የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን The Ethiopian Full Gospel Believers' Church

  • Home
  • Ethiopia
  • Addis Ababa
  • የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን The Ethiopian Full Gospel Believers' Church

የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን The Ethiopian Full Gospel Believers' Church ኢየሱስ ክርስቶስ ትናንትና፥ ዛሬም ለዘልዓለምም ያው ነው። ዕብ 13:8
Jesus Christ is the same yesterday and today and forever. Heb 13:8 We believe in unity and trinity of God.
(1)

The Ethiopian Full Gospel Believers' Church emerged out of the spontaneous gospel revival among students of high school and higher institutions in various parts of the country by the mid 1960s. In those successive years the revival broke throughout the country. Since then, the revival inundated the whole country the provincial towns, small towns and villages in the countryside. The church officially founded in 1966 at Addis Ababa. However the movement was not only limited in Addis Ababa rather it covers the whole country. This brought the issue that the believers had to form unity on a national level and be organized as a denomination. In 1974, leaders from different places of the country came and agreed to be organized at a denominational level. Organizing the denomination had many advantages; among those are that it enabled to guard against false teaching/heresy/ and the other was to obtain recognition by the government and other denominations. Besides these, the unity had contributed in holding common understanding of doctrine, as well the believers were able to encourage and help one another during years of hardship. With the change of the government in Ethiopia came new chapter of the church. The national office of the church is established in Addis Ababa and the Federal Democratic Republic of Ethiopia accorded the church its full recognition on November 10, 1991 in accordance with the constitutional provision of the religious liberty and freedom of worship. Now a days the Church is one of few big evangelical Churches in the country. It consists of more than 3093 local churches and 8000 fellowships divided into 38 regions . The Ethiopian Full Gospel Believers' Church Statement of Faith:

1. We believe that the Holy Bible, which contains the sixty-six books of the old and New Testament, is the inspired word of God. It is inerrant and is the final authority in all maters of faith and conduct.
2. This God revealed himself as the Father, the Son and the Holy Spirit.
3. We believe in the sovereignty of God in creation, providence, revelation, redemption and Final judgment
4. We believe in the Lord Jesus Christ, Son of God, born of the virgin Mary, True God and True Man, in his redemptive death on the cross, his burial, his bodily resurrection from the dead, his ascension to the Father's right hand and his glorious return to judge the living and the dead.
5. We believe that man was created in the image of God has fallen in sin and is therefore guilty. subject to the wrath and condemnation of God.
6. We believe that God delivered humanity from guilt, power and penalty of sin through 1 redemptive work of the sinless Son of God, Jesus Christ our Lord who died on the cross man's perfect substitute. Hence we believe that the sinner shall be saved by the grace of God through faith in Christ alone.
7. We believe that the Holy Spirit works in the life of the repentant sinner granting conviction of sin and creating him a new as a result of faith in Jesus Christ.
8. For the edification of the body and enable it to accomplish the assignment of the great commission and to edify the church Christ gave her apostles, prophets, evangelists, paste teachers and other ministry gifts.
9. We believe in the indwelling of the Holy Spirit in the believer. We believe that the belie' receives power and speak in tongues when baptized by the Holy Spirit and can be filled w the Spirit constantly.
10. We believe that God the Holy Spirit is active today dividing gifts of grace to the body Christ, to work miracles, heal the sick, cast out demons and do other deeds for the glory our Lord and Savior Jesus Christ, for the extension of God's kingdom and for the edification of the Church.
11. We believe in the one Holy Church, which is the body of Christ and to which all believers belong.
12. We believe that the repentant sinner who professes faith in Jesus Christ shall identify w the death and resurrection of Christ through water baptism by immersion in the name of the Father, and the Son, and of the Holy Spirit. We also believe that the believer partakes of the Lords' supper to declare the Lord's death till he comes and to show his fellowship with ot1 believers in the body of Christ.
13. We believe that Christ gave ordinances to the Church namely water baptism and Lon Supper.
14. We believe in the resurrection of the dead, in eternal judgment of the wicked and eternal bliss of the saved.

በኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን የደቡብ ምስራቅ  አዲስ አበባና አካባቢው ክልል 5 ተኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ በተሳካ ሁኔታ ተጠናናቀ። ቅዳሜ ነሐሴ 16/2018 ዓ.ም የደቡብ ም...
23/08/2026

በኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን የደቡብ ምስራቅ አዲስ አበባና አካባቢው ክልል 5 ተኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ በተሳካ ሁኔታ ተጠናናቀ።

ቅዳሜ ነሐሴ 16/2018 ዓ.ም የደቡብ ምስራቅ አዲስ አበባና አካባቢው ክልል 5 ተኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ በገርጂ ሙሉ ወንጌል አጥቢያ ለሁለት ቀናት ሲካሄድ የቤተ እምነቱ ምክትል ፕሬዝዳንት ፣የክልሉ ፕሬዝዳንት እና ከ105 አጥቢያዎች የተወጣጡ የቤተክርስቲያን መሪዎች ተገኝተዋል።

የቤተ እምነቱ ምክትል ፕሬዝዳንት መጋቢ ለወየሁ ስንሻው መንፈሳዊ ሰላምታ ለጉባኤው በማቅረብ በክልሉ ውስጥ ጌታ እያከናወነ ያለውን መልካም ስራ በማድነቅ እግዚአብሔርን አመስግነዋል።
እንዲሁም የክልሉን መሪዎች አበረታተዋል።
በመቀጠል የክልሉ ፕሬዝዳንት መጋቢ ፋሲል ተክሉ የ2018 ዓ.ም የስራና የፋይናንስ ሪፖርት ያቀረቡ ሲሆን የ 2019 ዓ.ም የስራና የፋይናንስ እቅድ አቅርበው ጉባኤው በሙሉ ድምጽ አጽድቀዋል።
ከጉባኤው የተለያዩ ጥያቄዎች የተነሱ ሲሆን የክልሉ ፕሬዚዳንት የሆኑት መጋቢ ፋሲል ተክሉ ተገቢውን ምላሽ ሰጥተዋል።

በተጨማሪም የሚጠበቅባቸውን ተገቢውን ፈሰስ በአግባቡ ለክልሉና ለቤተ እምነቱ ገቢ በማድረጋቸው እና በሕንጻ ግንባታ ላይ በጎ አስተዋጾ ላደረጉ አጥቢያዎች የከፍተኛ ዋንጫ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል ።
በመጨረሻም ለሚቀጥሉት አራት አመታት እንዲያገለግሉ ስራ አስኪያጅ ኮሚቴ በመምረጥ (በመሾም) 5ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋል።

ለበለጠ_መረጃ
👉በዩትዩብ፡ https://www.youtube.com/
👉ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/etfullgospel/
👉ቴሌግራም፡ https://t.me/EFGBC_HO እንዲሁም በሌሎች ፕላትፎርሞቻችን ይከታተሉን።

በኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን የሰሜን ምዕራብ አዲስ አበባና አካባቢው  ክልል 5 ተኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ በተሳካ ሁኔታ ተጠናቀቀ::የሰሜን ምዕራብ አዲስ አበባ እና አካባቢው...
22/08/2026

በኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን የሰሜን ምዕራብ አዲስ አበባና አካባቢው ክልል 5 ተኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ በተሳካ ሁኔታ ተጠናቀቀ::

የሰሜን ምዕራብ አዲስ አበባ እና አካባቢው ክልል በሸጎሌ አጥቢያ ለሁለት ቀናት ሲያካሄድ የቆየው 5ተኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ አርብ ነሐሴ 15/2018 በተሳካ ሁኔታ ሲጠናቀቅ የ2018 ዓ.ም የስራና ፋይናንስ ሪፖርት የቀረበ ሲሆን የ2019 የስራ ዕቅድ ቀርቦ ጉባኤው በሙሉ ድምጽ አጽድቋል።
እንዲሁም የክልሉ ስራ አስኪያጅ ኮሚቴ ምርጫ ተከናውኖ ጠቅላላ ጉባኤው በመልካም ሁኔታ ተጠናቋል።

ለበለጠ_መረጃ
👉በዩትዩብ፡ https://www.youtube.com/
👉ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/etfullgospel/
👉ቴሌግራም፡ https://t.me/EFGBC_HO እንዲሁም በሌሎች ፕላትፎርሞቻችን ይከታተሉን።

በኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን የደቡብ ምስራቅ አዲስ አበባና አካባቢው ክልል 5ተኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ተጀመረ።አርብ ነሐሴ 15/2018 ዓ.ም በገርጂ ሙሉ ወንጌል አጥቢያ ከ...
21/08/2026

በኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን የደቡብ ምስራቅ አዲስ አበባና አካባቢው ክልል 5ተኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ተጀመረ።

አርብ ነሐሴ 15/2018 ዓ.ም በገርጂ ሙሉ ወንጌል አጥቢያ ከ105 አጥቢያዎች የተወጣጡ የቤተክርስቲያን መሪዎች ተገኝተዋል።
የክልሉ ፕሬዚዳንት መጋቢ ፋሲል ተክሉ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ለጉባኤው አስተላልፈዋል።
በዘማሪት ዛብሎን በቀለ ዝማሬ ቀርቦ ጉባኤው እግዚአብሔርን አምልኮአል።
የክልሉ ስራ አስኪያጅ ኮሚቴ ሰብሳቢ የሆኑት መጋቢ ተመስገን አዋኖ "የጤናማ አገልጋይ ትኩረቶች" በሚል ርዕስ 2ተሰ 2:1 ያለውን ቃል በመጥቀስ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት ለጉባኤው አካፍለዋል።

በመቀጠል መጋቢ ታሪኩ ቴድሮስ "የመንፈስ አገልግሎት " በሚል መሪ ሀሳብ 2ቆሮ3:1 ያለውን ቃል በመጥቀስ የመንፈስ አገልግሎት ፣በክብር ማገልገል ፣ በጸጋ ማገልገል ፣በንጥቀት ማገልገል የሚሉ ነጥቦችን በማንሳት የእግዚአብሔርን ቃል አካፈለዋል።
የክልሉ ስራ አስኪያጅ ኮሚቴ አቃቤ ንዋይ የሆኑት መጋቢ ተክሉ ፕሮግራሙን በሚገባ መርተዋል።

የደቡብ ምስራቅ አዲስ አበባና አካባቢው ክልል 5 ተኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ነገ ቅዳሜ 16/2018 ዓ.ም የሚጠናቀቅ ሲሆን የ2018 ዓ.ም የስራና የፋይናንስ ሪፖርት እና የ2019 ዓ.ም የስራ እቅድ ቀርቦ የስራ አስኪያጅ ኮሚቴ ምርጫ እንደሚካሄድ ለማወቅ ተችሎአል።

ለበለጠ_መረጃ
👉በዩትዩብ፡ https://www.youtube.com/
👉ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/etfullgospel/
👉ቴሌግራም፡ https://t.me/EFGBC_HO እንዲሁም በሌሎች ፕላትፎርሞቻችን ይከታተሉን።

በኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን የሰሜን ምዕራብ አዲስ አበባና አካባቢው ክልል 5 ተኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ተካሄደ።እሮብ ነሐሴ 13/2018 ዓ.ም የሰሜን ምዕራብ አዲስ አበባና...
20/08/2026

በኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን የሰሜን ምዕራብ አዲስ አበባና አካባቢው ክልል 5 ተኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ተካሄደ።

እሮብ ነሐሴ 13/2018 ዓ.ም የሰሜን ምዕራብ አዲስ አበባና አካባቢው ክልል 5 ተኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ የተጀመረ ሲሆን የቤተ እምነቱ ምክትል ፕሬዝዳንት፣ የክልሉ ፕሬዚዳንት እና ከ88 አጥቢያዎች የተወጣጡ 85 የቤተክርስቲያን መሪዎች ተገኝተዋል።
5 ተኛ ጠቅላላ ጉባኤ በጸሎት የተከፈተ ሲሆን የክልሉ ፕሬዚዳንት መጋቢ ሰለሞን በንቲ የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር በማድረግ መልዕክት አስተላልፈዋል።
በዘማሪ ታማኝ ሙሉነህ ዝማሬ ቀርቦ ጉባኤው እግዚአብሔርን አምልኮአል።
በመቀጠል የቤተ እምነቱ ምክትል ፕሬዝዳንት የሆኑት መጋቢ ለወየሁ ስንሻው ነህምያ 1:1-18 ያለውን ቃል በመጥቀስ "የተሃድሶ ከሳች መሪ " በሚል ርዕስ የእግዚአብሔር ቃል ያካፈሉ ሲሆን የተሃድሶ ከሳች መሪ በመረጃ የተገነባ፣በጸሎት በልዑል እግዚአብሔር ፊት የሚንበረከክ ፣በተግባር ንሰሃ የሚመለስ፣ ምቾቱን የሚተው (መስዋትነት የሚከፍል) የሚሉ ነጥቦችን በማንሳት የጊዜውን መልዕክት አካፍለዋል።
እንዲሁም በክልሉ ላይ ጌታ እያከናወነ ያለውን መልካም ስራዎችን በማድነቅ መሪዎችን አበረታተዋል።

በመቀጠል የክልሉ ስራ አስኪያጅ ኮሚቴ ሰብሳቢ የሆኑት መጋቢ ጌታቸው ታሪኩ ምላተ ጉባኤው መሟላት አረጋግጠው 5 ተኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ በይፋ አስጀምረዋል።
በክልሉ ፕሬዝዳንት በመጋቢ ሰለሞን በንቲ የ2018 ዓ.ም የፋይናንስ እና የስራ ክንውን ሪፖርት የቀረበ ሲሆን የ2019 ዓ.ም በጀት አመት እቅድ ቀርቦ ጉባኤው በሙሉ ድምጽ አጽድቋል።
እንዲሁም ክልሉ በቀጣይ ሊሰራ ያሰበውን ለቢሮ እና ለተለያዩ መንፈሳዊ አገልግሎቶች የሚሰጥ ዘመናዊ ህንጻ ዲዛይን ለጉባኤው ቀርቦ ጌታ በነገር ሁሉ መከናወን እንዲሰጥ ጸሎት ተደርጓል።
እሮብ ነሐሴ 13/2018 ዓ.ም በቤተ እምነቱ የልጆች ፣ወጣቶች እና የቤተሰብ አገልግሎት ሀላፊ በሆኑት በመጋቢ ኤርሚያስ ገ/መድህን ወጣቶች የት ናቸው ? በሚል ርዕስ ጥናታዊ ጹህፍ የቀረበ ሲሆን ቤተክርስቲያን ከምንጊዜም በላይ ወጣቶች ላይ ትኩረት አድርጋ መስራት እንዳለባት አጽንኦት የተሰጠበት ሲሆን ውይይት ተደርጎ የተለያዩ አሳቦች ተነስቶ ለመሪዎች ዋና አጀንዳ ሆኖ ተሰጥቷል።

የሰሜን ምዕራብ አዲስ አበባና አካባቢው ክልል 5 ተኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ አርብ ነሐሴ 15/2018 ዓ.ም የሚጠናቀቀ እና የስራ አስኪያጅ ኮሚቴ ምርጫ በዕለቱ እንደሚከናወን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ለበለጠ_መረጃ
👉በዩትዩብ፡ https://www.youtube.com/
👉ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/etfullgospel/
👉ቴሌግራም፡ https://t.me/EFGBC_HO እንዲሁም በሌሎች ፕላትፎርሞቻችን ይከታተሉን።

በኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን  የምሥራቅ አካባቢው ክልል የአገልጋይ ሹመት ተካሄደ።በሐረር አራተኛ ሙሉ ወንጌል  አጥቢያ  እሁድ ነሐሴ 10/2018 ዓ.ም የመጋቢነት የሹመት ሥ...
17/08/2026

በኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን የምሥራቅ አካባቢው ክልል የአገልጋይ ሹመት ተካሄደ።

በሐረር አራተኛ ሙሉ ወንጌል አጥቢያ እሁድ ነሐሴ 10/2018 ዓ.ም የመጋቢነት የሹመት ሥርዓት ተከናውኖአል።
በፕሮግራሙ ላይ ከሐረር ወንጌላውያን አብያተክርስቲያናት ህብረት ፣ከሐረር ግሬት ኮሚሽን ቢሮ እንዲሁም በከተማው ከሚገኙ የሙሉ ወንጌል እህት አጥቢያዎች የተወጣጡ የመሪ ተወካዮች እና የክልሉ ፕሬዚዳንት መጋቢ አለም ጌታቸው የተገኙ ሲሆን በዕለቱ የእግዚአብሔርን ቃል በማካፈል የወንድወሰን ተክሌ የመጋቢ ሹመት ስርዓትን አስፈጽመዋል።
በመጨረሻም ለመጋቢ ወንደሰን እና ለቤተሰቡ ፀሎት ተደርጎ ፕሮግራሙ ተጠናቋል።

ለበለጠ_መረጃ
👉በዩትዩብ፡ https://www.youtube.com/
👉ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/etfullgospel/
👉ቴሌግራም፡ https://t.me/EFGBC_HO እንዲሁም በሌሎች ፕላትፎርሞቻችን ይከታተሉን።

በኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን የማዕከላዊ ደቡብ አካባቢው  ክልል ጠቅላላ ጉባኤ እና የፕሬዝዳንት ምርጫ ተካሄደ።ነሐሴ 08/2018 ዓ.ም በሆሳዕና አራዳ ሙሉ ወንጌል አጥቢያ ጠ...
17/08/2026

በኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን የማዕከላዊ ደቡብ አካባቢው ክልል ጠቅላላ ጉባኤ እና የፕሬዝዳንት ምርጫ ተካሄደ።

ነሐሴ 08/2018 ዓ.ም በሆሳዕና አራዳ ሙሉ ወንጌል አጥቢያ ጠቅላላ ጉባኤ ሲካሄድ የቤተ እምነቱ ምክትል ፕሬዝዳንት ፓስተር ለወየሁ ስንሻው ተገኝተው መንፈሳዊ ሰላምታ በማቅረብ የእግዚአብሔርን ቃል መልዕክት አካፍለዋል።

የክልሉ ስራ አስኪያጅ ኮሚቴ ሰብሳቢ የሆኑት አቶ ታደሰ ጫሚሶ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ለጉባኤው በማስተላለፍ የምላተ ጉባኤውን መሟላት አረጋግጠው ስብሰባውን በይፋ አስጀምረዋል።
በክልሉ ፕሬዝዳንት ፓስተር አለማየሁ ኤርሳዶ የ2018ዓ.ም የስራ ክንውን ሪፓርትና የ2019 ዓ.ም በጀት አመት ዕቅድ ቀርቦ ጉባኤው በሙሉ ድምጽ አጽድቋል።

በመጨረሻም ክልሉን ለሁለት ተርም በፕሬዝዳንትነት ያገለገሉት ፓስተር አለማየሁ ኤርሳዶ ጊዜያቸውን ስለጨረሱ መምህር አብርሃም መንገሻ ለቀጣይ አምስት አመታት ክልሉን በፕሬዝዳንትነት ለመምራት የተሾሙ ሲሆን በመቀጠልም የስራ አስኪያጅ ኮሚቴ ምርጫ ተካሂዶ የቤተ እምነቱ ምክትል ፕሬዝዳንት ፓስተር ለወየሁ ስንሻው የሹመት ስርዓቱን አስፈጽመዋል።
አዲስ ለተመረጡትም ለስራ አስኪያጅ ኮሚቴ አባላትንና አዲስ የተመረጡትን የክልሉን ፕሬዚዳንት በደንቡ መሠረት ቃል በማስገባት ጸሎት አድርገው የጉባኤው ፍጻሜ ሆኗል።

ለበለጠ_መረጃ
👉በዩትዩብ፡ https://www.youtube.com/
👉ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/etfullgospel/
👉ቴሌግራም፡ https://t.me/EFGBC_HO እንዲሁም በሌሎች ፕላትፎርሞቻችን ይከታተሉን።

በኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን የአርሲ ዞን አካባቢው ክልል 11ኛ ጠቅላላ ጉባኤ ተካሄደ። ነሐሴ 08-09/2018 ዓ.ም በአሰላ መሐል ከተማ ቁ.1 አጥቢያ የክልሉ 11ኛ ጠቅላላ...
16/08/2026

በኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን የአርሲ ዞን አካባቢው ክልል 11ኛ ጠቅላላ ጉባኤ ተካሄደ።

ነሐሴ 08-09/2018 ዓ.ም በአሰላ መሐል ከተማ ቁ.1 አጥቢያ የክልሉ 11ኛ ጠቅላላ ጉባኤውን ያካሄደ ሲሆን ቤተ ዕምነቱን በመወከል የተገኙት የሠላም ግንባታ ዲያሬክቶሬት ዲያሬክተር መጋቢ ሽፈራው ራጋ የእግዚአብሔርን ቃል ለጉባኤው አካፍለዋል። እንዲሁም መጋቢ ኤልያስ ወንድሙ ከቤተ እምነቱ ከማህበራዊ ዋስትና አገልግሎት ክፍል የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርት የሰጡ ሲሆን በየአጥቢያዎች አሰራር በተፈጠሩ ክፍተቶች ዙሪያ የማስተካከያ ሐሳብ ሰጥተዋል፡፡
የክልሉ ስራ አስኪያጅ ኮሚቴ ሰብሳቢ የሆኑት መጋቢ የኋላሸት ሙኩሉ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ለጉባኤው ካስተላለፉ በኋላ የምላተ ጉባኤውን መሟላት አረጋግጠው ስብሰባውን በይፋ አስጀምረዋል።

በመቀጠል በክልሉ ፕሬዘዳንት በመጋቢ ስዩም ከበደ የ2018ዓ.ም የስራ ክንውን ሪፖርት እንዲሁም የሒሳብ ሪፓርት በሒሳብ ሹሙ በወ/ም ዘሪሁን ተሾመ ቀርቦአል፡፡ የ2019 ዓ.ም በጀት አመት ዕቅድ ቀርቦ በሙሉ ድምጽ ጸድቋል። ጠቅላላ ጉባዔው የሥራ አስኪያጅ ኮሚቴ ምርጫ ያደረገ ሲሆን ክልሉን በቀድሞ አጠራሩ ጸሐፊ በአሁኑ አጠራር በፕሬዘዳንትነት ያገለገሉት መጋቢ ስዩም ከበደ ቢቂላ ለ11 ዓመት በማገልገላቸው የመጨረሻ የመውጫ ሪፓርት (Exit Report) አቅረበው በክብር የተሸኙ ሲሆን ለቀጣይም አምስት ዓመታት ክልሉን በፕሬዝዳንትነት እንዲያገለግሉ መጋቢ ኢንጋቡ ደቀባ ተመርጠዋል፡፡

በዕለቱም በአርሲ እና ባሌ ክልል ክላስተር የማራናታ የመጽሐፍ ቅዱስ ኮሌጅ በዲፕሎማ መርሃ ግብር ያስተማራቸውን 60 ተማሪዎች አስመርቆአል፡፡

ቤተዕምነቱን ወክለው የተገኙት መጋቢ ሽፈራው ራጋ የተመረጡትን የስራ አስኪያጅ ኮሚቴ አባላትንና አዲስ የተመረጡትን የክልሉን ፕሬዚዳንት በደንቡ መሠረት ቃል ያስገቡ ሲሆን አዲስ ለተመረጡትም ጸልየው የጉባኤው ፍጻሜ ሆኗል።

ለበለጠ_መረጃ
👉በዩትዩብ፡ https://www.youtube.com/
👉ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/etfullgospel/
👉ቴሌግራም፡ https://t.me/EFGBC_HO እንዲሁም በሌሎች ፕላትፎርሞቻችን ይከታተሉን።

በኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን የሰሜን ማዕከላዊ አካባቢው  ክልል 28 ኛ ጠቅላላ ጉባኤ ተካሄደ።     ቅዳሜ ነሐሴ  09/2018 ዓ.ም በደብረብረሃን 05 አጥቢያ ክልሉ 28ኛ...
15/08/2026

በኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን የሰሜን ማዕከላዊ አካባቢው ክልል 28 ኛ ጠቅላላ ጉባኤ ተካሄደ።

ቅዳሜ ነሐሴ 09/2018 ዓ.ም በደብረብረሃን 05 አጥቢያ ክልሉ 28ኛ ጠቅላላ ጉባኤውን ያካሄደ ሲሆን ቤተ ዕምነቱን በመወከል የተገኙት የእረኝነትና የቤተክርስቲያን ዕድገት ክፍል ኃላፊ የሆኑት ፓስተር ጥላሁን አስፋው የእግዚአብሔርን ቃል ለጉባኤው አካፍለዋል።
የክልሉ ስራ አስኪያጅ ኮሚቴ ሰብሳቢ የሆኑት ፓስተር ሰለሞን የሺጥላ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ለጉባኤው ካስተላለፉ በኋላ የምላተ ጉባኤውን መሟላት አረጋግጠው ስብሰባውን በይፋ አስጀምረዋል።

በመቀጠል በክልሉ ፕሬዘዳንት ፓስተር ጌታቸው አልታዬ የ2018ዓ.ም የስራ ክንውን ሪፖርትና የ2019ዓ.ም በጀት አመት ዕቅድ ቀርቦ በሙሉ ድምጽ ጸድቋል።
የስራ አስኪያጅ ኮሚቴ ምርጫ ተካሄዶአል።
በመጨረሻም ክልሉን ለአንድ ተረም በፕሬዘዳንትነት ያገለገሉት ፓስተር ጌታቸው አልታዬ ብቸኛ ተጠቋሚ ሆነው የቀረቡ ሲሆን ጉባኤው ለሁለተኛ ተርም ክልሉን በፕሬዝዳንትነት እንዲመሩ መርጦአቸዋል።

ቤተዕምነቱን ወክለው የተገኙት ፓሰተር ጥላሁን አዲስ የተመረጡ የስራ አስኪያጅ ኮሚቴ አባላትንና ለሁለተኛ ተርም የተመረጡትን የክልሉን ፕሬዚዳንት በደንቡ መሠረት ቃል ያስገቡ ሲሆን አዲስ ለተመረጡትም ጸልየው የጉባኤው ፍጻሜ ሆኗል።

ለበለጠ_መረጃ
👉በዩትዩብ፡ https://www.youtube.com/
👉ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/etfullgospel/
👉ቴሌግራም፡ https://t.me/EFGBC_HO እንዲሁም በሌሎች ፕላትፎርሞቻችን ይከታተሉን።

13/08/2026

Enjoy the videos and music you love, upload original content, and share it all with friends, family, and the world on YouTube.

Address

Kassanchis Road Around Womens Square
Addis Ababa
10470

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን The Ethiopian Full Gospel Believers' Church posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Place Of Worship

Send a message to የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን The Ethiopian Full Gospel Believers' Church:

Shortcuts

Share