ማኅበረ ማርያም ዘቀጨኔ ደብረ ሠላም መድኃኔዓለም ወደብረ ትጉኃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን

  • Home
  • Ethiopia
  • Addis Ababa
  • ማኅበረ ማርያም ዘቀጨኔ ደብረ ሠላም መድኃኔዓለም ወደብረ ትጉኃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን

ማኅበረ ማርያም ዘቀጨኔ ደብረ ሠላም መድኃኔዓለም ወደብረ ትጉኃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን This is the official face book page of Mahbere Mariam of Kechene Debre Selam Medhanialem & Debre Tiguhan St.Gebrael Church

29/05/2025

በእንተ ንድየት ………….ስለ ድኽነት
ለዚህ ጽሑፍ መነሻ የሆነኝ አንድ ወንድሜ ስለ ድኽነት በማኅበራዊ ድረ ገጹ ላይ ያሰፈረው ሀሳብ ነው፡፡ አንዳንድ ሰዎች ድኽነትን ሲያሽሞነምኑ ግርም ይለኛል የሚል የትዝብት ቃል በ Facebook ገጹ ላይ አጋርቶናል፡፡ ትዝብቱ በገደምዳሜም ቢሆን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን አስተምህሮን የመሞገት ዓላማ ያለው ይመስላል፡፡ እኛም በቻልነው መጠን ወንድማችንን ሳይሆን ሀሳቡን በጨዋነት እንሞግታለን፡፡ ድኻ ከዚኽ ዐለም ሀብት ቍርጭኝ ድኻን የኾነ ምናምን የሌለው ቍርጭኝ ድኻ። ደከታም ፣ ድክቱም ፣ ነዳይ. በእንግሊዘኛው ደግሞ needy poor የምንለው ቃል ይወክላል፡፡ መቼም ቢሆን ሰዎች ቤተ ክርስቲያንን ለመሞገት ረጅም ርቀት እስከተጓዙ ድረስ ቤተ ክርስቲያን ለምዕመኖቿ ድምጽ ማሰማቷ የማይቀር ጉዳይ ነው፡፡ በዚህ ረገድ የኔን ጽሑፍ እንደ አንድ የቤተ ክርስቲያን ድምጽ አድርጋችሁ ታዩልኝ ዘንድ እማጸናለሁ፡፡ ወዳጄ ሆይ ቤተ ክርስቲያን እኮ ምስካየ ህዙናን ናት፡፡ በሀዘን የተጨቆኑትን ፣ መውጪ መግቢያ ያጡትን፣ መረጋጋት የተሳናቸውን፣ ደዌ የጸናባቸውን ሁሉ ሰብስባ መያዟ አልፋም ለድሆች መጠጊያ መሆኗ የአምላኳን ፈቃድ መፈጸሟን እንደሆነ ልታውቅ ይገባል፡፡ እሷ ለድኾች መቆምን የተማረችው እኮ ከአምላኳ ነው፡፡ በመሆኑም ለወንድሜ ምላሽ ይሆን ዘንድ ንድየት ወይም ድኽነት በሚል ርዕስ የቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ ምን ይመስላል? የሚለውን ወደ መፈተሽ እንሂድ፡፡ አምላከ ቅዱሳን ፣ የድኾች አምላክ በመካከላችን ሆኖ እንዲያስተምረን የእርሱ ቅዱስ ፈቃዱ ይሁንልን፡፡
አዎ ድኽነት አስከፊ ገጽታ አለው፡፡ ደስም አይልም፡፡ ጉስቁልና ምን መልካም ነገር አለውና? ለመሆኑ ድኽነትን መጠየፍ አለብን ስንል ድኻን ወደ መናቅ እና ማዋረድ ደረጃ መድረስ አለብን ማለት ነው ወይ? በፍጹም ፡፡ በተለይ ለአንድ በክርስትና እኖራለሁ ለሚል ሰው ድኻን ማክበር አስፈላጊ ስለመሆኑ ክብርና ምሥጋና ይግባውና የጌታችን እና የአምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ምድራዊ ሕይወት ዋቢ ምስክሩ ነው፡፡ አምላካችን ኑሮው ሁሉ የድኽነት ነበር፡፡ ድኻን መናቅ ለድሆች የመንፈስ ዕረፍት ሲሰጣቸው አልፎ ተርፎም ሲፈውሳቸው የነበረው የአምላካችን ተግባሩን እንደመናቅ ይቆጠራል፡፡ ጌታ የሞተላቸው እኛ የናቅናቸውን ድኾችን ጭምር ነጻ ሊያወጣቸው መሆኑ ልብ ልንል ይገባል፡፡ ጌታ በመዋዕለ ሥጋዌው በቤተ መንግሥት ከሚኖሩ ነገሥታት ጋር መገኘትን አልመረጠም፡፡ ከዚያ ይልቅ ምስኪኖችን በፍቅሩ ሰበሰባቸው፡፡ ደቀ መዛሙርቱ በዘመኑ ከነበሩ ሀብት ንብረት ከሌላቸው የሚቆጠሩ ድኾች የሚል ስያሜ የተሰጣቸው ነበሩ፡፡ ስለሆነም ድሀ በእግዚአብሔር ዘንድ ዋጋ እንዳለው ካላወቅህ ከራስህ ክርስትና ጋር በተቃራኒ ቆመሃል ማለት ነው፡፡ ፈጣሪ ከእንዲህ ካለው ተቃርኖ ይሰውረን…………
የተወደደ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ በተለይም ክርስቲያን ሆነህ ድኾችን የምትንቅ ከሆነ ክርስቶስን እየሰደብክ እንደሆነ አስተውል ይለናል፡፡ የሰው ልጅ በአንድም በሌላም መንገድ ድኻ ሊሆን ይችላል፡፡ ዛሬ አግኝቶ ከሆነ ነገ ሊያጣ ይችላል፡፡ ድኽነት በሰው ልጅ የዕለት ተዕለት ሕይወት ውስጥ የምናየው የአዘቦት ክስተት ነው፡፡ በሀብት የከበሩ ከዘመን በኋላ ነዳያን የሆኑ ብዙዎች አሉ፡፡ ከታች ተነስተው በሀብት የከበሩም ብዙዎች ናቸው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ሳይቀር በዚህ ከፍታ እና ዝቅታ የነበሩትን ግለሰቦችን ታሪክ ሲያወሳ አንመለከታለን፡፡ ድኽነትን ማሽሞንመን የሚለው ቃሉን ማጉላት የተፈለገው በዋናነት ነዳያን በማትጥየፈው ቤተ ክርስቲያን ላይ ስላቅ ለመናገር ከሆነ ስህተት ነው፡፡ እኛ ኦርቶዶክሳውያን ቤተ ክርስቲያን ብቻ ሳትሆን እግዚአብሔርንም ጭምር አምላከ ነዳያን ወተስፋ ቅቡጻን እንለዋለን፡፡ እግዚአብሔር የምስኪኖች አምላክ በቀቢጸ ተስፋ ላሉት ተስፋቸው ነው ማለታችን ነው፡፡ ታዲያ ጌታ ያልተጠየፋቸውን ድኾች ቤተ ክርስቲያን የምትጠየፋቸው ስለምንድነው?
ሊቃውንት ከእንስሳት እና ከዕጸዋት ይልቅ የሰው ልጅ የበለጠ ድኽነት ይስማማዋል ሲሉ ያስተምሩናል፡፡ ዕጸዋት እስከ ምግቦቻቸው ተፈጠሩ፡፡ እንስሳት እስከ ልብሶቻቸው ተፈጠሩ፡፡ የሰው ልጅ ደግሞ ለመብሉ እና ለልብሱ ከዕጸዋቱ እና ከእንስሳቱ ላይ ጥገኛ ሆኖ ተፈጠረ ይላሉ፡፡ ሲወለድ ጀምሮ የሰው ልጅ በእቅፍ ውስጥ ያለ በእንክብካቤ የሚያድግ አቅመቢስ እንደሆነ ያሰምሩበታል፡፡ እንዲህ አይነት ድኻና ምስኪን ሆነህ ተወልደህ ሳለህ ሌሎችን በድኽነት ለመፈረጅ የሚያስችል አቅም ከየት እንዳገኘህ የምታውቀው አንተ ብቻ ነህ፡፡ ወገኖቼ እምብዛም መታበይ አያስፈልግም፡፡ በሚያልፍ እንደ ህልም እና እንደ ጤዛ በሆነ ጊዜያዊ ሀብት መመካት ሞኝነት ነው፡፡ ድኾች ሁሉ ልጆቻችን፣ ወንድሞቻችን፣ እህቶቻችን፣ አባቶቻችን፣ እናቶቻችን እና ወገኖቻችን ናቸው፡፡ እኛ ለክርስቶስ ህዋሱ እንደሆነው ሁሉ ድኾችም ለክርስቶስ ህዋሶቹ ናቸው፡፡ ይህን ተላልፈን ድኾችን የምንንቅ ከሆነ ሊቁ ቅዱስ ዮሐንስ እንዲህ ሲል ይገስጸናል፡፡ ወንድምህን ድኻ ነው ብለህ የምትንቅ ከሆነ አንተ ባደባባይ ጌታን ካስገረፈው ጲላጦስ ወገን ነህ፤ ይህም ብቻ ሳይሆን ጌታን ዕራቁቱን ከሰቀሉት፣ ሐሞት እና ከርቤን ቀላቅለው ካጠጡት፣ በፊቱ ላይ ምራቅ ከተፉበት አይሁዳውያኑ ከፈጸሙት ግፍ ያልተናነሰ አንተም በወንድምህ ላይ በደል ፈጽመሃል ይለናል፡፡ ድኾች ላይ ከመሳለቅ ይልቅ የእነርሱ መራቆት የእኔ መራቆት ነው ልንል በተገባ ነበር፡፡ የእነሱ መራብ የእኔ መራብ፣ መጠማታቸው የእኔ መጠማት፣ መቸገራቸው የእኔ መቸገር ካላልን የምናመልከው የትኛውን ጌታ ይሆን?
ወንጌላዊው ቅዱስ ማቴዎስ እንዲህ አለ፡፡ በመንፈስ ደሆች የሆኑ ብጹአን ናቸው፡፡/ማቴ 5፡1/ ይልቁንም በሀብት ብትሰለጥንም በድኽነት ሕይወት ውስጥ ብትኖርም ከእነዚህ ሁሉ የመንፈስ ድህነትን መምረጥ ይሻልሃል፡፡ ሀብት ኖሮህ እኔ ሀብት የለኝም፤ ብዕለ ጸጋ ሊባል የሚገባው እግዚአብሔር ነው ማለት በመንፈስ ድኻ መሆን ነው፡፡ በሰው ዘንድ የተማረ ጠቢብ ተብለን ከሆነ ከእኔ ይልቅ ብቸኛ አዋቂ እርሱ እግዚአብሔር ብቻ ነው የምንል ከሆነ ያ መንፈስ ድኽነት ነው፡፡ ሹመት ቢኖረን በሥልጣን ሁሉን ብንገዛ ከእኔ ይልቅ ሥልጣን እና ገዢነት የባሕርይው የሆነው እግዚአብሔር ብቻ ነው የምንል ከሆነ ወደ ብጽእና የሚያደርስ የመንፈስ ድኽነት ከዚህ ሌላ የለም፡፡ የመንፈስ ድኽነት ካለህ የሞላልህን እና የተትረፈረፈልህን ምድራዊ ሥጦታ ለፈጣሪ ሰጥተህ አንተ ባዶ ሆነህ መኖርን ትመርጣለህ፡፡ ይህንን ሕይወት ከቅዱሳን ወገን እነ አብርሐም፣ ኢዮብ፣ ቅዱስ ዳዊት፣ ንጉሥ ሰሎሞን ወዘተ ኖረውታል፡፡
ፍቅረ ነዋይ ያጠቃቸው ሰለ መንፈስ ድኽነት እምብዛም ላይገባቸው ይችላል፡፡ ሊቁ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ፍቅረ ነዋይ በሚመለከት የተናገረውን አድምጥ፡፡ "ፍቅረ ነዋይ ክፉ ነው፡፡ ፍቅረ ነዋይ ዓይነ ልቡናን ያሳውራል፡፡ እዝነ ልቡናን ያደነቁራል፡፡ ሰዎችን ከሰውነት አስወጥቶ እንደ አውሬ እንዲያስቡ ያደርጋቸዋል፡፡ በዚህ ፍቅረ ነዋይ ደዌ የተያዘ ሰው ሰማይ ወርቅ ታዘንብለት ዘንድ፣ ምድርም የብር ጋኖች ታፈራለት ዘንድ፣ ጳዝዮን የተባለውንም ጥሩ ዕንቁ ታመነጭለት ዘንድ፣ ተራሮችም ወደ ወርቅ ይለወጡ ዘንድ ይወዳል፡፡ ይሰጣቸው ዘንድ ይፈራልና ጦም አዳሪዎችንም ይጸየፋል፡፡ ወንድሞቹንና ዘመዶቹን፣ ወዳጆቹንና ወገኖቹንም ይክዳል፡፡ የገዛ ነብሱም ላይ እንዲጨክን ያደርጋል፡፡ ሁለንተናው የዚህ ገንዘብ ባርያ ያደርጋል፡፡ የባርነቱ አስከፊነት ደግሞ ይህ ሰው በዚህ ገንዘብ ተድላ ደስታ እንደሚገኝ ማሰቡ ነው፡፡" ወገኔ በመንፈዊ ዓይን ካየነው ፍቅረ ነዋይ በራሱ ደዌ እና የማይድን በሽታ ነው፡፡ ግያዝን ዓይኑን ያሳወረው ነቢይ ከመሆን የከለከለው ፍቅረ ነዋይ ነው፡፡ ፍቅረ ነዋይ አናንያን ከሚስቱ ጋር አስጠፍቶታል፡፡ የአይሁድ ረበናት በክርስቶስ ላይ ልቦናቸው እንዲደነድን ያደረገው ይኸው ፍቅረ ነዋይ ነው፡፡ በዓለማችን የብዙ ጦርነት መነሻ ይኸው ፍቅረ ነዋይ ነው፡፡ ስንቶች ንጹሐን በፍቅረ ነዋይ ምክንያት ሕይወታቸው ተቀጨ? ምድር በሰዎች ደም የጨቀየው ፣ ሕዝብ በለቅሶና በዋይታ ሕይወቱን የሚገፋው በዋናነት በፍቅረ ነዋይ በተጠቁ ሰዎች ምክንያት ነው፡፡ ይሁዳ በፍቅረ ነዋይ አምላኩን እስከመሸጥ ደርሷል፡፡ ፍቅረ ነዋይ አእምሮን ያሳጣል፡፡ ዓይነ ልቡናን ያጨልማል፡፡ የሃይማኖት መልክ ያጠፋል፡፡ የክርስቶስ ልብስ ከመሆን ያራቁታል፡፡ በኃጢአት ባሕር ውስጥ እንድንሰጥም ያደርገናል፡፡ በመጨረሻም ከሰይጣናት ጋር እንድንቆጠር ያደርገናል፡፡
ዛሬ በፍቅረ ነዋይ ጉጉት የወደቁ ካሉ ሰውን ያማከለ የክርስትና ሕይወት ቢኖራቸው መልካም ነው፡፡ ድኽነትን መጠየፍ ይገባል፡፡ ድኾችን መጥላት መናቅ ግን አልተፈቀደልንም፡፡ ሀብት ያላቸውም ቢሆን ካላቸው አውጥተው እንዲመጸውቱ በድኾች ላይ የተሾሙ ባለሥልጣናት ናቸው፡፡ የተሰጣቸው ከፈጣሪ መሆኑን ቢያውቁም መልካም ነው፡፡ እዚህ ጋር በሕጋዊ መንገድ ሀብት ያፈሩትን ማለቴ ነው፡፡ በሕገወጥ መንገድ በምድራዊ ሀብት የበለጸጉት ካሉ በምድርም በሰማይም የሚጠየቁ ወንጀለኞች መኾናቸው ልብ ይሏል፡፡ ቤተ ክርስቲያን ሀብት ያላቸውንም የሌላቸውንም ምዕመናን እና ምዕመናትን በእኩል ታያለች፡፡ ሀብት ስላላቸው የምታፍራቸው ምድራውያን ብዕለጸጋዎች የሏትም፡፡ በድኽነት የሚኖሩትንም ስለድህነታቸው ሳትሳቀቅ በቃለ እግዚአብሔር ትገስጻቸዋለች፡፡ ይልቁንም በምዕመናኑ ላይ ስለ ሰማያዊ ብልጽግናቸው ይበልጥ አበክራ ትሰራለች፡፡
አዎ ለአንድ ክርስቲያን በዚህ ዓለም ሲኖር ዋና የሚስፈልገው ነገር ቢኖር ለሰማያዊ ብልጽግና የሚያበቃው የመንፈስ ቅዱስ ፍሬ ነው፡፡ አንዳንዶቻችን በፍቅረ ነዋይ አስተሳሰብ ውስጥ ሆነን እከሌ በገንዘብ የከበረ ነው፤ የሚኖርበት ቤት በልዩ አሰራር የተዋበ ነው፡፡ የሚሄድበት መኪና ልዩ እና ፍጹም ዘመናዊ ነው፤ እከሌ የተባለ ባለሥልጣን ዘመድ አለው፤ ያሻውን ማዘዝ የሚችልበት ምድራዊ ሥልጣን ተችሮታል ወዘተ የምንልላቸው ሰዎች ይኖሩናል፡፡ እንዲህ አይነት ንግግርን የሚናገሩ ሰዎች ያህል በዚህ ዓለም ምስኪኖች እንደሌሉ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ያሰምሩበታል፡፡ ከላይ የተዘረዘሩት ገንዘብ፣ መኪና፣ ሥልጣን፣ የተዋበ ቤት ከእኛ ማንነት በአፍአ ያሉ ናቸው፡፡ እነዚህ ሁላ ለአንድ ሰው መንፈሳዊ ማንነቱ ገላጮቹ አይደሉም፡፡ እከሌ ትህትና፣ ቅድስና፣ ንጽሕና፣ በጎነት፣ ራስን መግዛት፣ ትዕግስት አለው ከተባለ ያ ሰማያዊ ብልጽግና ይባላል፡፡ በክርስትና የመኖራችን ምሥጢር ይኸው ሰማያዊ ብልጽግና ነው፡፡ የሚያሳዝነው ለእንዲህ ላለው ብልጽግና ሕይወታቸውን የሰጡ ጥቂቶች መሆናቸው ነው፡፡
እንግዲህ በሀቅ እና በእውነት ጠንክረው እንዲሰሩ ከምድራዊ በረከት እንዲካፈሉ ቤተ ክርስቲያን ምዕመኖቿን ትመክራለች፡፡ እርስበርስ እንዲረዳዱ አንዳቸው ለአንዳቸው በችግራቸው ጊዜ እንዲቆሙ የሰማያዊ አምላክ ትዕዛዛትን ታስተላልፋለች፡፡ በድኾች እና በድህነት መካከል ያለውን ድንበር በደንብ ትገነዘባለች፡፡ ከስስት ይልቅ ፍቅር በሰዎች መካከል እንዲናኝ ትለፋለች፡፡ በስስት ሕይወት ላለ ሰው ሲሰጥ ይጎድልበት ይሆናል፡፡ በፍቅር ስንኖር ግን እየሰጠን ይሞላልናል፡፡ በስስት ለሚኖሩ ስዝማውያን መመሪያቸው የዳርዊን the fittest only survive የሚለው መፈክር ነው፡፡ ይህ ከክርስቲያናዊ አስተምህሮ ያፈነገጠ ነው፡፡ የእኛ ጌታ ያስተማረን ወንድምህን እንደራስ አድርገህ ወደድ የሚለው ኃይለ ቃልን ነው፡፡ ድኸን መውደድ ድህነትን ማሽሞንመናችን አድርገው የሚያስቡ ካሉ መብታቸው ነው፡፡ እኛ ግን ድህነትን እንጠየፋለን፡፡ ድሆችን ግን በፍጹም አንጠላቸውም፡፡ ካለን ከፍለን እንመጸውታቸዋለን፡፡ ይህን እንድናደርግ ያዘዘን የአምላካችንን ቃል እንፈጽም ዘንድ ግዴታችን ነውና፡፡
አምላከ ቅዱሳን በረድኤቱ አይለየን፡፡
ወስብሀት ለእግዚአብሔር
ከመምህር ስንታየሁ

01/01/2024

Happy New Year 2024 for you whom follows Gorgorian Calendar.

At its core, the New Year is just a transition from one time cycle to another. And for the Orthodox, this is just a reminder of the coming Nativity of Christ, for which one needs to prepare physically, mentally and spiritually.
Any holiday presupposes a sense of joy, and this is a key moment. After all, joy is actually inside us. We just need to find it and share it with our neighbors. And if, instead of spending huge amounts of money on gluttony and drunkenness, we share this joy with those who lack it, it will bring joy not only to us. And it’s not even a matter of material wealth.
On holidays, people feel loneliness especially acutely, therefore it is worth sharing the warmth with those who lack it: with forgotten elderly relatives, perhaps with lonely elderly neighbors – here everyone knows better whom to help. But help is imperative. And then the feeling of spiritual emptiness, along with a full stomach, will be replaced by genuine spiritual joy.

18/09/2023
18/09/2023

To reveal the truth about Ethiopia's entity as the Kingdom of God and Ethiopians' identity as the People of the Holy Covenant with God; and so, to safeguard and promote all that pertains to Ethiopia and Ethiopians.

15/08/2023
29/07/2023

‹‹አቡነ ጴጥሮስ የተገደሉ ዕለት እዚያው ነበርኩ፡፡
መጀመሪያ በእጃቸው ይዘውት የነበረውን መጽሐፍ ቅዱሳቸውን ተሳለሙት።

ቀጥለውም በያዙት መስቀል አማትበው ሕዝቡን ባረኩ፡፡ የኪሳቸውንም ሰዓት አውጥተው ካዩ በኋላ መልሰው ከኪሳቸው ከተቱት፡፡

ወዲያው ወታደሮቸ በሩምታ ተኩሰው ገደሏቸው፡፡
ይህ እንደሆነ አስገዳዩ ኮሎኔል ተመልካቹን ሕዝብ አጨብጭቡ ብሎ አዘዘና ተጨበጨበ።

ማታ ከአስገዳዩ ኮሎኔል ጋር ተገናኝተን ስንጫወት ‹‹በዚህ ቄስ መገደል እኮ ሕዝቡ ተደስቷል›› አለኝ፡፡

‹‹እንዴት?›› ብለው ‹‹አላየህም ሲያጨበጭብ?›› አለኝ፡፡ ‹‹ባታውቀው ነው እንጂ የሕዝቡ ባሕል ሲናደድም ያጨበጭባል›› አልኩት፡፡

‹‹እንዴት?›› ቢለኝ እጄን አጨብጭቤ አሳየሁት፡፡"
አቡነ ጴጥሮስ ሲገደሉ በቦታው ሆነው የተከታተሉት ሙሴ ፓይላክን የተባሉ ግለሰብ በወቅቱ የነበረውን ሁኔታ ለጳውሎስ ኞኞ ከነገሩት የተወሰደ፡፡

በረከታቸው ይደርብን

ሐምሌ 22 ቀን 1928 ዓ/ም

29/07/2023

ሐምሌ 22 ሁለት ታላላቅ ኢትዮጵያውያን አባቶች በክብር ያረፉበት ታላቅ ቀን ነው። ሰማዕቱ አቡነ ጴጥሮስ እና ታላቁ ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ ዘሸዋ (ሀገረ ስብከት):: በረከታቸው ይደርብን። ጸሎታቸው እና አማላጅነታቸው የሚወዷትን ሀገራቸውን ሀገራችንን እና ሕዝቡን ይጠብቅልን። በዚሁ አጋጣሚ በ2006 ዓ.ም የጻፍኩትና አዲስ ጉዳይ ላይ የወጣውን ጽሑፍ እንድታነብቡ ልጋብዛችሁ።
+++++++++

“ምንም ብትሉ፣ ምንም ብትሉ፤ ይህ ሕዝብ አንድ ሕዝብ ነው!!!!” (ታላቁ ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ፤1933 ዓ.ም - ሐምሌ 22/ 1982 ዓ.ም)
+++++
(ኤፍሬም እሸቴ እንደጻፈው ከአዲስ ጉዳይ መጽሔት ሐምሌ 2ዐዐ6 ዓ.ም)

ሐምሌ 22/1982 ዓ.ም በመኪና አደጋ ሕይወታቸውን ያጡት በ20ኛው መቶ ክ/ዘመን የወንጌልና የታሪክ ብርሃንን በተለይ በወጣቱ ሕይወት ላይ የፈነጠቁት ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ፤ በድሮው የክፍላተ ሀገር አከፋፈል የሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ነበሩ። ከዚህ ዓለም ከተለዩ እነሆ 24 ዓመት ሞላቸው። መታወቂያቸው የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሊቀ ጳጳስነታቸው እና አባትነታቸው ቢሆንም በጽሑፋቸው፣ በትምህርታቸው እና ለኢትዮጵያና ለአፍሪካ ባላቸው ጽኑዕ ፍቅር ከእምነት ድንበር ባሻገር የሁሉንም ኢትዮጵያዊ ልቡና ሊገዛ የሚችል ስብዕና የነበራቸው አባት ነበሩ።

ብፁዕነታቸው ሚያዚያ 23/1982 ዓ.ም፣ ሻሸመኔ ቅ/ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ያስተማሩት ትምህርት ኢትዮጵያ አገራችን በዚያን ወቅት የነበረችበትን የጦርነት እሳት እና መጻዒውን የሕዝቧን ሁናቴ በቅጡ የሚያመለክት ነበር። ከተናገሯቸው ዐበይት ቃላት መካከል “ምንም ብትሉ ምንም ብትሉ፣ ይህ ሕዝብ አንድ ሕዝብ ነው። ቤተ ክርስቲያኒቱ ደህና አድርጋ መሥራታዋለችና” የሚለውን አባባላቸውን ዛሬም ድረስ በቃሌ አስታውሰዋለሁ። “ምንም ብትሉ ምንም ብትሉ” ያሉት በዓይነ ልቡናቸው ማን ምን እያለ ታይቷቸው ይሆን? እያልኩ ራሴን እጠይቃለሁ።

በተለይም የሃይማኖት አባቶች መንፈሳዊ እና አገራዊ አቋማቸው በሚዋዥቅበት በዚህ ዘመን እጅግ በጣም ባልራቀው ዘመን የነበሩትን የነአቡነ ጎርጎርዮስን ሕይወት መጥቀስ ዙሪያ ገባው ጨለማ እንዳልሆነ ለማሳየት አንድም በእውነት እና በዕውቀት ብርሃን ለመመላስ አንገቱን ቀና ለማድረግ ለሚታትር ማንም ሰውም ጥብዓት ለመስጠት ይጠቅማል።

ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ በጵጵስና ያገለገሉባቸው ዓመታት 10 ዓመታት ብቻ ናቸው። በነዚህ ጥቂት ዓመታት ያበረከቷቸው ተግባራት ግን ዛሬም ሕያው ሆነው ይታያሉ። ከአገር ቤት አገራዊውን ዕውቀት በቅጡ በማደላደል፣ ወደ ውጪውም ዓለም በመሔድም ከዘመናዊው ዓለም የዕውቀት ገበያ በመገብየት ሚዛናዊነቱን የጠበቀ ኅሊና ባለቤት የሆኑት ገና ከማለዳው ነው።

የአገሩን ዕውቀት ሲጨብጥ የውጪው፣ የውጪውን ሲይዝ የአገሩ ለሚጎድልበት አገርና ምሁር ጥሩ ማሳያ ናቸው። የአገራቸውን ሳያውቁ የውጪውን ብቻ በማነብነብ ያልተፈተነ መፍትሔ ለአገራቸው ችግር ለመስጠት በመሞከር መክነው የቀሩ ብዙ ትውልዶቻችንን ያጣነው በዚህ ምክንያት ነው። አገራችን ከአፍሪካዊ ማንነት በአንድ ጊዜ ተነቅላ ፈረንጃዊ ለመሆን ሞክራ በመካከል ደክማ የቀረችው መሠረቷን ሳታጠብቅ በውጪው ላይ ለመንጠላጠል ባደረገችው ሙከራ ነው።
ዕብራይስጥ፣ እንግሊዝኛ፣ ፈረንሳይኛ እና አረብኛ ቋንቋዎችን በቅጡ የሚያውቁት ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ በዝዋይ ሐመረ ብርሃን በመሠረቱት የቅዱስ ገብርኤል ገዳም የዕውቀት ዓምባ አቋቁመው ኢትዮጵያዊውን ታሪክ ከዓለሙ ጋር እያነጻጸሩ ለደቀመዛሙርቶቻቸው ሲያሰተምሩ ቆይተዋል። ጭው ጭው የሚል የሩቅ አገር ሬዲዮ ድምጽ ከደጃፋቸው የሚሰማው እኒህ አባት ለገዳማውያኑና ለትምህርት ከየከተማው ለሚሰባሰቡት ተማሪዎቻቸው ዓለም አቀፍ ጉዳዮችን ለተማሪዎቹ ዕውቀትና ሥነ ልቡና በሚመጥን መልኩ ሲያቀርቡ መስማት ያስደንቃል።

የሃይማኖትና የታሪክ ጥናትና ምርምራቸውን “የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ” እና “የቤተ ክርስቲያን ታሪክ ዓለም መድረክ” በሚሰኙ መጻሕፍቶቻቸው ቅልብጭ አድርገው አቅርበዋል። ለ፤መጻሕፍቱ መርጃነት የተጠቀሙባቸው ዋቤ መጻሕፍት ዝርዝር በሕዳግ በገጽ በገጹ ተጠቅሶ ይታያል። በአዋቂነት ድፍረት ሳይሆን በማስረጃ ጥንቁቅነት የቀረቡ፣ ከወጣት የሰንበት ት/ቤት ተማሪዎች እስከ ካህናት ብሎም ከየዩኒቨርሲቲው ትምህርት የዕረፍት ጊዜውን ወስዶ ከርሳቸው ሊማር ለሚመጣው ዘመናዊ ትውልድ በሚሆን መልኩ የተዘጋጁ የጥናት ሥራዎች ናቸው።

ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ የሃይማኖት አባቶች የሚያሳዩትን የቅምጥል ኑሮ እንደሚቃወሙ በአንድም በሌላም ቢገልጹም "እኛ የመነኮስነው ለፍትፍት አይደለም" የምትለው አባባላቸውን ብዙዎች ያስታውሱታል። መነኮሳት ይህንን መስመር የሚመርጡት እንደማንኛውም ተርታ አማኝ በተቀማጠለ ኑሮ ለመመላለስ ሳይሆን ራስን በሚጎስም መንፈሳዊ እና ማኅበራዊ አገልግሎት ለመጠመድ መሆኑን አበክረው ይናገራሉ። ለኑሮ የማይመቸውንና ከዝዋይ ሐይቅ በተጎራበተው የቅዱስ ገብርኤል ገዳማቸው ጠንካራ ኑሮን በመቋቋም ገዳሙን ለወላጅ አልባ ሕጻናት ማሳደጊያነት እና ለትምህርት ማዕከልነት የሚመች ሥፍራ ያደረጉት በዚሁ መርሐቸው ነበር። በተለይም በዚህ ዘመን፣ በሃይማኖት አባቶች ላይ የሚታየው የቅምጥል ኑሮ በብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ሕይወት ሲመዘን እጅጉን ጎዶሎ ይሆናል።

ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ አባትና እናት የሌላቸውን ሕጻናት ሰብስቦ ማሳደግ የቤተ ክርስቲያን አንዱ ዓላማ መሆኑን በተግባር አሳይተዋል። እርሳቸው ባረፉበት ወቅት ከ200 በላይ ሕጻናት የሚያድጉበት የነበረው ያ ገዳም የነገ ተስፋ የሆኑ ልጆችን በመንከባከቡ በኩል የሃይማኖት መሪዎች ያለባቸውን ታላቅ ኃላፊነት የሚያመለክት ነው። የሌላውን እንኳን ብንተው የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በጥቂቱ ከሚታዩ ሙከራዎች ውጪ ይህ ነው የሚባል ሕጻናትን የመታደግ እንቅስቃሴ ስታደርግ አይታይም። በሀብት ደረጃቸው የናጠጡ የከተማ አብያተ ክርስቲያናት ለዚህ ዓይነቱ ጉዳይ ጊዜ ያላቸውም አይመስሉም። የድሃ መብዛት የፈጣሪ ጸጋ ይመስል ድህነትንና ድሃውን በእነርሱ ኑሮ ማድመቂያነት የወሰዱት ይመስላል።

ሌላውና የዚህ ዘመን የአገራችንና የቤተ ክርስቲያን ሁነኛ ፈተና የሆነውን ዘረኝነትን በተመለከተ የብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ሕይወት ብዙ አስተማሪነት አለው። የሚያውቋቸው ሰዎች በሙሉ በአንድነት የሚመሰክሩላቸው በወገን፣ በወንዝ፣ በመንደርተኝነትን የማይጠረጠሩ፣ ዘረኝነትን በፍፁም የሚጠየፉ አባት መሆናቸውን ነው። ቤተ ክርስቲያናችንን ጨምድዶ ለያዛት የዘመነ መሳፍንት ዓይነት መንደርተኝነት፣ ጠባብነት እና ጎሰኝነት እንደ ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ያለ ሰው ያስፈልጋል።

በምድራውያን ባለ ሥልጣኖች ፊት በሃይማኖታዊ ግርማ እንጂ በማጎብደድ መቆም ያልለመደባቸው ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ራሳቸውን አክብረው አባትነትን፣ ሃይማኖተኝነትን፣ ቤተ ክርስቲያንን የሚያስከብሩ መሆናቸውን ብዙዎች ይስማሙበታል። የታሪክ ተመራማሪ እንደመሆናቸው ቤተ ክርስቲያን በቤተ መንግሥት መዳፍ ሥር ስትወድቅ ያለውን ጣጣ በመጻሕፍቶቻቸው መጥቀስ ብቻ ሳይሆን እርሳቸውም ያ ነገር እንዳይደገም በሕይወታቸው አብነት ሆነዋል።
በቤተ መንግሥት መዋጥን ብቻ ሳይሆን በዓለማቀፋዊነት (ሉላዊነት) መዋጥ እንዳይመጣ ማንነትን ጠብቆ በዓለም መድረክ መገኘትንም አበክረው ያሳስቡ ነበር። ቤተ ክርስቲያን በምትካፈልባቸው ዓለም አቀፍ መድረኮች በውክልና ከመገኘታቸውም በላይ የዓለም አቃዊነት መርሖ ማንነትን ካለማጣት ጋር እያነጻጸሩ አቅርበዋል።

ጠንካራ ኢትዮጵያዊነትን ብቻ ሳይሆን አፍሪካዊነትንም ከታሪክ አንጻር የሚያብራሩት እነዚህ አባት የዕውቀት ብርሃን ቀድሞ የተለኮሰባት አፍሪካ እንዴት ባለ መንገድ ወደ ጨለማው እንደገባችና የቅኝ ግዛት ቀንበር እንደተሸከመች ያትታሉ። ከ1983ቱ የመንግሥት ለውጥ አንድ ዓመት ቀድሞ “ምንም ብትሉ ምንም ብትሉ ይህ ሕዝብ አንድ ሕዝብ ነው” በሚለው ንግግራቸው አንድነት እና ኢትዮጵያዊነት የገጠመውንና የሚገጥመውን ፈተና በትንቢታዊነት አስረድተዋል። በአንድነት ውስጥ ብዝሕነት በጸጋነት መኖሩን የሚያስተምሩ አባት ነበሩ።

ከምንም በላይ ለተተኪው ትውልድ ትልቅ አክብሮት እና ጥንቃቄ በማሳየታቸው ይታወቃሉ። ወጣቶች “የቤተ ክርስቲያን የስስት ልጆች” ከማለታቸውም በላይ በዕውቀት እንዲበለጽጉ በብዙ ደክመዋል። ገና በ50 ዓመታቸው በመኪና አደጋ ከዚህ ዓለም ቢለዩም ትምህርታቸው፣ ዓላማቸው፣ ጽናታቸው፣ ኢትዮጵያዊ አርበኝነታቸው፣ ለአፍሪካዊነት ያላቸው ከበሬታ፣ ለወላጅ አልባ ሕጻናት ያላቸው ደራሽነት እና ለወጣቶች ያላቸው አክብሮት ሁሌም የማይረሱ ያደርጋቸዋል። በረከትዎ ይደርብን።

ይቆየን - ያቆየን

29/07/2023

☞ ሐምሌ 22 ለአባታችን ለ አቡነ ጴጥሮስ ሰማዕትነት ለተቀበሉበት 85 ተኛ ዓመት በሰላም አደረሳችሁ፡፡
☞- - - ሰው እንዴት ብቻውን ይቆማል? ከኅሊና በላይ በሆነ ፈታኝ ሰዓት ሰው
ብቻውን የሚቆመው እንዴት ነው?
☞አቡነ ጴጥሮስን የምናደንቃቸው በሌላ በምንም አይደለም፡፡ በነገራችን ላይ
በእርሳቸው ዘመን በዚህች ሀገር አምስት ጳጳሳት ነበሩ፡፡
☞በጣልያን ወራራ የካቲት 12 ሲከበረረ ግማሾቹ ጳጳሳት ከጣልያኖቹ ጋር
ተሰልፈው ነበር፡፡
☞አቡነ ጴጥሮስን ተውት ይቅርብዎ ይጠቀማሉ ይተውት ብለዎቸው ነበር፡፡
ታዲያ አቡነ ጴጥሮስ በዚያች ጊዜ ብቻቸውን ቆመው እንዲት እንቢ አሉ?
☞የገዛ ወዳጆቻቸው፤ እዮቻቸው፤ በእምነትም በሥልጣንም እኩዮቻቸው የነበሩት
ግን አቡነ ጴጥሮስን ይተው ለጣልያን እንግባ ሲሏቸው፤ አልቀበልም ብለው
እንዴት ብቻቸውን ቆሙ?
☞በወቅቱ እጅግ በጣም ብዙ አሳማኝ ነገሮች እንደሚያቀርብላቸው
በእርግጠኛነት መናገር ይቻላል፡፡
☞እኛ ያልሰማናቸው ብዙ ሊያሳምኑ የሚችሉ ነገሮችን ሊቀርቡላቸው፤መጽሐፍ
ጠቅሰው፤ታሪክ ጠቅሰው ልባቸውን ለሁለት ሊከፍል የሚችል ሐሳብ
ሊነግሯቸው ይችላሉ፡፡
☞ለምን ቢባል በወቅቱ አቡነ ጴጥሮስ በአንዲት እስር ቤት ብቻቸው ናቸውና፡፡
እሳቸው ማንም አልነበራቸውም፡፡ ብዙ ሰዎች ግን ወደ እርሳቸው መጥተው
መክረዋቸዋል፡፡ ግዴለም ጴጥሮስ በርታ ምንም የሚመጣ ክፋ ነገር የለም
የሚላቸው የለም፡፡ ከራሳቸው ከገዛ ነፍሳቸው በስተቀር ማንም በአጠገባቸው
ከእሳቸው ጋር የሚቆም አልነበረም፡፡
☞ያን ጊዜ አቡነ ጴጥሮስ በሰንሰለት ታስረው፤ ተይዘው በዚያ በዙሪያቸው
በተሰበሰበው ሰው ሁሉ መሐል ሲቆሙ፤ያቺ ብቻን የመቆም ዐቅም እንዴት
አገኙ?
☞ዛሬም በሀገራችን ብዙ ሰዎች እንዲህ ይባላሉ፡፡ ብዙ አርስቲቶች ስፖንሰር
አታገኝም፤ ደጋፊ አታገኝም፤ ፕሮጀክትህ ተቀባይነት አይኖረውም፤ መገናኛ ብዙኃን
ሁሉ ይኼንን ካልክ አያስተላልፋልህም፤ አያስተዋውቁልህም፤ ሲባሉ ገና
በመጀመሪያው አንገታቸው የሚደፋ አሉ፡፡ ብቻን መቆም ከባድ ዎጋ
ያስፈልገዋል፡፡
☞እኔ የምሰማው ድምፅ ማጉሉያ ስለያዝኩኝ አይደለም፡፡ የምሰማው
የምደመጠው፤ የምታወቀው መገናኛ ብዙኃን ስለዘገቡልኝ ስለአሰተላለፋልኝ
አይደለም፡፡ የምሰማው ብቻዬን ሰሸለቆምኩ ነው፤ ብሎ ማመንና በጽናት መቆም
ያስፈልጋል፡፡
☞አቡነ ጴጥሮስ በዚያ የፈተና ወቅት ምን እንደተናገሩ አልሰማናቸው ነገር ግን
ትውልድ ተሻግሮ ይኸው ዛሬ እንሰማቸዋለን፤ ወደ ፊት የሚቀጥለው ትውልድም
ሲሰማቸው ይኖራል፡፡
☞ዛሬ እዚያ አቡነ ጴጥሮስ አደባባይ የቆመው ሐውልት ሳይናገር ይሰማል፡፡
ዛሬም በየመገናኛ ብዙኃኑ፤በየመድረኩ በሰፊው ዕድሉን አግኝተው ከሚናገሩ
ሰዎች "እንዲህ ያለበት ሁኔታ ነው"ከሚሉ ሰዎች በበለጠና በሰፋ ሁኔታ አቢነ
ጴጥሮስ ይሰማሉ፡፡ ዛሬም ትውልድ ይሰማቸዋል፡፡
☞በዚህ ዘመንም ያለን የነጻ ዜጎች መፈክር ቢሆን ደስ የሚለኝ፤ ልክ እንደ አቡነ
ጴጥሮስ "ብቻዬን እቆማለሁ! ብሔሬ ባይቀበለውም፤ ፖርቲዬ ባይቀበለው፤
ወላጆቼ ባይቀበሉት፤ ክልሌ ባይቀበለውም፤ ዘመኑ ባይቀበለኝ፤ ፌስ ቡክ ስሜን
ቢያጠፋው፤ መገናኛ ብዙኃን እምቢ ቢለኝ፤ እኔ ግን ለእውነት ስል ብቻዬን
እቆማለሁ፡፡
☞(በዲያቆን ዳንኤል ክብረት"ብቻዬን እቆማለሁ ከሚለው መጽሐፍ የተወሰደ)
☞ሰማዕቱ አቡነ ጴጥሮስ የሀይማኖት ጽናትን ያድሉን፡፡ ስለ ሀይማኖታችን
ብቻችን ቆመን ለመመስከር ማስተዋሉን ያድሉን፡፡
☞ሲራክ ተክለጻዲቅ የተዋህዶ ልጅ

15/07/2023

ዜና ዕረፍት

መምህር የኔታ ዕዝራ ገ/መድኅን ከዚህ ዓለም ድካም ዐርፈዋል ። ቀብራቸውም ዛሬ 07/11/15 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 እስከ 9፡00 ረጅም ዓመት ባገለገሉበት የመናገሻ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን (አራዳ ጊዮርጊስ) ይፈጸማል ።

ሰ/ት ት/ቤታችን በአባታችን ኅልፈት የተሰማውን ሐዘን ይገልጻል ፤ ለቤተሰባቸውም መጽናናትን ይመኛል።

14/07/2023

አሜን አሜን አሜን

Address

Chilot Margeja
Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ማኅበረ ማርያም ዘቀጨኔ ደብረ ሠላም መድኃኔዓለም ወደብረ ትጉኃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share