06/08/2025
እንኳን ለእመቤታችን ጾም 🔔ጾመ🎤ፍልሰታ🔔 በሰላም አደረሳችሁ።የበረከት ጾም ያድርግልን ሕዝበ ክርስቲያን ።
1, ጾመ ፍልሰታን ማን ጾማት ?
2, ጾመ ፍልሰታን ለምን እንጾማለን ?
የ2014 ዓ.ም ጾመ ፍልሰታ እሁድ ነሐሴ 1 ይያዛል። ፍልሰታ በ ዋናነት የእመቤታችን ጾም ሲሆን ሐዋርያት የእመቤታችን እረገቷን ትንሳኤዋን ለማየት 2 ሱባኤ ይዘው ጾመውታል።
"ፍልሰታ" ቃሉ የግዕዝ ሲሆን ትርጓሜው ፈለሰ,ተነጠለ, ተለየ ተሰደደ ተዘዋወረ ተካፈለ ማለት ነው። አንድ ላይ ሲነበብ ደግሞ"ፍልሰታ ለ ማርያም" እያልን እንጠራታለን ይህም የእመቤታችንን በድነ ስጋዋ መፍለስ ማለት ነው።
አንድም እመቤታችን ከሚያልፈው ዓለም ወደ ማያልፈው ዓለም ከመቃብር የወጣችበትን የተነሳችበት ቀን ማለት ነው። ወይንም ደግሞ እመቤታችን ከስጋዊው ዓለም ወደ መንፈሳዊ ዓለም የተሸጋገረችበት ቀን ማለት ነው።
ፍልሰታ ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ መፍለስ (መሄድ)። ያመለክታል ። እመቤታችን ካረፈች በኋላ የስጋዋን መፍለስ አስመልክቶ ሐዋርያት የእመቤታችን ስጋ የት እንደተቀበረ አላወቁም ነበርና እግዚአብሔር አምላክ የእመቤታችንን ስጋ እንዲገልጥላቸው የጾሙት ጾም ነው።
ሐዋርያት ሁለት ሱባኤ ጾመው ጌታችን የእመቤታችንን በድነ ስጋዋን ሰጥቷቸዋል።ትንሳኤዋን እና እርገትዋን በማየት ታላቅ በረከት ያገኙበት ጾም ነው።
ቅዱስ ዮሐንስ እመቤታችንን እንዲጠብቃት ከተደረገ በኋላ ሐዋርያት የእመቤታችን ነገር እንዴት ነው ብለው በጠየቁት ጊዜ ዮሐንስም እመቤታችንማ በገነት በእፀ ሕይወት ስር ናት አላቸው።
በዚህን ጊዜ ሐዋርያት እመቤታችን ከመቃብር መነሳቷን ማረጓን ማየት አለብን እንዴት ዮሐንስ አይቶ እኛ ሳናይ እንቀራለን በሚል መንፈሳዊ ቅናት ተነሳስተው ነሐሴ 1 በእለተ ሰኞ ቀን ሁለት(7) ሱባኤን ያዙ ።በአስራ አራተኛው ቀን ጌታችን የእመቤታችንን ስጋ አንስቶ ሰጣቸውና በጌቴ ሴማኒ ቀበሯት።
እመቤታችን በ 64 አመቷ ጥር 21 ቀን አርፋ ነሐሴ 14 ቀን ተቀብራለች።ይኁንና ሐዋርያት ቢቀብሯትም ትንሳኤዋንና እርገትዋን አላዩም ነበር። ትንሳኤዋንና እርገቷን ያየው ሲቀብሯት ያላየው ሐዋርያው ቶማስ ነው።
ሐዋርያው ቶማስም እንዲያስተምር ወደ ሕንድ ሀገር ዕጣ ደርሶት ሄዶ ነበርና አስተምሮ በደመና ሲመለስ ነሐሴ 16 ቀን እመቤታችን ስታርግ እያለ በደመና ሕዋ ላይ ተገናኙ ለምልክት ይሆነው ዘንድ ሰበኗን ሰጠችው።
ጾመ ፍልሰታ ከ 7ቱ የአዋጅ አፅዋማት አንዷ ስትሆን የአመቱ የመጨረሻ የአዋጅ ጾም ናት። ስለኾነም ምዕመናን በየአመቱ ጾመ ፍልሰታን ከልጅ እስከ አዋቂ ሳይል ንቅል ብለው በጾም በፀሎት በመቁረብ በጋራ በፍቅር በደስታ የእመቤታችንን በረከት ያፍሳሉ ይቋደሳሉ።
በእውነቱ በዚህ ፆም እመቤታችን የሀገራችን የሐይማኖታችን የቤተክርስቲያናችን የህዝባችንን ሰላም ወደ ቀደመው ሰላም
ትመልሰልን።
ጾሙን ጾመን እቀድሰን ቆርበን ለትንሳኤዋ ብርሀን በሰላም ያድርሰን።
✞✞✞ የበረከት ጾም ይሁንልን ✞✞✞