ZimareTube

ZimareTube በየዕለቱ የተመረጡ የንስሐና የዓውደ አመት መዝሙሮች ፣ ዕለቱንና ወቅቱን በተመለከተ ስብከተ ወንጌልና
ትምህርተ ኃይማኖትን፣ ያባቶቻችን ገድልና መንፈሳዊ
(552)

Ethiopian Orthodox Tewahido preaching video, Amharic Orthodox Mezmur,
Amharic Preaching, Amharic Sibket, Spiritual Movies and Testimony

የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዕርገት ነሐሴ 16፤ እንኳን አደረሳችሁ፣ አደረሰን🙏ቶማስ ትንሣኤሽን አይቷልና እኛም በረከት አይቅርብንፍልሰታ የሚለው ቃል የተገኘው ፈለሰ ከሚለው የግዕዝ ...
22/08/2026

የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዕርገት ነሐሴ 16፤ እንኳን አደረሳችሁ፣ አደረሰን🙏

ቶማስ ትንሣኤሽን አይቷልና እኛም በረከት አይቅርብን

ፍልሰታ የሚለው ቃል የተገኘው ፈለሰ ከሚለው የግዕዝ ቃል የተገኘ ሲሆን በጥሬ ትርጉሙ መለየት፣ ማረግ፣ ወደላይ መውጣት የሚለውን ትርጉም ይይዛል። ኢትዮጵያዊው ሊቅ ቅዱስ ያሬድ “ቅድስት ድንግል ማርያም ከሚያልፈው ዓለም ወደማያልፈው ዓለም፣ ከምድር ሕይወት ወደ ሰማያዊ ሕይወት፣ ተሻገረች” በማለት ፍልሰታ የሚለውን ቃል ትርጓሜ አመሥጥሮ ገልጾታል፡፡ ጾመ ፍልሰታ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ሥጋዋ ከሞትና መቃብር መለየትና ማረግን ያመለክታል። ይህ በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ከተወሰኑት ሰባቱ አጸዋማት ለዓመቱ የመጨረሻው ጾም ነው። እመቤታችን በዚህ ዓለም ለ64 ዓመታት ከኖረች በኋላ ጥር 21 ቀን 49 ዓመተ ምሕረት ዐርፈለች፡፡ ዕረፍቷም እንደሌላው ሰው በሕማምና በድካም አይደለም፡፡ በገነት ዕፀዋት መዓዛ ተመስጣ ቅድስት ነፍሷ ከሥጋዋ ተለይታለች፡፡

ቅዱሳን ሐዋርያት እመቤታችንን በአጎበር አድርገው ሊቀብሯት ወደ ጌቴሴማኒ ይዘዋት ሲሄዱ አይሁድ ለምቀኝነት አያርፉምና፣ ቀድሞ ልጇን ተነሣ ዐረገ እያሉ ሲያውኩን ኖረዋል፤ እርሷን ደግሞ ተነሣች ዐረገች እያሉ ሊያውኩን ነውና ኑ የማርያምን ሥጋ በእሳት እናቃጥለው ብለው ተነሱ፡፡ ከመካከላቸው አንድ ታውፋንያ የሚባል አይሁዳዊ ከሐዋርያት እጅ ለመንጠቅ ዘሎ ሄዶ የአልጋውን ሸንኮር ሲይዝ የታዘዘ መልአክ በረቂቅ ሰይፉ እጆቹን ቆረጠው፡፡ እጆቹም በአልጋው ሸንኮር ላይ ተንጠልጥለው ቀሩ፡፡ የምሕረት እናት የሆነችው ድንግል ማርያም ቅዱስ ጴጥሮስ ጸልዮ እጆቹን እንዲመልስለት ነግራው እንደነበረ አድርጎለታል፡፡ መላእክት የእመቤታችን ሥጋዋን መላእክት ከዮሐንስ ወንጌላዊ ጋር በገነት ከዕፀ ሕይወት ሥር ወስደው አስቀምጠውታል፡፡ በስምንተኛው ወር በነሐሴ ሐዋርያት ቅዱስ ይህን በረከት አይቶ እኛ ሳናይ ቀረን ብለው ከነሐሴ 1 እስከ 14 ሁለት ሱባዔ ይዘው ከጌታችን ተቀብለው በጸሎትና በምህላ ቀበሯት።

ከአሥራ ሁለቱ ሐዋርያት አንዱ ቅዱስ ቶማስ ለሐዋርያዊ አገልግሎት ወጥቶ ነበርና ሲቀብሯት አልተገኘም። እመቤታችን በተቀበረች በሦስተኛው ቀን እንደ ልጇ ከሙታን ተነሥታ ስታርግ ቶማስ ከሀገረ ስብከቱ በደመና ተጭኖ ወደ ኢየሩሳሌም ሲመጣ አገኛት። በዚህን ጊዜ ትንሣኤዋን ሌሎች ሐዋርያት አይተው እርሱ የቀረበት መስሎት “ቀድሞ የልጅሽን ትንሣኤ ሳላይ ቀረሁ አሁን ደግሞ ያንችን ትንሣኤ ሳላይ ቀረሁ” ብሎ ራሱን ከደመና ላይ ሊወረውር ቃጣው። እመቤታችን ከእርሱ በስተቀር ትንሣኤዋን ያየ አለመኖሩን ነግራ ግን ቶማስን አፅናናችው፡፡ ለምስክርነት እንዲሆንም በቀብሯ ጊዜ የነበረውን ሰበኗን ሰጥታው አረገች። ቅዱስ ቶማስም ኢየሩሳሌም ሲደርስ የእመቤታችን ነገር እንዴት ሆነ አላቸው፡፡ እነርሱም አግኝተን ቀበርናት አሉት፡፡

እርሱም “ሞት በጥር፤ በነሐሴ መቃብር፤ ለሰሚውም አያምር፤ ይህ እንዴት ይሆናል?” ቢላቸው ቅዱስ ጴጥሮስ “ድሮም አንተ ተጠራጣሪ ነህ፤ ገንዘን የቀበረን እኛ እያለን እንዴት ትጠራጠራለህ” ብሎት ወደ መቃብሯ ሄደው መቃብሯን ቢከፍቱት ባዶ ሆኖ አገኙት፡፡ በዚህ ተደናግጠው ተያዩ፤ በዚህ ጊዜ ቅዱስ ቶማስ “አታምኑኝም ብዬ ነው እንጂ እመቤታችን ተነሣች፤ ዐረገች፤ ይኸው ምልክቱ” ብሎ ገንዘው የቀበሩበትን ሰበን አሳያቸውና ሰበኗን ለበረከት ተካፈሉት፡፡ በዓመቱም ቶማስ ትንሣኤሽን አይቷልና እኛም በረከት አይቅርብን ብለው ከነሐሴ አንድ ጀምረው ሱባዔ ገቡ። ነሐሴ 16 ጌታችን እመቤታችንን አምጥቶ ሐዋርያትን ቀድሶ አቁርቧቸዋል።

ቅዱሳን ሐዋርያት ከአንዴም ሁለቴ የጾሙትን ጾም አብነት አድርገን በረከታቸው እንዲያድርብን የእመቤታችንን ጾመ ፍልሰታ እንጾማለን። በተለይ ገዳማውያን አባቶች የስጋቸውን ጉዳይ ትተው ዓለምን ንቀው መንነዋልና ሁሌም ቢሆን በጾም ይኖራሉ። እኛ በቅበላውም በጾም ፍቺውም ከመብሉም ከመጠጡም ከልክ በላይ እንደፈለግን ስንሆን እነርሱ ግን እጅግ በሚያስቸግር ሁኔታ ውስጥ ሆነው፣ የገዳሙ ህልውና አደጋ ላይ ወድቋል። ካለን ከፍለን ልንደግፋቸው ይገባል።

የንግስተ ሰማይ ወምድር ልመናዋ፣ ክብራ፣ የልጇ የወዳጇ ቸርነት በኛ ላይ አድሮ ይኑር አሜን!!!

ድጋፍ ለማድረግ :-ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አድነት ገዳም

ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444

ለተጨማሪ መረጃ:-
የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957
ወይም 0938644444

የእናታችን ቅድስት ኪዳነ ምህረት ምልጃ እና ረድኤት አይለየን🙏የማያልፍ የምሕረት ቃል ኪዳኗ ዘወትር ይታሰባል ኪዳን የሚለው ቃል ተካየደ ከሚለው የግእዝ ግስ የወጣ ሲሆን ትርጉሙም ተማማለ፣ ተ...
21/08/2026

የእናታችን ቅድስት ኪዳነ ምህረት ምልጃ እና ረድኤት አይለየን🙏

የማያልፍ የምሕረት ቃል ኪዳኗ ዘወትር ይታሰባል

ኪዳን የሚለው ቃል ተካየደ ከሚለው የግእዝ ግስ የወጣ ሲሆን ትርጉሙም ተማማለ፣ ተስማማ፣ ውል ገባ ማለት ነው፡፡ ኪዳነ ምሕረት ማለትም ደግሞ የምሕረት ቃል ኪዳን ማለት ነው፡፡ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለእመቤታችን ድንግል ማርያም ስለሰው ልጆች ይቅርታ የገባላት ኪዳን ነው፡፡ እግዚአብሔርን ለሚፈሩት፣ ለሚያከብሩት፣ ለሚወዱትና ለሚወዳቸው ሁሉ በተለያዩ ጊዜያት ብዙ ኪዳናትን ሰጥቷል፡፡ የኪዳነ ምሕረት ሥዕል በመባል የሚታወቀው ሥዕል በቤተ ክርሰቲያናችን በስፋት ከሚሳሉት የወላዲተ አምላክ ሥዕል ጭብጦች ውስጥ አንዱ ሲሆን። ከጌታችን ኢየሱስ ቃልኪዳን ስትቀበል በጎሎጎታ የሚያሳየው ሥዕል ትክክለኛው ገላጭ ሥዕል ሲሆን፤ ይህ ሥዕል እንደ ቤተ ክርስቲያኑ ስፋት የሚጨመረው ጭብጥ ሊለያይ ይችላል፡፡

ለምሳሌ በዚህ ሥዕል ዘይቤ ላይ የሚታዩት መላእክት ቁጥራቸው ሊበዛ አሊያም ሊያንስ ይችላል፡፡ በዚህ ሥዕል እመቤታችንና ጌታችን ቆመው አሊያም ተቀምጠው ጌታችን በቅዱሳን እጆቹ የእናቱን ቅዱሳን እጆች በመያዝ ቃል ኪዳን ሲገባላት አሊያም በቅዱሳት እጁ ቃል ሲገባላት የሚያሳይ ዓይነት ሥዕል ነው፡፡ በዚህ መልኩ እመቤታችን ከተሳለችባቸው አብያተክርስቲያናት መካከል ጎርጎራ ደብረ ሲና (17ኛው መ.ክ.ዘ)፣ አብርሐወ አጽብሐ (19ኛው መ.ክ.ዘ)፣ መቐለ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ (20ኛው መ.ክ.ዘ)፤ ከጥንታውያን ብራና መጻሕፍት ከተመለከትን በአክሱም ጽዮን ቤተክርስቲያን ግምጃ ቤት የሚገኘው የ17ኛው መ.ክ.ዘ ተአምረ ማርያም ተጠቃሽ ናቸው፡፡ ገዳማውያንም ዘወትር በሥዕሏ ፊት ቆመው ይለምኗታል፡፡ እርሷም ልመናና ጸሎታቸውን ታሳርጋለች፡፡ ገዳማቸውን እንደግፍ፣ በዓታቸውን እናጽና፣ ከበረከታቸውመ እንካፈል፡፡

ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የተሰጠው ኪዳን፣ ቀድመው ለነበሩ ኪዳናት ማለትም ኪዳነ አዳም፣ ኪዳነ ኖህ፣ ኪዳነ መልከ ጸዴቅ፣ ኪዳነ አብርሃም፣ ኪዳነ ሙሴና ኪዳነ ዳዊት መደምደሚያ ነው፡፡ ዘለዓለማዊ ስለ ሆነው የማያልፍ የምሕረት ቃል ኪዳን እየታሰበም ዕለቱ በመዝሙር፣ በማኅሌትና በቅዳሴ ይከበራል፡፡ በክርስቶስ ክርስቲያን ለምንባል ለእኛ ለሐዲስ ኪዳን የቤተ ክርስቲያን ልጆችም ይህ አዲስ ውል የተደረገልን ለነፍሳችን ድኅነት በመሆኑ በስሟ እየተማጸንን እንዲሁም መታሰቢያዋን እያደረግን ለተራቡት ማብላት፣ ለተጠሙት ማጠጣትና የተቸገሩትን መርዳት ይገባናል፡፡ ገዳማውያን በበቃል ኪዳኗ ታምነው፣ ዘወትር በሥዕሏ ፊት በጸሎት ይተጋሉ፡፡ ገዳማቸውን እንደግፍ፣ በዓታቸውን እናጽና ከበረከታቸው እንካፈል፡፡

ድጋፍ ለማድረግ፦ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም

ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444

የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444

ቅዱስ ቂርቆስ የልባችሁን መልካም መሻት ይሙላላችሁ 🙏የሚያገኛቸውን መከራ ሳይፈሩ ስለ ክርስቶስ አምላክነት ከመስከሩ የክብር አክሊል ከተቀዳጁ ሰማዕታት የሦስት ዓመቱ ሕጻን ሰማዕት ቅዱስ ቂርቆ...
21/08/2026

ቅዱስ ቂርቆስ የልባችሁን መልካም መሻት ይሙላላችሁ 🙏

የሚያገኛቸውን መከራ ሳይፈሩ ስለ ክርስቶስ አምላክነት ከመስከሩ የክብር አክሊል ከተቀዳጁ ሰማዕታት የሦስት ዓመቱ ሕጻን ሰማዕት ቅዱስ ቂርቆስና እናቱ ቅድስት ኢየሉጣ ተጠቃሽ ናቸው፡፡ ቅድስት ኢየሉጣ የሮም ግዛት በሆነው አንጌቤን በክርስትና ሃይማኖት ጸንታ የምትኖርና ልጇ ቅዱስ ቂርቆስንም በስርዓት ያሳደገችው ደግ ሴት ነበርች፡፡ በዘመኑ የነበረውን አረማዊ አስተዳዳሪ እለእስክንድሮስን በመፍራት ከልጇ ጋር ከሮም ወደ ጠርሴስ ብትሰደድም እለእስክንድሮስ ተከትሎ ባለችበት ቦታም አገኛት።

ወታደሮችም እርሷንና ልጇን ይዘው ወደ መኮንኑ አቀረቧቸው። መኮንኑም "ስምሽን ንገሪኝ" ቢላት "ስሜ ክርስቲያን ነው" አለችው። መኮንኑ በብስጭት ሕጻኑ ቅዱስ ቂርቆስንም "ስምህን ንገረኝ" ሲለው "ስሜ ክርስቲያን ነው፤ እናቴ የሰየመችኝን ከፈለክ ግን ቂርቆስ ነው" ሲል መለሰለት። ቅድስት ኢየሉጣንም "ለጣዖት ልትሰግጂ ይገባል" ሲላት “የምንሰግድለት አንድ ክርስቶስ ብቻ ነው” አለችው፡፡ ቅዱስ ቂርቆስም እየደጋገመም "እኔ ክርስቲያን ነኝ" ብሎ በመጮሁ ምላሱን ቢያስቆረጠው እግዚአብሔር ፈውሶታል፡፡

መኮንኑ መከራ አጸናባቸው፤ በግርፋት የጀመረ ስቃይ ሊሰሙት ወደ ሚጨንቅ መከራ ቀጠለ። በፈላ ውሃ ውስጥ ሲከታቸውም ቅዱስ ገብርኤል አዳናቸው፡፡ እናትና ልጅ በክርስቶስ ታምነዋልና ጸኑ።

ከብዙ ስቃይና መከራ በኋላም ጥር 15 ቅዱስ ቂርቆስን ጥር 16 ደግሞ ቅድስት ኢየሉጣን ሰይፏቸው ሰማዕትነት ተቀብለዋል፡፡ የሕጻኑን ሥጋ በሠረገላ ኤልያስ አኑሮታል፣ ብዙ ቃል ኪዳን ሰጥቷቸዋል።

ዛሬም በየገዳማቱ ዓለምን ንቀው የሚኖሩ መነኮሳትና ገዳማውያን በጸሎታቸው ኃይል ያደርጋሉ፡፡ ከዓለም ክብር የክርስቶስን ክብር፣ ከሥጋ ደስታ መንግስተ ሰማያትን መርጠዋልና፡፡ ገዳማቸውን እናግዝ በዓታቸውን እናጽና፡፡

ድጋፍ ለማድረግ፦ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም

ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444

የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444

ቅዱስ ሚካኤል የልባችሁን መልካም መሻት ይሙላላችሁ!!!መልአኩም በመሠዊያው ነበልባል ውስጥ ወደ ሰማይ ዐረገ🙏በጾርዓ ከተማ የሚኖር፣ ከዳን ወገን የሆነና ሚስቱም መካን የነበረች ማኑሄ የሚባል ...
20/08/2026

ቅዱስ ሚካኤል የልባችሁን መልካም መሻት ይሙላላችሁ!!!

መልአኩም በመሠዊያው ነበልባል ውስጥ ወደ ሰማይ ዐረገ🙏

በጾርዓ ከተማ የሚኖር፣ ከዳን ወገን የሆነና ሚስቱም መካን የነበረች ማኑሄ የሚባል አንድ ሰው ነበረ፡፡ የእግዚአብሔር መልአክም ለሴቲቱ ተገልጦ “እነሆ ትጸንሻለሽ፤ አሁንም ተጠንቀቂ፤ የወይን ጠጅን የሚያሰክርም ነገር አትጠጪ፥ ርኩስም ነገር አትብዪ፤ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ፤ ልጁም ከእናቱ ማኅፀን ጀምሮ ለእግዚአብሔር የተለየ ናዝራዊ ይሆናልና በራሱ ላይ ምላጭ አይድረስበት፤ እርሱም እስራኤልን ከፍልስጥኤማውያን እጅ ማዳን ይጀምራል” አላት። ሴቲቱም ለባልዋ የሆነውን ሁሉ ነገረችው፡፡ ማኑሄም የተላከው ሰው ዳግመኛ ወደኛ ይምጣ፤ ብሎ ወደ እግዚአብሔር ለመነ። እግዚአብሔርም የማኑሄን ድምፅ ሰማ፤ መልአኩም ሴቲቱ በእርሻ ውስጥ ተቀምጣ ሳለች እንደገና ተገለጠላት፤ ማኑሄ ግን አልነበረም።

ሴቲቱም ፈጥና ሮጠች፤ ባልዋንም ጠራችው። ማኑሄም “ከዚህች ሴት ጋር የተነጋገርህ አንተ ነህን? ቃልህ በደረሰ ጊዜ የልጁ ሥርዓት ምንድን ነው? አለው። መልአኩም ማኑሄን “ሴቲቱ ከነገርኋት ሁሉ ትጠንቀቅ፣ በማለት ለሴቲቱ የነገራትን ደገመለት፡፡ ማኑሔም “የፍየል ጠቦት እስክናዘጋጅልህ ድረስ፤ እባክህ ቆይ” አለው። መልአኩም የሚቃጠለውንም መሥዋዕት ማዘጋጀት ብትወድድ ለእግዚአብሔር አቅርበው” አለው። ማኑሄም “ነገርህ በደረሰ ጊዜ እንድናከብርህ ስምህ ማን ነው?” አለው፡፡ መልአኩ “ስሜ ድንቅ ነውና ለምን ትጠይቃለህ?” ብሎ መለሰለት። ማኑሄም የፍየሉን ጠቦትና የእህሉን ቍርባን ወስዶ በድንጋይ ላይ ለእግዚአብሔር አቀረበው።

መልአኩም በመሠዊያው ነበልባል ውስጥ ወደ ሰማይ ዐረገ፤ ማኑሄና ሚስቱም በግምባራቸው በምድር ተደፉ። ማኑሄም የእግዚአብሔር መልአክ መሆኑን አወቀ። ሶምሶን ከተወለደ በኋላም የእግዚአብሔርም መንፈስ በጾርዓና በኤሽታኦል መካከል ባለው በዳን ሰፈር ውስጥ ሊያነቃቃው ጀመረ። ይህ ሶምሶንና ወላጆቹን የረዳው ኃያሉ መልአክ ቅዱስ ሚካኤል ነው፡፡

ታላቁ አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ዛሬም ገዳማውያንን በተጋድሏቸው ሁሉ እየተራዳ አብሯቸው ይኖራል፡፡ ስለ ክርስቶስ ፍቅር ዓለምን ትተው ወጥተዋልና ጸሎታቸው ኃይልን ታደርጋለች፡፡ ገዳማቸውን እንደግፍ በዓታቸውን እናጽና፡፡

ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም

ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444

ለበለጠ መረጃ:- 09 38 64 44 44/0918077957

የጻድቁ አቡነ  አረጋዊ ረድኤት እና ምልጃ ከሁላችን ጋር ይሁን 🙏ጻድቁ ገድላቸውን የፈጸሙት በኢትዮዽያ ቢሆንም ሃገረ ሙላዳቸው የጥንቱ የሮም ግዛት የሆነችው ታናሽ እስያ ናት፡፡ አቡነ አረጋዊ...
20/08/2026

የጻድቁ አቡነ አረጋዊ ረድኤት እና ምልጃ ከሁላችን ጋር ይሁን 🙏

ጻድቁ ገድላቸውን የፈጸሙት በኢትዮዽያ ቢሆንም ሃገረ ሙላዳቸው የጥንቱ የሮም ግዛት የሆነችው ታናሽ እስያ ናት፡፡

አቡነ አረጋዊ ከዘጠኙ ቅዱሳን አንዱ ናቸው፡፡ ዘጠኙ ቅዱሳን ዘራቸው ከቤተ መንግስት ሲሆን ተወልደው ያደጉት በአንድ የሮም ግዛት ሥር በተለያየ ቦታ ነው፡፡ አንድ ያደረጋቸው መንፈስ ቅዱስ ነው፡፡ ቅዱሳት መጻሕፍትን በሚገባ ያጠኑት እነዚህ አበው ሰማያዊውን ክብር መርጠው ክርስቲያኖች በሚሳደዱበት በ5ኛው ክፍለ ዘመን በቅድሚያ አባ ዸንጠሌዎንና አቡነ አረጋዊ ከዚያም ሌሎቹ ከሮም ወደ ግብጽ በርሃዎች፣ በ470ዎቹ ዓ.ም አልዓሜዳ በኢትዮዽያ ነግሦ ሳለ በአረጋዊ መሪነት ወደ ኢትዮጵያ በምናኔ መጥተዋል፡፡

ንጉሡም በመልካም ተቀብሎ በአክሱም ቤተ ቀጢን ማረፊያ ቦታ ሰጣቸው፡፡ እነርሱም የግዕዝ ቋንቋ ተምረው እዛው አክሱም አካባቢ በአቡነ ሰላማ፣ በአብርሃ ወአጽብሐና በአቡነ ሙሴ ቀዳማዊ የተቀጣጠለውንና በተወሰነ መንገድ ተቀዛቅዞ የነበረውን ክርስትና እንደገና አቀጣጠሉት፤ ለዓመታትም ወንጌልን ሰበኩ በርካታ መጻሕፍትንም ተረጎሙ፡፡ በኋላም የየራሳቸው የምናኔ ቦታ በመምረጥ ወንጌልን እየሰበኩና ስለሀገራችን እየጸለዩ ኖረዋል፡፡

አባታችን አቡነ አረጋዊ በደብረ ዳሞ ታላቅ ገድል ፈጽመዋል፡፡ ማኅሌታዊው ቅዱስ ያሬድና አፄ ገብረ መስቀልም ወዳጆቻቸው ነበሩ፡፡ ጻድቁ ተጋድሏቸውን ፈጽመው በተወለዱ በ99 ዓመታቸው ተሰውረው ብሔረ ሕያዋን ገብተዋል፡፡
ጌታም የምሕረት ቃል ኪዳን ሰጥቷቸዋል፡፡ ጥር 14ም ጻድቁ የተወለዱበት ቀን ነው፡፡

መናንያንና ገዳማውያን የዓለምን ክብር ንቀው ስለ ክርስቶስ ፍቅር ብዙ ዋጋ ከፍለዋል፡፡ የወንጌል ብርሃን እንዲበራ፣ ትልቅ ሥራ ሰርተዋል፡፡ ጸሎታቸው አሁንም ተአምር ያደርጋል፡፡ ገዳማቸውን እንደግፍ በዓታቸውን እናጽና፡፡

ድጋፍ ለማድረግ፦ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም

ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444

የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444

ቅዱስ ሩፋኤል ከክፉ ነገር ሁሉ ይከልለን፤ ምልጃ እና ረድኤቱም አይለየን🙏ቊጥሩ ከሰባቱ ሊቃነ መላእክት ሲሆን፤ “ሩፋ” ማለት ሐኪም፤ ኤል ማለት እግዚአብሔር ማለት ሲኾን ሩፋኤል ማለት “እግዚ...
19/08/2026

ቅዱስ ሩፋኤል ከክፉ ነገር ሁሉ ይከልለን፤ ምልጃ እና ረድኤቱም አይለየን🙏

ቊጥሩ ከሰባቱ ሊቃነ መላእክት ሲሆን፤ “ሩፋ” ማለት ሐኪም፤ ኤል ማለት እግዚአብሔር ማለት ሲኾን ሩፋኤል ማለት “እግዚአብሔር ሐኪሜ ነው” ማለት ነው፡፡
ቅዱስ ኤጲፋንዮስም በመጽሐፈ አክሲማሮስ “በራማ ሰማይ የሚገኘውን ሁለተኛውን ዐሥሩን ነገድ መናብርት ሲላቸው አለቃቸው ቅዱስ ሩፋኤል ነው፤ እነዚህም ረቂቅ የሆነ የመብረቅ ጋሻ የእሳት ጦር ይዘው ከነፋስ ይልቅ የፈጠኑ ሲሆኑ በራማ በሁለተኛው ክፍል ላይ አስፍሯቸዋል፡፡

ቅዱስ ሩፋኤል ነገደ መናብርት የሚባሉትን ራማ በሚባለው ሰማይ የሚኖሩትን ነገደ መላእክት የሚመራቸው ናቸው፡፡ አባ ጊዮርጊስም በሰዓታቱ “ጽርሐ አርያም አዳራሹ፤ የትጉሃን መኖሪያ ቦታው የሚኾን እግዚአብሔር ቅዱስ፣ ቅዱስ፣ ቅዱስ ተብሎ በአንድነት በሦስትነት ይመሰገናል፤ ካህናተ ሰማይ በዙሪያው ይቆማሉ፤ በዙፋኑ ፊት እየሰገዱ አክሊሎቻቸውን ያወርዳሉ፤ እሳትነቱ በሚበርቅ፣ በሚል ጊዜ እንዳይመታቸው ይንቀጠቀጣሉ” ይላል፡፡

ቅዱስ ሩፋኤል ከሚመራው ከዚህ ነገድ 24ቱ ካህናተ ሰማይ ወጥተዋል፡፡” ይለናል፡፡ በመጽሐፈ ሄኖክ 6÷3 ላይም “በሰው ቁስል ላይ የተሾመ ከከበሩ መላእክት አንዱ ቅዱስ ሩፋኤል ነው” ተብሏል፡፡ ሊቁ ቅዱስ ባስልዮስም “በፊቱ የሚቆሙ የመላእክት ሰራዊትም ሁሉ ጩኸው ያመሰግኑታል፤ የመላእክት አለቆችም ለማይታይ ለባለዚህ ስም ዘንበል ብለው ይሰግዳሉ፤ ዙፋኑን የሚሸከሙ አርባዕቱ እንስሳ ጩኸው ያመሰግኑታል፤ ዕጣንን የተመሉ የወርቅ ማዕጠንት በእጆቻቸው ያለ ሃያ አራቱ ካህናተ ሰማይ ይኸውም የቅዱሳን ጸሎት ነው እስከ ዘላለሙ ሕያው በሆነው ፊት የሚቀበለው መሥዋዕት አድርገው ወደ ላይ ያሳርጋሉ” በማለት አስተምሯል፡፡

ቅዱስ ሩፋኤል ፈታሔ ማኀፀን ወሰፋድል። መወለድ መንፈሳዊ። ወሐኪም ሰማያዊ ይባላል። የወላድ ማኀፀን እንዲፈታ በእግዚአብሔር ስለተሾመ አዋላጅ ብትኖርም ባትኖርም ቅዱስ ሩፋኤል በዚያ አይታጣም፡፡ በተለይ በባላገር ያሉ ሴቶች በምጥ ጊዜ ሁሉ መልክአ ሩፋኤል በአንገታቸው ያነግታሉ፣ ይጸልያሉ፣ የተጸለየበትንም ጸበል ይጠጣሉ፤ በፍጥነትም ይወልዳሉ። በየወሩ በ13 ቀን መታሰቢያ በዓሉ የሚከበር ሲሆን ጳጉሜ 3 ደግሞ ዓመታዊ በዓሉ ነው፡፡ የቅዱስ ሩፋኤል በረከትና ረድኤቱ አይለየን፤ ምልጃው ይጠብቀን፡፡ ገዳማውያንም ይህን ተራዳኢነቱን በመታመን ዘወትር በጸሎታቸው ይጠሩታል፡፡ ገዳማቸውን በመደገፍና በዓታቸውን በማጽናት የበረከታቸው ተሳታፊ እንሁን፡፡

ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም

ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444

የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444

“ከሚቀበል ይልቅ የሚሰጥ ብፁዕ ነው”🙏 ውዳሴ ማርያምን የደረሰው ቅዱስ ኤፍሬም በራዕይ ተመርቶ ወደ ቅዱስ ባስሊዮስ ዘቂሳርያ ይሔዳል፡፡ሲሔድ ግን በሰዋዊው ዓይን እንዳሰበው አይነት አባት ሆኖ...
19/08/2026

“ከሚቀበል ይልቅ የሚሰጥ ብፁዕ ነው”🙏

ውዳሴ ማርያምን የደረሰው ቅዱስ ኤፍሬም በራዕይ ተመርቶ ወደ ቅዱስ ባስሊዮስ ዘቂሳርያ ይሔዳል፡፡

ሲሔድ ግን በሰዋዊው ዓይን እንዳሰበው አይነት አባት ሆኖ አላገኘውም፡፡ በወርቅ አትሮንስ ላይ የወርቅ ወንጌል አዘርግቶ፣ ካባ ላንቃ ለብሶ፣ ኩፋር ጠምጥሞ፣ የወርቅ መስቀል ይዞ በሐር መነሳንስ አጊጦ ቢያየው ስጋዊ ይመስላል ሲል በልቡ ታዘበው፡፡ እርሱ ግን ይህን ሁሉ ጌጥና ውበት የሚደርበው ስለ ክብረ ወንጌል ነው እንጂ ከዚህ ሁሉ ስር በውስጥ የሚለብሰው ማቅ ነበር፡፡
ቅዱስ ኤፍሬም ስለ ቅዱስ ባስሊዮስ ዘቂሳርያ የተሰማው ነገር ስህተት እንደሆነ የገባው ጥቂት ቆይቶ ባያቸው ምልክቶች ነበር፡፡

በመጀመሪያ ሲያስተምር ከአፉ የሚወጣው ቃል እንደ እሳት መንፈስ እየሄደ ሆኖ ሕዝቡን ሲዋሀዳቸው ያያል፣ ሁለተኛ ተሕዋሲያን (ዝንቦች) በልብሱ ላይ ሲያርፉ እንደ ቆሎ ሲረግፉ ያያል፡፡ ምክንያቱም አባታችን ቅዱስ ባስሊዮስ ከአስሩ የቤተ ክርስቲያን ማዕረጋት “ከዊነ እሳት” ወይም እሳትነት የሚባለው ደረጃ ላይ ደርሶ ነበርና፡፡ ሶስተኛ ከዚያ በፊት የማይተዋወቁ ቢሆንም “ኤፍሬም ሶሪያዊ፣ ኤፍሬም ለብሐዊ” ብላችሁ ጠርታችሁ አምጡልኝ ብሎ ሰው ሰዶ ያስጠራዋል፡፡

ገዳማዊያን እናቶች ከጸሎት መልስ የሚቀመስ እህል እንኳን በሌለበት እጅግ አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ሆነው ዛሬም ስለእኛ ድኅነትና ሰላም ዘወትር ይጸልያሉ፡፡ “ቤተ ቅዱሳን ፈትለወርቅ ማርያም የእናቶች ገዳም” ቤተ መቅደሱ በከባድ ንፋስና ዝናብ ፈርሶ መነኮሳቱም በድርቅና በርሃብ ፈተና ውስጥ ናቸው።

“ከሚቀበል ይልቅ የሚሰጥ ብፁዕ ነው” (የሐዋርያት ሥራ 20፥35) እንዲል ቃሉ ለመነኮሳቱ ምግብና መሠረታዊ ፍላጎቶች ለማሟላት የድጋፍ እጃችንን እንዘርጋላቸው፤የበረከቱም ተካፋይ እንሁን፡፡

ድጋፍ ለማድረግ፡- ቤተ ቅዱሳን ፈትለወርቅ ማርያም የእናቶች ገዳም፡-

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

1000766349227

ወይም

አቢሲንያ ባንክ

262281132

የገዳሙ ስልክ ቁጥር፡- 0944672222 ወይም 0916106921

እንኳን ለብርሃነ መለኮቱ በዓለ ደብረ ታቦር (ቡሄ) አደረሳችሁ፤ አደረሰን🙏ጌታችን ምሥጢረ መለኮቱን የገለጠበት ብርሃንና በረከት ዘወትር ከሁላችን ጋር ይሁን! በዓለ ደብረ ታቦር ከጌታችንና ከ...
19/08/2026

እንኳን ለብርሃነ መለኮቱ በዓለ ደብረ ታቦር (ቡሄ) አደረሳችሁ፤ አደረሰን🙏

ጌታችን ምሥጢረ መለኮቱን የገለጠበት ብርሃንና በረከት ዘወትር ከሁላችን ጋር ይሁን!

በዓለ ደብረ ታቦር ከጌታችንና ከመድኃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ 9ኙ ዓበይት በዓላት አንዱ ሲሆን፤ በየዓመቱ ነሐሴ 13 ቀን በታላቅ መንፈሳዊ ሥርዓትና ደስታ ይከበራል። “ቡሄ” ማለት “ብራ፣ ገላጣ ወይም ብርሃን” ማለት ነው። ይህ ስያሜ የተሰጠው ጌታችን በታቦር ተራራ ላይ መለኮታዊ ክብሩንና ብርሃኑን የገለጠበትን ዕለት በማስመልከት ነው።

ቅዱስ ወንጌል እንደሚያስተምረን፤ ጌታችን ሦስቱን ደቀ መዛሙርት (ጴጥሮስን፣ ያዕቆብንና ዮሐንስን) ይዞ ወደ ደብረ ታቦር ተራራ ወጣ። በዚያም መልኩ በፊታቸው ተለወጠ፤ ፊቱ እንደ ፀሐይ በራ፤ ልብሱም እንደ ብርሃን ነጭ ሆነ። ከብሉይ ኪዳን ወገን ነቢያት የሆኑት ቅዱስ ሙሴና ቅዱስ ኤልያስ መጥተው ከጌታ ጋር ሲነጋገሩ ታይተዋል። ይህም ሞት የሰው ልጅ መጨረሻ እንዳልሆነና የሕያዋንና የሙታን አምላክ ክርስቶስ መሆኑን ያስረዳናል። ነቢየ እግዚአብሔር ኢሳይያስም “ኑ ወደ እግዚአብሔር ተራራ፣ ወደ ያዕቆብ አምላክ ቤት እንውጣ” በማለት ይህንን ቅዱስ ተራራ አስቀድሞ ትንቢት ተናግሮለታል (ኢሳ 2፥3)።

በዚህ ታላቅ ምሥጢር ወቅት ከደመና ውስጥ “የምወደው ልጄ ይህ ነው፤ እርሱን ስሙት” የሚል የአብ ድምፅ ተሰምቷል። ሐዋርያትም ከድምፁ ግርማ የተነሳ ደንግጠው በግንባራቸው ወድቀዋል። ዛሬ ሕፃናት ጅራፍ የሚያጮኹት ያንን የእግዚአብሔር አብን የድምፅ ግርማ ለማስታወስ ነው። በዓሉ ባህላዊና ማኅበራዊ ውበትም አለው፤ እናቶች ለሕፃናት “ሙልሙል ዳቦ” ያዘጋጃሉ፤ እረኞች በብርሃኑ ምሳሌ ችቦ ያበራሉ። በአገራችን ክረምቱና ጭጋጉ አልፎ፣ ወደ ማራኪው የበልግና የመፀው ብርሃን መሸጋገሪያችን በመሆኑ “ቡሄ ከዋለ የለም ክረምት” ይባላል።

የዚህ ታላቅ በዓል ባለቤትና የብርሃን ምንጭ የሆነው አምላካችን በረከቱንና ረድኤቱን ያድለን። ገዳማውያን አባቶቻችንና እናቶቻችን ይህንን መለኮታዊ ብርሃን በጸሎታቸውና በትሕትናቸው እያሰቡ ዘወትር በበዓታቸው ይማጸናሉ። እኛም በዚህ በተቀደሰ ዕለት የጌታችንን ታሪክና በዓል እያሰብን፣ ገዳማትን በመደገፍና በዓታቸውን በማጽናት የበረከታቸው ተሳታፊ እንሁን።

ሙትአንሳ ማር ቅዱስ ሚካኤል አንድነት ገዳምን ለመደገፍ፦

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ (CBE)
CBE: 1000442598391

አቢሲኒያ ባንክ (BoA)
Abyssinia: 141029444

የገዳሙ ስልክ ቁጥሮች፦
📞 0918077957
📞 0938644444

እንኳን ለቅዱስ ሚካኤል ወርሃዊ በዓል አደረሳችሁ፤ አደረሰን🙏 የቅዱስ ሚካኤል ምልጃ እና ረድኤት አይለየን!!!ቅዱሳት መጻሕፍት እንደሚነግሩን የመላእክት ሁሉ አለቃቸው ቅዱስ ሚካኤል በፈጣሪው ...
18/08/2026

እንኳን ለቅዱስ ሚካኤል ወርሃዊ በዓል አደረሳችሁ፤ አደረሰን🙏 የቅዱስ ሚካኤል ምልጃ እና ረድኤት አይለየን!!!

ቅዱሳት መጻሕፍት እንደሚነግሩን የመላእክት ሁሉ አለቃቸው ቅዱስ ሚካኤል በፈጣሪው ኃይል ብዙ ድንቆችን ሠርቷል፡፡ ከመጀመሪያው ሰው አዳም ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ አምነው ለሚጠሩት ረዳት ነው፡፡ በመዝሙር 33÷7 እደተጻፈው ዘወትርም ያድናቸው ዘንድ በሚፈሩት ሰዎች ዙሪያ ይሠፍራል፡፡ እግራችን እንዳይሰናከል ዘወትር ይጠብቀናል፡፡ የቅዱስ ሚካኤል ስሙ ድንቅ ነው፡፡ ነቢዩ ቅዱስ ዳንኤል እንደተናገረው ከእርሱ በቀርስ የሚያጸና ማን አለና! ለሕዝቡም የሚቆም ታዳጊ መልአክ ነው፡፡ ይህ ድንቅ መልአክ ከሺህ ዓመታት በፊት በሮም ከተማ ይህንን ድንቅ ተአምር መስከረም ዘጠኝ ቀን መሥራቱን ቤተ ክርስቲያን ትመሰክራለች፡፡ በቀድሞው የሮም ግዛት 'ሩፍምያ' የምትባል ከተማ ነበረች፡፡

ይህች ከተማ በእምነታቸው ጠንካሮች የሆኑ ጥቂት ክርስቲያኖችና በርካታ ኢአማንያን ተቀላቅለው የሚኖሩባት ናት፡፡ በተለይ ደግሞ የቤተ ክርስቲያኗ መጋቢ ፍጹም የእምነት ሰው ነበር፡፡ በቦታው የቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን በመኖሩም ብዙ ተአምራት ይደረግ ስለነበር ተበለጥን የሚል ስሜት የተሰማቸው አሕዛብ “ዮናናውያን”ይሕንን ቤተ ክርስቲያን ለማጥፋት ተማማሉ፡፡ በቀጥታ ሔደው ቢያፈርሱት ወይም ቢያቃጥሉት በሕግ እንደሚጠየቁ ያውቃሉና በሥጋዊ ጭንቅላታቸው ዘዴ ያሉትን መከሩና ወሰኑ፡፡ በከተማዋ ዳር የሚያልፍ አንድ ትልቅ ወንዝ አለ፡፡ በሞላ ጊዜ ያገኘውን ሁሉ ጠርጐ የሚወስድም ነበር፡፡ ታዲያ ክፋተኞቹ ሌሊት ሌሊት እየተነሱ የሚሔድበትን መንገድ ዘግተው ወደ ቤተ ክርስቲያኑ አቅጣጫ መንገድ ከፈቱለት ከቀናት በኋላ ከባድ ዝናብ በዚህች ቀን ጣለ፡፡
ወንዙ ትልቅ ነውና ያገኘውን ሁሉ እያገላበጠ ደረሰ፡፡ በወቅቱ በቅዱሱ መልአክ ቤተ መቅደስ ውስጥ ከመጋቢው በስተቀር ሰው አልነበረምና አስፈሪ ድምጽ ሰምቶ ሲወጣ ወንዙ እየደነፋ ወደ ቤተ ክርስቲያኑ እየመጣ ነው፡፡ ከደቂቃዎች በሁዋላ ቤተ ክርስቲያኑ እንዳልነበረ እንደሚሆን የተረዳው መጋቢ በታላቅ ድንግጤ ውስጥ ወደቀ፡፡ እርሱ አንድ ተስፋ ነበረውና ወደ ውስጥ ገብቶ በመላዕክት አለቃ በቅዱስ ሚካኤል ምስለ ስዕል ፊት ወድቆ ተማጸነ፡፡ ታላቁ ወንዝ ቤተ ክርስቲያኑን ጠርጎ የሚወወስደው ከሆነም የሚሆነውን ነገር ለመቀበልና ከዚያም ላለመውጣትም ወሰነ፡፡ ትንሽ ቆይቶ በታላቅ ኃይል ወንዙ ደረሰ፡፡ በዚህ ጊዜ የመላዕክት ሁሉ አለቃቸው ለጠራውም ፈጥኖ የሚደርሰው ቅዱስ ሚካኤል በግርማ ከሰማይ ወርዶ በወንዙ ፊት ቆመ፡፡

መጋቢውንም "ጽና አትፍራ፣ እኔ ካንተ ጋር ነኝና" ብሎት በያዘው የብርሃን በትረ-መስቀል መሬትን አንድ ጊዜ መታት፡፡ በዚያች ቅጽበትም ትልቅ ሸለቆ ተፈጠረ፡፡ በአስፈሪ ሁኔታ ሲመጣ የነበረው ወንዝም በሸለቆው ውስጥ አልፎ ሔደ፡፡ የሚገርመው ነገር የመላዕክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ሸለቆው የተፈጠረው ከቤተ ክርስቲያኑ በታች መሆኑ ነው፡፡ ቤተክርስቲያኑ ግን ጸንቶ ቆመ፡፡ መጋቢውም እግዚአብሔርንና ቅዱስ ሚካኤልን አመሰገነ፡፡ ቅዱስ ሚካኤል መጋቢውን ባርኮት በክብር ዐረገ፡፡ በማግስቱ ክርስቲያኖቹ ይህንን አይተው ደስ አላቸው፣ መልአኩንም አከበሩት፣ አሕዛብ ግን አፈሩ፡፡

ራሳቸውን ለእግዚአብሔር ያስገዙ ገዳማውያንና ቅዱሳን ጸሎታቸው ኃይልን ታደርጋለች፡፡ ገዳማቸውን እየደገፍን በዓታቸውን እያጸናን የበረከታቸው ተሳታፊ እንሁን፡፡

ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም

ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444

የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444

ቅድስት ኪዳነ ምህረት የልባችሁን መልካም መሻት ትሙላላችሁ!!!በአንቺ አማላጅነት፣በልጅሽ ምሕረት የታምንሁ ነኝእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነቷና ተራዳኢነቷ በብዙ መልኩ ዛሬም ድረ...
18/08/2026

ቅድስት ኪዳነ ምህረት የልባችሁን መልካም መሻት ትሙላላችሁ!!!

በአንቺ አማላጅነት፣በልጅሽ ምሕረት የታምንሁ ነኝ

እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነቷና ተራዳኢነቷ በብዙ መልኩ ዛሬም ድረስ ያልተለየን የዘለዓለም ቃል ኪዳን የተገባላትና በቃል ኪዳኗም አማልዳ የምታስምር ናት፡፡ በመዝሙር 88÷3 “ከመረጥኳቸው ጋር ቃል ኪዳን አደረግሁ” ተብሎ እንደተጻፈው ለመረጣቸው ቃል ኪዳን የሰጣቸው አምላካችን እግዚአብሔር ማደሪያው ትሆን ዘንድ ለመረጣት ለእናቱ ለቅድስት ድንግል ማርያም ከሌሎች ቅዱሳን በተለየ ይህን ቃል ኪዳን አብዝቶ ሰጥቷታል፡፡ ”መታሰቢያዋን የሚያደርግ፣ ስሟን የሚጠራ፣ ለድሆችና ለችግረኞች እስከ ቀዝቃዛ ውኃ የሚሰጥ” የአማላጅነት የእናትነት ቃል ኪዳን በነፍስም በስጋም ይጠብቀዋል፡፡ ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት “በወርቅ ልብስ ተጎናጽፋና ተሸፋፍና ንግሥቲቱ በቀኝህ ትቆማለች” ሲል በመዝሙር 44÷9 እንደገለጸው ከፍጥረት ሁሉ በላይ ነችና በቀኙ ቆማ በተሰጣት ቃልኪዳን ታማልደናለች፡፡

የዐሥራት ልጆቿ እኛ ክርስቲያኖችም ዘወትር “ንጽሕት ድንግል ማርያም የታመነች አምላክን የወለደች ናት። ለሰዎች ልጆችም የምሕረት አማላጅ ናት እንላለን። የቅዱስ ኤፍሬምን አንደበት አንደበታችን አድርገንም ኃጥአታችንን ያስተሠርይልን ዘንድ ወደ ልጅሽ ወደ ክርስቶስ ለምኝልን” እያልን እናመሰግናታለን እንለምናታለን። ከአባታችን አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ ጋርም በእሑድ አርጋኖን “ቅድስት ድንግል ማርያም ሆይ! እታመንሻለው፤ ከተሠወረው መከራ፣ በግልጽ ከሚመጣብኝ ጥፋት ሁሉ በዚህ ዓለም እንድታድኚኝ። በሚመጣውም ዓለም ከገሃነመ እሳት ጥርስ ማፋጨት ጽኑ ለቅሶም ካለበት፣ ከሚያስጨንቅ መቅሠፍትም ትሠውሪኝ ዘንድ፣ እኔም በአንቺ አማላጅነት፣ በልጅሽ ምሕረት የታምንሁ ነኝ። በፈረሰኞች ሰልፍ በሠረገላም መንኮራኩር የምታመን አይደለሁም በአንቺና በልጅሽ እታመናለው እንጂ።” እያልን እንማጸናታለን፡፡ እናታችን ቅድስተ ቅዱሳን ጸሎታችንን ትስማን

እኛም የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ሥጋዋ ከሞትና መቃብር መለየትና ማረግን አስመልክተን በምንጾመው ጾመ ፍልሰታ ለተቸገሩት ድጋፍ በማድረግ የበረከት ስራን እንስራ።በከባድ ንፋስና ዝናብ ምክንያት ቤተ መቅደሱ ለፈረሰበት “ቤተ ቅዱሳን ፈትለወርቅ ማርያም የእናቶች ገዳም” ድጋፍ በማድረግ ቤተ መቅደሱን መልሰን እንስራ፤በድርቅና በርሃብ በከባድ ፈተና ውስጥ ለሚገኙት መነኮሳት እንድረስላቸው።ለመነኮሳቱ ምግብና መሠረታዊ ፍላጎቶች ለማሟላት በአቅማችን እንረባረብ። በመስጠት ነፍሳችንን ደስ እናሰኛት፡፡

ድጋፍ ለማድረግ፡- ቤተ ቅዱሳን ፈትለወርቅ ማርያም የእናቶች ገዳም

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፡- 1000766349227

አቢሲንያ ባንክ ፡- 262281132

ለበለጠ መረጃ:- 0944672222 ወይም 0916106921

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ZimareTube posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Place Of Worship

Send a message to ZimareTube:

Shortcuts

Share