Ethiopian Evangelical Lutheran Church - EELC

Ethiopian Evangelical Lutheran Church - EELC ... but [be thou] in the fear of the LORD all the day long. Proverbs 23:27

29/05/2026

የቤተክርስቲያናችን ፕሬዚዳንት ቄስ አወቀ ጨፋ በChristian leadership የማስተርስ ዲግሪ በመመረቅዎ እርስዎ እና ቤተሰብዎ እንዲሁም ቤተክርስቲያን በመላው እንኳን ደስ ያለን!

Congratulations to our church president, Rev. Aweke Chefa, and, his family and, the entire church, on his graduation with Master's degree in Christian leadership!

18/03/2026

Rev. Eyob Dinku Tadesse, Rector of Assela Theological Seminary of Ethiopian Evangelical Lutheran Church (EELC), received his Master of Sacred Theology (STM) on March 8 at the annual commencement held at Lutheran School of Theology in Gothenburg (LSTG), CTSFW's international extension site for the STM program. EELC President Rev. Awoke Chefa Bedasso gave a beautiful decorative plaque with a letter to CTSFW as an expression of his thanks for the solid theological education that CTSFW offered to Rev. Tadesse together with LSTG. Dr. Naomichi Masaki, Director of STM, brought the plaque back to CTSFW and delivered it to President Jon Bruss and Provost Charles Gieschen.

EELC on ILC News.
10/12/2025

EELC on ILC News.

ETHIOPIA – The Ethiopian Evangelical Lutheran Church (EELC) held its Annual General Assembly from August 21-22, and has elected a new president: Rev. Awoke Chefa. At the time of his election, President Chefa had served 28 years as head pastor of the EELC’s congregation in Asella; 14 years as Pre...

22/11/2025
በዛሬው ዕለት የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ሉተራን ቤተክርስቲያን መሪዎች እና አገልጋዮች  በወንጌል እና በልማት ስራዎች ዙሪያ ከቤተክርስቲያኒቱ ጋር በአጋርነት በመስራት ላይ ከሚገኘው በፊንላንድ የ...
28/10/2025

በዛሬው ዕለት የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ሉተራን ቤተክርስቲያን መሪዎች እና አገልጋዮች በወንጌል እና በልማት ስራዎች ዙሪያ ከቤተክርስቲያኒቱ ጋር በአጋርነት በመስራት ላይ ከሚገኘው በፊንላንድ የስዊድን ሉተራን ወንጌላውያን ማህበር/SLEAF/ መሪዎች ጋር ከዚህ ቀደም በተከናወኑና በቀጣይ ሊከናወኑ በታቀዱ አገልግሎቶችና ስራዎችን አስመልክቶ ገንቢ ምክክር አድርገዋል፡፡

ክብር ለእግዚአብሔር ይሁን!
../

Today, leaders and pastors of the Ethiopian Evangelical Lutheran Church held a constructive discussion with the leaders of the Swedish Lutheran Evangelical Association in Finland (SLEAF), which is working in partnership with the church in evangelism and development work, regarding the services and works that have been carried out so far and those that are planned to be carried out in the future.

Soli Deo Gloria!
..//...

ቄስ አወቀ ጨፋ የEELC ፕሬዘዳንት ሆነው ስለተሾሙ እንኳን ደስ ያልዎት! አዲስ ለተሸሙበት ለዚህ ታላቅ አገልግሎት እግዚአብሔር ፀጋውን ያብዛልዎት! *እንዲሁም ቄስ ጌቱ ታዬ በምክትል ፕሬዘዳ...
23/10/2025

ቄስ አወቀ ጨፋ የEELC ፕሬዘዳንት ሆነው ስለተሾሙ እንኳን ደስ ያልዎት! አዲስ ለተሸሙበት ለዚህ ታላቅ አገልግሎት እግዚአብሔር ፀጋውን ያብዛልዎት!
*
እንዲሁም ቄስ ጌቱ ታዬ በምክትል ፕሬዘዳንትነት በመመረጥዎ እንኳን ደስ ያልዎት! የጌታ ጸጋ ይብዛልዎት!
*
ቄስ ሙሴ አላዛር የኢ.ወ.ሉ.ቤ. ፕሬዘዳንት በመሆን ለሁለት ጊዜያት/terms/ ላበረከቱት ላቅ ያለ አገልግሎት እናመሰግናለን ። እግዚአብሄር እርስዎን እና አገልግሎትዎን ይባርክ!

***
Congratulations to Rev. Awoke Cheffa on your new appointment as the president of EELC. May God bestow His grace upon you as you step into your new calling.
*
We would also like to congratulate Rev. Getu Taye on being elected Vice President!
*
Thank you so much, Rev. Musse Alazar, for your service as the president of EELC for two terms. May God bless you and your service in His kingdom!

 #የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ሉተራን ቤተክርስቲያን በአለም አቀፍ የሉተራን ካውንስል (ILC) “የአለም ኮንፈረንስ - 2025” በቄስ ሙሴ አልዓዛር ተወክላ ተሳትፎ በማድረግ ላይ ትገኛለች። ይህም...
19/09/2025

#የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ሉተራን ቤተክርስቲያን በአለም አቀፍ የሉተራን ካውንስል (ILC) “የአለም ኮንፈረንስ - 2025” በቄስ ሙሴ አልዓዛር ተወክላ ተሳትፎ በማድረግ ላይ ትገኛለች። ይህም ኮንፈረንስ እ.ኤ.አ ከሴፕቴምበር 14-19, 2025 በፊሊፒንስ ሃገር በመካሄድ ላይ ይገኛል።

#አለም አቀፍ የሉተራን ካውንስል (ILC) መጽሐፍ ቅዱስ በመንፈስ ቅዱስ ግልጠት የተጻፈ እና ስህተት አልባ የእግዚአብሔር ቃል ነው ብለው የሚታመኑ የሉተራዊያን አብያተ ክርስቲያናት ህብረት ነው፡፡

ክብር ለእግዚአብሔር ይሁን!

is participating on International Lutheran Council (ILC ), World Conference,2025 represented by Rev. Mussie Alazar. The conference is hosted by Philippines 🇵🇭, from September 14-19,2025.

is a confessional Lutheran church bodies fellowship,with an assertion that the Holy Scriptures are the inspired and infallible Word of God.

For more, https://ilcouncil.org/

Soli Deo Gloria!

https://www.youtube.com/watch?v=_DgGvDZFDFc
18/09/2025

https://www.youtube.com/watch?v=_DgGvDZFDFc

ይህ የኢቫንጀሊካል ቲቪ ነው ። ስርጭቱን በ Frequency 11105 - Symbol rate 45000 - Polarization Horizontal ላይ ታገኙታላችሁ። መረጃውን ለሌሎችም በማጋራት እንዲያገኙን ያድርጓቸው።አዳዲስ የኢቫንጀሊካል ቲቪ ...

የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ሉተራን ቤተክርስቲያን በጾታ ግንኙነት ጉዳዮች ላይ ጥብቅ የአቋም መግለጫ አወጣችየኢትዮጵያ ወንጌላዊት ሉተራን ቤተክርስቲያን መስከረም 8 ቀን 2018 ዓ.ም በተመሳሳይ ጾ...
18/09/2025

የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ሉተራን ቤተክርስቲያን በጾታ ግንኙነት ጉዳዮች ላይ ጥብቅ የአቋም መግለጫ አወጣች

የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ሉተራን ቤተክርስቲያን መስከረም 8 ቀን 2018 ዓ.ም በተመሳሳይ ጾታ ጋብቻ፣ የጾታ ቅይይር እና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ግልጽ የሆነ እና ጥብቅ የአቋም መግለጫ አውጥታለች።

ይህ መግለጫ ነሐሴ 15 እና 16 ቀን 2017 ዓ.ም. በተካሄደው የቤተክርስቲያኗ ጠቅላላ ጉባኤ ውሳኔ መሠረት ቤተክርስቲያኗ በውጭ እየተነገረ በሚገኘው የለዘብተኛ ስነ-መለኮት እና በ"ሉተራዊነት" ስም የሚጠሩ ድርጅቶች አስተምህሮች ምክንያት የራሷን አመለካከት ለህዝቡ እንድትገልጽ እንዳስፈለጋት አብራርታለች።

በመግለጫዋ ውስጥም ቤተክርስቲያኗ የሚከተሉትን ዋና ዋና ነጥቦች አቅርባለች፡-

በዚህም ቤተክርስቲያኗ መጽሐፍ ቅዱስ ሙሉ በሙሉ ምንም ስህተት የሌለበት እና የእግዚአብሔር ቃል መሆኑን በጽኑ እንደምታምን አስታውቃለች።

የጋብቻ ተፈጥሮ ፡- እግዚአብሔር ሰውን ወንድ እና ሴት በማድረግ ወንድ እና ሴት መካከል ያለው ጋብቻን ብቻ እንደፈጠረ በማመን፣ የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻ እና የጾታ ቅይይር ልምምዶች ከመለኮታዊው አላማ ጋር የሚጋጩ እንደሆኑ ገልፃለች።

የቤተክርስቲያን ህግጋት፡- የቤተክርስቲያኗ መተዳደሪያ ደንብ ላይ ጋብቻ በሁለት ተቃራኒ ጾታዎች (ወንድ እና ሴት) መካከል የሚደረግ መንፈሳዊ እና ህጋዊ ትስስር እንደሆነ በግልጽ እንደተገለጸ አስፍራለች፣ ከዚህም ውጭ ያሉ ልምምዶችን በሙሉ እንደምትቃወም ትገልጻለች።

ከሌሎች አባላት ልዩነት፡-ቤተክርስቲያኗ ከተመሳሳይ ጾታ ጋብቻን የሚደግፉ የለዘብተኛ ስነ-መለኮት አራማጆች እና በ"ሉተራን" ስም የሚጠሩ ድርጅቶች ጋር ምንም ዓይነት ግንኙነት እና ትብብር እንደሌላት ገልጻለች። እነዚህ አስተሳሰቦች ከእግዚአብሔር ቃል ጋር የማይጣጣሙ እና "በእግዚአብሔር ዕውቀት ላይ የተነሱ" እንደሆኑ ትገልጻለች።

ለሀገር ጥሪ፡-ቤተክርስቲያኗ ትክክለኛው መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትምህርት በሀገሪቱ ያሉ ሁሉም አብያተ ክርስቲያናት እና በህዝቡ ዘንድ ተከብሮ እንዲኖር የምትፈልግ መሆኗን አሳስባለች።

ቤተክርስቲያኗ ከታሪክ ጀምሮ የእግዚአብሔርን ቃል መሠረት በማድረግ ወንጌል በማዳረስ፣ ትምህርት እና ጤና ዘርፎችን በማራመድ ለሀገሪቱ ህዝብ አገልግሎት እያበረከተች እንደምትገኝም እና ለወደፊቱም ይህንን ራዕይ እንደምታስቀጥል በመግለጫው አስታውቃለች።

Via GMM TV NEWS

18/09/2025
የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ሉተራን ቤተ ክርስቲያን ከግብረሰዶማዊነት ፣ ጾታ ቅየራ እና ተያያዥ ጉዳዮች ጋር በተያያዘ ያላትን አቋም አስመልክቶ መግለጫ ሰጠች።መስከረም 8 በኢትዮጵያ ወንጌላዊት ሉተ...
18/09/2025

የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ሉተራን ቤተ ክርስቲያን ከግብረሰዶማዊነት ፣ ጾታ ቅየራ እና ተያያዥ ጉዳዮች ጋር በተያያዘ ያላትን አቋም አስመልክቶ መግለጫ ሰጠች።

መስከረም 8 በኢትዮጵያ ወንጌላዊት ሉተራን ቤተ ክርስቲያን በተሰጠው መግለጫ ላይ የቤተ ክርስቲያኒቱ አመራሮች እና አገልጋዮች ተገኝተዋል።
በሀገራችን ከአንድ ምዕተ ዓመት በላይ በመቆየት ወንጌል ባልደረሰባቸው አከባቢዎች ወንጌልን ለማድረስ ከፍተኛ አስተዋጽዖ እንዳደረገች የምተነሳው የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ሉተራን ቤተ ክርስቲያን ወንጌልን ከማድረስ በተጨማሪም በትምህርት እና በጤናው ዘርፍ ማህበራዊ አገልግሎትን ስትሰጥም ቆይታለች።

በሀገራችን በአሁኑ ወቅት የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻ ፣ የጾታ ቅይይራ ተያያዥ ጉዳዮች እየተስተዋሉ መምጣታቸውን ተከትሎ ቤተ ክርስቲያኒቱ ነሐሴ 15 እና 16 ቀን 2017 ዓ.ም ባካሄደችው ጠቅላላ ጉባኤ ያጸደቀችውን ውሳኔ መሰረት በማድረግ ባለ አምስት ነጥብ መግለጫ ይፋ አድርጋለች።

የመግለጫው ጭብጥም በዓለማችን በተለያዩ የሉተራን ቤተ እመነቶች ላይ ግብረሰዶማዊነት እና የጾታ ቅየራ ላይ የሚስተዋለው ለዘብተኛ አቋም የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ሉተራን ቤተ ክርስቲያንን እንደማይወክል በአንክሮ ለማስገንዘብ ያለመ ነው።

መስከረም 8 የተሰጠው መግለጫ የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ሉተራን ቤተ ክርስቲያን ዋና ጸሐፊ የሆኑት ቄስ አወቀ ጴጥሮስ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉ ሲሆን የቤተ እምነቷ የወንጌል ክፍል ዳይሬክተር ቄስ ዳዊት ቱፋ የቤተ ክርስቲያኒቱን የአቋም መግለጫ በጽሑፍ አቅርበዋል።

ለኢቫንጀሊካል ቲቪ ፡ አማኑኤል ዴቢሶ

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethiopian Evangelical Lutheran Church - EELC posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share