JIT Orthodox Tewahido Christian Group

JIT Orthodox Tewahido Christian Group # የጅማ ዩኒቨርስቲ ቅ/ገብርኤል ቤ/ክርስቲያን ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ክርስቲያን ተማሪዎችን ጥሩ ግንኙነት መፍጠር እና እርስ በእርስ እንዲረዳዱ ማድረግ።

1⃣.  ፨ይህን ፎቶ የምትመለከቱ በሀገር ውስጥም በመላውም ዓለም ያላችሁ ኢትዮጵያውያን ፦       ፨ይህ ቦታ በሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት በሞላሌ ከተማ አስተዳደር ስር የሚገኝ የጫ ደብረ ፀሃ...
25/12/2025

1⃣. ፨ይህን ፎቶ የምትመለከቱ በሀገር ውስጥም በመላውም ዓለም ያላችሁ ኢትዮጵያውያን ፦
፨ይህ ቦታ በሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት በሞላሌ ከተማ አስተዳደር ስር የሚገኝ የጫ ደብረ ፀሃይ አቡነ ሀብተማርያም ቤ/ክ ነው ።

፨አድራሻ ፦ መነሻችሁን ከመላው የሀገሪቱ ክፍል አድርጋችሁ ወደ 👇
ዘብር ቅ/ገብርኤል
እመጓ ኡራኤልና
አርብሃራ መድኀኔዓለም ቤ/ክ ለምትጓዙ መዳረሻ ከሆነችው ሞላሌ ከተማ በ 1.8 ኪ.ሜ በቅርብ ርቀት የሚገኝ ቦታ ነው።

2⃣. #በዚህ ቦታ_ብዙ_ዓይነት እንዲሁም #ተዓምራት በፃዲቁ አቡነ ሀብተማርያም ፀበል ተደርጓል።

፨ፀበሉን ጠጥተውና ተጠምቀው፦ ከራስ ህመም ፥ ከወገብ ህመም ፣ ከሆድ ህመም እንዲሁም ከጨጓራ ህመምና ከደም ግፊት ድነዋል።
በተጨማሪም ለረጅም ጊዜ በዊልቸር የነበረ ድህነትን አግኝቶ ቆሞ ለመሄድ ችሏል።

3⃣. ይህ ቤ/ክ እንደምትመለከቱት ምንም ዓይነት ግንባታ ያልተደረገለት በመሆኑ ይህንን ፈዋሽ የሆነ ፀበል ጥራቱን የጠበቀ ፀበል ቤት ለማሰራትና ቤ/ክርስቲያኑን ለመገንባት በመታሰቡ በሀገር ውስጥም በመላውም ዓለም ያላችሁ ኢትዮጵያውያን፦
፨በፀሎታችሁ ፥ በሀሳባችሁ ፥ በጥሬ-ዕቃ እንዲሁም በገንዘባችሁና በጉልበታችሁ ቤ/ክርስቲያኑን ትረዱ ዘንድ በፃዲቁ ስም ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።

4⃣. ቤ/ክርስቲያኑ በራሱ ስም የተከፈተ የኢትዮያ ንግድ ባንክ እንዲሁም የአባይ ባንክ አካውንት ያለው በመሆኑ በተከፈተው የአካውንት ቁጥር በማስገባት ቤ/ክርስቲያኑን መርዳትና የበረከቱ ተካፋይ መሆን እንደምትችሉ ለማሳወቅ እንወዳለን።

#⃣. ✍ በተጨማሪም ቤ/ክርስቲያኑ
https://t.me/Yecha_Debre_Tsehay_26

የሚል የቴሌግራም ግሩፕ ያለው በመሆኑ ማንኛውንም ሀሳብ ለመስጠትና መረጃ ለማግኘትና እርዳታ ማድረግ ለምትፈልጉ በሙሉ በተለጠፈው የቤ/ክርስቲያኑ አስተዳዳሪና የአስተባባሪዎች ስልክ ላይ በመደወል ማናገር የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር!
ወለወላዲቱ ድንግል!
ወለመስቀሉ ክቡር!
አሜን።

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when JIT Orthodox Tewahido Christian Group posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Place Of Worship

Send a message to JIT Orthodox Tewahido Christian Group:

Shortcuts

Share