23/08/2026
ቸርች እንዴት ነበር
(How was Church?)
"እምነት መለኪያ ነው!"
ዕብራውያን 3:12 NASV
[12] ወንድሞች ሆይ፤ ከእናንተ ማንም ከሕያው እግዚአብሔር የሚያስኰበልል፣ ኀጢአተኛና የማያምን ልብ እንዳይኖረው ተጠንቀቁ።
✍️ የልብ ክፋት እና እልከኝነት የእምነት ትልቅ ጠላት ሲሆን በአለማመን ውስጥ ሆነን እንድንቀር ያደርጋል።
አለማመን ተስፋውን ከመውረስ መከልከል፣ እግዚአብሔር ታማኝ እንዳልሆነ ማስመሰል፣ የእምነት እርምጃን ማስቆም፣ ፍርሃትን ማሳደግ እና ልብን ማደንደን ትልቁ በሕይወታችን የሚያመጣው ውድቀት ነው።
የእስራኤላውያን ሕይወት የአለማመን ምሳሌ የሆነበት ምክንያት ግብፃውያንን ሲቀሰፉ አይተው፣ መና ሲዘንብ አይተው፣ ባህርም እንደ ግርግዳ ሆኖ ሲከፈል አይተው እና በእሳትና በደመና አምድ ተመርተው ላሉ ይህን ሁሉ ዘንግተው ወደ አለማመን መግባታቸው ነው።
ኢያሱና ካሌብ የተለዩበት ምክንያት ችግሩን አልካዱም ግዙፎች ሰዎች እንዳሉ አውቀው ነበር። ነገር ግን "እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነዉ" ብለዉ በእምነት ጸኑ።
እንዲሁም አብርሃም የአለማመን ተቃራኒ ሲሆን፤ አለማመን ሁኔታውን ተመልከት ሲለው እርሱ ግን በእምነት ሁኔታውን አይቻለሁ ነገር ግን ተስፋውን የሰጠውን አውቃለሁ ብሎ አመነ።
በመጨረሻም ክርስትና ማስረጃ ይቃወማል ማለታችን ሳይሆን እምነት የሚታየውን ብቻ የመጨረሻው መለኪያ አያደርገውም ማለታችን ነው። ስለዚህ ከማመን ጠላት ከሆኑት በመራቅ በእምነት እንበርታ።
ዮሐንስ 20:29 NASV
[29] ኢየሱስም፣ “አንተ ስላየኸኝ አምነሃል፤ ሳያዩ የሚያምኑ ግን ብፁዓን ናቸው” አለው።
ሬቨ ዶ/ር ተዘራ ያሬድ
ቀን እሁድ 17/12/2018
⛪️ የክብር ሕይወት ቤተክርስቲያን
አዲስ አበባ/ ኢትዮጵያ
መልካም የመነሳትና የማብራት ምሽት