ምክረ ቅዱሳን

ምክረ ቅዱሳን "በእናንተ ሳይፈረድባችሁ አስቀድማችሁ እናንተ በራሳችሁ ላይ ፍረዱ!”
ሊቁ ቅዱስ መቃርዮስ

"  ምስለ ኅሩያንየ =   ቃል ኪዳኔን አደረግሁ።" መዝ.፹፰፥፫እንኳን አደረሰን!!!
23/02/2026

" ምስለ ኅሩያንየ = ቃል ኪዳኔን አደረግሁ።" መዝ.፹፰፥፫
እንኳን አደረሰን!!!

 #በቅድስት  #የቅድስና ትምህርቶች እነሆ!!!ጾምጸሎትምጽዋት
23/02/2026

#በቅድስት #የቅድስና ትምህርቶች እነሆ!!!

ጾም

ጸሎት

ምጽዋት

ጉልበተኛውን  #ሶምሶንን ፍልስጥኤማውያን እና ደሊላ ገድለው ከጣሉት በኋላ   ውሃን አጠጥቶት ያዳነው   እኛንም ከድካምና ከዝለት ይጠብቀን!!!
19/02/2026

ጉልበተኛውን #ሶምሶንን ፍልስጥኤማውያን እና ደሊላ ገድለው ከጣሉት በኋላ ውሃን አጠጥቶት ያዳነው እኛንም ከድካምና ከዝለት ይጠብቀን!!!

17/02/2026
16/02/2026

"እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ ቃሌን የሚጠብቅ ቢኖር ለዘላለም ሞትን አያይም።"
ዮሐ.፰፥፶፩

15/02/2026

የዐቢይ ጾም የመጀመሪያ እሑድ ዘወረደ ይባላል፤ የወረደው ማለት ነው።
ማነው የወረደው?

15/02/2026

እንኳን ለዐቢይ ጾም መግቢያ አደረሰን አደረሳችሁ!

 #የሚያስፈራና አስደንጋጭ ሕልም!!!"ሌሊትም በሆነ ጊዜ የሚያስፈራና የሚያስደነግጥ ታላቅ ራእይን አየ በነጋም ጊዜ ለአባቱ እንዲህ ብሎ ነገረው ዛሬ በዚች ሌሊት ታላቅ መከራና ብዙ ቅጣት ደረ...
14/02/2026

#የሚያስፈራና አስደንጋጭ ሕልም!!!

"ሌሊትም በሆነ ጊዜ የሚያስፈራና የሚያስደነግጥ ታላቅ ራእይን አየ በነጋም ጊዜ ለአባቱ እንዲህ ብሎ ነገረው ዛሬ በዚች ሌሊት ታላቅ መከራና ብዙ ቅጣት ደረሰብኝ ታላቅ ዙፋንንም አየሁ በላዩ የተቀመጠበት ሰው እጅግ የሚያስፈራ የሚያስደነግጥ ነው ፊቱም ከፀሐይ ይበራል የብዙ ብዙ የሆኑ ሠራዊት የጦር መሣሪያ ይዘው በዙሪያው ቁመው ነበር እኔና አንተም እሥረኞች ሁነን በኋላው ቁመን ነበር እኔም በዙፋን ላይ የተቀመጠው ማነው ብዬ ጠየቅሁ ትላንት አንተ የዘበትክበት የክርስቲያን ንጉሥ ክርስቶስ ይህ ነው አሉኝ ከዚህም በኋላ የጦር መሣሪያ ከተሸከሙት አንዱ ወደ እኔ መጥቶ ጐኔን በጦር ወጋኝ ጦሩንም ከጐኔ ውስጥ አላወጣውም።"

#የካቲት ፯
ከ፮ አላውያን ነገሥታት በላይ ስለ ክርስትናው መከራን ያበዙበት ሊቀ ጳጳስ #እለእስክንድሮስ!!!

  -ዋና የተባለበት ምክንያት➻አንዱ ክብር ይግባውና ጌታችን አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ራሱ ጾሞ ባርኮ የሰጠን በመሆኑ ነው።➻ ሁለተኛው ደግሞ በሚጾሙት ቀናት ብዛት ከሌሎቹ አ...
13/02/2026


-ዋና የተባለበት ምክንያት
➻አንዱ ክብር ይግባውና ጌታችን አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ራሱ ጾሞ ባርኮ የሰጠን በመሆኑ ነው።
➻ ሁለተኛው ደግሞ በሚጾሙት ቀናት ብዛት ከሌሎቹ አጽዋማት ስለሚበልጥ ነው።

#ታዲያ ይህን ጾም ለመቀበል ምንድነው ማድረግ ያለብን ዝግጅት?

#አብዛኛዎቻችን የምናስበው ሆድ አንዴ የተመገብነውን ከ6 ሰዓት በኋላ አላየሁም አልሰማሁም የሚል መሆኑን የዘነጋን በሚመስል ሁኔታ ሥጋን ለመብላት፣ ሌሎች ቅባታማ አመጋገቦችን ለመጠቀም የማናደርገው ነገር የለም።

ትልቁ ዝግጅት ይህ አይደለም።
የመጀመሪያውም የመጨረሻውም የቅበላ ጾም ዝግጅት #የሕሊና (የስሜት ሕዋሳት) ዝግጅት ነው።

#ጾም - እግዚአብሔርን የምንመስልበት ታላቅ በረከት ያለበት፣ እንስሳዊ ባህርያችንን አስወግዶ መልአካዊ ባህርያችንን የሚገልጥ፣ ከሰውነት ወደ አምላካችን የበለጠ የምንቀርብበት (ዘፍ.1፥26 እግዚአብሔርን የምንመስልበት) ወቅት ነውና :-
➻ እስከዛሬ ከሥጋ ጋር ከነበርንበት ሁኔታ ተለይተን በጾሙ ወቅት ከእግዚአብሔር ጋር የምንሆንበትን ሁኔታዎች ማመቻቸት፤

➻ #ለመመጽወት፣ አብዝቶ ለመጸለይ፣ ለስግደት፣ አብዝቶ መንፈሳዊ ትምህርቶችን ለመማር፣ በሦስቱም ጊዜያት ቤተ ክርስቲያን በመገኘት፣...ወዘተ. መርሐ ግብሮቻችንን ከወዲሁ ማስታካከል፤

➻ ...አይቻልምና የተጣላን መታረቅ፣ የበደልነውንም የበደለንም ሰው ካለ እርቀ ሰላም መፍጠር፣ በስሕተትም ሆነ በማታለል ያደረግነው ድርጊት ካለ ከወዲሁ ማስተካከል/መካስ ያስፈልጋል።

➻ #ስንጾም:-
- እራስን ጿሚ ለማስመሰል አለመሞከር፣ በጭራሽ አለማሰብ:- የምንጾመው ከሰው ጋር ለመሆን ሳይሆን ከእግዚአብሔር ጋር ለመሆን መሆኑን እንዳንዘነጋ!!!

- የማይጾሙ ሰዎች ቢያጋጥሙን ከመምከርና ከማስተማር ባለፈ መናቅና እንደረከሱ አድርጎ ማሰብን ማስወገድ፤ ያለ ትኅትና ልዕልና የለምና ትኁታን መሆን ያስፈልገናል።

- ጾሙን ጉዳይ አስፈጻሚ ቀብድ እንዳናደርገው መጠንቀቅ፤ ስለጾምኩ ይህን አድርግልኝ ወይም ይደረግልኛል የሚል ሐሳብ ይዞ መጾም #የቀብድ ጾም እንጂ የመቀደስ/የበረከት ጾም/ አያሰኘውም። የምንጾመው ከእግዚአብሔር ጋር ለመታረቅ፣ ስለ ሠራነው ኃጢአት መጸጸቻ ጊዜ እንጂ ለእግዚአብሔር ጥቅም የምንጾም እንዳናስመስለው መጠንቀቅ ያስፈልጋል።

#ሲጠቃለል ቅበላ ንፍሳዊ ዝግጅት እንጂ ሥጋዊ ድግስ ባለመሆኑ #ለቅበላው ሥጋ በላንም አልበላንም የምንጨምረውም የምንቀንሰውም አንዳች ነገር ባለመኖሩ ሥነ ልቦናችንን በማዘጋጀት፣ ከንስሐ አባት ጋር በመቀራረብ ንስሐ ገብቶ መቀበል ያስፈልገናል። በዚህ ጾም ዋናው መረሳት የሌለበት ሌላው ዐቢይ ጉዳይ #ምጽዋት ነው። #የቁርሳችን ለአቅመ ደካሞች፣ ለነዳያን በመስጠት፣ ደካሞችን በመርዳት፣ በዚህ ጾም ደሃውም ሀብታሙም እኩል ተመግቦ የሚያድርበት ወቅት መሆን ይጠበቅበታል።

#በሰላም ይግባልን!
ይቆየን!

ምክረ ቅዱሳን

"ጌታ ሆኖ የማይምር፣ ባሪያ ሆኖ የማይበድል የለምና ይቅር በለኝ!" በግ ጠባቂ የነበረው   የካቲት ፭
11/02/2026

"ጌታ ሆኖ የማይምር፣ ባሪያ ሆኖ የማይበድል የለምና ይቅር በለኝ!" በግ ጠባቂ የነበረው

የካቲት ፭

 #እግዘብሔር:-➻ልመናችንን ሁሉ እንዲሰማን፤ ➻ቅርባችን እንዲሆን/እንዳይርቀን፤➻ከሚፈራው ከሚወራው ክፉ ነገር ሁሉ እንዲያድነን፤➻ልመናችንን ሁሉ እንዲሰማን፤ ➻የምኞታችንን ሁሉ እንዲያሳካልን...
11/02/2026

#እግዘብሔር:-
➻ልመናችንን ሁሉ እንዲሰማን፤
➻ቅርባችን እንዲሆን/እንዳይርቀን፤
➻ከሚፈራው ከሚወራው ክፉ ነገር ሁሉ እንዲያድነን፤
➻ልመናችንን ሁሉ እንዲሰማን፤
➻የምኞታችንን ሁሉ እንዲያሳካልን
==> #እንጥራው!!!
👇👇👇👇👇👇👇👇👇
"እግዚአብሔር #ለሚጠሩት ሁሉ፥ በእውነት ለሚጠሩት ሁሉ ቅርብ ነው።
፥ ያድናቸውማል።"
መዝ.፻፵፬፥፲፰-፲፱

🌿"አባት ለልጆቹ እንደሚራራ እንዲሁ እግዚአብሔር ለሚፈሩት ይራራል።"🌿                      መዝሙረ ዳዊት ፻፪፥፲፫
11/02/2026

🌿"አባት ለልጆቹ እንደሚራራ እንዲሁ እግዚአብሔር ለሚፈሩት ይራራል።"🌿
መዝሙረ ዳዊት ፻፪፥፲፫

Address

ኢትዮጵያ
Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ምክረ ቅዱሳን posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share