Samuel demise

Samuel demise Daily thoughts and random moments 🤠

Ethiopia 🇪🇹 🇪🇹 🇪🇹

🌍ዓለምና ጊዜ🕒አንዱ ሥፍራ ሲለቅ አንዱ እየተተካ፤ሁሉም ርስቴ ነች እያለ ሲመካ፤ሞኝነት አድሮብን ሳናስበው እኛ፤ዓለም ሰፈር ሆና ህዝቡ መንገደኛ፤ትውልድ ፈሳሽ ውሃ መሬቷም ጅረት፤መሆኑን ዘንግ...
26/05/2026

🌍ዓለምና ጊዜ🕒

አንዱ ሥፍራ ሲለቅ አንዱ እየተተካ፤
ሁሉም ርስቴ ነች እያለ ሲመካ፤
ሞኝነት አድሮብን ሳናስበው እኛ፤
ዓለም ሰፈር ሆና ህዝቡ መንገደኛ፤
ትውልድ ፈሳሽ ውሃ መሬቷም ጅረት፤
መሆኑን ዘንግቶ ይህ ሁሉ ፍጥረት፤
ስትመለከቱት በሰልፍ ተጉዞ . . .
ሁሉም በየተራው ያልፋል ተያይዞ።

✍️✍️ ከበደ ማካኤል

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከ100 በላይ አውሮፕላኖችን ሊረከብነ ውየኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው አየር መንገዱ ከ100 በላይ አዳዲስ አውሮፕላኖችን ለመግ...
16/05/2026

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከ100 በላይ አውሮፕላኖችን ሊረከብነ ው

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው አየር መንገዱ ከ100 በላይ አዳዲስ አውሮፕላኖችን ለመግዛት ትዕዛዝ ማስተላለፉንና እነዚህንም እስከ ፈረንጆቹ 2032 ዓ.ም. ድረስ ሙሉ በሙሉ ለመረከብ እየተጠባበቀ መሆኑን በይፋ አስታውቀዋል።

ምንጭ ዘ ሪፖርተር

10/05/2026
10/05/2026

Celebrating my 11th year on Facebook. Thank you for your continuing support. I could never have made it without you. 🙏🤗🎉

ብሩኖ ፈርናንዴዝ በእንግሊዝ እግር ኳስ ጸሐፊዎች ማህበር የአመቱ ምርጥ ተጫዋች ተብሎ ተመርጧል የአርሰናሉ ተጨዋች ዴክላን ራይስ ሁለተኛ ሆኖ አጠናቋል በሴቶች የማንችስተር ሲቲዋ ካዲጃ ሾው የ...
08/05/2026

ብሩኖ ፈርናንዴዝ በእንግሊዝ እግር ኳስ ጸሐፊዎች ማህበር የአመቱ ምርጥ ተጫዋች ተብሎ ተመርጧል

የአርሰናሉ ተጨዋች ዴክላን ራይስ ሁለተኛ ሆኖ አጠናቋል

በሴቶች የማንችስተር ሲቲዋ ካዲጃ ሾው የአመቱ ምርጥ ሴት ተጨዋች ተብላ ተመርጣለች

የአርሰናሏ ተጨዋች አሌሲያ ሩሶ ሁለተኛ ሆና አጠናቃለች

 #የዘመነ መሳፍንት የመጨረሻው ጦርነት 166ኛው ዓመት መታሰቢያ ደጃዝማች ካሣ ኃይሉ፣ «ዳግማዊ ቴዎድሮስ ንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያ» ተብለው ከመንገሣቸው በፊት የሰሜንና የትግራይ ገዢ ከነበሩ...
06/05/2026

#የዘመነ መሳፍንት የመጨረሻው ጦርነት 166ኛው ዓመት መታሰቢያ ደጃዝማች ካሣ ኃይሉ፣ «ዳግማዊ ቴዎድሮስ ንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያ» ተብለው ከመንገሣቸው በፊት የሰሜንና የትግራይ ገዢ ከነበሩት ከደጃዝማች ውቤ ኃይለማርያም (የዳግማዊ ቴዎድሮስ ባለቤት የእቴጌ ጥሩወርቅ ውቤ አባት) ጋር የመጨረሻውን የዘመነ መሳፍንት ጦርነት ያደረጉት የካቲት 3 ቀን 1847 ዓ.ም ነበር።
ደጃዝማች ካሣ በኅዳር ወር 1845 ዓ.ም ደጃዝማች ጎሹ ዘውዴን ጉርአምባ ላይ፣ በሰኔ ወር 1845 ዓ.ም ደግሞ ራስ አሊ አሉላን (ዳግማዊ አሊን) አይሻል ላይ ካሸነፉ በኋላ ከወቅቱ የግዛት ኃያላን መሳፍንት መካከል ለደጃዝማች ካሣ ያልገበሩት የሰሜንና የትግራይ ገዢ የነበሩት ደጃዝማች ውቤ ኃይለማርያም ብቻ ነበሩ። ደጃዝማች ካሣም ወደ ደጃዝማች ውቤ ኃይለማርያም ለመዘመት አቀዱ። ከዘመቻቸው በፊትም ደጃዝማች ውቤ በሰላም እንዲገቡላቸውና እምቢ የሚሉ ከሆነ እምቢታቸው እንደማይበጃቸው የማስጠንቀቂያ መልዕክት ላኩላቸው።

#ደጃዝማች ውቤ ኃይለማርያም የደጃዝማች ካሣ መልዕክት ሲደርሳቸው ... «ምንም የጠገበ ነው?! ሳልዋጋ ይገባልኛል ብሎ ነው?!» በማለት ከተናገሩ በኋላ «አልገባም!» የሚል ምላሽ ሰጡ። ጳጳሱ አቡነ ሰላማም ለደጃዝማች ውቤ «ለካሳ ብትገብሩ ይሻላል» ቢሏቸውም የሰሜኑ ሰው ሃሳባቸውን ሳይቀይሩ ቀሩ። ደጃዝማች ካሣም ጣታቸውን አነካክተው «... ከእኔ የተለየህ ለራስህ አውቅ!በምን ጠፋሁ እንዳትል! አይዞህ ወታደር፤ እኔ ደስ ከሚልህ አገር አገባሀለሁ» የሚል አዋጅ አስነገሩ። ሕዝቡም ከራስ አሊ መሸነፍ በኋላ «ደጃች ካሣ መቼ ይነግሱ ይሆን? ስመ መንግስታቸዉስ ማን ይበል ይሆን?» እያለ ይጠይቅ ስለነበር «እኔ በመራሁህ ተጓዝ፤ ስሜን በሰሜን እነግርሃለሁ» ብለው ከአምባጫራ አልፈው በወገራ በኩል አድርገው ስሜን ገቡና ደረሰጌ ላይ «አንጨት ካብ» በተባለ ቦታ ሰፈሩ።
የደጃዝማች ዉቤ ጦርም በአካባቢዉ መከሁ በተባለች ቦታ ሰፍሮ ነበር::

የካቲት 3 ቀን 1847 ዓ.ም «ቧሂት» በተባለ ቦታ ላይ ተጀመረ። ጦርነቱ ተፋፋመና ደጃዝማች እሸቴ የተባሉት የደጃዝማች ውቤ ልጅ ተመተው ሲወድቁ የደጃዝማች ውቤ ጦር መሸሽ ጀመረ። ብላታ ኮከቤ የተባለው የደጃዝማች ውቤ የጦር አዛዥም አለቃውን ከድቶ ከነጭፍራው ወደ ደጃዝማች ካሣ ዞረ። ደጃዝማች ውቤም ቆስለው ተማረኩና ድሉ የደጃዝማች ካሣ ኃይሉ ሆነ።

ደጃዝማች ካሣም የተሸነፈውን ደጃዝማች ውቤን «እኔ እሳቱ የመይሳዉ ልጅ! ... አንተ ቆፍጣና ቁርጥማታም ሽማግሌ አክብሬህ 'ገብር' ብዬ ብልክብህ ምንው ሰደብከኝ? አሁንም ነፍጤንና ገንዘቤን አግባ!» አሏቸው። ደጃዝማች ውቤም «እግዚአብሔር ያሳየዎ የነበረኝ ነፍሴና ገንዘብ ሁሉ አንድም ሳያመልጥ ከእጅዎ ገባ፤ ሌላ ምን አለኝ?» ብለው መለሱላቸው።
ደጃዝማች ውቤ ቤቴል (አምባ ጠዘን) በሚባለው ቦታ ያከማቹት እጅግ በጣም ብዙ ወርቅ፣ ብር (40ሺ ማርቲሬዛ)፣ ጥይት፣ ጠመንጃ (ሰባት ሺ)፣ አህያ፣ ፈረስ፣ ግመል፣ ላም፣ በግ፣ ፍየል፣ በወርቅ የተለበጡ አልባሳት፣ የከበሩ ጌጣጌጦች፣ ውድ ምንጣፎችና ሌሎች ዕቃዎች ተገኙ። በዚህ ጊዜም ደጃዝማች ካሣ የታሰሩትን ደጃዝማች ውቤን አስጠግተው «ይኸን ሁሉ ሀብት የሰበሰብከው ምን ሊሰራህ ነው?» ሲሉ ጠየቋቸው። ደጃዝማች ውቤም «ለከፉ ቀኔ እንዲሆነኝ ብዬ ነው» አሏቸው።

ደጃዝማች ካሣም «ሰው ያለውን ሀብት ከተጠቀመ ምን ክፉ ቀን አለ?» በማለት መለሱና ወደ እስር ቤቱ እንዲመለሱ አዘዙ።
በመጨረሻም ... «የኮሶ ሻጭ ልጅ» ተብለው የተናቁት ... «... ደግሞ ለቆለኛ አንድ ወርች ሰጋ ምን አነሰው?» ተብለው በአማቾቻቸው የተቀለዱባቸው ... ካሣ ኃይሉ ... ደጃዝማች ውቤ ኃይለማርያም ሊነግሱበት አስጊጠው በሰሩት ደረሰጌ ማርያም ቤተ-ክርስቲያን የካቲት 5 ቀን 1847 ዓ.ም በጳጳሱ በአቡነ ሰላማ እጅ ተቀብተው፤ «ዳግማዊ ቴዎድሮስ ንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያ» ተብለው የኢትዮጵያ ንጉሥ ሆኑ!

 #ጽዮናዊነትየተባበሩት መንግሥታት ድርጅትም ፍልስጤምን ለሁለት ተከፍላ የአይሁዶች እና የአረቦች የተናጠል አገራት እንዲመሠረቱ ሃሳብ አቀረበ። በአውሮፓውያኑ 1948 እስራኤል በመካከለኛው ምስ...
05/05/2026

#ጽዮናዊነት

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅትም ፍልስጤምን ለሁለት ተከፍላ የአይሁዶች እና የአረቦች የተናጠል አገራት እንዲመሠረቱ ሃሳብ አቀረበ። በአውሮፓውያኑ 1948 እስራኤል በመካከለኛው ምስራቅ ውስጥ በአገርነት መመሥረቷ ታወጀ።
በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ፍልስጤማውያን ከቀያቸው እና ከቤታቸው ተፈናቅለዋል።

ከዚያም በኋላ እ.ኤ.አ በ1967 የተደረገውን የስድስቱን ቀን ጦርነት ተከትሎ የፍልስጤም ግዛቶች የሚባሉትን ዌስት ባንክ እና ምስራቅ እየሩሳሌምን እስራኤል በኃይል ተቆጣጥራ ትገኛለች። ባለፉት አምሳ አራት ዓመታትም በእነዚህ ግዛቶች የአይሁዶች የሰፈራ መንደሮችን አቋቁማለች። 700 ሺህ የሚቆጠሩ አይሁዳውያን በእነዚህ ሰፈራዎች ይኖራሉ።

የተባበሩት መንግሥታትን ጨምሮ የተለያዩ ተቋማት እስራኤል በቁጥጥሯ ስር ባሉ ግዛቶች የሰፈራ መንደሮችን ማቋቋሟ ዓለም አቀፍ ሕግን የሚጻረር እና ሕገወጥ ነው ሲሉ ይጠራሉ። የእስራኤል መንግሥት ምስረታ በፍልስጤም የሚኖሩ አረቦችን መብት የገፈፈ መሆኑን በመጥቀስ ፍልስጤማውያን እንዲሁም ሌሎች አረቦች ይቃወሙታል::

የጽዮናዊነትን እንቅስቃሴ የሚያንቀሳቅሱ አካላት እስራኤል እንደ አይሁድ ግዛትነቷ ጥበቃ ሊደረግላት እንዲሁም ልትስፋፋ ይገባል ብለው ያምናሉ። አንዳንድ ጽዮናውያን እስራኤል ካላት ግዛት በተጨማሪ ሌሎች ግዛቶችንም የመቆጣጠር መብት አላት ብለው የሚከራከሩ ሲሆን፣ ሌሎች በዚህ ሃሳብ አይስማሙም። አብዛኛው አይሁዳውያን ጽዮናውያን ቢሆኑም፣ ጥቂቶች በፖለቲካዊ እና በሃይማኖታዊ ምክንያቶች ጽዮን ሃሳብን ይቃወማሉ። አይሁዳዊ ያልሆኑ ሰዎች ጽዮናዊነትንም መደገፍ ይችላሉ።

ጽዮናዊነት በአውሮፓ በ19ኛው ክፍለ ዘመን የተጀመረ የፖለቲካ እንቅስቃሴ ነው። ፍልስጤም በምትባለውም ምድር የአይሁድ አገርን መመሥረት ዋነኛ ግቡ ነው። ይህ እንቅስቃሴ የአይሁዳውያን የጥንት ርስት ናት የሚሏትን የአይሁዳውያን አገር የሆነች እስራኤል ፍልስጤም ተብሎ በሚታወቀው መሬት የመመሥረት ፍላጎት የነበረ ነው።

ኢትዮጵያ ከ1928 ዓ.ም. ከሚያዝያ 27 ቀን (አዲስ አበባ በፋሽስት ኢጣሊያ የተያዘችበት) እስከ 1933 ሚያዝያ 27 ቀን (አዲስ አበባ በድል የተያዘችበት) ድረስ የጠላት ኰቴ በመስኮቿ ላይ...
05/05/2026

ኢትዮጵያ ከ1928 ዓ.ም. ከሚያዝያ 27 ቀን (አዲስ አበባ በፋሽስት ኢጣሊያ የተያዘችበት) እስከ 1933 ሚያዝያ 27 ቀን (አዲስ አበባ በድል የተያዘችበት) ድረስ የጠላት ኰቴ በመስኮቿ ላይ ቢዛወርም ገዢነቱን አላወቀችለትም፡፡ ጫካው ሁሉ የዳርቻ ወሰኗ ስለሆነላትና ሜዳውም ቢሆን እሾሀማ ብቻ ሆኖ ስለአስቸገረው ምን ያህል ጭንቀት እንዳደረሰበት አምስት ዓመት ያልሞላው የሥቃይ ዘመን ምስክር ነው

ሚያዝያ 27 ቀን 1928ፋሺስት ኢጣልያ አዲስ አበባን ሚያዝያ 27 ቀን 1928 ዓ.ም በዛሬዋ እለት አዲስ አበባን ያዘ። በአርበኞችና በህዝቡ ታላቅ ተጋድሎ ሚያዝያ 27 ቀን 1933 ዓ.ም ደግ...
04/05/2026

ሚያዝያ 27 ቀን 1928

ፋሺስት ኢጣልያ አዲስ አበባን ሚያዝያ 27 ቀን 1928 ዓ.ም በዛሬዋ እለት አዲስ አበባን ያዘ። በአርበኞችና በህዝቡ ታላቅ ተጋድሎ ሚያዝያ 27 ቀን 1933 ዓ.ም ደግሞ ድል ተበሰረ። የሄኖክ ያሬድ ብሎግ ዘውዴ ረታን ጠቅሶ "የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ መንግስት" በሚለው መጽሐፋቸው ስለ ታሪካዊቷ ሚያዝያ 27 እንዲህ መጻፋቸውን ያስታውሰናል።
"ሚያዝያ 27 ቀን 1933 ዓ.ም ንጉሰ ነገስቱ በከፍተኛ አጀብ እኩለ ቀን ስድስት ሰዓት ላይ ከታላቁ የቀዳማዊ ምኒልክ አደባባይ ላይ አረንጓዴ፣ ቢጫ፣ ቀይ ሰንደቅ ዓላማችንን መልሰው ሰቀሉ፡፡ የክብር ዘብ ተሰልፎ፤ በራስ አበበ አረጋይ የሚመራው አስር ሺህ አርበኞች ያሉት ጦር ዙሪያውን በሀገር ፍቅርና በብሔራዊ ስሜት እንደ ቆፈጠን፤ በሱዳን በኩል የመጣው በሻለቃ ዊንጌት የሚመራው የጌዴዎን ጦርም ተሰልፎ፤ መድፍ ተደጋግሞ እየተተኮሰ ሰንደቃችን በክብር ከፍ አለ፡፡"
ቀዳማዊ አጼ ኃይለ ሥላሴ ከስደት መልስ መናገሻ ከተማቸው ሚያዝያ 27 ቀን ገብተው የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ከማውለብለባቸው አራት ወር ግድም በፊት ጥር 12 ቀን ሱዳን ድንበርን ተሻግረው ኢትዮጵያ ገብተው ያውለበለቡት አሜድላ ላይ ነበር፡፡
የድሉን ብስራት አስመልክተው ባለቅኔው አምባሳደር ብርሃኑ ድንቄ፡-
"ኢትዮጵያ ከማር ለሚጣፍጥ ለስምሽ አጠራር ሰላምታ ይገባል፡፡
ባምላክ እጅ ለተሰራ ለራስ ጸጉርሽም ሰላምታ ይገባል፡፡
ምሳሌ የሌለሽ መቅደስ ኢትዮጵያ ጠላት ኢጣልያ ስላረከሰሽና፤
መሰዊያሽን ሰላጠፋ ከእንግዲህ ወዲህ ተቀደሺ ኃይልንም ገንዘብ አድርጊ፡፡" ብለው ተቀኝተውላት ነበር፡፡
የፋሺስት ኢጣልያ ወረራ በኢትዮጵያ ላይ ብዙ መከራዎችን ትቶ ማለፉ አይዘነጋም፡፡ አርበኞችም የሀገሪቱን ነጻነት ለማስከበርና የህዝቡን ልዕልና ለማስጠበቅ ባደረጉት ተጋድሎ ታሪክ ሲያስታውሳቸው ይኖራል፡፡
ኢጣልያ በአድዋ ላይ የደረሰባትን ሽንፈት ለመበቀል ከ40 አመት ቆይታ በኋላ በፋሺስታዊ መንግስቱ አማካኝነት በአምስቱ አመት (1928-1933) የሰራችው ግፍ ተነግሮ አያልቅም፡፡ ወረራውን በፈጸመች በአመቱ በየካቲት 12 ቀን 1929 ዓ.ም በአዲስ አበባና በአካባቢው ከፈጸመችው ግፍ አንስቶ በሁሉም የሀገሪቱ አካባቢዎች ብዙ ጥፋትን ማጥፋቷ የማይረሳ ነው፡፡ ከነዚህም መካከል የመጀመሪያው የፋሺስት ወንጀለኞች የኢትዮጵያን ሰራዊት በፈጁበት በተምቤንና በአሽንግ በመርዝ ጋዝ ያደረሱት እልቂት ይጠቀሳል፡፡
አቶ ጥላሁን ጣሰው በመጽሐፋቸው እንዳሰፈሩት፤ ፋሺስት ኢጣልያ በ1928 ዓ.ም ኢትዮጵያን የወረረችው በቅኝ በያዘቻቸው በሰሜን በኤርትራ በኩልና በደቡብ ምስራቅ በኢጣሊያ ሶማሊላንድ በኩል በ400,000 ወታደሮች፣ በ300 የጦር አውሮፕላኖች፣ በ30 ሺህ ተሽከርካሪዎችና በ400 ታንኮች አማካኝነት ነበር፡፡ ሙሶሎኒ በወቅቱ የደረሰበትን ሽንፈት ለመቋቋምና ለመቀልበስ የወሰደው እርምጃ ሰራዊቱ በመርዝ ጋዝ እንዲጠቀም ማዘዙ ነው፡፡ የታህሳስ 18 ቀን 1928 ዓ.ም የሙሶሎኒ ትእዛዝ በተምቤንና በአሽንግ ሀይቅ ለሺዎች እልቂት ሰበብ ሆኗል፡፡
"በተንቤን ጦርነት ጊዜ ኢትዮጵያውያን ዘመናዊ ባልሆኑ መሳሪያዎች ድል አድርገዋል፡፡ የኢትዮጵያ ጦር ድል በማድረጉ ፋሺስት የኬሚካል ጥቃት ፈጸመ፡፡ በዚያን ጊዜ ያለቁት 70,000 የሚደርሱ ናቸው፡፡"
አቶ ጥላሁን በተንቤን ጦር ግንባር አዛዥ የነበሩት ራስ ካሳ በመጽሐፋቸው የገለጹትን ከፈረንሳይኛ ተተርጉሞ ያገኙትን አውስተዋል፡፡
"የተምቤን ጦርነት ጊዜ አሸነፍን፤ ዳሩ ግን ኢጣልያ ሩቅ የሚመታ መሳሪያ አላቸው፡፡ እኛ በቅርብ ሆነን ማጥቃት እንችላለን፡፡ በዚህ ሁኔታ ላይ ተዝናንተን ሳለ፤ አንድ ቀን የእነርሱ አውሮፕላኖች ቢመጡ እንፈጃቸዋለን ስንል በጣም ከርቀት ሆነው ለእርሻ አረም ማጥፊያ የሚሆን መርጫ ማድረግ ጀመሩ፡፡ ጥይት የሚደርስበት አይደለም፡፡ ጋዝና ፈንጂዎችንም ጣሉ፡፡ ዋሻው ውስጥም ሆኖ መቋቋም አይቻልምና ሰው ሁሉ አለቀ፡፡ አንድም ኢጣልያዊ ከዚያ በኋላ አልሞተም፡፡"
በአሽንግ ሀይቅ ስለደረሰው እልቂት የራስ ካሳ አይረታም ደራሲው አስታውሷል፡፡ "ሁሉም የቀይ መስቀል ፈረንጆች ሰራተኞች ከተመለሱ በኋላ በአሽንግ ሀይቅ ሜዳ ላይ የሄዱት ሰዎች ሀይቁ ከተመረዘ በኋላ በሙሉ አልቀዋል፡፡"
ይህ ዘግናኝ ኩነት በውጭ አገር ታሪክ ጸሐፊዎች ሲቀርብ የተገለጸው "የንጉሰ ነገስቱ ጦር መሸነፉን በአሽንግ ሀይቅ ውስጥ በሞላው ሬሳ አውቀነው፤" ተብሎ ነው።
የዚያን ጊዜ ያለቁት ከወንድሞቻቸው ጋር ወደ ጦር ሜዳ የሄዱ በአብዛኛው ሴቶች፣ ሲቪልና ጥቂት ቁስለኞች መሆናቸውን ያመለከቱት አቶ ጥላሁን አጽንኦት የሰጡበት ነገርም አለ፡፡ "እኛ አዲስ አበባ ውስጥ ስለተደረገውና ጥቂት ሺህ ሰዎች ስላሉበት እናስባለን፤ ያኛው በገጠር የተከናወነው ግን እየተረሳ ይሄዳል፡፡ ከከተሞች ውስጥ የሚሞተው ሁል ጊዜ ይታወሳል፤ ገጠሮች ላይ የሚሞተው ይጠፋል፡፡ በማለት ታሪኩ ሲዘከር ሁሉንም ቦታ መዳሰስ እንዳለበት አስቀምጠዋል፡፡
እንግዲህ ጀግኖች አርበኞች እንዲህ እንዲህ እያሉ ነው ስለ ሀገራቸው ክብር አጥንታቸውን ከስክሰው ደማቸውን አፍሰው ኢትዮጵያን ያቆዩልን፡፡ እኛስ የዚህ ዘመን ትውልድ አባል የሆንነው የሀገር አጋሮቻችን በምን ይታወሳል? እንደ ቀደሞቹ ሀገርን ከወረራ ጦር በመከላከል? ወይስ አፈሙዙን የሰበቀብንን ድህነት በመዋጋት? ወይስ እጅና እግራችንን አጣጥፈን በመቀመጥ የሀገርና የቤተሰብ ሸክም በመሆን? ንገሩኝ እስኪ የኛስ የድል ብስራት ገደል ምን ይሆን? የመጡ ባህልን አለባበስ ማስተዋወቅ እንደማትሉኝ እርግጠኛ ነኝ፡፡ ይልቁንስ ጀግኖቻችን ሀገርን አስቀድመው የፈጸሙት ገደል ዛሬ ላይ ላለነው ተኝተን ላንቀላፋን ትውልዶች ዘመቻችን ከድህነት አረንቋ እንድንላቀቅ ጥሪው ይደርሰናል፡፡ ክብርና ምስጋና ለሰውት ጀግኖቻችን፡፡

አዲሱ ገረመው አዲስ ዘመን ጋዜጣ መዝናኛ አምድ፡፡

Address

Addis Ababa

Telephone

+251932510930

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Samuel demise posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Place Of Worship

Send a message to Samuel demise:

Share