ማኅበረ ኪዳነምህረት ዘ አየር ጤና

ማኅበረ ኪዳነምህረት ዘ አየር ጤና ኦርቶዶክሳዊ እሳቤን የተከተሉና ዘመኑን የዋጁ ሐሳቦችን በማፍለቅ በመግባባት፣በመመካከር እና በቅንነት ለተልእኮ አንድነት ብዝኃ ጸጋን በማክበር አብሮ ይሠራል::

28/06/2026

ቂልጦ ማርያም የድል ከተማችን መማጸኛችን😍

3 ጊዜ ተቃጥላ አምራ ደምቃ ዛሬ ያለችው የስልጤዋ ቂልጦ ማርያም 😘

እንዳትፈራ ተዋሕዶን አደራ!!!

"“እስከ መቼ..." መዝሙረ ዳዊት 82:2..ኢትሬእዪኑ ላሀ ዚአነ እንተ ረከበተነ...ወርኃዊ የቅድስት ሥላሴ ጉባኤ!ሰኔ 7 እሁድ/2018ከ11:30 ጀምሮ! #ሁላችንም 1  !"እለ ውስተ ሞቅሕ...
13/06/2026

"“እስከ መቼ..." መዝሙረ ዳዊት 82:2
..ኢትሬእዪኑ ላሀ ዚአነ እንተ ረከበተነ...

ወርኃዊ የቅድስት ሥላሴ ጉባኤ!

ሰኔ 7 እሁድ/2018

ከ11:30 ጀምሮ!

#ሁላችንም 1 !

"እለ ውስተ ሞቅሕ አድሕን ወለኵልነ ኩን ጸወነ።"

ማኅበረ ኪዳነ ምሕረት ዘአየር ጤና ከካቴድራሉ ስብከተ ወንጌል ቢሮ ጋር በአንድነት!

11/06/2026

ዝንጉ፣ ወረተኛም አይደለንምና አጀንዳችንን አንቀይርም ‼

አሩሲ! አሩሲ! አሩሲ! እንላለን።

በእንተዝ ኢንፈርህ ለእመ አድለቅለቀት ምድር
ወእመኒ ፈለሱ አድባር ውስተ ልበ ባሕር

ስለዚህ ምድር ብትነዋወጥ፥
ተራሮችም ወደ ባሕር ልብ ቢወሰዱ አንፈራም። መዝ 46÷2
Mahibere KidaneMihret

የአዲስ አበባ አድባራት አስተዳዳሪዎች እና ጳጳሳቱ ዛሬ ተሰብስበው በአርሲ የወደመውን ቤተ ክርስቲያን ሊሠሩ ወስነዋል። እኛ የምንፈልገው እሱን አይደለም። ቤተ ክርስቲያኑን እኛ እንሠራዋለን፤ ...
10/06/2026

የአዲስ አበባ አድባራት አስተዳዳሪዎች እና ጳጳሳቱ ዛሬ ተሰብስበው በአርሲ የወደመውን ቤተ ክርስቲያን ሊሠሩ ወስነዋል። እኛ የምንፈልገው እሱን አይደለም። ቤተ ክርስቲያኑን እኛ እንሠራዋለን፤ እናንተ ቅድሚያ ራሳችሁን ሥሩና ትክክለኛ እረኛ ሁኑ።
እንኳን የአርሲውን የአዲስ አበባን ግዙፍ አድባራት የሚሠሩት ምእመናን አይደሉምን? የአዲስ አበባን አብያተ ክርስቲያናት እና እናንተን የገነባ ምእመን የአርሲው እንዴት ይከብደዋል። ይልቁንስ ራሳችሁን ሥሩ፤ ገዳዮቻችንን አስቁሙልን፣ ልጆቻችንን አትግደሉ ብላችሁ ሕዝባችሁን ጠብቁ።
የሚያኖራችሁን ሕዝብ ለመጠበቅ ራሳችሁን ሥሩ እንጂ ቤተ ክርስቲያኑን እኛ እንሠራዋለን።

ታደለ ሲሳይ - Tadele Sisay

መሐረነ አብ ጸሎተ ምሕላ ዛሬ በደብራችን!..ኢትሬእዪኑ ላሀ ዚአነ እንተ ረከበተነ...ተስእረ መዝሙርነወወድቀ ስምዕነ ወተነሥተ መቅደስነወተመዝበረ ታቦተ ሕግነወውዕዩ ካህናቲነ ወተቀትላ ደናግሊ...
05/06/2026

መሐረነ አብ ጸሎተ ምሕላ ዛሬ በደብራችን!
..ኢትሬእዪኑ ላሀ ዚአነ እንተ ረከበተነ...

ተስእረ መዝሙርነ
ወወድቀ ስምዕነ
ወተነሥተ መቅደስነ
ወተመዝበረ ታቦተ ሕግነ
ወውዕዩ ካህናቲነ
ወተቀትላ ደናግሊነ
ወተፄወዉ ኃያላኒነ....

ድንግል ሆይ ኀዘናችንን ተመልከቺ
ጌታ ሆይ በቃችሁ በለን !!!!!

ዘወትር አርብ በአየር ጤና አንቀጸ ብርሃን ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ካቴድራል!

04/06/2026

አታጎብድድ!!

አትሽሞድሞድ!!!

+ + የአርሲው ጥቃት፦ የማንነት ምህንድስና እና ታሪክን የማክሰም ስልት + + +በምሥራቅ አርሲ ዞን ግንቦት 23 ቀን 2018 ዓ.ም. በኦርቶዶክሳውያን  ላይ የነደደው እሳት ተራ ሁከት ወይም...
03/06/2026

+ + የአርሲው ጥቃት፦ የማንነት ምህንድስና እና ታሪክን የማክሰም ስልት + + +

በምሥራቅ አርሲ ዞን ግንቦት 23 ቀን 2018 ዓ.ም. በኦርቶዶክሳውያን ላይ የነደደው እሳት ተራ ሁከት ወይም በአጋጣሚ የተከሰተ ግጭት ወለድ አይደለም። በሀገረ ስብከቱ መግለጫ መሠረት የ101 ዓመታት የታሪክ አሻራ ያለው ጥንታዊው የጠለታ ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ጋይቷል። የ9 ንጹሐን ኦርቶዶክሳውያን ደም በግፍ ፈሷል። ከ280 በላይ አባወራዎች በአንድ ጀንበር መኖሪያቸውን ጥለው ለስደት ተዳርገዋል።

ይህ ድርጊት ከጀርባው የተቀመረን የፖለቲካ ሴራን በግልጽ ያሳያል። ክስተቱ በውጫዊ ገጽታው የሃይማኖት ጽንፈኝነት መገለጫ ሊመስል ይችላል። መዋቅራዊ ይዘቱ እና ስልታዊ ግቦቹ ግን ሙሉ በሙሉ ከፖለቲካዊ ስሌት ጋር የተሳሰሩ ናቸው። ይህ ክስተት ግልጽ የሆነ ማንነትን መሠረት ያደረገ ፖለቲካዊ ጥቃት (Identity Based Violence) ነው። የተቀነባበረ ‘የሥነ ሕዝብ ምህንድስና’ (Demographic Engineering) መገለጫም ነው። የዚህ መዋቅራዊ ፍረጃ ቀጥተኛ እና ዋነኛ ሰለባ የሆነው ደግሞ ተዘውታሪው ኦርቶዶክሳዊው ነው።

በዘመናዊው የፖለቲካ ንድፈ ሐሳብ ውስጥ ሥልጣንን ለማጠናከር ወይም ክልላዊ ይዞታን በኃይል ለማስከበር ሲባል ‘ብሔር' እና ሃይማኖትን መሣሪያ ማድረግ (Weaponization of Identity Politics) የተለመደ ስልት ሆኗል። ታጣቂ ኃይሎች የኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያንን እና ምእመናንን ኢላማ ያደረጉት በሃይማኖታዊ ጽንፈኝነት ብቻ አይደለም። ቤተ ክርስቲያናችንን እና ተከታዮቿን ለአንድ የተወሰነ የፖለቲካ ሥርዓት፣ ታሪክ ወይም ‘የእነርሱ ማንነት’ (The Other) ለሚሉት ምልክት ሰለአደረጓት እና ሆን ብለው ሰለፈረጇት ነው።

ይህ ዓይነቱ ሥርዓታዊ እና መዋቅራዊ ፍረጃ በአርሲም ሆነ በሌሎች ቦታዎች የሚኖሩ ኦርቶዶክሳውያንን በቀላሉ የጥቃት ሰለባ አድርጓቸዋል። ለማኅበረሰባዊ መቃወስና ለታጣቂዎቹ የፖለቲካ ትርፍ አመቺ መደላድል ፈጥሯል። ይህንን ፍረጃ ተከትሎ የሚመጣው የጅምላ ማፈናቀል ተግባር ደግሞ ተራ ወንጀል አይደለም። የአንድን ዞን ሥነ ሕዝባዊ ይዘት በኃይል የመቀየር ስልታዊ ፍላጎት ነው። ንጹሐንን ከቀዬአቸው በማስወጣት ‘ክልላዊ የበላይነትን’ (Territorial Dominance) ለማረጋገጥ የሚደረግ ንቅናቄ ነው። ይህ ተግባር ጥንታውያን ቅርሶችን እና አብያተ ክርስቲያናትን በማውደም የማኅበረሰቡን ታሪካዊና ሥነ ልቦናዊ ትስስር ለመበጠስ ከሚቀመር ‘የባህል ማክሰም’ (Cultural Erasure) ሴራ ጋር ቀጥተኛ ቁርኝት አለው።

በቶማስ ሆብስ (Thomas Hobbes) የፖለቲካ ንድፈ አሳብ መሠረት የማንኛውም ሉዓላዊ መንግሥት ቀዳሚና የማይሸራረፍ ማኅበራዊ ውል (Social Contract) የዜጎችን ሕይወት፣ ንብረትና ሰላም ማስከበር ነው። በአርሲ ምድር በተደጋጋሚ የሚፈጸሙት ግድያዎች፣ ማፈናቀሎችና ንብረት ማውደሞች ግን የሕግ የበላይነት ይሁን ተብሎ መላላቱን ያሳያሉ። በመንግሥት መዋቅር ውስጥ የታየው ሰፊና የታቀደ የጸጥታ ክፍተት (Security Vacuum) በግልጽ ይመሰክራሉ።

የቤተ ክርስቲያናችን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ለጸጥታ አካላት እና ለባለሥልጣናት ያስተላለፉት አባታዊ መልእክትም ይህን ከማረጋገጡም በላይ፥ ጥልቅ የፖለቲካዊ ተጠያቂነት (Political Accountability) አንድምታ አለው። ቅዱስነታቸው ለመንግሥት አካላት የሰጡት ይፋዊ ማስጠንቀቂያ መዋቅሩ ያለበትን ክፍተት ይሞግታል። ቅዱስነታቸው በደብዳቤያቸው ላይ፦ “የዜጎችን ደኅንነት የመጠበቅና ሰላምን የማስፈን አደራ የተጣለባችሁ የጸጥታ አካላትና በየመዋቅሩ ያላችሁ ሓላፊዎች ከምንም በላይ ታሪክ የሚጠይቃችሁ በሥልጣን ዘመናችሁ ለዜጎች ደኅንነት በምትከፍሉት ዋጋ ነውና ይህንን የጥቃት ሰንሰለት በማስቆምና ወንጀለኞችን ለሕግ በማቅረብ ከታሪክ ባለዕዳነት ትድኑ ዘንድ በቤተ ክርስቲያናችን ስም አበክረን እናሳስባለን” በማለት በጥብቅ አሳስበዋል። ይህ ማስጠንቀቂያ መንግሥት ወንጀለኞችን ለሕግ የማያቀርብ ከሆነ በታሪክ ፊት የጥቃቱ ተባባሪ ወይም ተገብሮ አጋዥ (Passive Bystander) ተደርጎ እንደሚቆጠር ለማስገንዘብ ነው። ኦርቶዶክሳውያንን በተግባር የመጠበቅ ኃላፊነት የመንግሥት ነው።

በአርሲ ምድር በኦርቶዶክሳውያን ላይ የተቃጣውን ይህንን ፖለቲካ ወለድ መዋቅራዊ ጥቃት ማውገዝ የሁሉም ግዴታ ነው። ይህ የአንድ ተቋም ኃላፊነት ብቻ አይደለም። በሀገሪቱ የወደፊት አብሮነትና ህልውና ላይ የተደቀነ የጊዜ ቦምብ ነው። ስለዚህ የሁሉም ሰብአዊ መብት ተሟጋቾችና ዜጎች የጋራ ድምፅ ሊሆን ይገባል።

“በቤተ መንግሥት በመኖራችን ቤተ ክርስቲያን ተጠቀመች” የሚሉ ወገኖች አሉ። እነርሱ በየጥጋ ጥጉ ከንቱ ድምፅ ይደሰኩራሉ። ያንን ከንቱ ድምፃቸውን ለእነዚህ ግፉዓን ሰማዕታት ያሰሙ። ሌሎቹ ደግሞ “ከመንግሥት ጋር በመሥራታችን ቤተ ክርስቲያንን ታደግናት” ይላሉ። እነዚህ ሰዎች የወቅቱ የቤተ ክህነቱ ሹማምንት ናቸው። እስቲ ታዲያ ያንን ትድግናቸውን በተግባር ያሳዩን። ቤተ ክርስቲያን ስትደፈር ዝምታቸውን ሙሉ በሙሉ ይሰብሩ። በቁጭትም ፈጥነው ይነሡ። የይስሙላ መግለጫቸውን አሁኑኑ ይተዉ። የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ሕልውና በተግባር ያስከብሩ።

በሀገሪቱ ዘላቂ ሰላምና እኩልነት ሊረጋገጥ የሚችለው መንግሥት ከአስተዳደራዊ መግለጫዎች ባለፈ በተግባር ሲንቀሳቀስ ብቻ ነው። በአካባቢው የሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎችን የወንጀል ሰንሰለት መበጠስ ያስፈልጋል። ኦርቶዶክሳውያን በማንነታቸውና በእምነታቸው ምክንያት የማይሸበሩባትን፣ በክብርና በነፃነት የሚኖሩባትን ሀገር መገንባት ዛሬ የሚጠየቅ የፖለቲካ ቁርጠኝነት ነው።
ግንቦት 26 ቀን 2018 ዓ.ም
አዲስ አበባ

© ዲን ታደሰ ወርቁ

"እስከ መቼ?" — ቅዱስ ፓትርያርኩ በአርሲው ጥቃት የተሰማቸውን ጥልቅ ቁጭትና ኀዘን ገለጹብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ...
03/06/2026

"እስከ መቼ?" — ቅዱስ ፓትርያርኩ በአርሲው ጥቃት የተሰማቸውን ጥልቅ ቁጭትና ኀዘን ገለጹ

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት በአርሲ ሀገረ ስብከት በቤተ ክርስቲያናችን እና በኦርቶዶክሳውያን ላይ የደረሰውን ጥቃት በማስመልከት አባታዊ መልእክት አስተላልፈዋል።

ቅዱስነታቸው ያስተላለፉት አባታዊ የኀዘን መልእክት እንደሚከተለው ነው፦

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡

‹‹ወረሰዩ አብድንቲሆሙ ለአግብርቲከ መብልዐ ለአዕዋፈ ሰማይ፣ ወሥጋሆሙኒ ለጻድቃኒከ ለአራዊተ ገዳም፦ የአገልጋዮችህንም በድኖች ለሰማይ ወፎች መብል አደረጉ፥ የቅዱሳንህንም ሥጋ ለምድር አራዊት።››
(መዝሙረ ዳዊት ፸፰፥፪)

በአርሲ ሀገረ ስብከት በአሰኮ፣ በሽርካ፣ በሆንቆሎ፣ በዋቤ እና በሙኔሳ ወረዳዎች በመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችንና በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ላይ ስለደረሰው አሰቃቂ ጥቃት የሰማነው በተሰበረ ልብ ነው።
የእምነት ነፃነት ተደፍሮ መቶ ዓመታት ያስቆጠረው የጠላታ ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን በተቃጠለበት፣ እንዲሁም የካራ ኩፍቴና መድኃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን በተዘረፈበት በዚህ ክፉ ቀን፤ በርካታ ምእመናን በግፍ መሰዋታቸውና በመቶዎች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ከቀዬአቸው መፈናቀላቸው ቤተ ክርስቲያናችንን በእጅጉ ያሳዘነ ክስተት ነው።

የሰላም፣ የፍቅርና የታሪክ ማህደር የሆነችው ቤተ ክርስቲያን በምድራዊ መከራ ውስጥ ያሉትን ምእመናን በምታጽናናበት በዚህ ወቅት ራሷ በፈተና ውስጥ ሆና ከመቸገሯም በላይ በአርሲ ምድር በተደጋጋሚ የሚስተዋለው በደልና ግፍ በሁላችንም ልቡና ውስጥ "እስከ መቼ?" የሚል የቁጭት እና የኀዘን ጥያቄን ፈጥሯል።

በመሆኑም ይህ መከራ እያበቃ ሳይሆን እየሰፋ በመምጣቱ የዜጎችን ደኅንነት የመጠበቅና ሰላምን የማስፈን አደራ የተጣለባችሁ የጸጥታ አካላትና በየመዋቅሩ ያላችሁ ሓላፊዎች ከምንም በላይ ታሪክ የሚጠይቃችሁ በሥልጣን ዘመናችሁ ለዜጎች ደኅንነት በምትከፍሉት ዋጋ ነውና ይህንን የጥቃት ሰንሰለት በማስቆምና ወንጀለኞችን ለሕግ በማቅረብ ከታሪክ ባለዕዳነት ትድኑ ዘንድ በቤተ ክርስቲያናችን ስም አበክረን እናሳስባለን።

በየአካባቢው የምትገኙ ምእመናንና መላው ኢትዮጵያውያንም በወንድማማችነት መንፈስ ተጋግዛችሁ፣ የተፈናቀሉ ወገኖችን በመደገፍና በጸሎት ከቤተክርስቲያናችን ጎን እንድትሆኑ ጥሪያችንን እናቀርባለን።

በመጨረሻም ቤተ ክርስቲያናችን ለሰላም፣ ለይቅርታና ለሰው ልጆች ክብር ሁል ጊዜ የምትቆም መሆኑን በመግለጽ ይህንን የኀዘን ሰዓት አምላካችን በምሕረቱ ያሳልፍልን፣ የሞቱትን ነፍሶቻቸውን በመንግሥቱ ይቀበልልን፣ የተጎዱትንም በቸርነቱ ያጽናናልን በማለት አባታዊ የኀዘን መልእክታችንን በእግዚአብሔር ስም እናስተላልፋለን።

እግዚአብሔር አምላክ ኢትዮጵያንና ሕዝቦችዋን ይባርክ!!

ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!!
አሜን።

አባ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ
ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት
ግንቦት 26 ቀን 2018 ዓ.ም.
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ

© የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ጽሕፈት ቤት

➻የሞ*ት ዜና መዘገቡ ሰልችቶናል፦◈የተቃጠለ እና የተዘጋ ቤተመቅደስ፣ያለቀ እና የተሳደደ  ክርስቲያን፣ የወደመ እና የተሰረቀ ቅርስ፣ ያለቀ ንብረት እየቆጠርን የምንኖረው እስከመቸ ነው?◈በየደ...
02/06/2026

➻የሞ*ት ዜና መዘገቡ ሰልችቶናል፦
◈የተቃጠለ እና የተዘጋ ቤተመቅደስ፣ያለቀ እና የተሳደደ ክርስቲያን፣ የወደመ እና የተሰረቀ ቅርስ፣ ያለቀ ንብረት እየቆጠርን የምንኖረው እስከመቸ ነው?
◈በየደብሩ ያላችሁ መምህራን
◈በየመዋቅሩ ያላችው ተቆርቋሪ አባቶች
◈በየሰንበት ትቤቱ እና በማኅበራት ውስጥ ያላችሁ ኦርቶዶክሳውያን
◈ከዚህ በላይ ምን ዓይነት የጥፋት ምልክት ማየት ትፈልጋላችሁ?
➻መ*ሞት እኮ ትልቅ ዕረፍት ነው። ስለ ቤተ ክርስቲያናችን መቀበል ያለብንን ሁሉ ተቀብለን ብንሞት ትልቅ ጸጋ ነው።
◈ከዚህ በላይ ውድመቱ ከቀጠለ ነበሩ በሚለው ትርክት ይቋጫል። ደግሞም በአርሲና በገጠሩ ኦሮምያ ቁመን እየሄድን ዐይናችን እያየ ነበሩ በሚለው ታሪክ እየተቋጨ ነው።
◈ክርስቲያኑ ማኅበረ ሰብ የሚበዛበትን ክፍል፡ ተረክ ፈጥሮ፡ ሰሜኑን ለጦርነት ብሎ ፈርጆ፦ በጦር እና በረሀብ፣ በማፈናቀልና በስደት፣ አሳሩን ሲያበላው ከባጀ አምስተኛ ዓመቱ ነው።
◈የብልጽግና ሥርዓት ብትወደው እንኳ ኦርቶዶክስ በመሆንህ አዛኘን ነው የምልህ አይለቅህም። ጊዜ ጠብቆ ነጣጥሎ ያጠፋሀል።
◈ጠላቱ ኦርቶዶክስነት እና አጠቃላይ በእስልምናም ነባርነት ያለው ባለእሴቱ ሕዝብ ነው።
◈እኔ በግሌ ከዚህ ድክርት የሞ*ት ሥርዓት ለሃይማኖታችን እና ለሀገራችንን የሚጠቅም አንዲትም መልካም ነጥብ አላገኘሁበትም።
◈በያለንበት በውስጥም በውጪም እንተባበርና ቤተ ክርስቲያናችንንም ሀገራችንንም ከጥፋት እንታደግ!!

➻የሞ*ት ዜና መዘገብ ሰልችቶናል።

መምህር ገብረ መድኅን እንየው
ግንቦት 15/2018 ዓ.ም

ገብረ መድኅን እንየው

Address

Ayertena
Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ማኅበረ ኪዳነምህረት ዘ አየር ጤና posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share