23/08/2026
የእሁድ የቅባት የመጀመሪያው አገልግሎት
መዝ 95:1-5
- ምስጋና ለእግዚአብሔር የሚቀርብ መስዋዕት ነው።
- ምስጋና ከዝማሬ ያለፈ መስዋዕት ነው።
- ያዳህ የዕብራይስጥ ቃል ሲሆን እግዚአብሔርን ማመስገንን፣ ማወደስን፣ ታላቅ ስራውን መመስከርን ፣ በእንቅስቃሴ ማመስገንን ይገልፃል።
- እውነተኛ ምስጋና በጓዳ የሚቀር አይደለም።
እግዚአብሔርን ለማመስገን ፦
1. ውለታን ማስታወስ
- እግዚአብሔር ያደረገልንን አስተውሎ ማመስገን ጥበብ ነው !
- በዚህ አመት እግዚአብሔር ምን አደርገልኝ?
2. የእግዚአብሔርን ባህሪ ከበረከቱ ለይቶ ማየት
- ስጦታ ዛሬ ሊኖር ይችላል ፣ ነገ ላይኖር ይችላል ፤
ስለዚህ ምስጋናችን አብሮ መቀያየር የለበትም።
- የማይቀያየር የእግዚአብሔር ማንነት አለ።
3. ልባችንን ከመራርነትና ከቅሬታ ማፅዳት
1 ተሰ 5:18
4. በምስጋናችን ክርስቶስን ማዕከል ማድረግ አለብን
- ከስጦታዎች ሁሉ በላይ የሆነውን ኢየሱስን ስለሰጠን እናመስግናለን 2 ቆሮ 9:15
5. ምስክርነታችን ማዘጋጀት
- ያዳህ በልብ ውስጥ የሚቀር ብቻ ሳይሆን የእግዚአብሔርን ታላቅ ስራ የምናውጅበት ነው።
- መቆማችን፣ መኖራችን፣ መዳናችን ምስክርነት ነው።
- እግዚአብሔር አደረገልኝ ብሎ መዘርዘር ትዕቢት አይደለም።
6. በህይወታችን በረከት የሆኑ ሰዎችን ማስታወስ
- በህይወታችን እግዚአብሔር ተጠቅሟቸው የላካቸውን ሰዎች ማመስገን
ፊሊ 1:3
7. እርቅና ይቅርታ
እጆቻችንን ወደ እግዚአሔር ከማንሳታችን በፊት ዕርቅና ይቅርታ ማድረግ አለብን።
ማቴ 5፡ 23-24
8. ለማህበረሰባችን፣ ለሀገራችን ፣ ለቤተ ክርስቲያን ልባችንን ማስፋት
- የምንወጣው የምንገባው በእግዚአብሔር ረድኤት ስለሆነ ስለሀገራችን እናመሰግናለን።
ኤር 29:7
9. በምስጋና ልብ መምጣት
- እምነታችንን አነሳስተን እንመጣለን
10. ነገን በተስፋ መቀበል
- 2019 እያመሰገንን መቀበል እንችላለን