New Creation International Church

New Creation International Church This Page is official page for NEW CREATION INTERNATIONAL CHURCH ETH.
(243)

24/08/2026
ርእስ፣ የሚሰማ የሚመልስ አምላክ‎‎        በፓስተር አማን ‎‎¶ ክርስቲያን የሆነ በክርስቶስ አምኖ የዳነ ሰው ጸሎቱ የማይሰማበት ምንም አይነት ምክንያት አይኖርም።‎‎¶ እግዚአብሔር ሃሳ...
19/08/2026

ርእስ፣ የሚሰማ የሚመልስ አምላክ

‎ በፓስተር አማን

‎¶ ክርስቲያን የሆነ በክርስቶስ አምኖ የዳነ ሰው ጸሎቱ የማይሰማበት ምንም አይነት ምክንያት አይኖርም።

‎¶ እግዚአብሔር ሃሳቡን የማይቀይር፣ከእኛ ጋር ያለ አምላክ ነው፣ ይሰማናል ይመልስልናል።

‎ 1ኛ ነገስት 18

‎24 እናንተም የአምላካችሁን ስም ጥሩ፥ እኔም የእግዚአብሔርን ስም እጠራለሁ፤ ሰምቶም በእሳት የሚመልስ አምላክ፥ እርሱ አምላክ ይሁን። ሕዝቡም ሁሉ፡— ይህ ነገር መልካም ነው፡ ብለው መለሱ።

‎¶ ጸሎት እንዲመለስ የሚያስፈልገው ጸሎት ነው።ጸሎት
‎ጥያቄ የምናቀርብበት ሳይሆን እግዚአብሔር ከእኛ ጋር የሚያሳልፈው የናፍቆት ጊዜ ነው።

‎¶ እግዚአብሔር አባታችን ስለሆነ በማንኛውም ሰአትና ሁኔታ እኛን ለማየት የሚናፍቅ አምላክ ነው።

‎¶ በጠላት ፊት ስንጠራው የሚመጣና የሚመልስልን አምላክ አለን።

‎ 2ኛ ዜና 7

‎14 በስሜ የተጠሩት ሕዝቤ ሰውነታቸውን አዋርደው ቢጸልዩ፥ ፊቴንም ቢፈግሉ፥ ከክፉ መንገዳቸውም ቢመለሱ፥ በሰማይ ሆኜ እሰማለሁ፥ ኃጢአታቸውንም ይቅር እላለሁ፥ ምድራቸውንም እፈውሳለሁ።
‎15 አሁንም በዚህ ስፍራ ለሚጸለይ ጸሎት ዓይኖቼ ይገለጣሉ፥ ጆሮቼም ያደምጣሉ።

‎¶ እኛ ባለንበት ሁሉ እግዚአብሔር አለ።

‎¶ ብዙዎች ከከባድ ነገር የወጡበት የጸሎት አይነቶች አሉ።

‎ ኤርሚያስ 29

‎13 እናንተ ትሹኛላችሁ፥ በፍጹም ልባችሁም ከሻችሁኝ ታገኙኛላችሁ።
‎14 ከእናንተም ዘንድ እገኛለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር፥ ምርኮአችሁንም እመልሳለሁ፥ ከአሕዛብም ሁሉ ዘንድ እናንተንም ካሳደድሁበት ስፍራ ሁሉ እሰበስባችኋለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር፤ እናንተንም ለምርኮ ወዳፈለስሁበት ስፍራ እመልሳችኋለሁ።

‎¶ ጸሎት የእግዚአብሔር ልብ ከእኛ ልብ ጋር ሲገናኝ ማለት ነው። የምንጸልየው አንዳች ነገር ፈልገን ብቻ ሳይሆን ከእግዚአብሔር ጋር ልብ ለልብ ለመጨዋወት ነው።

‎¶ ከልባችን ከፈለግን እግዚአብሔር እንደዛው እንደልባችን መሻት ይሆንልናል።

‎¶ ከእግዚአብሔር ጋር ከልባችን ለመሆን የሚያስፈልገን የእግዚአብሔር ቃል ነው ።

‎ መዝሙር 119

‎89 አቤቱ፥ ቃልህ በሰማይ ለዘላለም ይኖራል።

‎¶ የእግዚአብሔር ቃል ሁሉን የፈጠረ ፣ያጸና፣ ፍጥረተ አለምን በስርአት እንዲሄድ ያደረገ ነው።

‎¶ ያልተመለሰ ጸሎታችን ከእግዚአብሔር ቃል ጋር ያልተስማማን ብቻ ከሆነ እንጂ ከቃሉ ጋር ከተስማማን
‎አለመሆን አይችልም።

‎ መዝሙር 103

‎20 ቃሉን የምትፈጽሙ፥ ብርቱዎችና ኃያላን፥ የቃሉንም ድምፅ የምትሰሙ መላእክቱ ሁሉ፥ እግዚአብሔርን ባርኩ።

‎¶ የምንጠይቀው ነገር ምንድነው?

‎ መዝሙር 27

‎4 እግዚአብሔርን አንዲት ነገር ለመንሁት እርስዋንም እሻለሁ፤ በሕይወቴ ዘመን ሁሉ በእግዚአብሔር ቤት እኖር ዘንድ፥ እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኘውንም አይ ዘንድ፥ መቅደሱንም እመለከት ዘንድ።

‎ ¶ የምንጠይቀውን አለማወቅ ጸሎቶቻችን እንዳይሰሙ ያደርጋል ለዚህ ነው የምንጸልየው ነገር ቅድሚያ የሚሰጠው የቱ እንደሆነ መለየት አለብን።

‎¶ ስንጸልይ ተወራርደን መሆን አለበት።በቃ ያልነው ጉዳይ እስኪመለስ ድረስ መንበርከክ አለብን።

‎¶ የእግዚአብሔር ሃሳብ እንዲፈጸም፣ቤተክርስቲያን በምድር ላይ ተጽዕኖ ማምጣት እስከምትችል ድረስ መጸለይ ያስፈልጋል።

‎ ማቴዎስ 18

‎19 ደግሞ እላችኋለሁ፥ ከእናንተ ሁለቱ በምድር በማናቸውም በሚለምኑት ነገር ሁሉ ቢስማሙ በሰማያት ካለው ከአባቴ ዘንድ ይደረግላቸዋል።

‎¶ ለጸሎት ስንሰባሰብ የተስማማንበት ጉዳይ መኖር አለበት።

‎¶ ስንጸልይ ጽናት ያስፈልገናል።

‎ ሉቃስ 18

‎1 ሳይታክቱም ዘወትር ሊጸልዩ እንዲገባቸው የሚል ምሳሌን ነገራቸው፥.......

‎7 እግዚአብሔር እንኪያስ ቀንና ሌሊት ወደ እርሱ ለሚጮኹ ለሚታገሣቸውም ምርጦቹ አይፈርድላቸውምን?
‎8 እላችኋለሁ፥ ፈጥኖ ይፈርድላቸዋል። ነገር ግን የሰው ልጅ በመጣ ጊዜ በምድር እምነትን ያገኝ ይሆንን?

‎¶ ዕምነት መጽናት ነው።መታገስ፣ መቆየት፣እግዚአብሔር ላይ መታመንን ይጠይቃል።

‎¶ እግዚአብሔር የሚመልስ አምላክ ነው፣ህብረታችንን፣
‎ተስፋ አለመቁረጣችንን ይፈልጋል።

‎¶ ከመልሳችን ጋር ላለመተላለፍ መቆየትን መልመድ አለብን።አቋርጠን በመሄድ የምናተርፈው ነገር የለም።
‎እግዚአብሔር ፊት በመቆየት ግን ማትረፍ፣መቀበል ይሆንልናል፣ምክንያቱም አባታችን የሚወደን፣የሚሰማን ፣
‎የሚመልስልን አምላክ ነው።

‎¶ ጸሎታችን አማራጭ የሌለው መሆን አለበት።

‎¶ የእኛ ምርጫ ቃሉ እንጂ ሁኔታ አይደለም።

‎ 1ኛ ሳሙኤል 1

‎10 እርስዋም በልብዋ ትመረር ነበር፥ በእግዚአብሔር ፊት ጸለየች፥ ጽኑ ልቅሶም አለቀሰች።

‎ ¶ የጨከኑ ሰዎች ሁሉ ጸሎታቸው ተመልሷል።ጨክነን
‎አይሆንም ማለት፣መቁረጥና የእግዚአብሔር ሃሳብ በእኛ የሚፈጸምበት ጊዜ መሆን አለበት።

‎¶ የጠላትን ሃሳብ ከእቅዱ ጀምሮ ማፍረስ ያለብን በጸሎት ነው፣የሚሰማን ደግሞም የሚመልስ አምላክ ስላለን በድል አድራጊነት መመላለስ አለብን።

‎ ማንም በክርስቶስ ቢሆን አዲስ ፍጥረት ነው።

ማክሰኞ በፍጹም አይቀርም!!!!!ሁላችሁም ተጋብዛችኋል!!አድራሻ:- አዲስ አበባ ሪቼ አጥቢያይህንን የgooglemap Link ይጠቀሙhttps://maps.app.goo.gl/rEaKdmYsYDFKep...
17/08/2026

ማክሰኞ በፍጹም አይቀርም!!!!!
ሁላችሁም ተጋብዛችኋል!!
አድራሻ:- አዲስ አበባ ሪቼ አጥቢያ
ይህንን የgooglemap Link ይጠቀሙ
https://maps.app.goo.gl/rEaKdmYsYDFKepLT6?g_st=atm (https://maps.app.goo.gl/rEaKdmYsYDFKepLT6?g_st=atm...)
09 40 40 00 00 / 09 40 50 00 00
Connect with us on:
Facebook - New Creation International Church
TikTok
tiktok.com/?lang=en (http://tiktok.com/?lang=en...)
YouTube
https://www.youtube.com/ (https://www.youtube.com/...)
NEW CREATION INTERNATIONAL CHURCH/ ኒው ክርኤሽን አለም አቀፍ ቤተክርስቲያን አዲስ አበባ ሪቼ አጥቢያ Addis Ababa, Ethiopia
★★★★★

Address

New Creation Church
Addis Ababa

Opening Hours

Tuesday 17:30 - 20:30
Friday 17:30 - 20:30
Sunday 10:00 - 12:30

Telephone

+251940400000

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when New Creation International Church posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Place Of Worship

Send a message to New Creation International Church:

Share