የጽርሐ ጽዮን ሐዋርያት ጎላ ቅዱስ ሚካኤል ፍኖተብርሃን ሰ/ት/ቤት

  • Home
  • Ethiopia
  • Addis Ababa
  • የጽርሐ ጽዮን ሐዋርያት ጎላ ቅዱስ ሚካኤል ፍኖተብርሃን ሰ/ት/ቤት

የጽርሐ ጽዮን ሐዋርያት ጎላ ቅዱስ ሚካኤል ፍኖተብርሃን ሰ/ት/ቤት ይህ ገጽ የጽርሐ ጽዮን ሐዋርያት እና ጎላ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ፍኖተ ብርሃን ነዉ።

መስከረም 8"...ሙሴ... ለጊዜው በኃጢአት ከሚገኝ ደስታ ይልቅ ከእግዚአብሔር ሕዝብ ጋር መከራ መቀበልን መረጠ:: ብድራቱን ትኩር ብሎ ተመልክቷልና..." ዕብ. 11:24 በዛሬው ዕለት ከሚታ...
17/09/2026

መስከረም 8

"...ሙሴ... ለጊዜው በኃጢአት ከሚገኝ ደስታ ይልቅ ከእግዚአብሔር ሕዝብ ጋር መከራ መቀበልን መረጠ:: ብድራቱን ትኩር ብሎ ተመልክቷልና..." ዕብ. 11:24

በዛሬው ዕለት ከሚታሰቡ ቅዱሳን በረከትና ረድኤት ያሳትፈን!

ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተከፈቱ የማሕበራዊ ሚዲያ ገጾቻችን ናቸው። ቤተሰብ በመሆንና ለሌሎች በማጋራት አብረውን ያገልግሉ።

የቴሌግራም ቻናል
https://t.me/finotebirhan12

የዩቲዩብ ቻናላችን https://youtube.com/

የቲክቶክ አካውንታችን https://www.tiktok.com/?_t=8i8eHwFI3Es&_r=1

የፌስቡክ ገጻችን
https://www.facebook.com/Fbirhan?mibextid=2JQ9oc

"...ኤልሳቤጥም የማርያምን ሰላምታ በሰማች ጊዜ ፅንሱ በማኅፀንዋ ውስጥ ዘለለ፤ በኤልሳቤጥም መንፈስ ቅዱስ ሞላባት፥ በታላቅ ድምፅም ጮኻ እንዲህ አለች፦ አንቺ ከሴቶች መካከል የተባረክሽ ነሽ...
16/09/2026

"...ኤልሳቤጥም የማርያምን ሰላምታ በሰማች ጊዜ ፅንሱ በማኅፀንዋ ውስጥ ዘለለ፤ በኤልሳቤጥም መንፈስ ቅዱስ ሞላባት፥ በታላቅ ድምፅም ጮኻ እንዲህ አለች፦ አንቺ ከሴቶች መካከል የተባረክሽ ነሽ፥ የማኅፀንሽም ፍሬ የተባረከ ነው። የጌታዬ እናት ወደ እኔ ትመጣ ዘንድ እንዴት ይሆንልኛል? እነሆ፥ የሰላምታሽ ድምጽ በጆሮዬ በመጣ ጊዜ ፅንሱ በማኅፀኔ በደስታ ዘሎአልና። ከጌታ፤ የተነገረላት ቃል ይፈጸማልና ያመነች ብፅዕት ናት።"
ሉቃ 1፥41-45

በዛሬው ዕለት ከሚታሰቡ ቅዱሳን በረከት ያሳትፈን!

ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተከፈቱ የማሕበራዊ ሚዲያ ገጾቻችን ናቸው። ቤተሰብ በመሆንና ለሌሎች በማጋራት አብረውን ያገልግሉ።

የቴሌግራም ቻናል
https://t.me/finotebirhan12

የዩቲዩብ ቻናላችን https://youtube.com/

የቲክቶክ አካውንታችን https://www.tiktok.com/?_t=8i8eHwFI3Es&_r=1

የፌስቡክ ገጻችን
https://www.facebook.com/Fbirhan?mibextid=2JQ9oc

"...ለወይኔ ያላደረግሁለት፥ ከዚህ ሌላ አደርግለት ዘንድ የሚገባኝ ምንድር ነው? ወይንን ያፈራል ብዬ ስትማመን ስለ ምን ሆምጣጣ ፍሬ አፈራ?..." ትንቢተ ኢሳይያስ 5፥4በዚህች ዕለት ከሚታ...
15/09/2026

"...ለወይኔ ያላደረግሁለት፥ ከዚህ ሌላ አደርግለት ዘንድ የሚገባኝ ምንድር ነው? ወይንን ያፈራል ብዬ ስትማመን ስለ ምን ሆምጣጣ ፍሬ አፈራ?..." ትንቢተ ኢሳይያስ 5፥4

በዚህች ዕለት ከሚታሰቡ ቅዱሳን በረከት ያሳትፈን!

ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተከፈቱ የማሕበራዊ ሚዲያ ገጾቻችን ናቸው። ቤተሰብ በመሆንና ለሌሎች በማጋራት አብረውን ያገልግሉ።

የቴሌግራም ቻናል
https://t.me/finotebirhan12

የዩቲዩብ ቻናላችን https://youtube.com/

የቲክቶክ አካውንታችን https://www.tiktok.com/?_t=8i8eHwFI3Es&_r=1

የፌስቡክ ገጻችን
https://www.facebook.com/Fbirhan?mibextid=2JQ9oc

"እንግዲህ እነዚህን የሚያህሉ ምስክሮች እንደ ደመና በዙሪያችን ካሉልን፥ እኛ ደግሞ ሸክምን ሁሉ ቶሎም የሚከበንን ኃጢአት አስወግደን፥ የእምነታችንንም ራስና ፈጻሚውን ኢየሱስ ክርስቶስን ተመል...
14/09/2026

"እንግዲህ እነዚህን የሚያህሉ ምስክሮች እንደ ደመና በዙሪያችን ካሉልን፥ እኛ ደግሞ ሸክምን ሁሉ ቶሎም የሚከበንን ኃጢአት አስወግደን፥ የእምነታችንንም ራስና ፈጻሚውን ኢየሱስ ክርስቶስን ተመልክተን፥ በፊታችን ያለውን ሩጫ በትዕግሥት እንሩጥ፤" ዕብራውያን 12፥1

በዛሬው ዕለት ከሚታሰቡ ቅዱሳን በረከት ያሳትፈን!

ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተከፈቱ የማሕበራዊ ሚዲያ ገጾቻችን ናቸው። ቤተሰብ በመሆንና ለሌሎች በማጋራት አብረውን ያገልግሉ።

የቴሌግራም ቻናል
https://t.me/finotebirhan12

የዩቲዩብ ቻናላችን https://youtube.com/

የቲክቶክ አካውንታችን https://www.tiktok.com/?_t=8i8eHwFI3Es&_r=1

የፌስቡክ ገጻችን
https://www.facebook.com/Fbirhan?mibextid=2JQ9oc

መስከረም 4/2019 ዓ.ም"...የምታመልኩትን ዛሬ ምረጡ። እኔና ቤቴ ግን እግዚአብሔርን እናመልካለን።" ኢያሱ 24፥15በዚህች ዕለት ከሚታሰቡ ቅዱሳን ሁሉን ረድኤትና በረከት ያድለን!ይህ በጽ...
14/09/2026

መስከረም 4/2019 ዓ.ም

"...የምታመልኩትን ዛሬ ምረጡ። እኔና ቤቴ ግን እግዚአብሔርን እናመልካለን።" ኢያሱ 24፥15

በዚህች ዕለት ከሚታሰቡ ቅዱሳን ሁሉን ረድኤትና በረከት ያድለን!

ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተከፈቱ የማሕበራዊ ሚዲያ ገጾቻችን ናቸው። ቤተሰብ በመሆንና ለሌሎች በማጋራት አብረውን ያገልግሉ።

የቴሌግራም ቻናል
https://t.me/finotebirhan12

የዩቲዩብ ቻናላችን https://youtube.com/

የቲክቶክ አካውንታችን https://www.tiktok.com/?_t=8i8eHwFI3Es&_r=1

የፌስቡክ ገጻችን
https://www.facebook.com/Fbirhan?mibextid=2JQ9oc

 (የመጨረሻው ክፍል)ጥያቄ ፬---የአዲሱ ዓመት መጀመሪያ ቀን “ ዕንቍጣጣሽ ” በሚል ስያሜም ይታወቃል ፡፡ “ ዕንቍጣጣሽ ” ማለት ምን ማለት ነው ፡፡መልስ ፬ ከኢትዮጵያ መሠረት ጋራ የተያያ...
13/09/2026

(የመጨረሻው ክፍል)

ጥያቄ ፬---የአዲሱ ዓመት መጀመሪያ ቀን “ ዕንቍጣጣሽ ” በሚል ስያሜም ይታወቃል ፡፡

“ ዕንቍጣጣሽ ” ማለት ምን ማለት ነው ፡፡

መልስ ፬ ከኢትዮጵያ መሠረት ጋራ የተያያዘ ነው ፡፡ “ዕንቍጣጣሽ” ማለት በተንቈጠቈጠ ተፈጥሮ እግዚአብሔር ከሠራት ምድር ጋራ የተገኘ ስያሜ ነው ፡፡ አዎ እግዚአብሔር ፍጥረቱን አስጊጧል። ሰማይን በከዋክብት ምድርን በአበባ። ስለዚኽ አምላካችን እግዚአብሔር የፈጠራት ምድር የአጌጠች የለመለመች የአበበች የተንቈጠቈጠች ናት ለማለት “ ዕንቍጣጣሽ ” ትሰኛለች ፡፡ ይኸውም “ ዕንቍጣጣሽ ” የምትሰኘው ከላይ በጠቀስነው የዓመቱ መጀመሪያ ላይ ከሌሎች አበቦች ቀድማ የምትታየው የምድራችን የመጀመሪያይቱ ጌጥ መልኳ ቢጫ የኾነ አረንጓዴ ሣርና ልዩ ልዩ ዕፀዋትን በለበሰው መስክ መኻል ፈክታ የምትታየው አበባ ናት ፡፡በተለምዶ አነጋገር “ አዴ አበባ ትባላለች ፡፡ትክክለኛው አጠራር ግን አደይ አበባ ነው። ይኸውም አደይ ማለት በኢትዮጲያዊው የትግራዋይ ቋንቋ እናት ማለት ነው። አደይ አበባ ስንልም ከእናት ምድር የተገኘች የመጀመሪያው ዓመት አበባ ማለታችን ነው።

በተጨማሪም አንዳንድ የታሪክ መምህራን "ዕንቁጣጣሽ" ስለተባለበት ምክንያት ሲገልጹ ኢትዮጵያይቱ ንግሥት ሳባ ወደ ንጉሡ ሰሎሞን ዘንድ በሄደች ጊዜ ለጣቷ የሚሆን ዕንቁ " ዕንቁ-ለጣጥሽ" ብሎ የመጀመሪያውን የክብር ስጦታ ስለሰጣት ከዚያ ተያይዞ " ዕንቁጣጣሽ" የሚለው ቃል መጥቶ የዓመቱ የመጀመሪያ ቀን ተባለ ብለው የሚተርኩም አሉ።

ሴቶች ከሕፃናት እስከ ኮረዶች ድረስ እርሷን የመጀመሪያይቱን አዴ አበባና መጀመሪያ የተገኘውን እንግጫ ሣር በእጃቸው ይዘው ወይም አንድ አንዶቹ በወገባቸው ዙሪያ ቄጤማ አስረው “ አበባየ ሆሽ ለምለም ” እያሉ ከቤታቸው ጀምረው በእየአንድ አንዱ ቤት ደጃፍ እየዘመሩ እንግጫውን አዴ አበባን እየሰጡ ዞረው አዳርሰው ለቤተ እግዚአብሔርም አምኃ ገጸ በረከት ያቀርባሉ ፡፡
ይልቁንም ከጥፋት ውሃ በኋላ የኖኅ ልጆች ከመርብ በወጡ ጊዜ ዓለምን በዕጣ ተካፍለው የዐባይን ወንዝ ተከትለው ወደደጋይቱ ምድር በወጡ ጊዜ ለምለም የኢትዮጵያ ምድር መስክ በ“ አዴ አበባ” አሸብርቆ ተንቈጥቍጦ ስለአዩ ተደንቀው ተገርመው ውብ ድንቅ ዕንቍ፣ ዕጣ፣ ወጣልን። ዕንቍ ዕጣ ወጣሽልን የአሉት ብሂል “ ዕንቍ ዕጣ ወጣሽ ” ወደሚለው ትርጕም መጥቶ “ ዕንቍጣጣሽ ” የሚለውን ስያሜ አግኝቷል ፡፡

ከክፍል አንድ እስከ አራት ላጋራናቸው የበዓላት ጽሑፎች ምንጭ ከአበው ሊቃውንት፦
መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀንበሬ
ሊቀ ሊቃውንት አለቃ አያሌው ታምሩ ሰማዕት ዘእንበለ ደም
አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ
መልዐከ ብርሃን ዐይኔ
አለቃ አስፋው ዘተድባበ ማርያም
ሊቀ አበው ኤፍሬም ዘቀበና አቦ
ቀኝ ጌታ ዘለቀ ዘአትሮንሰ ማርያም
ደብተራ ዘኢየሱስና ቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሤ ዘቀበና አቦ
ሊቀ ሊቃውንት ብዙ አየሁ
የኔታ ተስፋ ዘቀራንዮ
የኔታ መንግሥቱ ዘባሕር ዳር
የኔታ ጥበቡ ዘዛራ
የንታ ይባቤ
አለቃ ሰዋስው
የንታ አእመረ
የንታ ኒቆዲሞስ
የንታ ያሬድ
የንታ ፍሥሓ
የንታ አንዳርጌ
የንታ በኵረ (ድጓ በጕንጩ )
የንታ ማእምር
የንታ ውቤ

ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተከፈቱ የማሕበራዊ ሚዲያ ገጾቻችን ናቸው። ቤተሰብ በመሆንና ለሌሎች በማጋራት አብረውን ያገልግሉ።

የቴሌግራም ቻናል
https://t.me/finotebirhan12

የዩቲዩብ ቻናላችን https://youtube.com/

የቲክቶክ አካውንታችን https://www.tiktok.com/?_t=8i8eHwFI3Es&_r=1

የፌስቡክ ገጻችን
https://www.facebook.com/Fbirhan?mibextid=2JQ9oc

12/09/2026

YouTube Description🎉 አዲስ ዓመት 2019 | ልዩ መርሐ ግብር 🎉በጽርሐ ጽየን ሐዋርያት ...

 ጥያቄ ፫፦  የአዲሱ ዓመት መጀመሪያ በኢትዮጵያውያን አገላለጽ “ ርእሰ ዐውደ ዓመት ”፤ “ ዐውደ ዓመት ”፤ "ቅዱስ ዮሐንስ" ይባላል ፡፡ ምክንያቱ ምንድር ነው ፡፡መልስ ፫፦  ዐውደ ዓመት...
11/09/2026



ጥያቄ ፫፦ የአዲሱ ዓመት መጀመሪያ በኢትዮጵያውያን አገላለጽ “ ርእሰ ዐውደ ዓመት ”፤ “ ዐውደ ዓመት ”፤ "ቅዱስ ዮሐንስ" ይባላል ፡፡ ምክንያቱ ምንድር ነው ፡፡

መልስ ፫፦ ዐውደ ዓመት ማለትስ ምንድነው ፡፡ ወበዐውዱ ለውእቱ መንበር ፡፡ ይቀውሙ ዐውዶ ፡፡ እንዲሁም ዐውደ ዐበቅቴ…ዐውደ ወርኅ…ዐውደ ዓመት…ዐውደ ማኅተም…ዐውደ ነገሥት…ዐውደ ዕለት…ዐውደ ፀሐይ…ዐውደ ቀመር የሚሉ ንባባትንና ቃላትን እናገኛለን ፡፡

ዐውደ ዓመት = በዐሥራ ዘጠኝ ዓመት ጨረቃና ፀሐይ የሚገናኙበት ማለት ነው ፡፡ ዐውደ ወርኅ = ከመባቻ እስከ መባቻ (ከልደታ እስከ ልደታ ) እንደማለት ነው ፡፡ ዐውደ ወርኅ = የጨረቃ ክንውን ሦስት መቶ ኀምሳ አራት ቀን ነው ፡፡ ዐውደ ማኅተም = ሰባ ሰባት ቀን ነው ፡፡ ዐውደ ዕለት = ማለት ሰባት ቀናት ማለት ነው ፡፡ ከእሁድ እስከ ቀዳም ወይም ቅዳሜ ድረስ ፡፡ ዐውደ ፀሐይ = ኻያ ስምንት ዓመት ነው ፡፡ ወንጌላውያን የሚገናኙበት ማለት ነው ፡፡ ዕለቱ ረቡዕ ወንጌላዊው ማቴዎስ ነው ፡፡ ዐውደ ቀመር = አምስት መቶ ሠላሳ ኹለት ዕለት ነው ፡፡ በዚኹ ዕለትም ወንጌላዊም ዐበቅቴም ይገናኙበታል ፡፡ ዕለቱ ሠሉስ ፡፡ ወንጌላዊው ማቴዎስ ፡፡ ዐበቅቴው አልቦ ነው ፡፡ ጥቅል ትርጉሙ ግን ዐውድ ማለት ዙሪያ ክብ ዐደባባይ የተጠረገ የተሰለቀ ስፍራ ሸንጎ ጉባኤ ዐውራጃ ቀበሌም የሚኾንበት ጊዜ አለ ማለት ነው ፡፡

ዳን = ፫ ፥ ፪ ፡፡ ሩት = ፪ ፥ ፩ ፡፡ ግብ = ፲፰ ፥ ፲፪ ፡፡
ስለዚኽ ርእሰ ዐውደ ዓመት ማለት የእሊኽ ዕለታት አውራኅ ዓመታት አዝማን መነሻ መገኛ መገለጫ መጀመሪያ ማለት ነው ፡፡ ይኽንንም በአምስተኛው ዓመተ ምሕረት መግቢያ ላይ የነበረው ኢትዮጵያዊ ቀዳማዊ ሊቅ ቅዱስ ያሬድ የወርኃ መስከረም መዝሙር
የመጀመሪያ ዕለት የሚዘመረውን መዝሙር “ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዮሐንስ ” ብሎ ሰይሞታል፡፡ የድጓውም መጀመሪያ ዮሐንስ ይባላል ፡፡



#1ኛ ወርኁ የኹሉ ነገር መጀመሪያ ነው ፡፡ ቅዱስ ዮሐንስም ወንጌሉን የጀመረው ከዕለተ ፍጥረት ጋራ አያይዞ በነቢይ ሙሴ የአጻጻፍ መንገድ ነው ፡፡ ነቢይ ሙሴ ጽሑፉን ሲጀምር “ በቀዳሚ ገብረ እግዚአብሔር…እግዚአብሔር በመጀመሪያ ሰማይንና ምድርን ፈጠረ…” በመጀመሪያ ብሎ ነው የጀመረው ፡፡ ቅዱስ ዮሐንስም “ መጀመሪያ ቃል ነበረ ፡፡ ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ ፡፡ ቃልም እግዚአብሔር ነበረ…” በማለቱ ቅዱስ ዮሐንስ ተብሏል።

#2ኛ ወንጌላውያን ኹሉ ወንጌላቸውን የጀመሩት በመጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ስብከት ነው ፡፡ ማቴዎስ በምዕራፍ 3 ፡፡ ማርቆስ በምዕራፍ 1 ፡፡ ሉቃስ በምዕራፍ 3 ፡፡ ዮሐንስ በምዕራፍ 3 ስለ መጥምቀ መለኮት ዮሐንስ ስለጠቀሱ የዘመን መጀመሪያም "ቅዱስ ዮሐንስ" ተብሎ ተሰይሟል።

#3ኛ ይኸው መጥምቅ ቅዱስ ዮሐንስ በንጉሥ ኄሮድስ በወርኃ ጰጉሜን ፩ ቀን ታስሮ #መስከረም ፪ ቀን በሰማዕትነት ዐርፏል ፡፡ ስለዚኽ መጥምቁ ቅዱስ ዮሐንስ ስለጌታ ምሥክርነቱ ደሙ የፈሰሰበት ዕለት ስለሆነ "ቅዱስ ዮሐንስ" ተብሏል ፡፡

ወንጌላዊ ቅዱስ ዮሐንስም ቢኾን ወንጌሉን “ መጀመሪያ ” ብሎ ከመጀመሪያው ዕለተ ፍጥረት ጋራ አያይዞ እንደ ጀመረው ይታወቃል ፡፡ በአቡሻኽር ስሌት እየለካን ወደኋላ ብንመለስ ዕለተ ፍጥረት የሚውለው በዘመነ ዮሐንስ ነው ፡፡ ቅዱስ ያሬድም ከእኒኽ መሠረታውያን ጥልቅ ምሥጢራተ አዝማን ጋራ አያይዞ የድጓውን መጀመሪያ “ ዮሐንስ ” ብሎታል ፡፡ እንግዲህ “ ብፁዕ አንተ ዮሐንስ ” ስለተባለበት “ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዮሐንስ ” ብሎ ስለተነገረበት “ ዮሐንስ ” የሚለውም ስም የወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስንና ስለጌታ መምጣት አስቀድሞ የመሠከረ የመጥምቁ ቅዱስ ዮሐንስን ስም ስለሚያስተባብር ዕለተ በዓሉ “ ዐውደ ዓመትም…ርእሰ ዐውደ ዓመትም…ቅዱስ ዮሐንስም ”…ተብሎ ይጠራል ማለት ነው ፡፡

!

ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተከፈቱ የማሕበራዊ ሚዲያ ገጾቻችን ናቸው። ቤተሰብ በመሆንና ለሌሎች በማጋራት አብረውን ያገልግሉ።

የቴሌግራም ቻናል
https://t.me/finotebirhan12

የዩቲዩብ ቻናላችን https://youtube.com/

የቲክቶክ አካውንታችን https://www.tiktok.com/?_t=8i8eHwFI3Es&_r=1

የፌስቡክ ገጻችን
https://www.facebook.com/Fbirhan?mibextid=2JQ9oc

 ጥያቄ ፪---አዲስ ዓመት ሲመጣ በእየጊዜው “ እንኳን ከዘመነ ማቴዎስ ወደ ዘመነ ማርቆስ ከዘመነ ሉቃስ ወደ ዘመነ ዮሐንስ አሸጋገረዎ ” ሲባል ይሰማል ፡፡ ምክንያቱ ምንድነው ፡፡------/...
11/09/2026



ጥያቄ ፪---አዲስ ዓመት ሲመጣ በእየጊዜው “ እንኳን ከዘመነ ማቴዎስ ወደ ዘመነ ማርቆስ ከዘመነ ሉቃስ ወደ ዘመነ ዮሐንስ አሸጋገረዎ ” ሲባል ይሰማል ፡፡ ምክንያቱ ምንድነው ፡፡
------////--------
መልስ ፪----በነገራችን ላይ እንኳን ከዘመነ ማርቆስ ወደ ዘመነ ሉቃስ በሰላም እና በጤና አሸጋገረንና አሁን የአለንበት ዘመን ዘመነ ሉቃስ ይባላል፡፡ ኢትዮጵያውያን ዘመናትን የምንቈጥረው ዓመተ ዓለም ብለን ከዕለተ ፍጥረት ጀምሮ ነው ፡፡

ዓመተ ዓለምም በኹለት ይከፈላል ዓመተ ኵነኔ ፤ ዓመተ ምሕረት ተብሎ ፡፡እነዚህም በሥጋችን ርደተ መቃብር በነፍሳችን ርደተ ሲኦል የነበረበትን ቅድመ ልደተ ክርስቶስንና ትንሣኤና ሕይወት የተገኘበትን ጊዜ ልደተ ክርስቶስን ድኅረ ልደተ ክርስቶስን የሚገልጡ ናቸው ፡፡

ቍጥርን ወደፊትም ወደኋላም መምራት የተለመደ ጥበባዊ ሻኂር ነው ፡፡ አበው ጥንታውያኑ በአራቱ አፍላጋት በአራቱ ነፋሳት በአራቱ ኪሩቤል ልዩ ልዩ ምሳሌ ይሰጡ ነበር ፡፡ ለምሳሌ አራቱን አፍላጋት ( ኤፌሶን ጤግሮስ ኤፍራጥስ ግዮን---ግዮን የተባለውም የእኛው (ዐባይ) መኾኑን ልብ ይሏል ባለሕዳሴው ) እነዚህን እናውሳ ፡፡

እሊኽ ከገነት ከአንድ ዕፀ ሕይወት ሥር ነቅተው (ፈልቀው) ውኃነታቸውን ይኽን ዓለም ዙረው አጠጥተው ዕፀዋትን ከይብሰት ወደልምላሜ ፤ ከልምላሜ ወደ ጽጌ ፤ ከጽጌ ወደፍሬ ያደርሳሉ ፡፡

አራቱ ወንጌላውያንም ( ማቴዎስ ማርቆስ ሉቃስ ዮሐንስ ) ወንጌልን ከአንድ ጌታ ተምረው ይኽን ዓለም ዙረው አስተምረው ምእመናንን ከይብሰተ ኀጢአት ወደ ልምላሜ ንሥሓ ፤ ከልምላሜ ንሥሓ ወደ ጽጌ ትሩፋት ፤ ከጽጌ ትሩፋት ወደፍሬ ክብር ያደርሳሉና ፡፡

ኤፌሶን ፈለገ ሐሊብ ነው ፡፡ ርስትነቱም የሕፃናት ነው ፡፡ ማቴዎስ በዚኸ ይመሰላል ፡፡ ከመ ሐሊብ ሐለብከኒ ወከመ ግብነት አርጋዕከኒ እንዲል ፡፡ በዘርእ የሚወለዱ የአበውን ልደት ይጽፋልና ፡፡ አንድም ኄሮድስ የአስፈጃቸውን የሕፃናቱን ነገር ይናገራልና ፡፡

ግዮን ፈለገ ወይን ነው ፡፡ ርስትነቱም ቢጾሙ ቢጸልዩም ሥራቸውን ደስ ብሏቸው የሚሠሩ ሰዎች ርስት ነው ፡፡ ማርቆስ በዚኸ ይመሰላል ፡፡ ወይን ያስተፌሥሕ ልበ ሰብእ እንጂ ይላል ወንጌሉን ኹሉን ደስ በሚያሰኝ በዕርገት ይጨርሳልና ፡፡ በዚኽስ ኹሉም ይተባበሩበታል ብሎ ቅብዐ ትፍሥሕት መንፈስ ቅዱስ በሚሰጥበት በጥምቀት ወንጌሉን ይጀምራልና ፡፡
እነዚኽ ምሳሌያት ናቸው ፡፡ ልክ እንደእነዚኽ የዓመተ ምሕረትን አቈጣጠር በአራት በመክፈል በአራቱ ወንጌላውያን ማቴዎስ ማርቆስ ሉቃስ ዮሐንስ ስም ተሰይሟል ተጠርቷል ተመድቧል ፡፡ ወደፊት እንደመቍጠር ኹሉ ወደኋላም ተመልሰን እስከ ዕለተ ፍጥረት ብንቈጥር የአኒኽን አራት ወንጌላውያንን ስያሜ እናገኛለን ፡፡

ዘመኑ እኮ የክርስቶስ ነው ፡፡ የምሕረት ነው ፡፡ የመዳን ነው ፡፡ የፍቅር ነው የሰላም ነው ፡፡ ስለዚኽ ከክርስቶስ በተገኘው የወንጌል ውኃ አጠጥተው ምእመናንን ከይብሰተ ኀጢአት ወደ ልምላሜ ንሥሓ ፤ ከልምላሜ ንሥሓ ወደ ጽጌ ትሩፋት ፤ ከጽጌ ትሩፋት ወደፍሬ ክብር ያደርሳሉና፤ ፍሬ ክብር ማለትም ወንድም ከወንድሙ ጋራ የሚመካከርበት የሚስማማበት የሚፋቀርበት የሰላም ዘመን ይኾን ዘንድ በስማቸው ተሰይሟል ፡፡

!

ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተከፈቱ የማሕበራዊ ሚዲያ ገጾቻችን ናቸው። ቤተሰብ በመሆንና ለሌሎች በማጋራት አብረውን ያገልግሉ።

የቴሌግራም ቻናል
https://t.me/finotebirhan12

የዩቲዩብ ቻናላችን https://youtube.com/

የቲክቶክ አካውንታችን https://www.tiktok.com/?_t=8i8eHwFI3Es&_r=1

የፌስቡክ ገጻችን
https://www.facebook.com/Fbirhan?mibextid=2JQ9oc

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የጽርሐ ጽዮን ሐዋርያት ጎላ ቅዱስ ሚካኤል ፍኖተብርሃን ሰ/ት/ቤት posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Place Of Worship

Send a message to የጽርሐ ጽዮን ሐዋርያት ጎላ ቅዱስ ሚካኤል ፍኖተብርሃን ሰ/ት/ቤት:

Shortcuts

Share