Kolfe Kal Heywet Church Offical page

Kolfe Kal Heywet Church Offical page Welcome to where impossible is possible !

በቸርነትህ ዓመትን ታቀዳጃለህ፥ ምድረ በዳውም ስብን ይጠግባል።መዝሙረ ዳዊት 65:11ውድ  የእግዚአብሔር  ቤተሰቦች ወደ አዲስ የምህረት ዓመት እንኳን አደረሳችሁ!አሁድ  ከጠዋቱ 3:30 ጀምሮ...
10/09/2026

በቸርነትህ ዓመትን ታቀዳጃለህ፥ ምድረ በዳውም ስብን ይጠግባል።መዝሙረ ዳዊት 65:11
ውድ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች ወደ አዲስ የምህረት ዓመት እንኳን አደረሳችሁ!
አሁድ ከጠዋቱ 3:30 ጀምሮ አብረን ጌታን የምናመሰግንበትና የጌታንእራት የምንወስድበት ስለሆነ እንዳትቀሩ።

የ21ቀን የፆም ፀሎት መርዓ ግብር ማጠቃለያ ኘሮግራም  "... በልመናህ መጀመሪያ ላይ ትዕዛዝ ወጥቷል ..."ዳን 9:20በነሐሴ 24/2018 ዓመተ ምህረት በነበረው የአምልኮ ኘሮግራም መጋቢ ...
30/08/2026

የ21ቀን የፆም ፀሎት መርዓ ግብር ማጠቃለያ ኘሮግራም "... በልመናህ መጀመሪያ ላይ ትዕዛዝ ወጥቷል ..."ዳን 9:20
በነሐሴ 24/2018 ዓመተ ምህረት በነበረው የአምልኮ ኘሮግራም መጋቢ ሚሊዬን ጉደታ «እንደ ብርሃን ልጆች በጥበብ መመላለስ» በሚል ርዕስ የእግዚአብሔርን ቃል ከኤፌሶን መጽሐፍ 5:15-20 አካፍለዋል። በመልእክታቸው የኤፌሶን መፅሐፍ በሁለት መሠረታዊ ክፍሎች እንደሚከፈል ከምዕረፍ 1-3በክርስቶስ የተደረገልን ማንነት የሚየወሳ እንደሆነና ምዕራፍ 4 እና5 ፣ እንደ ብርሃን ልጆች በጥበብ ስለመመላለስ የሚናገር ክፍል እንደሆነ አስተምረዋል።
እንደ ብርሃን ልጅ በጥበብ ለመመላለ
* የጌታ ፈቃድ ምን እንደሆነ አስተውሉ እንጂ ሞኞች አትሁኑ.
* መንፈስ ይሙላባችሁ እንጂ በወይን ጠጅ አትስከሩ
* በመዝሙርና በዝማሬ በመንፈሳዊ ቅኔ እርስ በእርስ መነጋገር
* በሁሉ ማመስገን
ቀኖቹ ክፉዎች እንደሆኑ በመረዳት በጥበብ መመላለስ እንድንችል ጌታ ይርዳን።
በዕለቱ 16 ወንድሞችና እህቶች ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ተቀላቅለዋል! አሜን!

እግዚአብሔር ሉዓላዊ ነው!በነሐሴ 17/2018 ዓ.ም በነበረን የአምልኮ ጊዜ መጋቢ ዳን አግዘው «እግዚአብሔር ሉዑላዊ ነው» በሚል ርዕስ ከትንቢተ ዳንኤል (4:34-37) የእግዚአብሔርን ቃል ...
23/08/2026

እግዚአብሔር ሉዓላዊ ነው!
በነሐሴ 17/2018 ዓ.ም በነበረን የአምልኮ ጊዜ መጋቢ ዳን አግዘው «እግዚአብሔር ሉዑላዊ ነው» በሚል ርዕስ ከትንቢተ ዳንኤል (4:34-37) የእግዚአብሔርን ቃል አካፍለውናል።የጌታ ሉዓላዊነት በሁኔታዎች የማይወሰን፣ በዕለት ተዕለት ሕይወታችን የምናየው እንደሆነና በዳንኤል መፅሐፍ በአመጋገባቸው፣ በናቡከደነፆር ሕልም (ዳን 2:28) እና በእቶን እሳት ውስጥ እንኳን ሳይቀር እንዴት ኦንደተገለፀ አስተምረዋል።
አክለውም የእግዚአብሔርን ሉዓላዊነት የተረዳ ትውልድ፦
1. በቅድስና ይኖራል (ዳን 1:8)
2. እግዚአብሔርን ብቻ ያመልካል (ዳን 3:17)
3. በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ ይጸልያል (ዳን 6:10) ጸሎት የተስፋ መቁረጥ ምልክት ሳይሆን የፍቅር፣ የአባትና የልጅ ግንኙነት ነው! ዳንኤል ብዙ ሀገራትን እያስተዳደረ በቀን 3 ጊዜ ይጸልይ ነበር። ዛሬም እኛ በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ ስንሆን አባታችንን እግዚአብሔርን ማናገር እንዳለብን አስተምረዋል።
በዕለቱ 18 ወንድሞችና እህቶች ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ተቀላቅለዋል!
ዛሬ አብራችሁን ለነበራችሁ ጌታ አብዝቶ ይባርካችሁ! ያልነበራችሁ ደግሞ በሚቀጥለው እሁድ እንድትገኙ በፍቅር እንጋብዛችኋለን

ልዩ የወጣቶች SUMMER CAMP ከነሐሴ 6  እስከ 17 / 2018 ዓመተ ምህረት ከሰዓት 10:00-እስከ ማታ 2:00 ሰዓት በኮልፌ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን ይካሄዳል። በነዚህ ቀናት  በተ...
12/08/2026

ልዩ የወጣቶች SUMMER CAMP ከነሐሴ 6 እስከ 17 / 2018 ዓመተ ምህረት ከሰዓት 10:00-እስከ ማታ 2:00 ሰዓት በኮልፌ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን ይካሄዳል። በነዚህ ቀናት በተለያዩ ርዕሶች ላይ የትምህርት ጊዜ፣ የማማከር ጊዜ፣ በተለያዩ ርዕስ የፀሎት ጊዜ ፣ የጨዋታዎች እና የሻይ ቡና ጊዜ ይኖረናል። በመሆኑም ፕሮግራሙ ላይ በጊዜ በመገኘት እንድትካፈሉ ተጋብዛችኋል።

የጾም እና የፀሎት ኘሮግራም ስለተጀመረ ኑ! አብረን የእግዚአብሔርን  ፊት እንፈልግ ከነሐሴ 4 እስከ 24/2018 ዓመተ ምህረት  ከጠዋቱ 3:00 ሰዓት ጀምሮ
11/08/2026

የጾም እና የፀሎት ኘሮግራም ስለተጀመረ ኑ! አብረን የእግዚአብሔርን ፊት እንፈልግ ከነሐሴ 4 እስከ 24/2018 ዓመተ ምህረት ከጠዋቱ 3:00 ሰዓት ጀምሮ

በነሐሴ 3/2018 ዓ.ም በነበረው የመጀመሪያው የፀሎት ወር መርሃ-ግብራችን ላይ መጋቢ ብስራት በቀለ «ፀሎት» በሚል ርዕስ  የእግዚአብሔርን ቃል አካፍለዋል። በመልእክታቸው የነቢዩ ዳንኤልን፣...
10/08/2026

በነሐሴ 3/2018 ዓ.ም በነበረው የመጀመሪያው የፀሎት ወር መርሃ-ግብራችን ላይ መጋቢ ብስራት በቀለ «ፀሎት» በሚል ርዕስ የእግዚአብሔርን ቃል አካፍለዋል። በመልእክታቸው የነቢዩ ዳንኤልን፣ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን እና የሐዋርያትን የጸሎት ሕይወት መሠረት በማድረግ፣ ጸሎት ከእግዚአብሔር ጋር የሚደረግ ዘላቂና ጥልቅ ሕብረት መሆኑን አስተምረዋል።
ውጤታማ የጸሎት ሕይወት በሙሉ እምነት ከመጸለይ ባሻገር ከዕለታዊ ቅድስና ጋር የተሳሰረ፣ በመንፈስ ቅዱስ መሪነት የሚከናወን፣ እንዲሁም የራሳችንን ፍላጎት ከመፈለግ ይልቅ የእግዚአብሔርን ክብርና የትውልድን ጥቅም የሚያስቀድም መሆን እንዳለበት አስተምረዋል። በመጨረሻም በአንድነት የጌታን እራት መታሰቢያ በመካፈል ከጌታ ጋር ያለንን ህብረት አድሰናል።
🙏 ዛሬ አብራችሁን ለነበራችሁ እንዲሁም ወደ እግዚአብሐር መንግሰት የተቀላቀለችሁ ሁሉ ጌታ አብዝቶ ይባርካችሁ፤ ያልነበራችሁ ደግሞ በሚቀጥለው ሳምንት እንድትገኙ በፍቅር እንጋብዛችኋለን!

በኮልፌ ቃለ ህይወት ቤተክርስቲያን በአዳጊ ወጣቶች አገልግሎት የተዘጋጀው  የክረምት ስልጠና ከሐምሌ 27 ጀምሮ "በሁለንተና ማደግ"በሚል  መሪ ቃል፤ አዳጊ ወጣቶችን በእግዚአብሔር ቃል ለቀጣይ...
06/08/2026

በኮልፌ ቃለ ህይወት ቤተክርስቲያን በአዳጊ ወጣቶች አገልግሎት የተዘጋጀው የክረምት ስልጠና ከሐምሌ 27 ጀምሮ "በሁለንተና ማደግ"በሚል መሪ ቃል፤ አዳጊ ወጣቶችን በእግዚአብሔር ቃል ለቀጣይ ዘመን የማስታጠቅ አገልግሎት እየተከናወነ ይገኛል፣ እግዚአብሔርም ድንቅና መልካም የሆነ የትምህርት፣ የጨዋታ እና የህብረት ጊዜ አየሰጠን ነው።
እስከ ነሐሴ 9 ቀን 2018 ይቀጥላል አዳጊ ወጣቶች የሆናቹህ ሁሉ ከእኛ ጋር እንድታሳልፉ እንጋብዛችኋለን።

ሐምሌ 26/2018 ዓመተ ምህረት  በነበረው የቤተሰብ ሁለተኛ ሳምንት ላይ እህታችን ቤተልሔም ከግሬት ኮሚሽን በኤርምያስ 35፥1-19 ላይ ተመሠርታ  «ድንበር ተሻጋሪ ወላጅነት» በሚል ርዕስ ...
03/08/2026

ሐምሌ 26/2018 ዓመተ ምህረት በነበረው የቤተሰብ ሁለተኛ ሳምንት ላይ እህታችን ቤተልሔም ከግሬት ኮሚሽን በኤርምያስ 35፥1-19 ላይ ተመሠርታ «ድንበር ተሻጋሪ ወላጅነት» በሚል ርዕስ ያስተማረች ሲሆን፣ በመግቢያዋም ኢዮናዳብ አንስታ እንዴት ለልጆቹ ትዕዛዝ እንደሰጠና ሕይወቱ ቢያልፍም ምክሩና ተግባሩ በትውልድ እንደቀጠለ ሁሉ፣ ዛሬም ወላጆች ከዓለምና ከቴክኖሎጂ ጎጂ ተጽዕኖዎች ተለይተው ዘላቂ መንፈሳዊ ውርስ ማስተላለፍ እንዳለብን አስተምራለች። ድንበር ተሻጋሪ ወላጅነት:-
* በፍጹም ልብ እግዚአብሔርን በማምለክ (ዘዳ 6፥1)፣
* የእግዚአብሔርን ቃል በልብ በመያዝ፣
* ቃሉን ከማውራት ይልቅ ሰርቶ በሚያሳይ ተምሳሌታዊ ሕይወት ልጆችን በመቅረጽ፣ እንዲሁም
*እንደ ዮሴፍና ዳንኤል ተግዳሮቶችን ተቋቁሞ በሚያሸንፍ እምነት ትውልድን በማስተማር መገልጥ እንዳልብት አጠንክራ አስትመራለች በምድር ከተመሠረቱት ሦስት ታላላቅ ተቋማት 1.ቤተሰብ፣
2. ቤተክርስቲያንና
3. ቤተመንግሥት
ሲሆኑ መጀመሪያ በእግዚአብሔር የተቋቋመው ቤተሰብ ዋና ተልዕኮው ወንጌልን መስበክና ደቀ-መዝሙር ማድረግ በመሆኑ፣ ከእኛ በኋላ ለሚመጡት ትውልዶች:-
* የአምልኮ፣
* የቃሉ ሙላት፣
* የተምሳሌትነትና
* ትውልድን የመተካት
ዘላቂ መሠረት ልንጥልላቸው ይገባል።
ትውልዱን የምናሻግር ወላጆች እግዚአብሔር ያድርገን!

ልዩ የአዳጊ ወጣቶች SUMMER CAMP ከሀምሌ 27  ጀምሮ እስከ ነሐሴ 17 / 2018 ዓ.ም ከሰዓት 7:00-11:00 ሰዓት በኮልፌ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን ይካሄዳል። በዚህ ፕሮግራም በ...
30/07/2026

ልዩ የአዳጊ ወጣቶች SUMMER CAMP ከሀምሌ 27 ጀምሮ እስከ ነሐሴ 17 / 2018 ዓ.ም ከሰዓት 7:00-11:00 ሰዓት በኮልፌ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን ይካሄዳል። በዚህ ፕሮግራም በተለያዩ ርዕሶች ላይ የትምህርት ጊዜ፣ የፓናል ውይይቶች፣ የሕይወት ተሞክሮ የማካፈል፣ የተለያዩ ጨዋታዎች እና የሻይ ቡና ጊዜ ይኖረናል። በፕሮግራሙ ላይ በመገኘት ከእኛ ጋር በረከቱን እንድትካፈሉ ተጋብዛችኋል።

24/07/2026

Enjoy the videos and music you love, upload original content, and share it all with friends, family, and the world on YouTube.

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Kolfe Kal Heywet Church Offical page posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Place Of Worship

Send a message to Kolfe Kal Heywet Church Offical page:

Shortcuts

Share

Category