የጎፋ ቤዛ ብዙኃን ቅድስት ኪዳነምሕረት ካቴድራል መዝገበ ምሕረት ሰንበት ት/ቤት Gofa Beza Bizuhan

  • Home
  • Ethiopia
  • Addis Ababa
  • የጎፋ ቤዛ ብዙኃን ቅድስት ኪዳነምሕረት ካቴድራል መዝገበ ምሕረት ሰንበት ት/ቤት Gofa Beza Bizuhan

የጎፋ ቤዛ ብዙኃን ቅድስት ኪዳነምሕረት ካቴድራል መዝገበ ምሕረት ሰንበት ት/ቤት Gofa Beza Bizuhan የጎፋ ቤዛ ብዙኃን ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ካቴድራል መዝገበ ም? የጎፋ ቤዛ ብዙኃን ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ካቴድራል መዝገበ ምሕረት ሰንበት ት/ቤት

እንኳን ከዘመነ ማርቆስ ወደ ዘመነ ሉቃስ አሸጋገረን... 🙏 ዓመቱ የበረከት የፍቅር የአገልግሎት እንዲሆንላችሁ እንመኛለን🌼መልካም አዲስ ዓመት🌼መዝገበ ምሕረት ሚድያ
11/09/2026

እንኳን ከዘመነ ማርቆስ ወደ ዘመነ ሉቃስ አሸጋገረን... 🙏 ዓመቱ የበረከት የፍቅር የአገልግሎት እንዲሆንላችሁ እንመኛለን

🌼መልካም አዲስ ዓመት🌼

መዝገበ ምሕረት ሚድያ

1 ቀን ቀረው💥💥💥💥💥የጳጉሜ የመሐረነ አብ ጸሎት💥💥በየዓመቱ በጳጉሜ የሚደረገው የመሐረነ አብ ጸሎት ከነገ ነሐሴ 30 ከምሽቱ 11:30 ጀምሮ ይካሄዳል 💥  በመክፈቻው በነሐሴ 30/2018 ዓ....
04/09/2026

1 ቀን ቀረው💥💥💥

💥💥የጳጉሜ የመሐረነ አብ ጸሎት💥💥

በየዓመቱ በጳጉሜ የሚደረገው የመሐረነ አብ ጸሎት ከነገ ነሐሴ 30 ከምሽቱ 11:30 ጀምሮ ይካሄዳል

💥 በመክፈቻው በነሐሴ 30/2018 ዓ.ም በካቴድራላችን እና በሰንበት ትምህርት ቤታችን አገልግለው ያለፉ አባቶች እናቶች ወንድሞች እህቶች ይታሰባሉ፤

ሁላችንም በመገኘት የጸሎቱ ተሳታፊዎች እንድትሆኑ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን🙏

መዝገበ ምሕረት ሰ/ት/ቤት

የ2018 ዓ.ም የተማሪዎች ምረቃ መርሐ ግብር ተካሄደ!በሰንበት ትምህርት ቤታችን መዝገበ ምሕረት ሰንበት ትምህርት ቤት በ2018 ዓ.ም መንፈሳዊ ትምህርታቸውን የተከታተሉ ከ1ኛ ክፍል እስከ ራ...
31/08/2026

የ2018 ዓ.ም የተማሪዎች ምረቃ መርሐ ግብር ተካሄደ!

በሰንበት ትምህርት ቤታችን መዝገበ ምሕረት ሰንበት ትምህርት ቤት በ2018 ዓ.ም መንፈሳዊ ትምህርታቸውን የተከታተሉ ከ1ኛ ክፍል እስከ ራብዓይ የሚገኙ ተማሪዎች እና የበገና ተማሪዎችን በ24/12/2018 የምረቃ መርሐ ግብር ተካሂዷል...

በዕለቱ የካቴድራላችን አስተዳዳሪ መልዓከ መዊዕ ስብሐት ባይህ በመገኘት ለተመራቂዎች አባታዊ ቡራኬ የሰጡ ሲሆን ቃለ ወንጌል በመምህር ዲ/ን ሚኪያስ አስረስ እንዲሁም ልዩ ልዩ መርሐ ግብሮች በተመራቂዎች ቀርበዋል::

ሙሉ መርሐ ግብሩን በሰንበት ትምህርት ቤታችን "መዝገበ ምሕረት" ዩቲዩብ ቻናል ያገኙታል

https://www.youtube.com/live/CVcoEvH_O18?si=6VIToP0MaqxHKocq

መዝገበ ምሕረት ሚድያ

የመልስ መርሐ ግብር ተካሄደ! በሰንበት ትምህርት ቤታችን በየዓመቱ የሚደረገው የመልስ መርሐ ግብር ዘንድሮም በ2018 ዓ.ም ጋብቻቸውን ለፈጸሙ የሰንበት ትምህርት ቤታችን አባላት በዛሬው ዕለት...
23/08/2026

የመልስ መርሐ ግብር ተካሄደ!

በሰንበት ትምህርት ቤታችን በየዓመቱ የሚደረገው የመልስ መርሐ ግብር ዘንድሮም በ2018 ዓ.ም ጋብቻቸውን ለፈጸሙ የሰንበት ትምህርት ቤታችን አባላት በዛሬው ዕለት ነሐሴ 17/2018 ዓ.ም በደመቀ ሁኔታ ተካሂዷል💥💥💥

በመርሐግብሩ ልዩ ልዩ የኅብረት ዝማሬዎች ፣ ቃለ እግዚአብሔር ፣ የኪነጥበብ ዝግጅቶች የቀረቡ ሲሆን ከዚህ ቀደም ስጦታ ላልወሰዱ ሙሽሮችም በሰንበት ትምህርት ቤቷ ስጦታ ተበርክቶላቸዋል🙏

መዝገበ ምሕረት ሚድያ

የእናታችን የቅድስት ኪዳነምሕረት ዓመታዊ በዓል በድምቀት ተከበረ💥ነሐሴ 16/2018 ዓ.ም - በካቴድራላችን ጎፋ ቤዛ ብዙኃን ቅድስት ኪዳነምሕረት ካቴድራል የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያ...
23/08/2026

የእናታችን የቅድስት ኪዳነምሕረት ዓመታዊ በዓል በድምቀት ተከበረ💥

ነሐሴ 16/2018 ዓ.ም - በካቴድራላችን ጎፋ ቤዛ ብዙኃን ቅድስት ኪዳነምሕረት ካቴድራል የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም የፍልሰቷ መታሰቢያ በዓል በድምቀት ተከብሯል..

በዕለቱ የአኃት ሰንበት ትምህርት አባላት በመገኘት ከሰንበት ትምህርት ቤታችን መዝገበ ምሕረት ሰ/ት/ቤት ጋር በአንድነት በማገልገል የበረከቱ ተሳታፊ ሆነዋል🙏

ለዓመቱ በሠላም ያድርሰን
መዝገበ ምሕረት ሚድያ

የመዝገበ ምሕረት ሰ/ት/ቤት 35ኛ ዓመት የመዝጊያ መርሐ ግብር ተካሄደ!ዓመቱን ሙሉ በልዩ ልዩ ዝግጅቶች ሲከበር የቆየው የሰንበት ትምህርት ቤታችን 35ኛ ዓመት በትላንትናው ዕለት በልዩ የመዝ...
03/08/2026

የመዝገበ ምሕረት ሰ/ት/ቤት 35ኛ ዓመት የመዝጊያ መርሐ ግብር ተካሄደ!

ዓመቱን ሙሉ በልዩ ልዩ ዝግጅቶች ሲከበር የቆየው የሰንበት ትምህርት ቤታችን 35ኛ ዓመት በትላንትናው ዕለት በልዩ የመዝጊያ መርሐ ግብር ተጠናቋል!

በዕለቱ የካቴድራላችን አስተዳዳሪ፣ የደብሩ ካህናት ፣ አንጋፋ የሰንበት ትምህርት ቤታችን መስራቾች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው ምዕመናን መርሐ ግብሩን ታድመዋል::

በአባላትም የኅብረት ዝማሬዎች እና ሌሎች መርሐ ግብሮች የቀረቡ ሲሆን የሰንበት ትምህርት ቤቷን ምስረታ የሚገልጽ የዶክመንተሪ ፊልም ለታዳሚው ቀርቧል
(ሙሉ መርሐ ግብሩን በዩቲዩብ ቻናላችን ያገኙታል)

ለዓመቱ በሰላም ያድርሰን!
መዝገበ ምሕረት ሚድያ

የ35ኛ ዓመት የመዝጊያ መርሐ ግብር!እንኳን አደረሰንዓመቱን ሙሉ በልዩ ልዩ ዝግጅቶች ሲከበር የቆየው የሰንበት ትምህርት ቤታችን 35ኛ ዓመት የፊታችን እሁድ በልዩ የመዝጊያ መርሐግብር ይጠናቀ...
31/07/2026

የ35ኛ ዓመት የመዝጊያ መርሐ ግብር!

እንኳን አደረሰን
ዓመቱን ሙሉ በልዩ ልዩ ዝግጅቶች ሲከበር የቆየው የሰንበት ትምህርት ቤታችን 35ኛ ዓመት የፊታችን እሁድ በልዩ የመዝጊያ መርሐግብር ይጠናቀቃል🙏🙏

በዕለቱ:- ቃለ እግዚአብሔር በዲ/ን ሕሊና በለጠ/ዘኆኅተ ብርሃን/ የሚሰጥ ይሆናል

ሁላችንም በዕለቱ በመገኘት የመርሐ ግብሩ ተሳታፊ እንድንሆን ጥሪያችንን እናስተላልፋለን

መዝገበ ምሕረት ሰ/ት/ቤት

የ35ኛ ዓመት ዓውደ ርዕይ ተከፈተ!የሰንበት ትምህርት ቤታችን 35ኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ የተዘጋጀው ዓውደ ርዕይ በዛሬው ዕለት በመሐረነ አብ ጸሎት የካቴድራላችን አሰተዳደሪ መልአከ መዊእ...
29/07/2026

የ35ኛ ዓመት ዓውደ ርዕይ ተከፈተ!

የሰንበት ትምህርት ቤታችን 35ኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ የተዘጋጀው ዓውደ ርዕይ በዛሬው ዕለት በመሐረነ አብ ጸሎት የካቴድራላችን አሰተዳደሪ መልአከ መዊእ ስብሐት ባይህ በተገኙበት ተመርቆ ተከፍቷል!

ዓውደ ርዕዩ ከነገ ሐሙስ እስከ ቅዳሜ ከጠዋቱ 2:00 ሰዓት እስከ ምሽቱ 2:00 የሚቀጥል በመሆኑ ከወዳጅ ዘመድ ጋር በመሆን እንድትጎበኙ ኮሚቴው ጥሪውን አስተላልፏል🙏

መዝገበ ምሕረት ሚድያ!

የመክፈቻ ቀን 💥💥💥💥የ35ኛ ዓመት ልዩ ዓውደ ርዕይ! ዛሬ ምሽት 12 ሰዓት ላይ በኅብረት ጸሎት ይከፈታል💥💥ሁላችሁም በመገኘት የሰንበት ትምህርት ቤታችንን የ35 ዓመት ጉዞ እንድትመለከቱ በክ...
29/07/2026

የመክፈቻ ቀን 💥💥💥💥
የ35ኛ ዓመት ልዩ ዓውደ ርዕይ!

ዛሬ ምሽት 12 ሰዓት ላይ በኅብረት ጸሎት ይከፈታል💥💥

ሁላችሁም በመገኘት የሰንበት ትምህርት ቤታችንን የ35 ዓመት ጉዞ እንድትመለከቱ በክብር ተጋብዛችኋል!

መዝገበ ምሕረት ሰ/ት/ቤት

Address

ጎፋ ሰፈር፤ Gofa Campe
Addis Ababa
43163ADDISABABA

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የጎፋ ቤዛ ብዙኃን ቅድስት ኪዳነምሕረት ካቴድራል መዝገበ ምሕረት ሰንበት ት/ቤት Gofa Beza Bizuhan posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share