አዲስ ፍጥረት New Creation

አዲስ ፍጥረት New Creation any man be in Christ he is a new creation . . .ማንም በክርስቶስ ቢሆን አዲስ ፍጥረት ነው

...Therefore if any man [be] in Christ, [he is] a new creature፡ old things are passed away; behold, all things are become new. (2cor 5፡17)
ስለዚህ ማንም በክርስቶስ ቢሆን አዲስ ፍጥረት ነው፤ አሮጌው ነገር አልፏል፤ እነሆ፥ ሁሉም አዲስ ሆኗል።...
(፪ኛ ቆሮንቶስ ፭፥፲፯)
� � �

የጸና ግንብ ነው የእግዚአብሔር ሥምወደ እርሱ እሮጣለሁ አሃ ከፍ ከፍ እላለሁ ኦሆሆወደ እርሱ እሮጣለሁ አሃ ከፍ ከፍ እላለሁ ኦሆሆ (፪x)ድል ድል ይሸተኛል ኦሆሆ አሃሃማሸነፍ ማሸነፍ ኦሆሆ ...
14/01/2022

የጸና ግንብ ነው የእግዚአብሔር ሥም
ወደ እርሱ እሮጣለሁ አሃ ከፍ ከፍ እላለሁ ኦሆሆ
ወደ እርሱ እሮጣለሁ አሃ ከፍ ከፍ እላለሁ ኦሆሆ (፪x)

ድል ድል ይሸተኛል ኦሆሆ አሃሃ
ማሸነፍ ማሸነፍ ኦሆሆ አሃሃ
ይህንን ተራራ ኦሆሆ አሃሃ
ሜዳ አድርጌው ልለፍ ኦሆሆ አሃሃ

ድል ድል ይሸተኛል ኦሆሆ አሃሃ
ማሸነፍ ማሸነፍ ኦሆሆ አሃሃ
ይህንን ተራራ ኦሆሆ አሃሃ
ሰባብሬው ልለፍ ኦሆሆ አሃሃ

ይታየኛል ይታየኛል ብዙ ነገር
ያየሁትን አየዋለሁ አንድም አይቀር (፪x)

ጨካኝ አድርጐኛል ጠላቴ
ጀግና አድርጐኛል አባቴ
አልበገርም ለፍርሃት
አልፌያለሁኝ በእሳት

ለጌታዬ እኔ አልፈራም
ለኢየሱስ እኔ አልፈራም
ለአምላኬ እኔ አልፈራም
በፍፁም እኔ አልፈራም

ጻድቅ እንደ አንበሳ
ያለ ፍርሃት ይኖራል
ኃጥእ ግን ፈሪ ነዉ
ሳይነኩት ይሸሻል (፪x)

የጸና ግንብ ነው የእግዚአብሔር ሥም
ወደ እርሱ እሮጣለሁ አሃ ከፍ ከፍ እላለሁ ኦሆሆ
ወደ እርሱ እሮጣለሁ አሃ ከፍ ከፍ እላለሁ ኦሆሆ

ኧረ ተነሥ ጀግናው ተነሥ
ወንዱ ተነሥ የእቃ ጦርህን ሁሉ ልበስ
ኧረ ተነሽ ጀግና ተነሽ
ሴቷ ተነሽ የእቃ ጦርሽን ሁሉ ልበሽ

ማነው ጀግና ማነው ደፋር
ጐልያድን የሚዘርር
እኔ አለሁኝ ፣ እኔ አለሁኝ
ምድር/አገር ሁሉ አይሸበር (፪x)

ጠላቴ/ሰይጣን እንዳይተወኝ እየተነኮሰኝ
ይብሱን ኃይለኛ ኃይለኛ አደረገኝ (፪x)

ኃይለኛ አደረገኝ ፣ ኃይለኛ አደረገኝ

ድል ድል ይሸተኛል ኦሆሆ አሃሃ
ማሸነፍ ማሸነፍ ኦሆሆ አሃሃ
ይህንን ተራራ ኦሆሆ አሃሃ
ሜዳ አድርጌው ልለፍ ኦሆሆ አሃሃ

ድል ድል ይሸተኛል ኦሆሆ አሃሃ
ማሸነፍ ማሸነፍ ኦሆሆ አሃሃ
ይህንን ተራራ ኦሆሆ አሃሃ
ሰባብሬው ልለፍ ኦሆሆ አሃሃ

ይታየኛል ይታየኛል ብዙ ነገር
ያየሁትን አየዋለሁ አንድም አይቀር (፪x)

ድል ድል ይሸተኛል ኦሆሆ አሃሃ
ማሸነፍ ማሸነፍ ኦሆሆ አሃሃ
ይህንን ተራራ ኦሆሆ አሃሃ
ሜዳ አድርጌው ልለፍ ኦሆሆ አሃሃ

ድል ድል ይሸተኛል ኦሆሆ አሃሃ
ማሸነፍ ማሸነፍ ኦሆሆ አሃሃ
ይህንን ተራራ ኦሆሆ አሃሃ
ሰባብሬው ልለፍ ኦሆሆ አሃሃ (፪x)

 ታዮ ነ ማሊ ባ . . . ጦሶ ነ ማሊ ባ . . .የህይወቴ ምዕራፍ ፡ የተጀመረበት በመስቀሉ ጣር ሞት ፡ ስረየት የሆነበትየፍቅርህ ምርኮኛ ፡ ሆኛለሁ በስራህአልደክም አልታክት ፡ ስላንተ ባወ...
13/01/2022



ታዮ ነ ማሊ ባ . . .
ጦሶ ነ ማሊ ባ . . .
የህይወቴ ምዕራፍ ፡ የተጀመረበት
በመስቀሉ ጣር ሞት ፡ ስረየት የሆነበት
የፍቅርህ ምርኮኛ ፡ ሆኛለሁ በስራህ
አልደክም አልታክት ፡ ስላንተ ባወራ. ..

ድኛለሁ በስራህ . . .

የአባቴ ብሩካኖችጌታ ያየለትን ሳይወርስ አይመለስም (፪x)የሕያው አምላክ ጭፍራ በምድረ በዳ አይቀርም (፪x)ሙዋርትኞቹማ በእስራኤል ላይ አይሰራምአስማትም በያቆብ ላይ የለም (፪x)አዝ፦ ገና ...
13/01/2022

የአባቴ ብሩካኖች

ጌታ ያየለትን ሳይወርስ አይመለስም (፪x)
የሕያው አምላክ ጭፍራ በምድረ በዳ አይቀርም (፪x)
ሙዋርትኞቹማ በእስራኤል ላይ አይሰራም
አስማትም በያቆብ ላይ የለም (፪x)

አዝ፦ ገና እንወርሳለን ገና
ከእግዚአብሄር አፍ ቃል ወጥቷልና (፪x)

ከህልሙ የሚያኑን??? እናያለን ያሉ (፪x)
እየተዘባበቱ ጉድጓድ ውስጥ የጣሉት (፪x)
ዮሴፍ በሕይወት አለ ብለው እስኪያወሩ (፪x)
አምላኬ አሳያቸው በድንቅ አሰራሩ (፪x)

ቀስተኞች ቢያስቸግሩትም
ቢነድፉት እጅጉም ቢቃወሙትም
የያዕቆብ አምላክ ክንድ አበረታ
በመከራ አገር አፈራው

በወንዶችና በሴቶች ባሪያዎቹ ላይ
በሥጋ ለባሽ ሁሉ ላይ
አምላኬ ያፈሳል መንፈሱን ከሰማይ (፪x)
በነብዩ በእዩኤል የተባለዉ
የተስፋው ቃል ለእኛም ነው

አዝ፦ ገና እንወርሳለን ገና
ከእግዚአብሄር አፍ ቃል ወጥቷልና (፪x)

ከህልሙ የሚያኑን??? እናያለን ያሉ (፪x)
እየተዘባበቱ ጉድጓድ ውስጥ የጣሉት (፪x)
ዮሴፍ በሕይወት አለ ብለው እስኪያወሩ (፪x)
አምላኬ አሳያቸው በድንቅ አሰራሩ (፪x)

ቀስተኞች ቢያስቸግሩትም
ቢነድፉት እጅጉም ቢቃወሙትም
የያዕቆብ አምላክ ክንድ አበረታ
በመከራ አገር አፈራው

አዝ፦ ገና እንወርሳለን ገና
ከእግዚአብሄር አፍ ቃል ወጥቷልና (፪x)

እጅ የምታህል ትንሽ ደመና
ብታዩ ዝናቡ እጅግ ነውና (፪x)
በጊዜው የሚፈጸመውን ቃል
የሰማ ለክብሩ አሜን ይበል
በጊዜው የሚፈጸመውን ቃል
የሰማ በደስታ እሰይ ይበል

የዘንዶ ራስ ተቀጥቅጦ
የእግዚአብሔር ክብር በኢትዮፕያ በሙላት ተገልጦ

አዝ፦ ገና እናያለን ገና
ከእግዚአብሄር አፍ ቃል ወጥቷልና (፪x)
ገና እንወርሳለን ገና
ከእግዚአብሄር አፍ ቃል ወጥቷልና (፪x)
ገና እናያለን ገና
ከእግዚአብሄር አፍ ቃል ወጥቷልና (፪x)

ዘማሪ፡ ወርቅነህ አላሮ

♥እንዲሁ በፀጋ♥ያደረኩት የለም ስለ መዳኔ (፪x)የከፈልኩት የለም ስለ መዳኔ (፪x)እንዲው በነፃ የዳንኩት እንዲው በነፃእንዲው በፀጋ ነው እንዲው በፀጋያደረኩት የለም ስለ መዳኔ (፪x)የከፈ...
01/06/2019

♥እንዲሁ በፀጋ♥
ያደረኩት የለም ስለ መዳኔ (፪x)
የከፈልኩት የለም ስለ መዳኔ (፪x)

እንዲው በነፃ የዳንኩት እንዲው በነፃ
እንዲው በፀጋ ነው እንዲው በፀጋ

ያደረኩት የለም ስለ መዳኔ (፪x)
የከፈልኩት የለም ስለ መዳኔ (፪x)

ጌታ ኢየሱስ ነው ለኔ የሞተልኝ
ከኀጢአት እርግማን ነጻ ያወጣን
ስራዬን መስቀል ላይ ሰርቶ ጨርሶታል
በሞቱ ሂወቴን በሞቱ ዋጅቷታል

ያደረኩት የለም ስለ መዳኔ (፪x)
የከፈልኩት የለም ስለ መዳኔ (፪x)

እንዲው በነፃ የዳንኩት እንዲው በነፃ
እንዲው በፀጋ የዳንኩት እንዲው በፀጋ

ግራ አልተጋባሁም አልተቅበዘበዝኩም
ድነትን ፍለጋ እየዞርኩ ወጥቼ አልወረድኩም
በማመኔ ብቻ በልጁ በኢየሱስ
እኔን አድርጎኛል በአብ ቀኝ ከእርሱ እንድወርስ

ቤቴን በሰማይ እርሱ ሰርቶልኛል
መኖሪያዬን በላይ እርሱ አዘጋጅቶልኛል
አርፌአለው በርሱ በነፍስ በስጋዬ
የዘላለም ሂወት ሰቶኛል ኢየሱስ ጌታዬ

እንዲው በነፃ የዳንኩት እንዲው በነፃ
እንዲው በነጻ ነው እንዲው በነጻ (፪x)
እንዲው በፀጋ የዳንኩት እንዲው በፀጋ (፪x)

የእኔን ነገር የእኔን ጉዳይየያዘልኝ ጌታ አለ ከሰማይ (፪x)ማደሪያው ልግባናላምልከው አንስቼ በገና (፪x)የማማርረው አልሞላም ብዬስሙን ላወድስ ሀዘኔን ጥዬቢጐድልም እንኳን ወይኑ በለሱበዚህ ...
16/03/2019

የእኔን ነገር የእኔን ጉዳይ
የያዘልኝ ጌታ አለ ከሰማይ (፪x)

ማደሪያው ልግባና
ላምልከው አንስቼ በገና (፪x)

የማማርረው አልሞላም ብዬ
ስሙን ላወድስ ሀዘኔን ጥዬ
ቢጐድልም እንኳን ወይኑ በለሱ
በዚህ አይለካም ጌታ ነው እርሱ

ጌታ ነው (፫x) ጌታ
ላመስግነው ሳለይ ሁኔታ (፪x)

እኔ አለሁኝ አለሁኝ አበዛለው ብዙ ምስጋና
ሰው ሆኛለሁ ጌታዬ ኢየሱሴ በሰራው ስራ
ከትላንቱ ከአስፈሪው ከጨለማው ከዚያ ግዛት
ያመለጠ የዳነ ለጌታዬ ይስገድለት
አምጡለታ አምጡለታ
ሲያንስበት ነው እልልታ ለዚህ ጌታ (፪x)

አዝ፦ የእኔን ነገር የእኔን ጉዳይ
የያዘልኝ ጌታ አለ ከሰማይ (፪x)

ማደሪያው ልግባና
ላምልከው አንስቼ በገና (፪x)

የዘላለም አባት የመዳኛ ደግሞም ካህኔ
እጅግ ብዙ ብዙ ነው አምለኬ የሆነው ለእኔ
ከአባቱ ቀኝ ሆኖ ስለእኔ እየማለደ
ዛሬም አለው በእቅፉ ጠላቴን እያዋረደ
አምጡለታ አምጡለታ
ሲያንስበት ነው እልልታ ለዚህ ጌታ (፪x)

አዝ፦ የእኔን ነገር የእኔን ጉዳይ
የያዘልኝ ጌታ አለ ከሰማይ (፪x)

ማደሪያው ልግባና
ላምልከው አንስቼ በገና (፬x)

ተመችቶኝ ነው ጌታ ፍቅርህ ተመችቶኝ ነው (፬x)ከአንተ ጋራ መዋል ማደር ከአንተ ጋራ (፬x)ሲከፋኝ ስጨነቅ ሆድ ሲብሰኝከጐኔ ሲጠፋ የሚረዳኝብቻዬን ያልተውከኝ ምድረ በዳአለሁኝ የምትል ለተጐዳ...
16/03/2019

ተመችቶኝ ነው ጌታ ፍቅርህ ተመችቶኝ ነው (፬x)
ከአንተ ጋራ መዋል ማደር ከአንተ ጋራ (፬x)

ሲከፋኝ ስጨነቅ ሆድ ሲብሰኝ
ከጐኔ ሲጠፋ የሚረዳኝ
ብቻዬን ያልተውከኝ ምድረ በዳ
አለሁኝ የምትል ለተጐዳ

አዝ፦ ከአንተ ጋራ መዋል ማደር ከአንተ ጋራ (፬x)

ከወረት ያልሆነ ታላቅ ፍቅርህ
ሀዘኔን የሚያልፍ መፅናናትህ
እምባዬን ያበሰከው ደጋፊዬ
ስተክዝ ሆንክልኝ መፅናኛዬ

አዝ፦ ከአንተ ጋራ መዋል ማደር ከአንተ ጋራ (፬x)

አትከዳኝ አትለወጥ በሁኔታ
አተወኝ ስደክም ስበረታ
ፍቅርህ የፍቅሮች ሁሉ አውራ
ዘለዓለም የሚቀጥል እያበራ

አዝ፦ ተመችቶኝ ነው ጌታ ፍቅር ተመችቶኝ ነው (፬x)
ከአንተ ጋራ መዋል ማደሩ ከአንተ ጋራ (፪x)

ሲከፋኝ ስጨነቅ ሆድ ሲብሰኝ (ከአንተ ጋራ)
ከጐኔ ሲጠፋ የሚረዳኝ (ከአንተ ጋራ)
ብቻዬን ያልተውከኝ ምድረ በዳ (ከአንተ ጋራ)
አለሁኝ የምትል ለተጐዳ (ከአንተ ጋራ) (፪x)

በጨለማ እያለሁ ነፍሴ ተንከራትታ መቼ ተውከኝ የኔ ጌታ (፪x)የሰይጣን ምርኮኛ ሆኜ የተጠቃሁ አወጣኸኝ የኔ ጌታ (፪x)ብቻዬን ሳለቅስ ሁሌ ጠዋት ማታ ስጮህ ብዬ የኔ ጌታ (፪x)ድምጼን ሰምተ...
15/03/2019

በጨለማ እያለሁ ነፍሴ ተንከራትታ መቼ ተውከኝ የኔ ጌታ (፪x)
የሰይጣን ምርኮኛ ሆኜ የተጠቃሁ አወጣኸኝ የኔ ጌታ (፪x)
ብቻዬን ሳለቅስ ሁሌ ጠዋት ማታ ስጮህ ብዬ የኔ ጌታ (፪x)
ድምጼን ሰምተህ ደረስክ ሳትቆይ እስከማታ ክበርልኝ የኔ ጌታ (፪x)

አዝ፦ እኔ ያልዘመርኩኝ ማን ይዘምርልህ ላረግክልኝ ነገር
ከቶ እንዲህ በቀላል ተዘርዝሮ አያልቅም ምህረትህ ቢቆጠር
ትንሽ ከቀለለኝ ብዬ እንጂ አያልቅም ብዘምር ባወራ
ስላረግከው ተዓምር ስላሸጋገርከኝ ያንን ተራራ

በጠላቴ መንግስት በእቅዱ ውስጥ ሆኜ አይተኸኛል መድኃኒቴ (፪x)
አወጣኸኝ ከእጁ ሳትጠፋ ሕይወቴ ክበርልኝ መድኃኒቴ (፪x)
ልትጠቀምብኝ በኔ ልትሰራ ፈልገህ ነው የኔ ጌታ (፪x)
ነጥቀህ የታደግከኝ ከዚያ ባለ ጋራ ክበርልኝ የኔ ጌታ (፪x)

አዝ፦ እኔ ያልዘመርኩኝ ማን ይዘምርልህ ላረግክልኝ ነገር
ከቶ እንዲህ በቀላል ተዘርዝሮ አያልቅም ምህረትህ ቢቆጠር
ትንሽ ከቀለለኝ ብዬ እንጂ አያልቅም ብዘምር ባወራ
ስላረግከው ተዓምር ስላሸጋገርከኝ ያንን ተራራ

ለኃጥዕ ለጻድቅ ፀሐይህ ይወጣል ለፍጥረትህ ሁሉ ይወጣል (፪x)
ቸርነትህ ፍቅርህ መች ይበላለጣል ለሁሉም ሰው ሰጥተኸዋል (፪x)
ለኔ ግን አወጣህ ብርሃን ሌላ ፀሐይ ካልጠበቅኩት አቅጣጫ ላይ (፪x)
የንጋቱ ኮከብ ወልድ ወረደ ከላይ ክበርልኝ በምድር በሰማይ (፪x)

አዝ፦ እኔ ያልዘመርኩኝ ማን ይዘምርልህ ላረግክልኝ ነገር
ከቶ እንዲህ በቀላል ተዘርዝሮ አያልቅም ምህረትህ ቢቆጠር
ትንሽ ከቀለለኝ ብዬ እንጂ አያልቅም ብዘምር ባወራ
ስላረግከው ተዓምር ስላሸጋገርከኝ ያንን ተራራ

ከእኔ የሆነ ፣ ከእኔ የሆነከእኔ የሆነ ምን አለ ጌታከእኔ የሆነ ምን አለ ኦሃሁሉ በአንተ ነዉ ፣ ሁሉ በአንተ ነዉሁሉ በአንተ ነው ጌታ ኢየሱሴሁሉ በአንተ ነው የሆነው አሃ (፪x)ፀንቼ መቆሜ...
16/02/2019

ከእኔ የሆነ ፣ ከእኔ የሆነ
ከእኔ የሆነ ምን አለ ጌታ
ከእኔ የሆነ ምን አለ ኦሃ
ሁሉ በአንተ ነዉ ፣ ሁሉ በአንተ ነዉ
ሁሉ በአንተ ነው ጌታ ኢየሱሴ
ሁሉ በአንተ ነው የሆነው አሃ (፪x)

ፀንቼ መቆሜ ምህረትህ በዝቶ ነዉ (፪x)
መውጣቴ ምግባቴም ክንድህ ደግፎኝ ነዉ (፪x)
አንደም ነገር የለ ከእኔ ነው የምለው (፪x)
መላው እኔነቴ ኢየሱስ የአንተ ነው
ጌታዬ የአንተ ነው

ከእኔ የሆነ ፣ ከእኔ የሆነ
ከእኔ የሆነ ምን አለ ጌታ
ከእኔ የሆነ ምን አለ ኦሃ
ሁሉ በአንተ ነዉ ፣ ሁሉ በአንተ ነዉ
ሁሉ በአንተ ነው ጌታ ኢየሱሴ
ሁሉ በአንተ ነው የሆነው አሃ (፪x)

ሃዘኔን ለውጠህ ደስታ ሰጥተኸኛል (፪x)
መከራዬን ሁሉ አስረስተኸኛል (፪x)
ሁሉን ማከናወን መፈጸም ታውቃለህ (፪x)
እስረኛውን ፈተህ ትከብርበታለህ (፪x)

አምላኬ ሆይ በአንተ ብርታት በአንተ አሃ አሃ
ሃዘኔን እረሳሁት
ያስተከዘኝ ያ ጨለማው አልፎ አሃ አሃ
በአንተ ብርሃን አየሁኝ (፪x)

ይሁን ያልከው ሁሉ ሆኗል በሕይወቴ (፪x)
አሁንም አንተው ነህ የምትመራኝ ረድኤቴ (፪x)
በምንም አልፈራም ተደግፌሃልሁ (፪x)
አንተ ሁሉ ቻይ ነህ በጥላህ አርፋለሁ (፪x)

አምላኬ ሆይ በአንተ ብርታት በአንተ አሃ አሃ
ሃዘኔን እረሳሁት
ያስለቀሰኝ/ያስጨነቀኝ ያ ጨለማው አልፎ አሃ አሃ
በአንተ ብርሃን አየሁኝ (፪x)

ፍቅሩ የማይለወጥ ወረትን አይዎድም (፪x)
እስከዛሬ ድረስ ሰልችቶኝ አያውቅም (፪x)
በምህረቱ ብዛት እየደጋገፈኝ (፪x)
እዚህ ደርሻለሁ እስቲ አመስግኑልኝ (፪x)

አምላኬ ሆይ በአንተ ብርታት በአንተ አሃ አሃ
ሃዘኔን እረሳሁት
ያስጨነቀኝ ያ ጨለማው አልፎ አሃ አሃ
በአንተ ብርሃን አየሁኝ (፪x)
'el_AmdeMicha'el1st

♥አንተ ክበር♥በእድሜ ጠዋት ልጅ ሣለሁ አጊንተህተንከባክበህ ያዝከኝ  በሚያስገርም ትግስትህእንዳገለግልህ እድሉን አገኘሁኝስላንተ እንድናገር በህዝብህ ፊት አቆምከኝእኔን ልታከብር ክብርህን ትተ...
10/02/2019

♥አንተ ክበር♥
በእድሜ ጠዋት ልጅ ሣለሁ አጊንተህ
ተንከባክበህ ያዝከኝ በሚያስገርም ትግስትህ
እንዳገለግልህ እድሉን አገኘሁኝ
ስላንተ እንድናገር በህዝብህ ፊት አቆምከኝ

እኔን ልታከብር ክብርህን ትተሃል
ከሰማይ ሰማያት ስለ እኔ ወርደሃል
የማልጠቅም ስሆን ሰው አድርገኸኛል
ልጅህ አርገኸኛል
በእኔ ፈንታ ሞተህ አስገኝተኸኛል

ውድዬ አንተ ክበር
ኧረ አንተ ንገስ
አንተ ነግሰህ ታይ
በእኔ ላይ
አንተ ከብረህ ታይ

ከመሬት አንስተህ በከፍታ ስፍራ እግሮቼ ሲቆሙ
ጌትነትህ ይግነን ከፍ ከፍ ያድርጉህ ባንተ ይደመሙ
ዛሬ ቀን ከወጣ በህዝብህ ፊት ብቆም በኔ ላይ ብትሰራ
ሰው ሁሉ አንተን ይይ በሀገር በምድሩ ስላንተ ይወራ

አንተ ተወራ ክብሬ ነህ
አንተ ተወራ ድምቀቴ
አንተ ተወራ ውበቴ
አንተ ተወራ የኔ ጌታ
አንተ ከብረህ ታይ
በኔ ላይ
አንተ ገንነህ ታይ

እኔን ልታከብር ክብርህን ትተሃል
ከሰማይ ሰማያት ስለ እኔ ወርደሃል
የማልጠቅም ስሆን ሰው አድርገኸኛል
ልጅህ አርገኸኛል
በእኔ ፈንታ ሞተህ አስገኝተኸኛል

ውድዬ አንተ ክበር
ኧረ አንተ ክበር
አንተ ድመቅ
ኢየሱስ አንተ ድመቅ
ጌታዬ አንተ ክበር
ኧረ አንተ ድመቅ

በበደሌ ምክንያት የታፈረብኝ ነበርኩኝ የወደኩ
ጌታዬ አነሳኸኝ ኃጢአቴ ተሽሮ በደምህ ታጠብኩኝ
ባይገባኝም እንኳ ለኔ የሆንከው ነገር ፍቅርህን ገልጦልኛል
መርገሜን ወስደህልኝ ውዴ በኔ ፈንታ በአብ ፊት ታይተሃል

አንተ ተወራ
አንተ ተሰበክ
አንተ ከብረህ ታይ በኔ ላይ
አንተ ተወራ
አንተ ተሰበክ
ኧረ ከብረኽ ታይ በኔ ላይ
አንተ ነግሰህ ታይ
አንተ ጎልተህ ታይ
አንተ በርተህ ታይ
አንተ ደምቀህ ታይ
አንተ ጎልተህ ታይ
_________✝________
(Meski)1st

Address

ፒያሳ
Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when አዲስ ፍጥረት New Creation posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category