31/07/2022
የመንግስት ዜና አገልግሎት ቅጥፈት
~~~~~~~~~~~~~~~~~~
ቅድስት ቤተክርስቲያን ያለአዋጅ የምታደርገው ጸሎተ ምህላ (የምስጋናም ይሁን የልመና) የላትም።
ቢኖራትም በመላው አለም ካላት አብያተክርስቲያናት በሙሉ ተነጥላ በአንዱ አጥቢያ ብቻ የምትፈጽመውም የምስጋናም መርኃግብር አካሂዳም ሆነ ፈጽማ አታውቅም። ነገም አታደርገውም።
እስከአሁኗ ሰዓት ድረስ በየትኛውም የቤተክህነት መዋቅርና ሆነ መንፈሳዊ አባት የታወጀ የምስጋናም ሆነ የጸሎተ ምህላ መርኃግብራት የሉም። አልታወጁም።
ይህቺ ቤት ስርዓት ህግ እና መንፈስቅዱስ ያለባት ቤት ናት። የቄሳር ቃል በክርስቶስ ቤት ውስጥ አይፈጸምም።
ቤተመንግስት እና ቤተ ክህነትን እየለየን ወገን
ልክ እንደ ከዚህ ቀድሞ ባሉት ሳምንታት ከሰንበትን በረከት ለማግኘት ፣ቅዱስ ቁርባንን ለመቀበል፣ከስርዓተ ቅዳሴው ኅብረት ለማድረግ፣ቅዱስ ቃሉን ሊማሩ የመጡትን ምዕመናንን የቄሳርን የግብዝነት የአዋጅ ምስጋና አስፈፃሚ አድርገው ማሳዬት ትልቅ ቅጥፈት ነው
መቅደሳችን ለሁለት ጌቶች አትገዛም።