ቁስቋምማርያም የዱንኳኗ ማርያም

ቁስቋምማርያም የዱንኳኗ ማርያም ቁስቋምማርያም የዱንኳኗ ማርያም

03/08/2025
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤት ኢየሱስ ማን ነው?+++++++++++++++++++++++ኢየሱስ ክርስቶስ፦ከሦስቱ አካላት አንዱ የሆነ፤ (ማቴ ፳፰፥፲፱)ከአብ ጋር ዕሪና ያለው፤   (ዮሐ ፲፥...
05/07/2025

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤት ኢየሱስ ማን ነው?

+++++++++++++++++++++++
ኢየሱስ ክርስቶስ፦

ከሦስቱ አካላት አንዱ የሆነ፤ (ማቴ ፳፰፥፲፱)

ከአብ ጋር ዕሪና ያለው፤ (ዮሐ ፲፥፵)

ዓለም ሳይፈጠር የነበረ፤ (ዮሐ ፩፥፩)

ዓለምን የፈጠረ ፈጣሪ፤ (ዕብ ፲፩፥፪)

በቅድምና ከአብ የተወለደ፤ (መዝ ፪፥፯)

ሥጋ እንደሚለብስ በራሱ የመሰከረ፤ (ዘፍ ፫፥፳፪)

ወደ ገነት ገብቶ አዳምን የፈለገ፤ (ዘፍ ፫፥፱)

በነቢያት አስቀድሞ የታወቀ፤ (ኢሳ ፵፪፥፩-፭)

አብ ልጄ ብሎ የጠራው፤ (ማቴ ፲፯፥፭)

ምሳሌ የተመሰለት፤ (፩ኛ ቆሮ ፲፥፬)

ሱባዔ የተቆጠረለት፤ (ገላ ፬፥፬)

በብሥራተ መልአክ የተጸነሰ፤ (ሉቃ ፩፥፴፩)

ሥጋን የለበሰ (ማቴ ፩፥ ፳፫)

ቁራኝነትን ያጠፋ፤ (፩ኛ ቆሮ ፲፭፥፳፬)

በማሕጸን ጽንስን ያዘለለ፤ (ሉቃ ፩፥፵፩)

መላእክት የዘመሩለት፤ (ራእ ፬፥፰)

ተጸንሶ ሳል በሰማይም ያለ፤ (ሉቃ ፪፥፲፬)

በሕቱም ድንግልና የተወለደ ፤ (ማቴ ፩፥፳፫)

ያለ አባት ከሴት ብቻ የተወለደ፤ (ገላ፥ ፬፥፬)

አለቅነት በጫንቃው ላይ ያለ፤ (ኢሳ ፱፥፮)

ከሁለት አካል አንድ አካል የሆነ፤ (ዮሐ ፩፥፲፬)

ከሁለት ባሕርይ አንድ ባሕርይ የሆነ፤ (ዮሐ ፪፥፲፱)

ንጉሥ ሆኖ የተወለደ፤ (ማቴ ፪፥፩-፪)

ለቤዛነት የተሰደደ፤ (ማቴ ፪፥፲፬-፲፭)

መምህር ሆኖ ሳለ ለመማር የሚሻ፤ (ሉቃ ፪፥፵፮)

በዮሐንስ እጅ የተጠመቀ፤ (ዮሐ ፫፥፲፭)

ላመኑት የዘላለም ሕይወትን የሚያድል፤ (፫፥፴፮)

የአብ ኃይሉና ቀኙ የሆነ፤ (፪ኛ ጤሞ ፫፥፭)

ጥምቀትን መዳኛ ያደረገ (ማር ፲፮፥፲፮)

ወንጌልን የሠራ፤ (ዮሐ ፩፥፲፯)

አዲስ ቃል ኪዳን የገባ፤ (ማቴ ፳፮፥፳፮)

መጾምን ያስተማረ፤ (ማቴ ፬፥፪)

ፍቅርን የሰበከ፤ (ዮሐ ፲፭፥፲፫)

ኦሪትን የፈጸመ፤ (ማቴ ፭፥፳፩-፵፰)

ከአብርሃም በፊት የነበረ፤ (ዮሐ ፰፥፶፰)

አልፋና ዖሜጋ የሆነ፤ (ራእ፩፥፲፯)

ምሕረቱ እጅግ የበዛ፤ (ዮሐ ፰፥፲፩)

ሐዋርያትን የጠራ፤ (ማቴ ፭፥፲፱-፳፩)

ሥጋውንና ደሙን የሰጠ፤ (ማቴ ፳፮፥፳፮)

ዓርአያነትን የሰጠ፤ (፲፫፥፲፭)

አዳኝ ሆኖ የተገለጠ፤ (ሉቃ ፱፥፶፮)

ለአዳም ቤዛ የሆነ፤ (ኤፌ ፩፥፯)

ይቅርታን ያስተማረ፤ (ሉቃ ፲፯፥፬)

ገነትን በደሙ የከፈተ፤ (ማቴ ፳፭፥፴፭)

፮ቱ ትዕዛዛተ ወንጌልን የነገረ፤ (ማቴ ፳፭፥

ሞትን ያሸነፈ፤ (፩ኛ ቆሮ ፲፭፥፶፬)

በመላእክት የተመሰገነ፤ (ማቴ ፬፥፲፩)

በሐዋርያት የተሰበከ፤ (ሐዋ ፪፥ ፳፪)

ፍርድ ሁሉ ለእርሱ የሆነ፤ (ዮሐ ፭፥፳፯)

ሊቀ ካህን ሆኖ የተገለጠ፤ ( ዕብ፯፥፳፮)

አምላክነት ገንዘቡ የሆነ፤ (ሮሜ ፱፥፭)

በሰውነቱ የሚራብ፤ (ማር ፲፩፥፲፪)

በአምላክነቱ የሚያጠግብ፤ (ሉቃ ፱፥፲፯)

ሊያገለግል የመጣ፤ (ማቴ ፳፥፳፰)

ሕይወትና ትንሣኤ ተብሎ የሚጠራ፤ (ዮሐ ፲፩፥፳፭)

እውነተኛ የበጎች ጠባቂ፤ ( ዮሐ ፲፥፲፩)

የቤተ ክርሰቲያናችን ራስ፤ (ኤፌ ፬፥፲፭)

ብርሃነ መለኮቱን የገለጠ፤ (፪ኛ ጴጥ ፩፥፲፮-፲፱)

ሙሴና ኤልያስን ያነጋገረ፤ (ማር ፱፥፬)

ለሙሽራይቱ ሙሽራ የሆነ፤ (ዮሐ ፫፥፳፱)

ዳግም ለመምጣት ቀጠሮ የያዘ፤ (ራእ ፳፪፥፲፪)

ትንቢተ ነቢያትን የፈጸመ፤ (ማቴ ፩፥፳፫)

የነቢያት አለቃቸው፤ (ሉቃ ፯፥፲፮)

የታመነ ምስክር፤ (ማቴ ፲፤፴፪)

ከአባቱ የሰማውን የሚናገር፤ (ዮሐ ፲፭፥፲፭)

አንድ ጊዜ ወደ ቅድስተ ቅዱሳኑ የገባ፤ (ዕብ ፱፥፲፪)

ገዳማዊ ሕይወትን የጀመረ፤ (ማቴ ፬፥፩)

ተባሕትዎን የወጠነ፤ (ማቴ ፰፥፳)

ጋብቻን ተገኝቶ የባረከ (ዮሐ ፪፥፪)

እናቱን እነኋት ብሎ የሰጠ፤ (ዮሐ ፲፱፥፳፯)

የመስቀል ሞትን የሞተ፤ (ፊል ፪፥፰)

በብዙ ወገን የተገፋ፤ (ዮሐ ፭፥፲፮)

ደዌአችንን የተሸከመ፤ (ኢሳ ፶፫፥፬)

ነፍሱን ስለ እኛ የተወ፤ (ዮሐ፲፱፥፴)

ለነፍሳት ግዕዛንን የሰበከ፤ (፩ኛ ጴጥ ፫፤፲፱)

ለደካሞች ማረፊያ የሆነ፤ (ማቴ ፲፩፥፳፰)

በግርማ መለኮት የሚመጣ፤ (መዝ ፶፥፫)

ሙታንን የሚያስነሣ፤ (ዮሐ ፮፥፵፬)

የጌቶች ጌታ የሆነ፤ (ሮሜ ፲፥፲፪)

ከእውነቸኛ ብርሃን የተገኘ ብርሃን፤ (ዮሐ ፰፥፲፪)

ፈራጅነት ገንዘቡ የሆነ አምላክ ነው! (ራእ፳፪፥፲፪)

እንዲህ እናምናለን እንዲህም እንታመናለን!

የት ነው ???????
10/12/2024

የት ነው ???????

04/10/2024

እንኳን ለታላቋ የጽጌ ጾም በሰላም አደረሰን!

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ቁስቋምማርያም የዱንኳኗ ማርያም posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share