መንፈሳዊ ግጥሞች ዘ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ Menfesawigetmoch Ze Ortodox Tewahedo

  • Home
  • Ethiopia
  • Addis Ababa
  • መንፈሳዊ ግጥሞች ዘ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ Menfesawigetmoch Ze Ortodox Tewahedo

መንፈሳዊ ግጥሞች  ዘ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ Menfesawigetmoch Ze Ortodox Tewahedo ከነፍስ የሆኑ ኦርቶዶክሳዊ ግጥሞች በዚህ ገፅ ላይ ይጻፋሉ

"ምን እላለሁ፤ምን እናገራለሁ፤የጌታዬ ልደቱ ድንቅ ነው።የአማኑኤል ልደቱ ድንቅ ነው።"*፣አለምን በቃሉ፥ የፈጠረ ጌታ፥ ሁላችንን ሊያድን ሊወስድ፥ የኛን ተርታ።ያለም ጌታ ሆኖ፥ ያየነው በበረት...
06/01/2026

"ምን እላለሁ፤
ምን እናገራለሁ፤
የጌታዬ ልደቱ ድንቅ ነው።
የአማኑኤል ልደቱ ድንቅ ነው።"*

አለምን በቃሉ፥ የፈጠረ ጌታ፥
ሁላችንን ሊያድን ሊወስድ፥ የኛን ተርታ።
ያለም ጌታ ሆኖ፥ ያየነው በበረት፤
ምን አይነት ፍቅር ነው፥ ምን አይነት ደግነት።

በናቱ እቅፍ ሆኖ፥ በሰማያት አለ፤
በሰማያት ሆኖ፥ በናቱ እቅፍ አለ።
ከኪሩቤል ጀርባ፥ ሳይወርድ ከዙፋኑ፤
ይገርማል ይደንቃል፥ በኛ መመስገኑ።

ቅድመ አለም ያለ እናት ተወልዶ ከአባቱ
ድህረ አለም ያላአባት ወለደች እናቱ
ይህን ድንቅ ጥበብ፥ ፍጥረቱ ተማክሮ፤
ድንቅ ይባላል እንጂ፥ ማን ያውቃል መርምሮ።

ነብያት የናፈቁት፥ ትንቢታቸው መጣ ፤
ከድንግል ማህፀን፥ ያለድካም ወጣ፤
መለኮት ሳይከፈል፥ ወደ አለም መጣ፤
የጽድቃችን ጸሀይ፥ ከሰማያት ወጣ።
++++++
እንኳን ለብርሀነ ልደቱ በሰላም አደረሳችሁ

*("ምን እላለሁ ምን እናገራለሁ..."
ሐይማኖተ አበው ዘቅዱስ ዮሀንስ አፈወርቅ)
©ታዜና

t.me/Menfesawigetmoch

12/08/2025

Celebrating my 11th year on Facebook. Thank you for your continuing support. I could never have made it without you. 🙏🤗🎉

የመዳን ቀን....ሀጥያት በደል ቢከበኝም፤ካንተ በቀር ሰው የለኝም።ነውሬ በዝቶ ከዘመኔ፥ ከፀጋህ ቢያጎድለኝም፤ይቅር የሚል የሚያድነኝ ፥ካንተ በቀር ሰው የለኝም።ሙሉ መስሎ ያለም ደስታ፥ ሞኙን...
06/06/2025

የመዳን ቀን....
ሀጥያት በደል ቢከበኝም፤
ካንተ በቀር ሰው የለኝም።
ነውሬ በዝቶ ከዘመኔ፥ ከፀጋህ ቢያጎድለኝም፤
ይቅር የሚል የሚያድነኝ ፥ካንተ በቀር ሰው የለኝም።
ሙሉ መስሎ ያለም ደስታ፥ ሞኙን ልቤን ያማለለ፤
ያልወጣሁት የሀጢያት ማጥ፥የጠለቀ ገደል አለ።
(አቤቱ...)
:
ሲጎድልብኝ ላንተ ማልቀስ፥ ሲሞላልኝ ወደ ሀጢያት፤
አንተ ግን አልቸኮልክም፥ ለበደሌ እኔን መቅጣት።
ነብሴን ፀፀት እያወካት፥ ሰውነቴ ሰላም አቶ፤
ተስፋ ከልቤ ተሰዶ፥ መጽናናቴ ውስጤ ሞቶ።
(ማረኝ...)

አይነ ህሊናዬ ታወሮ፥ ልቦናዬ ድንጋይ ሆኗል፤
በህይወቴ ብርሀን የለም፥ የጨለማዬ ዋሻ ገኗል።
ከሀጢያቴ ጉድጓድ እጮሀለሁ፥ ትሰማለህ ስጠራህ፤
እኔን ወዳንተ ሚመመልስ፥ አንድ ቃልስ ታጣለህ?
(ይቅር...)

ያሳየኛል ያ ጠላቴ፥ በምናቤ ከፍታዬን፤
ዛሬን ንዶ አደላድሎ፥ ያሳለፍኩት ያን ደስታዬን።
የቆሮንጦሱ ፈተናህ፥ ዛሬም እኔን ይገጥመኛል፤
ድንጋይ-ዳቦ ስልጣን-ጀብዱ፥ ይሄን ሁሉ ያስመኘኛል።
(በለኝ...)

ጌታዬ ሆይ እባክህን?
አምላኬ ሆይ እባክህን፧
ልብ ስጠኝ፤
ጊዜ ስጠኝ፤
አውጣኝ ከዚህ ከቅዠቱ፥ ከከንቱ አለም፤
ካንተ በቀር ሌላ ማንም፥ እውነት መንገድ ህይወት የለም።
(እግዚአብሔር...)

ልናዘዛት ያቺን ሀጢያት፥ የማፍራትን የዘውትሬን፤
ልናዘዛት ከኔ ትውጣ፥ በንስሐ ልጠብ ነውሬን።
ልናዘዛት ያቺን ሀጢያት፥ ህሊናዬ ነጻ ይውጣ፤
ልናዘዛት እሷን ልተው፥ የመዳን ቀን እንዲመጣ።
(በሚገኝበት ጊዜ ፈልጉት፥)

በምህረትህ ብዛት፥ ወደ ቤትህ አስገባኝ፤
በተወደደ ጊዜ ስማኝ፥ በማዳንህ ቀን ርዳኝ።
እስክወጣ ጥቂት ታገስ፥ በመአትህ አትቅሰፈኝ፣
እስክናዘዝ ጥቂት ታገስ፥ ይቺን አመት ብቻ ተወኝ።
(ቀርቦም ሳለ ጥሩት፤)
+++
“በተወደደ ሰዓት ሰማሁህ
በመዳንም ቀን ረዳሁህ ይላልና፤
እነሆ፥ የተወደደው ሰዓት አሁን ነው፤
እነሆ፥ የመዳን ቀን አሁን ነው።”
— 2ኛ ቆሮ 6፥2
+++
©ታዜና

t.me/Menfesawigetmoch

ሳሪስ ቅድስት ኪዳነምህረት እና ቅዱስ ገብርኤል
19/01/2025

ሳሪስ ቅድስት ኪዳነምህረት እና ቅዱስ ገብርኤል

የጥምቀት በዓል አከባበር በሳሪስ አዲስ ሰፈር. | Check out ፍኖተ ሎዛ ሰንበት ት/ቤት LIVE videos on TikTok! Watch, follow, and discover the latest content from ፍኖተ ሎዛ ሰንበት ት/ቤት.

28/04/2024

++++++++++++++++++++
ሆሣዕና....
ወደ ኢየሩሳሌም፥ ቤተ ፋጌ ሲደርስ፤
የታሰረች አህያ፥
ፈተው እንዲያመጡ፥ ላካቸው ክርስቶስ።
እነዚህ ለጌታ፥ ያስፈልጋሉና፤
የታሰረችውን፥ አምጡልኝ ፍቱና።
ኢየሩሳሌም ሆይ፥ ላሳየሽ በጎነት ላሳየሽ ትህትና፤
እልል በይ ዘምሪ፥ እያልሽ ሆሣዕና።

አዳኝና ትሁት፥ ፃድቅ ንጉስሽ፤
በውርንጫ ጀርባ፥ መቷል አዳኝሽ።
ዘንባባ አንጥፉ፥ ህፃናትም ውጡ፤
አሁን አድን በሉት፥ ምስጋናችሁን ስጡ።
ሆሣዕና....
ደግሞም በዚያችው ቀን፥ ከመቅደስ ገባና፤
የሻጮችን ዙፋን፥ ገለበጠውና።
የወንበዴዎች ዋሻ፥ ያረጉትን ቤቱን፤
ርግብ ሻጩን ሰዶ፥ አፀዳ መቅደሱን።
የገንዘብ ለዋጩን፥ ወንበር ገለበጠ፤
በመቅደሱ ዙፋን፥ ጌታ ተቀመጠ።

ከሚጠቡትም አፍ፥ ምስጋና አዘጋጀ፤
አምላክነቱንም፥ ለአለም አወጀ።
የምትቀድሙ የምትከተሉ፥ ሆሣዕና እያላችሁ፤
በአርያም ይሰማ፥ መዝሙር እልልታችሁ።

አቤቱ ጌታ ሆይ፥ አሁን አድን በሉት፤
ልብሳችሁን ዘርጉ፥ ዘምባባ አንጥፉለት።
አሁን አድን ብለን፥ ወተናል በመንፈስ፤
በውርንጫ ጀርባ፥ አምላካችን ሲደርስ።
የዘካርያስ ትንቢት፥ አልቀረም ተፈቷል፤
በውርንጫ ጀርባ ፥ንጉሳችን መቷል።
+++++++++++++++++++++

©ታዜና
" የሚቀድሙትም የሚከተሉትም። ሆሣዕና፤ በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው፤"
(የማርቆስ ወንጌል 11:9)

፲፮ ኪዳነ ምህረት ፲፮ ያከበረሽ ሊከብር ፥ኪዳን አለሽና፤አይቆምም ለስምሽ፥ እልልታ ምስጋና።የጠሩሽ ቢበዙ፥ አንቺ ባርከሻቸው፤የወደዱሽ ሁሉ፥ ቀና መንገዳቸው። ፲፮ ፲፮ ፲፮ ልጆችሽ ስለሆን፥ ...
24/02/2024

፲፮ ኪዳነ ምህረት ፲፮

ያከበረሽ ሊከብር ፥ኪዳን አለሽና፤
አይቆምም ለስምሽ፥ እልልታ ምስጋና።
የጠሩሽ ቢበዙ፥ አንቺ ባርከሻቸው፤
የወደዱሽ ሁሉ፥ ቀና መንገዳቸው።

፲፮ ፲፮ ፲፮

ልጆችሽ ስለሆን፥ እናቴ እንላለን፤
እስከ ዘለአለም፥ ገና እንወድሻለን።
ከወዴት ይገኛል፥ እንዳንቺ ያለ እናት፤
ዘውትር እንላለን፥ ኪዳነ ምህረት።

፲፮ ፲፮ ፲፮

ከአምላክ መታረቂያ፥ የምህረት ኪዳን ነሽ፤
እንኳን ለወደደሽ፥ ለጠላሽ እናት ነሽ።
"ኪዳነምህረት፥ ኪዳንኪ ኮነ፤
በልጅሽ ቤዛነት፥ ፍጥረት ሁሉ ዳነ።"
+++++++++++++++++++++++
™ ©ታዜና

+እንኳን ለ አስተርዮ ማርያም አደረሳችሁ++++የመረጋጋቴ፥ የማረፌ ምስጢር፤የሹመቴ ግርማ፥ የወንበሬ ክብር የህይወቴ አክሊል፥ ማርያም ትባለች።ምግብ ይውሆነውን፥ ልጇን ሰታኛለች።+++©ታዜና  ...
30/01/2024

+እንኳን ለ አስተርዮ ማርያም አደረሳችሁ+
+++
የመረጋጋቴ፥ የማረፌ ምስጢር፤
የሹመቴ ግርማ፥ የወንበሬ ክብር
የህይወቴ አክሊል፥ ማርያም ትባለች።
ምግብ ይውሆነውን፥ ልጇን ሰታኛለች።
+++
©ታዜና

t.me/Menfesawigetmoch

21/01/2024

አገኘኸኝ...የእማማ ፀሎት

Address

Addis Ababa

Telephone

+251911358850

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when መንፈሳዊ ግጥሞች ዘ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ Menfesawigetmoch Ze Ortodox Tewahedo posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share