Semen MKC

Semen MKC የአዲስ አበባ ሰሜን አጥቢያ መሠረተ ክርስቶስ ቤ/ክ ከሰሜን ሆቴል ከፍብላ ከፋሲል ትምህርት ቤት ጀርባ የምትገኝ ስትሆን፣ በአጥቢያነት የተመሰረተችው በ1980ዓ.ም. ነው፡፡

16/08/2026
13/08/2026
🎓🌿 ሳምንታዊ የክረምት የዩኒቨርስቲና የኮሌጅ ተማሪዎች ፕሮግራምበዚህ ሳምንት በእግዚአብሔር ጸጋ በተካሄደው የወጣት የዩንቨርሲቲና የኮሌጅ ተማሪዎች ፕሮግራም፣ "አማተርነት ወይስ ፕሮፌሽናሊዝም...
05/08/2026

🎓🌿 ሳምንታዊ የክረምት የዩኒቨርስቲና የኮሌጅ ተማሪዎች ፕሮግራም
በዚህ ሳምንት በእግዚአብሔር ጸጋ በተካሄደው የወጣት የዩንቨርሲቲና የኮሌጅ ተማሪዎች ፕሮግራም፣ "አማተርነት ወይስ ፕሮፌሽናሊዝም?" በሚል ርዕስ የተዘጋጀው የክርክር መድረክ በእውቀት፣ በውድድር ፣ በዝግጅት እና በመንፈሳዊ አንድነት የተሞላ ነበር። 🙏❤️

💡 በውይይቱ ውስጥ፦
📖 የአማተርነትና የፕሮፌሽናሊዝም ጽንሰ ሐሳብን፣
⚖️ የሁለቱን ጥንካሬና ድክመት፣
❤️ የተሰጥኦ እና የሙያ ብቃት ያላቸውን ሚና፣
✝️ እንዲሁም በክርስቲያናዊ አገልግሎት ያላቸውን ዋጋ በሰፊው ተወያይተናል።
🌱 በመጨረሻም የደረስንበት እውነት...
አማተርነት የነገሮችን ጅማሬ ያቀጣጥላል፤
ፕሮፌሽናሊዝም ደግሞ ያንን እውነት በሥርዓት ተፅዕኖ እንዲሰጥ ያደርጋል። 🔥
ሁለቱ ተቃራኒዎች ሳይሆኑ፣ እግዚአብሔርን ለማክበር እርስ በርሳቸው የሚደጋገፉ ሁለት ውብ ስጦታዎች መሆናቸውን ተረድተናል። 🤝✨

🎤 በዶ/ር ዳንኤል በተሰጠው ማጠቃለያ፣ ይህ ሚዛናዊ አመለካከት ለተማሪዎቻችን በትምህርት፣ በሙያ፣ በአገልግሎት እና በህይወት ጉዞ ጠንካራ መሠረት እንደሚሆን ተገልጿል። 🌍📚

🙌 ይህ የክረምት ጊዜ እግዚአብሔር ለእድገታችን የሰጠን ውድ እድል ነው። ስለዚህ ሁሉንም የዩኒቨርስቲና የኮሌጅ ተማሪዎች በቀጣዮቹ ሳምንታዊ ፕሮግራሞቻችን እንድትመጡ በፍቅር እንጋብዛለን። 💙

📖 "የምታደርጉትን ሁሉ ከልባችሁ እንደ ጌታ እንጂ ለሰው አይደለም ብላችሁ አድርጉ።" (ቆላስይስ 3፥23) ✝️

🕊️ ቀጣይ ሳምንት እስክንገናኝ፣ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ፀጋ፣ የእግዚአብሔር ፍቅር እና የመንፈስ ቅዱስ ኅብረት ከሁላችን ጋር ይሁን! አሜን! 🤍✨

#የክረምትፕሮግራም 🌿
#የወጣቶችኅብረት 🤝
#የዩኒቨርስቲእናየኮሌጅተማሪዎች 🎓
#አማተርነት
#ፕሮፌሽናሊዝም
#እግዚአብሔር





✝️🙌

ዛሬ የእሁድ አምልኮ ድንቅ ትምህርት ወንድማችን ዶ/ር ጸጋ ዘፕራጋ በቆላስይስ 1፡9-14 ላይ ተመስርቶ "ለፍሬያማ ሰዎች ስለሚደረግ ጸሎት" ጥልቅ የሆነ የእግዚአብሔርን ቃል ተካፍለናል። ክርስ...
02/08/2026

ዛሬ የእሁድ አምልኮ ድንቅ ትምህርት ወንድማችን ዶ/ር ጸጋ ዘፕራጋ በቆላስይስ 1፡9-14 ላይ ተመስርቶ "ለፍሬያማ ሰዎች ስለሚደረግ ጸሎት" ጥልቅ የሆነ የእግዚአብሔርን ቃል ተካፍለናል። ክርስቲያን ዘወትር በቃሉ እና በመንፈስ ቅዱስ መሞላት እንዳለበት እና የእግዚአብሔርን የፈቃዱን እውቀት ስንሞላ ለጌታ የተገባና እርሱን በሁሉ ደስ የሚያሰኝ ኑሮ መኖር እንደምንችል በሰፊው ተምረናል።

በህይወታችን የእግዚአብሔርን ፈቃድ መሞላት እና ማወቅ ለምትፈልጉ ሁሉ ይህ መልእክት ትልቅ አቅም እና በረከት ይሆንላችኋል!
📌 በትምህርቱ የተዳሰሱ ዋና ዋና ነጥቦች፦
⚬ የሚጸለይላቸው ሰዎች እነማን ናቸው? (በወንጌል ፍሬ እያፈሩ ያሉ ቅዱሳን)
⚬ የጸሎቱ ርዕስ፦ የእግዚአብሔርን የፈቃዱን እውቀት መሞላት
⚬ ለእግዚአብሔር ደስታ የመኖር 4 መገለጫ መንገዶች (መልካም ስራ፣ ማደግ፣ ጽናት/ትዕግስት፣ እና ምስጋና)

ሙሉ ስብከቱን ይመልከቱ!

ዛሬ የእሁድ አምልኮ ድንቅ ትምህርት ወንድማችን ዶ/ር ጸጋ ዘፕራጋ በቆላስይስ 1፡9-14 ላይ ተመስርቶ "ለ...

ከ 13 ዓመት በታች ልጆች ላሏችሁ ወላጆች እና አሳዳጊዎች፡በሰሜን አዲስ አበባ መሠረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን የልጆች አገልግሎት ክፍል ከጋብቻና ቤተሰብ አማካሪዎች (ጋቤማ) ጋር በመሆን ለጌ...
16/07/2026

ከ 13 ዓመት በታች ልጆች ላሏችሁ ወላጆች እና አሳዳጊዎች፡
በሰሜን አዲስ አበባ መሠረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን የልጆች አገልግሎት ክፍል ከጋብቻና ቤተሰብ አማካሪዎች (ጋቤማ) ጋር በመሆን ለጌታ የተገባ ትውልድ በሚል ርዕስ ባዘጋጀው ልዩ ውይይት እና ሥልጠና ላይ ቅዳሜ ሐምሌ 18 ቀን 2018 ዓ.ም ሙሉ ቀን እንድትገኙ በታላቅ አክብሮት እንጋብዛለን።

እግዚአብሔር አምላክ በመካከላችን ስለነበረ ስሙ የተመሰገነ ይሁን! 🙏✨የሰሜን አዲስ አበባ መሠረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ቤተሰቦች፤ በሐምሌ 4, 2018 ዓ/ም ባዘጋጀነው ልዩ የመዝሙርና የም...
14/07/2026

እግዚአብሔር አምላክ በመካከላችን ስለነበረ ስሙ የተመሰገነ ይሁን! 🙏✨
የሰሜን አዲስ አበባ መሠረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ቤተሰቦች፤ በሐምሌ 4, 2018 ዓ/ም ባዘጋጀነው ልዩ የመዝሙርና የምስጋና ምሽት ላይ ጥሪአችንን አክብራችሁ በመገኘት ከእኛ ጋር በህብረት ስላመለካችሁ ከልብ እናመሰግናለን።

Address

Addis Ababa
34523

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Semen MKC posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Place Of Worship

Send a message to Semen MKC:

Shortcuts

Share