Pastor Sintayehu Bekele

Pastor Sintayehu Bekele to discuss different spiritual & social issues.

ይህን በቀላሉ መቀበል ይከብዳል😭😭😭። ይህ እንደ ኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን የሚያጎድለን ነው። መጽናናት ለሁሉ ይሁን!
30/10/2024

ይህን በቀላሉ መቀበል ይከብዳል😭😭😭። ይህ እንደ ኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን የሚያጎድለን ነው። መጽናናት ለሁሉ ይሁን!

"የወደፊት አባወራ ስለኾንኩ እስቲ ተንከባከቡኝ!" ይላል ይኼ ጎረምሳ። ምእመናን ልብ አድርጉልኝ፣ እኔ አባወራ ነኝ ምናምን በሚል አክት አድርጌ አይደለም። አልፎ አልፎ "ለአባ ለምን እንዲህ ...
26/08/2024

"የወደፊት አባወራ ስለኾንኩ እስቲ ተንከባከቡኝ!" ይላል ይኼ ጎረምሳ። ምእመናን ልብ አድርጉልኝ፣ እኔ አባወራ ነኝ ምናምን በሚል አክት አድርጌ አይደለም። አልፎ አልፎ "ለአባ ለምን እንዲህ ይደረጋል?" ሲል፤ ሴቶቹ አባወራ ስለኾነ ብለውት ነው።

በቀደም ታዲያ "እኔ ወደፊት ሚስቴን አንድ ሥራ አላሠራትም!" ቢል እኅቶቹ ካፉ ተቀብለው በአንድ ድምጽ "ለምን አሁን ከእኅቶችህ አትጀምርም!"
ያው ሁሉም ነገር ከቤት ሲጀምር ደስ ይላል ለማለት ነው።

በመንገዴ ላይ!አሁን አሁን በእኛ አገር አስቀያሚ ከኾኑ ነገሮች መካከል አንዱ መጓዝ ነው። የገዛ መኪናችሁን ይዛችሁም ኾነ በትራንስፖት መጓዝ ከባድ ኾኗል። መንገዶች ሁሉ ስጋት የረበበባቸው ና...
20/04/2024

በመንገዴ ላይ!

አሁን አሁን በእኛ አገር አስቀያሚ ከኾኑ ነገሮች መካከል አንዱ መጓዝ ነው። የገዛ መኪናችሁን ይዛችሁም ኾነ በትራንስፖት መጓዝ ከባድ ኾኗል። መንገዶች ሁሉ ስጋት የረበበባቸው ናቸው። እንግዲህ ምን ይደረጋል? አለመጓዝ ደግሞ አትችሉም።

ወደ ቡታ ጅራ ጉዞ ነበረኝ፤ በየመንገዱ የሚያስቆማችሁ አበዛዙ! ትራፊኩ፣ የመንገድ ተቆጣጣሪው፣ ሚሊሻው (ሊያውም ከየት ወገን እንደኾነ እንኳ የማታውቁት)።

አስቁመዋችሁ በልከኛ ስነምግባር ቢያነጋግሯችሁ ደግ ነበር፤ እነሱ እቴ። ያለ አግባብ መንገዳቸው ላይ የሄዳችሁባቸው ነው የሚያስመስሉት። ቅጥ ባጣ ሁኔታ "ወዴት ነው!" ይሏችኋል፤ ትመልሳላችሁ። "ለምንድነው!" ይሏችኋል፤ ትመልሳላችሁ። ፍትሻ አይሉት ምን ግራ የሚያጋባ! ይቀጥላሉ፤ "ምን አለ!" ምንም የለም! ትመልሳላችሁ። ከዛ እንደ ሰዐቱ ሁኔታ ትጠየቃላችሁ፤ ጠዋት ከኾነ "እና ቁርስ ግዛኣ?" ረፈድ ካለ "የምሳ ስጠና!" ካነሰ ካነሰ የሻይ ወይ የውሃ ይሏችኋል። መንግሥት ለምናችሁ ብሉ ብሎ አሰማርቷቸው እንደሁ እንጃ!
እግዚአብሔር ያሳያችሁ? ረጭ ያለ መንገድ ላይ መሣሪያ የያዘ ሰው አስቁሟችሁ እንዲህ ያለ ነገር ሲገጥማችሁ? ስንት ቦታ አምሳና መቶ ብር ትሰጣላችሁ? እንደማንኛውም ለማኝ "እግዚአብሔር ይስጥልኝ!" ብላችሁ አትሄዱ ነገር መሣሪያውስ? እኔማ ዛሬ ሊፍት ሁሉ ሰጠሁ ሆሆሆ! "ግራህን ይዘህ ቁም!" ሲለኝማ፣ ነፍሴ ጉሮሮዬ ስር ተወተፈች።"እግዚአብሔር ይስጥልኝ! መልካም መንገድ" ብሎኝ ሲወርድ፤ አጠገቤ የነበረውን ውሃ ገልብጬ ነው ነፍሴን ወደ ቦታዋ የመለስኳት። እና እባካችሁ አታሳቅቁን!

የመካር ክርስቲያናዊ ወጎች መርሐ ግብር፣ ወቅታዊና ፈያጅ የሆኑ ክርስቲያናዊ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ የተሻለ ጥናትና አሳባቸውን በጥራት የማቅረብ ብቃት ያላቸው አገልጋዮች የሚናገሩበት ነው፡፡ ተናጋ...
19/02/2024

የመካር ክርስቲያናዊ ወጎች መርሐ ግብር፣ ወቅታዊና ፈያጅ የሆኑ ክርስቲያናዊ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ የተሻለ ጥናትና አሳባቸውን በጥራት የማቅረብ ብቃት ያላቸው አገልጋዮች የሚናገሩበት ነው፡፡ ተናጋሪዎች፣ የአገራችን ወንጌላዊ ክርስትና እየተጋፈጣቸው ያሉ ልዩ ልዩ ፈተናዎችን የተመለከቱ ርዕሰ ጉዳዮችን አንስተው በማብራራት፣ መጽሐፍ ቅዱስን መሠረት ያደረገ ፈያጅ የመፍትሔ አሳብ በነጻነት ያቀርቡበታል፡፡
ተናጋሪዎች አሳባቸው በተመጠኑ ደቂቃዎች፣ በጥናት የታገዘ የአሳብ ጥልቀትን፣ ሳቢነትንና በአድማጩ ዘንድ ተነሣሽነት መፍጠርን አጣምሮ በያዘ አቀራረብ እንዲያቀርቡ የሚጠበቅ ሲሆን፤ ከዚህ በተጨማሪ በመድረኩ በሥነ መለኮታዊ ይዘታቸው ጠንካራ የሆኑና የመድረኩን ዕሴቶች እንደሚያንጸባርቁ የታመኑባቸው ቀደምት ዝማሬዎች፣ እንዲሁም አስተማሪና ሞጋች የኪነ ጥበብ ሥራዎች ይቀርባሉ፡፡

የዩቲዩብ ቻናላችን መካር ወጎች (Mekar Wegoch) ሲሆን በፌስቡክ፣ ቲክቶክና ኢንስታግራም በተመሳሳይ ስያሜ ያገኙናል፡፡

ከዚህ በታች የቀረበው የምክር ቃል ወንድም አበባዬ በሁለተኛው የመካር መድረክ ያቀረበው ሲኾን፤ እንድትከታተሉ እየጋበዝን፣ እግረ መንገድ ቻናሉን ሰብስክራይብ ያድርጉ!

በመካር ክርስቲያናዊ ወጎች መድረክ፥ በወንድም አበባዬ ቢተው የቀረበ "የምክር ቃል" Bitew Kal

የሁለት ነቢያቶች ወግየመጀመሪያው ነቢይም ቢሉ ነቢይ ነው፡፡ የማይደበዝዘውን አሻራ ትቶ ያለፈ እውነተኛ ነቢይ፡፡ የትዳር አጋሩን ጨምሮ በቅርብ የሚያውቁት ሁሉ ስለ ፈሪሃ እግዚአብሔሩ የሚመሰክ...
22/01/2024

የሁለት ነቢያቶች ወግ

የመጀመሪያው ነቢይም ቢሉ ነቢይ ነው፡፡ የማይደበዝዘውን አሻራ ትቶ ያለፈ እውነተኛ ነቢይ፡፡ የትዳር አጋሩን ጨምሮ በቅርብ የሚያውቁት ሁሉ ስለ ፈሪሃ እግዚአብሔሩ የሚመሰክሩለት ነቢይ፡፡ ይህ ሰው እግዚእሔርን በመፍራት በጽድቅ እንዳገለገለ መጠራጠር አይቻልም፡፡ እግዚአብሔር የሰጠውን ነቢያዊ ጸጋ ወደ ገንዘብ የመለወጥ ዝንባሌ አልነበረውም፤ ምናልባትም ከአገልግሎቱጋ ተያይዞ በፊቱ የቀረቡ እጅ መንሻዎችንም “የሚገባን ነው ያደረግነው!” በሚል ንጹሕ መንፈስ ሳይገፋም አልቀረም፡፡ ንጹሕ ሕይወት እና የጽድቅ ኑሮ የሚጠይቀውን ዋጋ ሁሉ በጄ ብሏል፡፡

የማይቀረው ሞት ወደ እርሱ ሲመጣ ለሚስቱ እና ለልጆቹ ትቶ መሄድ የቻለው ብዙ ዕዳ እና ትልቅ እግዚአብሔርን መፍራት ነበር፡፡ በአልባሌ ሁኔታ ከተሰበሰበ እልፍ ሀብት ይልቅ እግዚአብሔርን መፍራት በስንት ጣእሟ! የሚጠፋውን ረብ በመፈለግ ከጽድቅ ጎድሎ፣ በእግዚአብሔር ስም በማምታታት ጥሪት አከማችቶ ሞቶ ቢሆን ኖሮ፣ ልጆቹ ላይ “የሌባው ነቢይ ልጆች!” የሚል ተቀጽላ ይለጠፍባቸው ነበር፡፡ ከዚህ ይልቅ የባለ ዕዳው ነቢይ ልጆች መባል ክብር ነው፡፡ ሚስት ስለ ባሏ የጽድቅ ሕይወት በአደባባይ ጮክ ብላ ለመናገር አታፍርም፡፡ እንዲህ ላሉት እግዚአብሔር ከዙፋኑ መውረዱ አይቀርም! እናም ተአምራት ኾነ፡፡ ጻድቅ ሲጣል፣ ዘሩም እህል ሲለምን አላየሁም ማለትም ይኸው ነው፡፡

እዚህ ደግሞ አለልህ ነቢይ የሚል ማዕረግ ራሱ ላይ የደረተ፤ ዓይኑን በጨው አጥቦ የእግዚአብሔርን ስም ተገን አድርጎ ሲረዝፍ የኖረ፡፡ በደሃ እንባ፣ በሐሳዊ ትንቢት እና በሽያጭ ጸሎት ከብሮ ሲያበቃ “በሁሉ የተሳካሁ ነኝ!” ሊል አደባባይ ለመውጣት ሌላውን ቢቀር ራሱን የማይፍር፡፡ እንደ ጎበዝ ተዋናይ በውሸት ቱሪ ናፋ፤ ለማጨብጨብ የተፈጠረ የሚመስለውን እድምተኛ ያስጨበጭባል፡፡ ይኸው ነው ነውር ሱፍ ለብሳ፣ በከረቫት አጊጣ እውነትን በአደባባይ ረምርማለች፡፡ ለነውረኞች ሁሉም አደባባዮች ክፍቶች መኾናቸውም ተረጋግጧል፡፡ የትም ፍጭው ዱቄቱን አምጭው እንዲሉ፤ በየትኛውም መንገድ ይዞ መገኘትን ጎሽ የሚሉት አነቃቂቆች ግብራቸው ሥነ ምግባርን በአደባባይ መቅበር እንደሆነም በዚህ አስረገጡ፡፡ አሳዛኙ ጉዳይ ለውሸት ጀግና የሚያጨበጭብ፤ የሐሰትን ከበሬታ የሚቋምጥ ትውልድ እዚህም እዚያም መፈጠሩ ነው፡፡

ሐሳዊው ነቢይ በአደባባይ ለልጆቹ በሸፍጥ ያከማቸውን ሀብት ሳይሆን፣ ፈሪሃ እግዚአብሔርን ሊያወርሳቸው እንደሚሻ ተናገረ፡፡ ያልዘሩት እንደምን ኾኖ ይበቅላል? በፈሪሃ እግዚአብሔር ያልታነጸ ወላጅ ለልጆቹ ፈሪሃ እግዚአብሔርን ሊያወርስ የሚችልበት መለኮታዊ ስሌት የለም እኮ፡፡

ያ ዘኪዎስ ዐጭሩ ሰው፣ በእውነተኛ መነካት በጌታ በተነካ ጊዜ አንዳች እንዳገኘው የለፈለፈው ኑዛዜ ያለ ሀቅ የሰበሰብኩትን ሁሉ እክሳለሁ የሚል ነው፡፡ አንገት በሚያስደፋ ክፉ ድርጊት ቀና ማለት እብሪተኝነትን እንጂ ጽድቅን አያሳይም፡፡ ያለፈው እንዳለ ኾኖ ልባም ሰው ቀልብ ገዝቶ ይሰበሰባል፤ መንገዱ ደግሞ ንስሐ ነው፡፡ ለሚመለሱ ምልስ ጌታ አለ፤ አንገቱን ያደነደነ ግን ድንገት ይሰበራል፡፡ የልጆች በፈሪሃ እግዚአብሔር የታነጸ ሕይወት፤ ፈሪሃ እግዚአብሔር ካላቸው ወላጆች ይቀዳል፡፡ አሁንም በሕይወት የመኖር ጥቅሙ የንስሐ ዕድል ማግኘቱ ነውና፣ በሸፍጥ ልብን አሳብጦ አደባባይ ከመሙላት ልብን ሰብሮ ንስሐ መግባት፡፡

ይህ ደሀነትን ጎሽ ለማለትና ሀብትን ለማንኳሰስ የተጻፈ ጽሑፍ አይደለም።

 !የአምላክ ሰው መሆን ጉዳይ ባለፈው ዘመን ሲያነጋግር የኖረ፤ የዘመን ዕድሜ እንደረዘመ ልክም ሲያነጋግር የሚኖር የዝንተ ዓለም አጀንዳ ነው፡፡ በእውነትም መጽሐፍ እንደሚናገር ይህ ምስጢር ታ...
26/04/2023

!

የአምላክ ሰው መሆን ጉዳይ ባለፈው ዘመን ሲያነጋግር የኖረ፤ የዘመን ዕድሜ እንደረዘመ ልክም ሲያነጋግር የሚኖር የዝንተ ዓለም አጀንዳ ነው፡፡ በእውነትም መጽሐፍ እንደሚናገር ይህ ምስጢር ታለቅ ነው፡፡ ይህ ርእሰ ጉዳይ ምንተዳዬ ተብሎ የሚታይ፣ እንደፍጥርጥሩ ተብሎ የሚተውም አይደለም፡፡ ጉዳዩ የሞት እና የሕይወት ጉዳይ ነውና፡፡ ስለ ምንም ነገር ማወቅ በራሱ በጎ ሊሆን ይችላል፤ የዘላለምን የሕይወት ዕጣ ፈንታ በመወሰን ጉዳይ ግን ያንያህል ላይፈይድ ይችላል፡፡ የአምላክ ሰው መሆን ምስጢርን መረዳት እና በዚህ አሠራር ለተገለጠ መለኮታዊ አደራረግ ራስን ማማጠን ግን ዘላለማዊ ዕጣ ፈንታን የሚወስን ነው፡፡ ስለዚህ ከዚህ ፍለጋ መቦዘን የተገባ አይደለም፡፡

የእግዚአብሔር አንድያ ልጅ ፍጹሙ አምላክ ክርስቶስ ጌታ ስለ ዓለሙ ሁሉ ኃጢአት ራሱን መስዋዕት ከከፈለ እነሆ ሁለት ሺህ ዘመን አለፈ፡፡ ሰሞኑን የዘከርነው ስቅለት እና ትንሳኤም የእዚያ መታሰቢያ ነው፡፡
ታዲያ እግዚአብሔር የተሰበረበትን ዓለም፤ የጠፋውንም የሰው ልጅ ወደ ክብር/ሕይወት ለመመለስ ይህን የሚያህል ዋጋ ከሚከፍል ሌላ መንገድ አልነበረም ወይ? ብሎ መጠየቅ የተገባ ሊሆን ይችላል፡፡ ነገር ግን ምላሹ የማያወላዳ ነው”አዎን ሌላ መንገድ አልነበረም!” እውነት እውነት እላችኋለሁ ቢኖር እግዚአብሔር በቅዱሱ ቃሉ ይገልጠው ነበር፡፡

ለምን? የሚል ካለ ምክንያቱ፣ ሁሉ በአንድነት የረከሱ ስለነበረ ነው፡፡ ፍጹሙ ጻድቅ እግዚአብሔር ያለ በደል ካሳ ዓለሙን ማዳን ስለማይቻለው ነው፡፡

አስቀድሞ በቅዱሱ መጽሐፍ እንደተነገረ ደም ሳይፈስስ ስርየት ባለመኖሩ (ዘጸ 29÷21, ዕብ 9÷22)፣ ለዓለሙ ሁሉ የኃጢአት ማስተስረያ የሚበቃ የአንድ ንጹሕ ሰው ደም ሊፈስ የተገባ ነበር፡፡ ለዚህ የሚበቃ ደግሞ በፍጥረት ዓለሙ መካከል የለም፤ ጨርሶ የለም፡፡ ማንም ማንንም ሊዋስ እስከማይችል ድረስ ሁሉ በአንድነት ረክሷልና፡፡

ሐዋርያው ጳውሎስ በሮሜ መልእከቱ ምዕራፍ ሦስት ላይ ይህን አብራርቶ ይናገራል፤ (ሮሜ 3÷9-25) ጠቅለል ባለ ሁኔታ ክፍሉ፣ ያለ ልዩነት የሰው ልጆች ሁሉ በአንድነት እንደረከሱና ጻድቅ ማንም እንደሌለ ያትታል፡፡ ሕግም ኃጢአትን አረጋጋጭ እንደመሆኑ፣ በሕግ ኃጢአት ታወቀ እንጂ ለማንም የጽድቅ ብቃትን አልሰጠም፤ በመሆኑም በሕግ ሥራ በኩል ማንም ሊጸድቅ አይቻለውም ይላል፡፡ ሐዋርያው በገላትያ መልእክቱም እንዳረጋገጠው “ጽድቅ በሕግ በኩል የሚገኝ ከሆነማ፣ ክርስቶስ እንዲያው በከንቱ ሞተ ማለት ነዋ!” (ገላ 2÷21 ዐ.መ.ት) ይላል፤ ሕጉ እያለ ክርስቶስ መጥቶ እንደተሰዋም ልብ ይሏል፡፡

እንግዲህ ኃጢአተኛው ሰው ሌላ የሚጸድቅበት መንገድ ስለሌለው፤ ኃጢአተኛውን በሚያጸድቅ፣ ለዓለሙ ሁሉ ኃጢአት ማስተስረያ ይሆን ዘንድ ደሙን አፍስሶ ቤዛ በሆነን፣ በእርሱ በኩል በጸጋው ይጸድቃል፡፡ “ጸጋው በእምነት አድኖአችኋልና፤ ይህም የእግዚአብሔር ስጦታ ነው እንጂ ከእናንተ አይደለም፡፡” ኤፌ 2÷8

የመስቀል ሞቱ እግዚአብሔር የኃጢአትን ቅጣት ያወራረደበት እና ጽድቁን ያሳየበት ነበር፤ “ይህም በፊት የተደረገውን ኃጢአት በእግዚአብሔር ችሎታ ስለ መተው ጽድቁን ያሳይ ዘንድ ነው” (ሮሜ 3÷25)፡፡ ክርስቶስ ቤዛችን በመሆኑ ይህ ሊሆን ግድ ነበር፡፡

ክርስቶስ በምድር መጥቶ ያየው መከራ በእውነት የሚያስገርም ነው፡፡ ካየው ሁሉ መከራ በላይም ሰው መሆኑ ብቻውን የውርደት ውርደት ነው፡፡ ነገር ግን እኛን የወደደበት ታላቅ ፍቅሩ ይህን እንዲያደረግ አስገደደው፡፡ በኃጢአታችን ይገባን የነበረውን ሞት ወስዶ ሞተልን፤ እኛንም ስለማጽድቀ ተነስቶ፣ በትንሳኤው አጸደቀን፡፡ (ሮሜ 4÷24)

አዎን ሌላ መንገድ ስለሌለ፣ ብቻውን ሊያድነን ይህን ሁሉ ዋጋ ከፈለ፡፡ እግዚአብሔር ሊድኑ ለተገባቸው ሰዎች ሁሉ አማራጭ በሮችን አላዘጋጀም፡፡ እነሆ አንድ መንገድ መርቆ ከፍቶልናል፡፡ መጽሐፍ እንደሚያረጋግጥልን በእርሱ/በክርስቶስ በኩል የሚመጡትንም ፈጽሞ ያድናቸዋል፡፡ መዳን እንዲሆንልን ስለዚህ ሞተ፣ ተቀበረ፣ ተነሳ እና በክብር በሚሆን አመጣጡ ተመልሶ ይመጣል!!!

“እነሆ የዓለምን ኃጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ።” የዮሐንስ ወንጌል 1÷29

#ማሳሰቢያ ይህን ጽሑፍ ሼር ማድረግ ይበረታታል!

መውረድ ያልከበደው!“ውረድ አይባልም፤ እንውረድ ነው የሚባለው፡፡” የሚል ንግግር በቅርቡ ሰምተናል፡፡ (ደሞ ፖለቲካ አይደለም፤ ለነገሬ ማዋዣ ነው፤ በርግጥ መውረድ ምን ያህል ከባድ መሆኑንም ...
17/04/2023

መውረድ ያልከበደው!

“ውረድ አይባልም፤ እንውረድ ነው የሚባለው፡፡” የሚል ንግግር በቅርቡ ሰምተናል፡፡ (ደሞ ፖለቲካ አይደለም፤ ለነገሬ ማዋዣ ነው፤ በርግጥ መውረድ ምን ያህል ከባድ መሆኑንም ሳያስረዳ አይቀርም፡፡) በእኛ መንደር መድረኩ የሞቀው ዘማሪ ከአሁን አሁን ወረደልን ብለን ስንጠብቅ፤ “ማነው ውረድ የሚለኝ!?” ብሎ ይቀውጠዋል፡፡ (በነገራችን ላይ ማነው ውረድ የሚለኝ? የሚለው ከመዝሙር ይልቅ ለአቋም መግለጫ ይቀርባል፡፡ እውነትም ታዲያ አቋማቸውን ካሳወቁን በኋላ ለሚቀጥሉት ሠላሳ እና አርባ ደቂቃዎች አይወርዱም፡፡)

እንዲያ ብቻ አይደለም በየቤተክርስቲያኑ የአገልግሎት ሹመት ማገልገያነቱ ቀርቶ እንደ ስልጣን ስለሚቆጠር፤ የስልጣን ወንበሩን የተቆጣጠሩት ሰዎች መውረድ ይቸግራቸዋል፡፡ በስማቸው ቤተክርስቲያን አቋቁመው ለዘላለም ከሚነግሡት ጀምሮ በየአጥቢያው እና በየቤተ እምነቱ ራሳቸውን እንደ ሹመኛ ቆጥረው “ማነው ውረድ የሚለኝ?” የሚሉ የትየለሌ ናቸው፡፡ አንዳንዶች ከተቋሙ ይልቅ የራሳቸውን ጥቅምና ክብር የሚያስከብር መመሪያ እና ደንብ ሳይቀር ያዋቅራሉ፤ ሁሉም ነገር ስለ እነርሱ እና ስለ እነርሱ ብቻ ይሆናል፡፡ በዚያ ላይ መንፈሳዊ ስብዕናን የማይመጥነው ኩፈሳቸው አይጣልባችሁ፡፡

በጣም አስገራሚው ነገር ደግሞ፣ እንዲህ ያሉት መውረድ የሚቸገሩቱ ከምንም የተነሱ መሆናቸው ነው፡፡ ምንም ያልነበሩ ናቸው አንዳች የሆኑት፤ በጌታ ጸጋ እና ምሕረት፡፡

በዚህ የፋሲካ ሰሞን፣ ለሁልጊዜውም ይህን ማሰብ የተገባ ነው፡፡ ሐዋርያው ጳውሎስ በፊልጵስዮስ መልእክቱ በክርስቶስ ኢየሱስ የነበረውን አስቡ ይለናል፡፡ ለዘመኑ ጥንት ለሕይወቱም ፍጻሜ የሌለው አምላክ፣ የማይወሰነው እና ዘመን የማይቆጥረለት አምላክ፤ በአጭር ቁመት፣ በጠባብ ደረት ተወሰነ፡፡ ርቀቱ ይህ ነው ከማይባል ከፍታ፣ ልክ ወደሌለው ዝቅታ ወረደ፡፡ ቀዳሚ እና ተከታይ የሌለው የአብ አንድያ ልጅ ሰው ሆነ፡፡ እርሱ ራሱም ከአብ አባቱ የማያንስ አምላክ ነው፡፡ የአምላክ ሰው መሆን ምስጢር ከመለኮት የብርሃን ረድኤት ለወረደለት ካልሆነ በቀር፣ ለፍጥረታዊ አእምሮ የሚገጥምም አይደለም፡፡

ከሰው ጋር ሊለካ በማይችል ፍቅር የወደቀው አምላክ ግን የፍቅር ስበት ዙፋኑን አስለቀቀው፣ ከማይወረድበትም ወረደ፡፡ ፍጹም ሰው ሆነ፤ በሰዎች መካከል አደረ፤ ከኃጢአት በቀር ሰው የሚሆነውን ሁሉ ሆነ፡፡ መጽሐፈ ቅዳሴ ስለ እርሱ እንደሚለው ሹመታትን እና ስልጣናትን ሁሉ የፈጠረው እርሱ ወረደ፡፡

አዎን በኃጢአት ረክሼ ስለተበላሸሁት ስለ እኔ ወረደ፤ ነፍሴን ከመቀመቅ ሊያወጣ፣ ሕይወትን፣ የዘለአለም ሕይወትን ሊያቀዳጀኝ ወረደ፡፡ አምላክነቱ፣ ባሕሪያዊ ክብር እና ከፍታው መውረድን የማይቻል አላደረገበትም፡፡ ስለ እኔ መውረድ አልከበደውም፤ ወረደልኝ፤ ተዋረደልኝ!!! ያለ ልክ አከብረው ዘንድ ዘመኔ የእርሱው ነው!!!!

“በምስሉም እንደ ሰው ተገኝቶ ራሱን አዋረደ፥ ለሞትም ይኸውም የመስቀል ሞት እንኳ የታዘዘ ሆነ።” ፊል 2፡8

የእኔነት አባዜ፣ የግለኝነት ስካር!የዚህ ዘመን የቤተክርስቲያን አንዱ ምናልባትም ዋነኛው ተግዳሮት እኔነት ሳይሆን አይቀርም፡፡ እጅ ለእጅ ተያይዞ ማገልገል፣ ተከባብሮ መንግሥቱን ማስፋት፣ አን...
30/03/2023

የእኔነት አባዜ፣ የግለኝነት ስካር!

የዚህ ዘመን የቤተክርስቲያን አንዱ ምናልባትም ዋነኛው ተግዳሮት እኔነት ሳይሆን አይቀርም፡፡ እጅ ለእጅ ተያይዞ ማገልገል፣ ተከባብሮ መንግሥቱን ማስፋት፣ አንተ ትብስ የሚል መንፈስ ጨርሶ እየጠፋ ይመስላል፡፡ ባመዛኙ በቤተክረስቲያን መካከል ያለ ክፍፍልም ምንጩ ይኸው ነው፡፡ እኔነት አዙሪቱ ከባድ ነው፡፡ እኔነት ራስን የማንገሥ ሩጫ ነው፡፡ እኔነት ዙሩ ሲከርር “ከእኔ በቀር!” ያሰኛል፤ ይህ ደግሞ አንጋጦ ከመትፋት አይተናነስም፡፡ “ከእኔ በቀር” ሊል የተገባው አንዱ አንድዬ ብቻ ነውና፡፡

ለእኛ “እኔነት” ከፍጥረታችንም ጋር እንኳ አይገጥምም፡፡ ስሪታችን በእኔነት ክንፍ ለብቻ ለመክነፍ የሚያበቃ አይደለም፡፡ አንዳችን ያለሌላችን ምንም ነን፡፡ የቤተክርስቲያን ክብር ደግሞ በአብሮነት ውስጥ የሚገለጥ ልምላሜ ነው፡፡ ማንም ብንሆን ለብቻችን ምንም ነን፡፡ ለዚህ ነው መጽሐፍ ቅዱስ ምንነታችንን በአካል መስሎ የሚያስተምረን፡፡ ከአካል ክፍሎች አንዱ የጎደለ እንደሁ፣ በሙሉነት መድመቅ አይቻልም፡፡ ያው “ጎዶሎ” የሚል ተቀጥላ ያስከትላል፡፡

ብቻ የመድመቅ አባዜ የሉሲፈር መንገድ ነው፡፡ የገነነ እኔነት ውስጥ ትእቢት አሸምቆ አለ፡፡ ዶ/ር ኃይሉ ቸርነት በአንድ ወቅት “ትእቢት በእኔነት ጢም ብሎ መሞላት ነው” ሲል ሰምቼዋለሁ፡፡ እውነት ነው፤ የገነነ እኔነት መጨረሻን ያከፋል፡፡ አብሮት በሚያገለግለው ወንድም ምክንያት በቂ ከበሬታ ያጣ የመሰለው ወንድም፣ “ሁለት ፀሐይ በአንድ ሰማይ ላይ አይደምቅም” በሚል አመክንዮ ከወንድሙ ተለይቶ ብቻውን የሚደምቅበትን የገዛ ቸርቹን ከፍቷል፡፡ (በነገራችን ላይ የአገልግሎት ጥሪ ግብ ራስን ማድመቅ ሳይሆን፣ ራስን መደበቅ ነው፡፡) እዩኝ እዩኝ ማለት የልከኛ መንፈሳዊነት መገለጫ አይደለም፡፡ የአገልግሎቱ እና የጸጋው አሠራር ግብ እርሱን እዩልኝ የማለት ነው፡፡

የዚህ ዘመን የአገልግሎት ዝንባሌ ግን ባመዛኙ ሐዲዱን የሳተ ይመስላል፡፡ የአዲስ ኪዳን ጸሐፍት አብሮነትን በእጅጉ ያበረታታሉ፡፡ ሐዋርያው ጳውሎስ በአብዛኞቹ መልእክቶቹ ውስጥ እኔ በማለት ፈንታ “እኔና…” ሲል እናነባለን፡፡ ሰላምታ እንኳ ሲያቀርብ “እኔና አብረውኝ…” ይላል፤ ምን ጸጋ የበዛለት ቢሆን፣ ብቻውን እንዳልቆመ ጠንቅቆ ያውቃል፡፡

አሁን የእኔነት አባዜ በእጅጉ ገንኖ ይታያል፡፡ እኔነት በአልባሌ ጭብጨባ ይፋፋል፤ ያልተካደ እኔነት የመስቀሉ ጠላት አድርጎ ያቆማል፡፡ የደረስንበት ጥግ እኔነትን የሁሉ መፍትሔ እና መላ አድርጎ እስከማቅረብ የተለጠጠ ነው፡፡ “እኔ እንደሌላው አይነት አይደለሁም” እስከማለት ደፍረናል፡፡

በየግል ቤተክርስቲያኖቻችን እንደነገሥን ለማሳየት በየደጆቻችንን ደማቅ ፎቶዎቻችንን በየአቅጣጫው ሰቅለናል፡፡ በየመርሐግብሮቻችን “ዋነኛው እኔ ነኝ!” ለማለት፣ ከጋበዝናቸው ሰዎች አናት ላይ ደማቅ ፎቶዎቻችንን እናኖራለን፡፡ በአዳራሹ መካከል የተለየ የከበሬታ ወንበር አሰናድተን በእርሱ ላይ እንሰየማለን፤ በሌለን ጊዜ እንኳ ሌላ አይቀመጥበትም፡፡ ክርስቶስ ራስ በሆነለት አካል ውስጥ፣ ከአካሉ ብልቶች መካከል እንደ አንዱ በመሆን ፈንታ፣ ከ“ራሱ” በላይ ጠቃሚ መሆናችንን ለፍፈን በሕዝቡ ላይ ሰልጠነናል፡፡ የመለኮት ሙላት ሁሉ ተጠቅልሎ እጃችን እንደገባ አምነን በእኔነታችን ሰክረናል፡፡ ክርስቶስ በእኛነታችን እንዳይገለጥ እኔነት ትልቁ መጋራጃ ነው፤ ቢያምም የእኔነትን መጋረጃ ገፍፎ መጣል የተገባ ነገር ነው፡፡

ይኸው ሩጫችን ደግሞ መጨረሻ ያለው አይመስልም፡ በየዕለቱም በእኔነት የፋፉ ሰዎች ብቅ ብቅ እያሉ ነው፡፡ በዘመን እላቂ እንደመኖራችን ብዙ ተስፋ ማድረግ ላይኖርብን ይችል ይሆናል፡፡ ነገር ግን ደግሞ ልኩ ይኸው መስሏቸው በቅንነት እና ባለማወቅ በዚህ መንገድ የተጠመዱትን ማዳን ይቻል እንደሆን እውነትን እንናገራለን፡፡ ከገነነ እኔነት መዳን ከብዙ ነገር መዳን ነው፡፡ የእኔነት ስካር ወስዶ ወስዶ የት እንደሚደፋ አይታወቅም፡፡ ከእኔነት መዳን ሌለውን በልኩ ለማየት እና ንጉሡን በእውነት ለማላቅ ዕድል ይሰጣል፡፡

ሕዝብ ሁሉ ግርርርር ብሎ ይከተለው የነበረው መጥምቁ ዮሐንስ በጮክታ “እኔ አይደለሁም!” ብሎ ወደ መሲሁ እጁን ጠቁሟል፡፡ ይህ አይነተኛው ማምለጫ ነው፡፡

“እርሱ ሊልቅ እኔ ግን ላንስ ያስፈልጋል።” ዮሐ 3፡30

15/01/2023

የአንዳንድ ሰው መንፈሳዊ ትጋት የትዕቢቱ ምግብ ነው። በተጋ መጠን የትዕቢት ጡንቻው ይፈረጥማል።
እግዚአብሔር ከትዕቢት ይጠብቀን!!

 !ሐዋርያው ጳውሎስ ለቲቶ በጻፈው መልእክት ሦስተኛው ምዕራፍ “ሰዎች…ክፉ እንዳይናገሩ፣ ሰላማውያን እንዲሆኑ፣ ለሰዎችም ሁሉ ከልብ የመነጨ ትሕትና እንዲያሳዩ አስገንዝባቸው፡፡” ቁ. 1-2 የ...
26/09/2022

!

ሐዋርያው ጳውሎስ ለቲቶ በጻፈው መልእክት ሦስተኛው ምዕራፍ “ሰዎች…ክፉ እንዳይናገሩ፣ ሰላማውያን እንዲሆኑ፣ ለሰዎችም ሁሉ ከልብ የመነጨ ትሕትና እንዲያሳዩ አስገንዝባቸው፡፡” ቁ. 1-2 የሚል ማሳሰቢያ ያስተላልፍለታል፡፡

ክርስትያን መኾን ካለፈው አሮጌ የሕይወት ስርዓት ድኖ፣ ለአዲስ ልደት በሆነው መታጠብ ታድሶ፤ የክርስቶስን ፈለግ እየተከተሉ መኖር ነው፡፡ ክርስትናን ከክርስቶስ ሕይወት ውጭ ማሰብ ከቶውኑም አይቻልም፡፡

ከክርስቶሳዊው ሕይወት ከምንቆረሰው ብዙ ነገር መካከል አንዱ ጥላቻን መጥላት ነው፡፡ ጥላቻ ያለፈው ሕይወታችን ኹነኛ መገለጫ ነው፡፡ በቀድሞው ሕይወት ጥላቻ ይቀናናል፡፡ ፈጥኖ ልባችን የሚያዘነብለው ወደ ጥላቻ ነው፡፡ ከምንም ተነስተን ሳይቀር እንጠላለን፤ እንጠላላለን፡፡

ጥላችን አንዳንዴ ድንበር የለሽ ነው፤ ማንንም ቢኾን እንጠላለን፤ ወዳጆቻችንን፣ የስጋ ዘመዶቻችንን፣ ውለታ ያደረጉልን፣ በሆነ ዘመን አብረናቸው እፍ ያልናቸውን ሰዎች ሁሉ፡፡ በተዋደድንበት ልክ ልንጠላላ እንችላለን፡፡ በአንድ ጀልባ አብረን ካልቀዘፍን፤ በአንድ አእምሮ ካላሰብን፤ በአንድ አፍ ካልተናገርን ስንል ከርመን ሁሉ፣ ድነገት ዐይንህ ለአፈር እንባባላለን፡፡

ዓለሙን በጦርነት የሚንጠው ይህ ከግለሰብ ጀምሮ ተወልዶ የሚያድገው የጥላቻ ወጀብ ሳይሆን አይቀርም፡፡

እውነቱን ለመናገር ጥላቻ አብሮነትን የሚፈትን ጨለማ ነው፡፡ ጥላቻ በኃጢአት ጦስ በሰዎች ላይ የነገሠ ክፉ ባላንጣ ነው፡፡ በዚህ ዓለም ከዚህ ሊያድን የሚችል አንዳችም መላ የለም፡፡ በኃጢአት ተበክሎ ባለው ማንነት ውስጥ ሁሉ ጥላቻ መሽጎ አለ፤ አጋጣሚውን ባገኘ ጊዜ ሁሉ ከምሽጉ ወጥቶ ግዳዩን ይፈጽማል፡፡ ለዚህ ነው በዓለሙ መካከል ዘላቂ ወዳጅነትን አስሶ ማግኘት ቸጋራ የሚኾው፡፡

ጥላቻ በጌታችን የመስቀል ሥራ ብቻ ድል ሊነሳ ችሏል፡፡ ጌታችን በመስቀሉ ጥልን ገድሎ ሰላምን አንግሷል፡፡ ጥልን ገዳዩ ጌታም ከራሱ ጋር አስታርቆን፣ ላይጠላን ወዶናል፡፡ መውደድ ብቻም ሳይኾን ደግሞ ፍቅሩን በልባችን አፍስሶታል፡፡ እናም ቅዱሳን በጥላቻ መርዝ ሳይበከሉ በዚህ ሕይወት እንዲግሡ ይጠበቃል፡፡

ከላይ ባነሳሁት ጥቅስ ላይ ሐዋርያው ጳውሎስ ወረድ ብሎ “ቀደም ሲል እኛ ራሳችን ማስተዋል የጐደለን፣ የማንታዘዝ፣ የተታለልን፣ ለተለያየ ምኞትና ምቾት ባሪያ ሆነን የተገዛን ነበርን፤ እየተጣላንና እርስ በርስ እየተጠላላን በክፋትና በምቀኝነት እንኖር ነበር።” ቁ.3 ይላል፡፡

ምናልባትም እንዴት ነበርን? የሚለው ከተነሳ ከላይ የተነሳው ብቻ በቂ ሊሆን አይችልም፡፡ ክፋታችን ጥግ የለሽ ነበር፤ የውድቀታችን ጥልቀትም መግለጫ አልነበረውም፡፡ የኾነው ኾኖ ግን ሐዋርያው ነገር ግን ብሎ ይለጥቃል፤

“ነገር ግን የአዳኛችን የእግዚአብሔር ቸርነትና ፍቅር በተገለጠ ጊዜ፣ ስላደረግነው የጽድቅ ሥራ ሳይሆን፣ ከምሕረቱ የተነሣ አዳነን። ያዳነንም ዳግም ልደት በሆነው መታጠብና በመንፈስ ቅዱስ መታደስ ነው፤ ይህንም መንፈስ እግዚአብሔር በአዳኛችን በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል በእኛ ላይ አትረፍርፎ አፈሰሰው፤ ይኸውም በጸጋው ጸድቀን የዘላለምን ሕይወት ተስፋ ይዘን ወራሾች እንድንሆን ነው። ይህም የታመነ ቃል ነው። በእግዚአብሔር ያመኑቱ መልካሙን ነገር ለማድረግ ራሳቸውን አሳልፈው ይሰጡ ዘንድ እነዚህን ነገሮች አስረግጠህ እንድትናገር እፈልጋለሁ። ይህ መልካምና ለማንኛውም ሰው የሚጠቅም ነው፡፡” ቁ. 4-8

እንግዲህ ከዚሁ ሁሉ መዐት እና ጥፋት አዳነን፡፡ ሐዋርያው በማሠሪያው ላይ እንደሚያሳስበው የዳንነው፣ መልካሙን ነገር ለማድረግ ራሳችንን ደግሞ አሳልፈን እንድንሰጥ ነው፡፡

የአሮጌው ሕይወት እርሾ/ ርዝራዥ ወደ ኋላ እየሳበ እንደነበርን እንድንሆን መተናነቁ አይቀሬ ሊሆን ይችል ይሆናል፡፡ ቢሆንም የዳንንበት ጸጋ ወደ ፊት ደግሞ በልከኛ ሕይወት ለመቀጠል ዋስትናችን ነውና፤ እንደነበርን መሆናችን በምንም ስሌት ልክ አይመጣም፡፡ ስለዚህም በማንኛውም መንገድ ሕይወታችንን ሊቀናቀን የሚፈልገውን ጥላቻ መጥላትና ከሕይወታችን ማስወገድ ያስፈልጋል፡፡ ወደ ጥላቻ የሚገፋ ብዙ ነገር ቢገጥመን እንኳ፣ በክፋት እስራት ውስጥ በነበርንበት ሰዓት የተወደድንበትን ምክንያት የለሽ ፍቅር በማሰብ፣ ወደ ሌሎች ደግሞ በፍቅር እንዘርጋ፡፡

ባጭር ቃል ክርስትና እና ጥላቻ መሳ ለማሳ መሄድ አይችሉም፡፡ ጥላቻ ያለፈው ሕይወታችን መገለጫ፣ የአሬጌው ሕይወት መታወቂያ ነው፡፡ ስለዚህም እንደነበርን አንሁን!

#ማሳሰቢያ፡ እምነትን በመመከት ረገድ የሚከወኑ ሥራዎችን በጥላቻ ለሚመንዝሩ የተጻፈ አይደለም፡፡ ከጥላቻ የጸዳ ሕይወት ማለትም ሁሉን እያግበሰበሱ ማቀፍ እና ያለ ዳር ድንበር መኖር ጨርሶውኑ አይደለም፡፡

የከበሬታ ነገር!በአገልግሎት ምክንያት ያገኘኋት አንዲት የባለቤተስኪያን ሚስት ጋር እናወራለን፡፡ ግንኙነታችን ገራም እና ደኅነኛ ስለነበር፣ በጥሩ የወዳጅት መንፈስ እናወራለን፡፡ በእኔ በኩል ...
27/06/2022

የከበሬታ ነገር!

በአገልግሎት ምክንያት ያገኘኋት አንዲት የባለቤተስኪያን ሚስት ጋር እናወራለን፡፡ ግንኙነታችን ገራም እና ደኅነኛ ስለነበር፣ በጥሩ የወዳጅት መንፈስ እናወራለን፡፡ በእኔ በኩል የመቀራረባችን ምክንያት እንደው አንዳንድ ወጣ ወጣ ያሉ ነገሮችን በመቀራረብ መግራት ይቻል እንደሁ ከሚል የዋሕነት ነበር፡፡

ልጅቱ አብዝታ አገልጋዮች ከበሬታ ይገባቸዋል የሚል ሙግት ታነሳለች፡፡ ከበሬታውም በልዩ ልዩ መንገድ መገለጥ አለበት ባይ ነች፡፡ ለምሳሌ የተመረጠው እና የተሻለው ነገር ሁሉ ለአገልጋዮች ይገባል፤ የተሻለ መኪና መንዳት፣ በተሻለ ቤት መኖር፣ የተሻለ መብላት፣ መልበስ...
ይሄ ሁሉ መሆኑ የከፋ ባልሆነ፤ ነገር ግን ይህ ሁሉ የሚሆነው በሕዝብ ጫንቃ መሆኑ ነው አሳዛኙ ትራጀዲ፡፡ ይህን መሳዮቹ አገልጋዮች ግባቸው ይኸው ስለሆነ ይህንን ለማሳካት ሁሉን ነገር ከዚህ አንጻር ይቃኙታል፡፡ ስብከቱ፣ መዝሙሩ፣ መዋቅሩ ሁሉ ከዚህ አንጻር ይገነባል፡፡

የምእመናን ስኬትም ይሁን ውድቀት ለ“አገልጋዮቹ” ካለ ከበሬታ ጋር እንደሚያያዝ አድምተው ይለፍፋሉ፡፡ ምእመናን ወጥተው የሚገቡት በእነሱ ጥላ ከለላነት እንደሆነ አድርገው ያሳምናሉ፤ ቡራኬያቸው የምእመናን ወጥቶ መግቢያ ቀለብ እንደሆነ በየምእመኖቻቸው ልብ ውስጥ አጽንተዋል፡፡

ራሳቸውን በየተከታዮቻቸው ልብ ውስጥ አግዝፈው፣ ዙፋናቸውን ዘርግተዋል፡፡ “ከመረቅሁሁ” የሚል ማበራቻ ብቻ ሳይሆን፣ “ከረገምሁህ” የሚል ማስፈራሪያም አላቸው፡፡ ምእመናን መጋቢው፣ ነቢዩ ወይም ሐዋርያው እንዳይረግመው /ቃል እንዳያወጣበት ፀጥ እና ዝግ ብሎ ይኖራል (በ“አገልጋዩ” ፊት) እግዚአብሔርን በቅጡ አያውቀውም፤ ካወቀውም አገልጋይ ተብዬው በሳለለት ልክ እንጂ የመጽሐፉን እግዚአብሔር አያውቀውም፡፡ በክርስቶስ ነጻ እንደወጣ ሰው ሳይኾን፣ ልክ በአንድ ዓይነት ባዕድ አምልኮ እንደተተበተበ ሰው ዓይነት ድንብርብሩ እየወጣ ይኖራል፡፡ የእርሱ እግዚአብሔር ሁልጊዜ በእርሱ “አገልጋይ” በኩል ብቻ የሚፈስ ነው፡፡ አገልጋይ ተብዬዎቹም ምእመናቸው ከዚህ እንቅልፉ እንዲነቃ አይፈልጉም፡፡ ቅምጥል ኑሯቸውን ባንቀላፉ ምእመናን ላይ መስርተዋል፡፡

የቸርቻቸውን ዙሪያ በገዛ ፎቷቸው ያጥራሉ፤ ቢሮው እና መድረኮቻቸው ሳይቀር በተንቆጠቆጡ ምስሎቻቸው ይሞላሉ፡፡ አንዳንዶቹ ሚስት እና ልጆቻቸውን ሳይቀር ቸርች ባሉት ይዞታቸው ላይ ይሰቅላሉ፡፡ አንዳንዶቹም ምስሎቻቸውን አትመው በየዋሌቱ እንዲያዝ ያድላሉ፡፡ በዚህም ያለ ልክ ተንሰራፍተው፣ የጌታን ጌትነት ተጋፍተው በየሰዎቻቸው ላይ ይነግሣሉ፡፡

በዚህም ያን ያነገቡትን የቅንጦት ኑሮ ይኖራሉ፡፡ “ምርጥ ምርጡን ለሕፃናት!” እንደተባለው ዓይነት በምርጥ ምርጡ ይምነሸነሻሉ፡፡ ልዕልናቸውን ያለ ልክ ከፍ አድርገው “መጡ መጡ፤ ገቡ ገቡ” ይባልላቸዋል፡፡ በማንኛውም መንገድ ልዕለ ሰብ እንደሆኑ ያውጃሉ፡፡ ተራ በሚሉት ምእመን ላይ ጢባ ጢቤ ይጫወታሉ፡፡

መቸም መከባበር ክርስቲያናዊ እሴታችን ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያዊነት ትርፉታችንም ነው፡፡ እርስ በርስ ለመከባበርም ደግሞ የቃለ እግዚአብሔር መመሪያ አለን፡፡ ቢሆንም አገልጋዮች በተለየ መንገድ ይደግደግላቸው የሚል መመሪያ ግን ጨርሶውኑ የለንም፡፡

መሪ መምህራችን ጌታ ኢየሱስ አብዝቶ ካስተማራቸው ነገሮች መካከል ስለ ዝቅታ እና ትሕትና ያስተማረውን የሚያህል ያለ አይመስለኝም፡፡ ለተወሰኑ ጊዜያት በእኔ እበልጥ እና በፉክክር መንፈስ ይንገላቱ የነበሩትን ደቀመዛሙርቱን ደጋግሞ ገስጿል፡፡ ማገልግል በራሱ የታችኛውን ስፍራ መምረጥ ነው፡፡ ጌታችን ስለ ራሱ እንኳን ሲናገር “የሰው ልጅ ሊያገለግል፣ ነፍሱንም ስለ ብዙዎች ቤዛ ሊሰጥ እንጂ እንዲያገለግሉት አልመጣም” ብሏል፡፡ በዚህም አገልጋይነት ባርነት መሆኑን አጽንቷል፡፡

ከዚህም ሲያልፍ መምህር እና ጌታ የሆነው እርሱ በእውነተኛ መዋረድ እና ዝቅታ ወገቡን አሸርጦ የደቀ መዛሙርቱን እግር አጥቧል፡፡ ይህም የተወሰኑ ኦኬዥኖች እየጠበቅን ለማስመሰል ድራማ እንድንሠራ ሳይሆን፤ አገልጋይነት የሁልጊዜ የሕይወት ሥርዓታችን እንዲሆን የተሰጠ ትምህርት ነው፡፡

ይህንኑ ፈለግ የተከተሉትም ደቀመዛሙርት ይህንኑ ቅኝት ጠብቀው ነበር ሲያገለግሉ የነበሩት፡፡ አገልግሎታቸውን የገዛ ፍላጎታቸው መሙያ ሲያደርጉ ለአፍታም እንኳ አናይም፡፡ በማንኛውም መንገድ ራሳቸውንም አላሻሻጡም፡፡ በገዛ ቃላቸውም “ክርስቶስ ኢየሱስ ጌታ እንደሆነ እንጂ ራሳችንን አንሰብክም!” ብለው መስክረዋል፡፡ በስማቸው የተቋቋመ ቡድንንም አምርረው ኮንነዋል፡፡ አለፍ ብሎም የተለየ ከበሬታ በተዘጋጀላቸው ወቅትም በመንቀጥቀጥ ልብሳቸውን ቀደዋል፡፡
ግባቸው አንድ እና አንድ ክርስቶስ ኢየሱስ በአገልግሎታቸው እንዲገለጥ እና የሁሉን ሕይወት እንዲወርስ ብቻ ነበር፡፡ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ይህ አገልግሎት የሚጠይቀውን ዋጋ በደስታ ከፈሉ እንጂ፣ ማንንም ዋጋ አላስከፈሉም፤ ሰማይ ሙሉ ዋጋ ይዞ እንደሚጠብቃቸው ግን እርግጠኞች ነበሩ፡፡ በአገልግሎታቸውም በአንዳች ስንኳ ማሰናከያ አልሰጡም ነበር፡፡

ከበሬታን ግብ ያደረገ አገልግሎት ጨርሶውኑ ከጌታ አይደለም፡፡ የእኛ ክብር የእግዚአብሔር አንድያ ልጅ የከበረ ‘ለታ ብቻ ነው፡፡ በተለያየ መንገድ ራስን ማሻሻጥ በሚመስል መልኩ እርሱን ጋርዳችሁ የደመቃችሁ ሆይ ወዮላችሁ፡፡ ምስሉን እያደበዘዛችሁ፣ ምስላችሁን በየሰዉ ልብ ለማተም የምትታትሩ ሆይ ወዮላችሁ፡፡ እራሳችሁን እያዋደዳችሁ ዙፋናችሁን ከእግዚአብሔር ከዋክብት በላይ ልትገነቡ ያማራችሁ ሆይ ወዮላችሁ፡፡ የጌታ ቤት ባላችሁት ቸርቻችሁ ላይ ደማቅ ምስላችሁን ሰቅላችሁ ራሳችሁን ያነገሣችሁ ሆይ ወዮላችሁ፡፡
ቀን ሳይጨለም ለልባችሁ ሰው መሆናችሁን ንገሩት፤ ከፍ ብላችሁ በመፋነን ፋንታ የዝቅታን አገልግሎት ምረጡ፡፡ በጌታ ዘንድ ራሱን ከፍ ከፍ ሚያደርግ ሁሉ ይዋረዳል፤ ራሱንም የሚያዋርድ ከፍ ይላል፡፡
ጆሮ ያለው ይስማ!!

ማገናዘቢያ፡ ማቴ 20÷20-28፣ ሉቃ 14÷11፣ ዮሐ 13÷12-15፣ 2 ቆሮ 4÷5፣ 1 ጴጥ 5÷6

Address

Addis Ababa
188

Telephone

0912919014

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Pastor Sintayehu Bekele posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Place Of Worship

Send a message to Pastor Sintayehu Bekele:

Share