Mk kiremu

Mk kiremu Mahiber Kidusan organized under the Ethiopian Orthodox tewahido Church. It provides spiritual agenda exclusion by its sub center participants of the church.

09/04/2026

"Foon Isaa kabajamaa fi Dhiiga Isaa ulfaataadhan ni fayyise"

Kamisni kadhannaa Torbee dhukkubbii keessatti argamtu hiika Afuurawaa adda ta'ee fi jaalala ittiin beekkamtu qabdi. Guyyaan tuni moggaasota gurguddoo afuriin beekkamti.

1. Kamisa Kadhannaa:- Gooftaan keenya iddoo kudraalee Geeteesemaanitti kadhannaa inni kadhate guyyaa itti yaadannuudha. Gara qorumsaa akka hin galle jabaadhaatii kadhadhaa. (Maat. 26:41)

2. Miila Dhiqaa:- Fayyisaa addunyaa ta'ee osoo jiruu miila duuka bu'oota isaa dhiquun kasoomina daangaa hin qabne mul'ise. Nu'is walii walii keenyaan akka gadi jennu arjummaa isaatiin nu haa yaadatu.(Yoh. 13:14)

3. Guyyaa Iccitii:- Iccitiin Foonii fi Dhiiga Isaa itti hundeeffame guyyaa ulfaattuu! Dhiifama cubbuu hedduudhaaf kan dhangala'u dhiignikoo kakuu haaraa isa kana."
(Maat. 26:28)

4. Kamisa Bilisummaa:- Ilmi namaa gabrummaa cubbuu jalaa bilisa bahuun isaa guyyaa missiraachoon itti himamu, guyyaa nagaa qooda dukkanaa ifni itti laatame.
[4/9/2026 10:34 AM] Bruk Mk: kamisaa # Torbee dhukkubbii # Ortodooks Tawaahidoo # EOTCMK # Afuurawaa

09/04/2026

"ብኽቡር ስግኡን ብቅዱስ ደሙን ፈወሰና"

ኣብ ሰሙነ ሕማማት እትርከብ ዕለተ ሓሙስ ፍሉይ መንፈሳዊ ትርጕምን መግለፂ ፍቕርን ኣለዋ። እዛ ዕለት ብኣርባዕተ ስያመታት ትፍለጥ።

፩. ጸሎተ ሐሙስ፦ ጐይታና ኣብ ጌቴሰማኒ ናይ ኣታኽልቲ ቦታ ዝጸለዮ ጸሎት ዝዝከረሉ እዩ። "ናብ ፈተና ኸይትኣትዉስ፥ ትግሁን ጸልዩን" (ማቴ. 26፥41) ብምባል ኣድላይነት ጸሎት ዘምሀረሉ ዕለት እዩ።

፪. ሕጽበተ እግር፦ መድሓኒት ዓለም እንከሎ እግሪ ደቀ መዛሙርቱ ብምሕፃብ ፀግዒ ትሕትንኡ ኣርኣየና። ንሕና'ውን ነንሕድሕድና ንኽንከባበር ብትሕትና ኣተሓሳሰበና። (ዮሐ 13፥14)

፫. መዓልቲ ምሥጢር፦ ምሥጢር ቅዱስ ስግኡን ክቡር ደሙን ዝተመስረተሉ ዓብዪ ዕለት! "እዙይ ምእንቲ ብዙሓት ንሕድገት ሓጢኣት ዝፈስስ ና ሓድሽ ኪዳን ደመይ እዩ።"
(ማቴ. 26፥28)።

፬. ናይ ነጻነት ሓሙስ፦ ወድሰብ ካብ ባርነት ሓጢኣት ሓራ ምውፅኡ ዝተበሰረሉ፣ ኣብ ክንዲ ፀልማት ባርነት፡ ብርሃን ነጻነት ዝተዓደለሉ ዕለተ ሰላም እዩ።

#ጸሎተሐሙስ #ሰሙነሕመማት #ኦርቶዶክስ #ተዋሕዶ #መንፈሳዊ

09/04/2026

Welcome to Mahibere Kidusan TV (MKTV) — the official media platform of the Ethiopian Orthodox Tewahedo Church Sunday School Department.📺 Subscribe & Stay Co...

09/04/2026
09/04/2026
15/01/2026

በዓለ ግዝረት

EOTCMK TV ጥር 6 ቀን 2018 ዓ.ም

ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቅድመ ዓለም በህሊና ያሰበውን፤ ድኅረ ዓለም በነቢያት ያናገረውን ለመፈጸም ሰው ሆነ፣ ሥጋ ለበሰ፤ ሕግ ጠባያዊን ሕግ መጽሐፋዊን እየፈጸመ በጥቂቱ አደገ። ሕግ ጠባያዊ፤ አበ፣ እመ ማለት፣ ለዘመድ መታዘዝ፣ በየጥቂቱ ማደግ ነው። “ወልህቀ በበኅቅ እንዘይትኤዘዝ ለአዝማዲሁ ወለይእቲ እሙ” እንዲል። ሕግ መጽሐፋዊ በስምንት ቀን ቤተ ግዝረት በአርባ ቀን ዕጉለ ርግብ ዘውገ ማዕነቅ ይዞ ቤተ መቅደስ መግባት የመሳሰሉት ናቸው፤ በማለት የመጻሕፍተ ሐዲስ ኪዳን ሊቃውንት በሐዲስ ኪዳን ትርጓሜ መግቢያ ላይ ያመሰጥራሉ፣ ያስተምራሉ።

ቅዱስ ሉቃስ በጻፈው የጌታችን የመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ወንጌል ምዕራፍ 1 ቁጥር 59 ላይ ዘግቦልን እንደምናገኘው፤ በዘመነ ብሉይ ወንድ ልጅ በተወለደ በስምንተኛው ቀን ሲገረዝ ስም ይወጣለት ነበር።በመሆኑም ግዝረት የሥጋ ሸለፈት መቆረጥን ያመለክታል።

የግዝረት ሥርዓት ዝም ብሎ የመጣ ሳይሆን እግዚአብሔር ለአብርሃም የሰጠው የቃል ኪዳኑ ምልክት ነው። ዘፍ17 ፤ 7-14 በሙሴ የመሪነት ዘመንም ለእስራኤል ህዝብ ምልክትና መለያ ነበር።ዘፀ 12፤43 ፈሪሳውያን ግን ከአብርሃም የመጣ መሆኑን ሳይረዱ በሙሴ እንደተሰጠ ሕጋዊና ሕዝባዊ ምልክት አድርገው ያምኑ ነበር።የሐዋ 15፤1-5 ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ግን፤ መጀመሪያ ራሱ የሰጠው ለአብርሃም እንደነበርና መንፈሳዊ ምልክትም እንደሆነ አስረድቷቸው ነበር።ዮኀ 7፤22።

የሚከተሉት ሦስት ነጥቦች የግዝረት ዋና ዋና ዓላማዎች ናቸው።

እግዚአብሔር የተገረዘውን ሰው ለራሱ መርጧልና አምላኩ ነው፤ ዘፍ 17፤8
የተገረዙት የእግዚአብሔር ህዝቦች ናቸውና ክፋትንም ከህይወታቸው ማስወገድ አለባቸው፤ ዘጸ 10፤16
እግዚአብሔር በእምነት ስለተቀበላቸው የጽድቃቸው መሠረት ነው፤ ሮሜ 4፤11
ሆኖም በሐዲስ ኪዳን ሥርዓት ሣይሆን፤ የሚያድነው የእግዚአብሔር ህግ መሆኑን ቅዱስ ጳውሎስ ያብራራል።ሮሜ 2፤25 ዋናው ነገር የሥጋ ሸለፈት መገረዝ ሳይሆን የልብ መለወጥና በእግዚአብሔር ማመን ሕጉንም መፈጸም ነው፣ ሲል ቅዱስ ጳውሎስ ምዕመናኑን በመንፈስ የተገረዙ መሆናቸውንም ጨምሮ አብራርቷል።ፊሊጵ 3፤30 በተለይም ህዝብና አህዛብ ማለትም ትንቢት የተነገረላቸው፣ ተስፋ የተነገራቸው እስራኤላውያን እና ከአህዛብ ወገን የመጡት ሁለቱም የክርስትና አማኞች በግዝረት ምክንያት ያስነሱትን አለመግባባት አስመልክቶ በጻፈው መልእክቱ በሐዲስ ኪዳን ዘመን ጥምቀት በግዝረት ፋንታ መተካቱን ያስረዳል።ቆላ 2፤11 ግዝረትም አሁን አይጠቅምም ይለናል። ገላ 5፤6።

ወደ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ግዝረት ስንመለስ ደግሞ፤ በመግቢያው እንደተገለጸው ኦሪትና ነቢያትን ልፈጽም እንጂ ልሽራቸው አልመጣሁም እንዳለ፤ ለስም አጠራሩ ክብር ይግባውና እርሱ ራሱ ሥርዓቱን ለመፈጸም ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም በተወለደ በስምንተኛው ቀን እናቱ ወደ ቤተ መቅደስ ወስዳው ሊገረዝ በታሰበ ጊዜ በፍጡራን እጅ አልተገረዘም። ምላጩ በገራዡ እጅ እንዳለ ውኃ ሆኖ ተገኝቷል (መጽሐፈ ስንክሳር ጥር ስድስት)።ይህም በመለኮታዊ ኃይሉ ነው። እርሱም በግብር መንፈስ ቅዱስ ተገርዞ ተገኝቷል።ይህንንም ያደረገው ሰውን ንቆ ስርዓቱንም ጠልቶ ሳይሆን ደመ መለኮቱ ያለ ዕለተ ዓርብ የማይፈስ ስለሆነ እርሱ ባወቀ ይህን አደረገ ስሙንም አስቀድሞ በመልአኩ እንደተነገረ ኢየሱስ አሉት። ሉቃ 2፤21

በዚህም ምክንያት ቅድስት ቤተክርስቲያናችንም የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን የግዝረት በዓል በየዓመቱ ጥር 6 ቀን ታከብራለች (መጽሐፈ ስንክሳር ጥር ስድስት)። ስታከብርም በግዝረቱ እለት የተፈጸሙትን ተአምራት በማስተማርና በማሳወቅ ነው።

ለጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ክብርና ምስጋና ይሁን! አሜን!

15/01/2026

#ማስታወቂያ
በማኅበረ ቅዱሳን የአዲስ አበባ ማእከል እያስገነባ ያለውን ትውልድ መገንብያ እና አገልግሎት ማስፋፊያ ሕንጻ ለማጠናቀቅ ይረዳው ዘንድ የተለያዩ የገቢ ማሰባሰብያ መንገዶችን እያካሄደ ነው፡፡ ከነዚህ ውስጥ አንዱ ወደ ኢየሩሳሌም የጉብኝት ጉዞን ጨምሮ በርካታ ሽልማቶችን ያካተ ልዩ የበረከት ትኬት ነው። ትኬቱ በ100 ብር የሚሸጥ ሲሆን በመደበኛው መንገድ እንዲሁም በዲጂታል መንገድ ትኬቱ ለምእመኑ ተዘጋጅቷል።
ይህ የበረከት ትኬት ለሁለተኛ ጊዜ የሚካሄደ ሲሆን በ2017 በተካሄደው ሽያጭ ላይ በርካታ ምእመናን ተሳትፈው የዕጣ አሸናፊዎችም ሽልማቶቻቸውን ተረክበዋል ከተሸላሚዎቹ መካከል በጥበቃ ሥራ የሚተዳደሩ ባለዕድል የአንደኛ ዕጣ ወደ ኢየሩሳሌም ደርሶ መልስ ሽልማት መረከባቸው ይታወሳል፡፡
ስለሆነም የዘንድሮው ተሸላሚ እርስዎ ሊሆኑ ስለሚችሉ ዕጣውን በ100 ብር ገዝተው ከበረከት እየተሳተፉ በዛውም ይሸለሙ፡፡ ትኬቶቹን በአሐዱ ባንክ ቅርንጫፎች ፣ በማኅበረ ቅዱሳን ንዋየ ቅዱሳት መሸጫ ሱቆች እንዲሁ በዲጂታሉ መንገድ በብራና ፔይ መቁረጥ ይቻላል።
አንድ ትኬት ለመቁረጥ በስልኮ ንግድ ባንክ አፕልኬሽን በመክፈት pay for በመግባት ማኅበረ ቅዱሳን ውስጥ ኮድ mk2018 በመጠቀም መቁረጥ ይችላሉ፡፡
እንዲሁም ከአንድ በላይ ትኬት ለመቁረጥ፡-
https://links.branapay.com/lottery/2018 ይህን ሊንክ መጠቀም ይችላሉ፡፡

ይህን ትውልድ የሚገነባበት፣ የማኅበሩ አገልግሎት የሚጠናከርበት ትልቅ ፕሮጀክት በገንዘብና በማቴሪያል መደገፍ ከፈለጉ ተጨማሪ መረጃ
0944718282/ 0946383892 / 0944718282

Address

FINFINNE
Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Mk kiremu posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share