ እንጂ ከእንንተ አንድ ነፍስ እንኳ አይጠፋም።

ዘዳ 31-:8
በፊትህ የሚሄድ እርሱ እግዚአብሔር ነው። ከአንተ ጋር ይሆናል ፥ አይጥልህም ፥ አይተውህም ፤ አትፍራ አትንግጥ።

ለመንግስታት ለሀያላንና ለእኛም ትልቅ የሆኑ ነገሮች ትልቅነታቸው ለእኛ ነው።

ፍርሀት ችግር በሽታ ጭነቀት ተስፋ መቁረጥ ሰላም ማጣት .....ትልቅና ግዙፍ ሆነው የሚታዩበት ሁኔታ ሊፈጠር ይችላል።

ነገር ግን እግዚአብሔር ከሁሉ በላይ ነው።
ማር 5:36
እመን እንጂ አትፈራ

እምነት ከመስማት ነው። መስማትም በእግዚአብሄር ቃል ነው። ሮሜ 10፣ 17

እምነታችን ብዙ በምንሰማው ነገር ይወሰዳል። በአለም ያለውን ነገር መስማት አስፈላጊ ነው። ጥንቃቄም ጥሩ ነው።
አብዝተን ከሰማነውና ካወራነው ካሰላሰልነው እምነታችን ይሸረሸራል እንሸበራለን እንፈራለን።
በእግዚአብሄር ቃል ላይ መታመን ይጠፋል።
አሁን ያለው የኮሮና ቫይረስ መስፋፋት መንግስታትን ሁሉ ያስጨነቀ ጉዳይ ሆኗል። ወሬው ሁሉ ከባድ እንደሆነ ነው። ልክ ነው ችግሩ ግዙፍ ነው።
ነገር ግን ወሬውን ደጋግመን በመስማትና በመናገር እምነታችን እንዳየጠፋና የእግዚአብሔርን ሁሉን ቻይነት ቸል እንዳንለው ያስፈልጋል።
ክርስቲያን እምነቱ ይፈተናል። ተፈትነን እንዳነወድቅ እምነታችንን አጥብቀን ልንይዝ ይገባል። ወደ እግዚአብሔር ይበልጥ መቅረብና ድምጹን መስማት ያስፈልጋል።

ጳውሎስ በሚናወጥ መርከብ ከብዙ ሰዎች ጋር እየተጓዘ ሌሎች ሲጨነቁ እርሱ ግን ከወጀቡ ድምፅ ጎን የእግዚአብሔርነ ድምፅ ይሰማ ነበር።
እራሱ ተጽናንቶ ሌሎችን ያጽናና ነበር።

ሐዋ 27፣ 22-24
አሁንም፦ አይዞአችሁ ብዬ እመክራችኋለሁ፤ ይህ መርከብ እንጂ ከእናንተ አንድ ነፍስ እንኳ አይጠፋምና።
የእርሱ የምሆንና ደግሞ የማመልከው የእግዚአብሔር መልአክ በዚች ሌሊት በአጠገቤ ቆሞ ነበርና፥ እርሱም፦
ጳውሎስ ሆይ፥ አትፍራ፤ በቄሣር ፊት ልትቆም ይገባሃል፤ እነሆም፥ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር የሚሄዱትን ሁሉ ሰጥቶሃል አለኝ።

አሁን ከሚወራውና ከሚያስጨንቀው በሽታ
ከምንፈራው ነገር በላይ እግዚአብሔር ትልቅ ነው። እርሱ ያድነናል።
የምንሰማወን ሁሉ በእግዚአብሄር ቃል ወስጥ እንየው።

25 ስለዚህ እናንተ ሰዎች ሆይ፥ አይዞአችሁ፤ እንደ ተናገረኝ እንዲሁ እንዲሆን እግዚአብሔርን አምናለሁና።

ከራሳችን አልፈን ሌሎችን ልናስመልጥ በእግዚአብሄር ፊት ልንወድቅ ግዜው አሁን ነው። ወጀቡ ያልፋል።
አይዟችሁ። ጌታ ይባረካችሁ።
በጸሎት እንበረታ።
ሚሊዮን

Address

Mekanissa
Addis Ababa

Telephone

+251911610515

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Bethel International Prayer Ministry posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Place Of Worship

Send a message to Bethel International Prayer Ministry:

Share