26/05/2026
የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተ ክርስቲያን የልማት ኮሚሽን አገር አቀፍ የአንድነት ጊዜ አከናወነ
***************************
የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተ ክርስቲያን የልማት ኮሚሽን አገር አቀፍ ዓመታዊ የመሪዎችና የሠራተኞች የአንድነት ጊዜ ፕሮግራም በድምቀት ተከናወነ።
ከግንቦት 13 - 15 ቀን 2018 ዓ.ም በሀዋሳ ከተማ በተደረገው በዚህ ፕሮግራም ላይ የቤተ እምነቱ ፕሬዚዳንት ፓስተር ላኮ በዳሶ፣ የልማት ኮሚሽኑ ኮሚሽነር ፓስተር ብርሃኑ ታረቀኝ፣ የልማት ኮሚሽኑ የቦርድ አባላት፣ የቤተ ክርስቲያን መሪዎች፣ ሠራተኞች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
በፕሮግራሙ ላይ የቀረቡ ዋና ዋና ትምህርቶችና መልዕክቶች
«የእግዚአብሔር ቃል ገዥ ሥፍራን መያዝ»
በነብይ የሽጥላ መቺ
መጽሐፍ ቅዱስን መሠረት በማድረግና መንፈስ ቅዱስን በመደገፍ ገዥ ሥፍራን መቆጣጠር እንደሚቻል ያስተማሩ ሲሆን፣ ለጉባኤውም በሰፊው ጸልየዋል።
የመንፈስ ቅዱስ ታሪካዊና ወቅታዊ ሥራ
ፓስተር ላኮ በዳሶ (የቤተ እምነቱ ፕሬዚዳንት)
የሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ ሁለትን ከታሪካዊ ዳራው በመነሳት ያብራሩ ሲሆን፣ ዛሬም እንደ ጥንቱ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ መንፈስ ቅዱስ በኃይል እንደሚሠራና እንደሚገለጥ አፅንኦት ሰጥተው አስተምረዋል።
«ሁለንተናዊ አገልግሎት»
ፓስተር ብርሃኑ ታረቀኝ (የልማት ኮሚሽኑ ኮሚሽነር)
ለተሰበሰበው ጉባኤ የሁለንተናዊ አገልግሎትን አስፈላጊነትና ምንነት በስፋት አስገንዝበዋል።
የአምልኮና የዝማሬ አገልግሎት
የአምልኮ አገልግሎት፦ በመርሃ ግብሩ በነበረው የጸሎትና የአምልኮ ጊዜ ላይ ዘማሪ ታማኝ ሙሉነህ በምስጋናና በዝማሬ ጉባኤውን አገልግሏል።
በተጨማሪም በፕሮግራሙ ላይ የተለያዩ መርሐ ግብሮች የተከናወኑ ሲሆን፣ የኮሚሽኑን ሥራ ይበልጥ ውጤታማ ለማድረግ የሚያግዙ አስተዳደራዊ ጉዳዮች ተነስተው ውይይት ተደርጎባቸዋል። በቀጣይ መከናወን ለሚገባቸው ሥራዎችም አቅጣጫዎችና ማሳሰቢያዎች ተሰጥተው ፕሮግራሙ በስኬትና በሰላም ተጠናቋል።