Mekane Hiwot Sunday School

Mekane Hiwot Sunday School Mekane Hiwot Sunday School is found in Kebena Mekane Hiwot Abune Gebre Menfes Kidus Church in Addis Ababa, Ethiopia.

14/08/2026
09/08/2026

እግዚአብሄርን እንዲህ በሉት….
መልካም ሱባኤ

"ኹለቱም አንድ አካል ይኾናሉ፤ ይኽ ነገር ጥልቅ፤ ረቂቅ ምሥጢር ነው፤ እኔም ለክርስቶስና ለቤተክርስቲያን ምሳሌ አድርጌ እናገረዋለኹ፡፡"         ሃይማኖተ አበው ዘስምዓት     በወርኃ ...
01/08/2026

"ኹለቱም አንድ አካል ይኾናሉ፤ ይኽ ነገር ጥልቅ፤ ረቂቅ ምሥጢር ነው፤ እኔም ለክርስቶስና ለቤተክርስቲያን ምሳሌ አድርጌ እናገረዋለኹ፡፡"
ሃይማኖተ አበው ዘስምዓት

በወርኃ ሐምሌ ጋብቻችሁን በሥርዓተ
ቤ/ክ የፈጸማችሁት የሰ/ት/ቤታችን አገልጋይ እህታችን ቤተልሄም ስጦት እና አለበል ደሴው እንዲሁም እህታችን ወርቄ ጥላሁን እና ያለምዘው ድልቅናው የፈጸማችኹትን ጋብቻ፤ የአብርሃምንና የሳራን ጋብቻ የባረከ አምላክ፤ የትዳር ሕይወታችኹን ይባርክላችኹ፥ ያጣምራችኹ፥ ያዋሕዳችኹ

የጻድቁ አቡነ ገብረ መንፈስቅዱስ ምልጃ በሕይወታችኹ ሞገስ ይኾናችኹ ዘንድ በፍቅርና በጤና ይባርካችኹ ዘንድ መልካም ምኞታችን ነው መልካም የትዳር ዘመን ይሁንላችኹ

መካነሕይወት ሰንበት ት/ቤት

👉የቅዱስ_ጴጥሮስ_ወጳውሎስ እንዲሁም የደብራችን ቅዳሴ ቤት የከበረበት ዓመታዊ ክብረ በዓል ምስል ሐምሌ አምስት በዚች ቀን የክቡራንና የዐበይት አባቶቻችን ሐዋርያት   እና   የሰማዕትነታቸው ...
17/07/2026

👉የቅዱስ_ጴጥሮስ_ወጳውሎስ እንዲሁም የደብራችን ቅዳሴ ቤት የከበረበት ዓመታዊ ክብረ በዓል ምስል

ሐምሌ አምስት በዚች ቀን የክቡራንና የዐበይት አባቶቻችን ሐዋርያት እና የሰማዕትነታቸው መታሰቢያ ነው።

ጴጥሮስ ማለት ዓለት ማለት ነው፡፡ ማቴ. 16፥18 በዕብራይስጥ ኬፋ ይለዋል፡፡ የመጀመሪያ ስሙ ስምዖን ነው፤ ትውልዱም ከነገደ ሮቤል ነው፡፡ አባቱ ዮና ይባላል፡፡ የተወለደው በገሊላ አውራጃ በቤተ ሳይዳ ነው፡፡ ጴርቴዋ የምትባል ሚስት ነበረችው የሚተዳደረው ዓሣ በማጥመድ ነበር፡፡ ከወንድሙ ከእንድርያስ ጋር ዓሣ ከሚያጠምድበት ተጠርቶ ሐዋርያ ሆኗል፡፡ ማቴ. 4፥19

ጴጥሮስ የዋህ፣ ፈጣን ቁጡ ነበር፡፡ የዋህነቱ ጌታ በባሕር ላይ ሲሄድ አይቶ ጌታ አንተስ ከሆንክ ወደ አንተ እንድመጣ አሰናብተኝ ብሎ በባሕር ላይ ሲሄድ በመሞከሩ ማቴ. 6፥45፣ ፈጣንነቱ ጌታ ደቀመዛሙርቱን በቂሣርያ ሰዎች ማን ይሉኛል ብሎ ጠይቋቸው ሙሴ ነው፣ ኤልያስ ነው ይሉሃል ባሉትና እርሱም መልሶ እናንተስ ማን ትሉኛላችሁ ብሎ በጠየቃቸው ጊዜ ጴጥሮስ ፈጥኖ አንተ የሕያው የእግዚአብሔር ልጅ ክርስቶስ ነህ ብሎ በመመለሱ ማቴ. 16፥16 ቁጡነቱም አይሁድ ጌታን በያዙት ጊዜ ተቶጥቶ የማልኮስን ጆሮ በሰይፍ በመቁረጡ ዮሐ. 18፥10 ላይ ያስረዳል፡፡ መዋዕለ ስብከቱ 50 ዓመት ነው፡፡ /ገድ ሐዋ፣ ዜና ሐዋ/

ንጉሡ ኔሮን ቄሣር መምለኬ ጣዖት ነበረና በሃይማኖት ምክንያት አስሮት ነበር፡፡ አካይያ ዘምቶ ጠላቱን ድል ነሥቶ ሲመለስ ለጣዖት ስገድ ቢለው አልሰግድም አለ፡፡ በችንካር ተቸንክሮ በመስቀል ተሰቅሎ ይሙት ብሎ ፈረደበት ከዚህ በፊት አሕዛብ ሊጣሉት ሲነሱ ወደ ጌታ ሲያመለክት እሳት ከሰማይ ወርዳ ታጠፋለት ነበር አሁንም እሳት ከሰማይ ወርዳ ትብላቸው ብሎ ወደ ጌታ ቢያመለክት ጌታ በመስቀል ተሰቅሎ ታየው ዳግመኛ በሮም ሰቀሉህን? አለ አንተ ብትፈራ እንጂ ነዋ አለው፡፡ ፈቃድህስ ከሆነ ብሎ እንደ ጌታዬ አቁማችሁ ሳይሆን ቁልቁል ዘቅዝቃችሁ ስቀሉኝ አላቸው በራሱ ዘቅዝቀው ሰቅለውታል፡፡ ዕረፍቱ በዚህች ሐምሌ 5 ቀን ይታሰባል፡፡ ሥጋውንም ደቀመዝሙሩ መርቄሎስ ከመስቀሉ አውርዶ በወተት በወይን አጥቦ ሽቶ ቀብቶ በነጭ ሐር ገንዞ እንዳይፈርስ በማር በተመላ ሣጥን አድርጎ ቀብሮታል፡፡

ጳውሎስ ማለት ንዋይ ኅሩይ (የተመረጠ ዕቃ) ማለት ነው፡፡ ሐዋ.9፥15 አንድም ብርሃን ማለት ነው፡፡ አንድም መድቅሕ ማለት ነው፡፡ ደንጊያ በመዶሻ ተጠርቦ ለሕንፃ ሥራ እንዲውል አሕዛብም በእርሱ ትምህርት ታንፀው ለገቢረ ጽድቅ ይበቃሉና የመጀመሪያ ስሙ ሳውል ነው፤ ሳውልም ማለት ጸጋ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡ ትውልዱ ከነገደ ብንያም ማለት ነው፡፡ ፊል. 3፥5 አባቱ ዮስአል ይባላል፡፡ የተወለደው ጌታ በተወለደ በ5 ዓመት በጠርሴስ ነው፡፡ ከ15 ዓመቱ ጀምሮ ኢየሩሳሌም ከመምህር ገማልያል ሕገ ኦሪትን መጻሕፍተ ነቢያትን ሲማር አድጓል፡፡ ሐዋ. 22፥3 ለሕገ ኦሪት ቀናዒ ከመሆኑ የተነሣ ክርስቶስን ዕሩቅ ብእሲ ወንጌልን ዲቃላ ሕግ እያለ ሐዋርያትን ይቃወም ምእመናንን ያሳድድ ነበር፡፡ በወንጌል ያመነው ጌታ በዐረገ በ8ኛ ዓመት ነው፡፡ ምዕመናንን ለማሳደድ ከሊቀ ካህናት የሹመት ደብዳቤ ተቀብሎ ወደ ደማስቆ ሲሄድ መብረቅ ጣለበት፤ ደንግጦ ወደቀ ወዲያውም ሳውል ሳውል ለምን ታሳድደኛለህ የሚል ድምጽ ሰማ፡፡ አንተ ማነህ አለ ምእመናንን ከዋሉበት አላሳድር ካደሩበት አላውል የምትልብኝ የናዝሬቱ ኢየሱስ ነኝ፣ ሰይፍ ቢረግጡት የረገጠው ሰው እንጂ ሰይፉ ይጎዳልን፣ አንተስ እኔን ብትክድ ምእመናንን ብታሳድድ አንተ እንጂ እኔ እጎዳለሁን አለው፡፡ አሁን ምን ላድርግ አለው ተነሥተህ ወደ ከተማ ግባ የምታደርገውን ይነግሩሃል አለው፡፡ ከእርሱ ጋር የነበሩም ድምጹን ይሰማሉ መልኩን ግን አላዩም፤ ከወደቀበት ተነሥቶ ዓይኑ ጠፍቷልና ሰዎች እየመሩት ቤተ ይሁዳ አደረሱት እኅል ውኃ ሳይቀምስ 3 ቀን ውሎ አድሯል፡፡ ሐናንያ በደማስቆ ይኖር ነበርና ጌታ በራዕይ ታይቶት ጳውሎስን አጠመቀው፡፡ ሐዋ. 9፥1-19

በ69 ዓ.ም ሮም ገብቶ ሲያስተምር ንጉሡ ኔሮን ቄሣር አሥሮት ነበርና አካይያ ዘምቶ ጠላት ድል ነሥቶ ሲመለስ ጥሩት አለ፤ መስቀሉን በእጁ ይዞ ቀረበ፤ ተቆጥቶ በሰይፍ ቅጡት አለ፤ እንደ በግ እየነዱ ሲወስዱት የንጉሡ ልጅ አገኘቻቸው፤ አምና ነበርና መጎናጸፊያሽን ስጪኝ አላት ሰጠችው በዚያ ሸፋፍነው ሰይፈውታል፡፡ ደሙም ሰማየ ሰማያት ወጥቶ ቀተሉኒ በዓመጻ እያለ ተካሷቸዋል፡፡ እሱን ገድለው ሲመለሱ የንጉሥ ልጅ አገኘቻቸው ጳውሎስስ? አለቻቸው፡፡ በልብስሽ ሸፋፍነን በሰይፍ ገደልነው አሏት፡፡ ልብሴን መልሶልኝ ከጴጥሮስ ጋር አሁን በዚህ ሲያልፍ እያየሁት ገደልነው ትሉኛላችሁን አለቻቸው ልብሷን አይተው አምነዋል፡፡ ተቆርጦ የወደቀ ራሱንም ከአንገቱ ቢያጋጥሙት እንደ ቀድሞው ሆኖላቸው ቀብረውታል፡፡ ዕረፍቱ በዚች ሐምሌ 5 ይታሰባል፡፡

የቅዱሳን አባቶች ጸሎታቸው በረከታቸው በሁላችን ላይ ይደር፡፡

(ገድለ ሐዋርያት፣ ዜና ሐዋርያት፣ ስንክሳር ዘወርኀ ሐምሌ)

👉የቅዱስ_ጴጥሮስ_ወጳውሎስ እንዲሁም የደብራችን ቅዳሴ ቤት የከበረበት ዓመታዊ ክብረ በዓል ምስል ክፍል ፩👈ሐምሌ አምስት በዚች ቀን የክቡራንና የዐበይት አባቶቻችን ሐዋርያት   እና   የሰማዕ...
14/07/2026

👉የቅዱስ_ጴጥሮስ_ወጳውሎስ እንዲሁም የደብራችን ቅዳሴ ቤት የከበረበት ዓመታዊ ክብረ በዓል ምስል ክፍል ፩👈

Address

Ferensay Legasion
Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Mekane Hiwot Sunday School posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Place Of Worship

Send a message to Mekane Hiwot Sunday School:

Shortcuts

Share