Yefikr ENAT የፍቅር እናት

Yefikr ENAT የፍቅር እናት የጌታችን የመድሐኒታችን የእየሱስ ክርስቶስ እናት ቅድስት ድ? Ye Maryam lijoch
Ye getachin yemedhanitachn yeyesus kirstos enat kidist dingl maryam wedajoch

20/01/2022

ለተሰውት ነፍስ ይማርልን
ሀይላችን መስቀል ነው
ፍርድ በክርስቶስ ነው
እንጠብቃለን

Wow thank you dear bro for sharing us a wonderful story
19/05/2020

Wow thank you dear bro for sharing us a wonderful story

10/04/2019
ነጥቡን ለ15 ሰከንዶች ተመልከቱና በመቀጠል ባዶ ቦታውን ተመልከቱ ማን እንደሚወዳችሁ ታውቃላችሁ። ሲታያችሁ Share
27/01/2019

ነጥቡን ለ15 ሰከንዶች ተመልከቱና በመቀጠል ባዶ ቦታውን ተመልከቱ ማን እንደሚወዳችሁ ታውቃላችሁ። ሲታያችሁ Share

በቤተክርስቲያናችን  ስርአት  መሰረት  7 ጊዜ  እንፀልያለን   የእነሱም  ትርጉም  1⃣ 🌺  ጠዋት  12 አንድ  ክርስቲያን   እግዚአብሔርን  አምላክን  በፀሎት  የሚያመሰግንበት  ምክንያ...
24/11/2018

በቤተክርስቲያናችን ስርአት መሰረት 7 ጊዜ እንፀልያለን የእነሱም ትርጉም

1⃣ 🌺 ጠዋት 12 አንድ ክርስቲያን እግዚአብሔርን አምላክን በፀሎት የሚያመሰግንበት ምክንያት (ሚስጥር)

1 እግዚአብሔር አምላክ ሌሊቱንና ጨለማውን አሳልፎ ብርሀን እንድናይ ስላበቃን በዚህ ሰአት እግዚአብሔር አምላካችንን እንድናመሰግን ታዝዝዋል አንድም በዚህ ሰአት ጌታችን ለክስ ከጲላጦ ፊት ቆሞ የተወቀሰበት ሰአት ስለሆነ አንድም በዚ ሰአት አባታችን አዳም ያልተፈቀደለትን እፅ በልቶ ከገነት የተባረረበት ሰአት ስለሆነ ነው አንድ ክርስቲያን ይህን ሁሉ እያሰበ ወደ አምላኩ እንዲፀልይ ታዝዋል

2⃣ 🌺 ሰልቱ ሰአት ከጠዋቱ 3 ሰአት አንድ ክርስቲያን እንዲፀልይ የታዘዘበት ምክንያት (ሚስጥር)

1 በዚህ ሰአት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ብስራተ ገብርኤልን የሰማችበት ሰአት ስለሆነ ነው አንድም በዚህ ሰአት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ጌታችንን የፀነሰችበት ሰአት ስለሆነ ነው አንድም ጌታችን መድሀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከ ጲላጦስ ፊት ቀርቦ የተገረፈበት ሰአት ስለሆነ ዮሐ 19 ፥1 ሐዋ ስራ 2፥15 እያንዳንዱ ክርስቲያን ይሔንን የመሳሰሉ ሁሉ እያሰበ እግዚአብሔር አምላኩን እንዲያመሰግን ታዝዋል

3⃣ 🌺 6:00 አንድ ክርስቱያን እኩለ ቀን (ከ ቀኑ 6ሰአት) ሲሆን እንዲፀልይ የታዘዘበት ምክንያት ወይም (ሚስጥር )

1 ጌታችን በቀራኔዎ አደባባይ በመስቀል ተሰቅሎበታልና አንድም ልብሱን ተገፎበታል አንድም ሳዶር አላዶር ዳናት ሮዳስ በተባሉ ችንካሮች ተቸንክሮበታል አንድ ክርስቲያን ይህን ሁሉ እያሰበ በዚህ ሰአት እንዲፀልይ ታዞበታል

9⃣ 🌺 ተስአተ ከ ቀኑ 9:00 ሰአት ሲሆን አንድ ክርስቲያን የሚፀልይበት ምክንያት (ሚስጥር)

1 አይሁዶች ጌታችን መድሀኒታችን ኢየ�ሱስ ክርስቶስን መራራ ሐሞት አጠጥተውበታል አንድም ቅድስት ነፍሱን ከ ክቡር ስጋው የለየበት ሰአት ነውና አንድም በመስቀል እንዳለ 7ቱን አፅርሀ መስቀል የተናገረበት ማር 15፥34 ማቴ 27፥50 አንድ በዚህ ሰአት ይህንን እያሰበ እንዲፀልይ ታዝዋል

5⃣ 🌺 የሰርክ ሰአት ከቀኑ 11፡00 ሰአት አንድ ክር�ቲያን እንዲፀልይበት የታዘዘበት ምክንያት ወይም (ሚስጥር)

1 ጌታችን መድሀኒታችን እየሱስ ክርስቶስ ወደ ከርሰ መቃብር የወረደበት ሰአት ስለሆነ አንድም ቀኑን በሰላም አሳልፎ ወደ ምሽት በሰላም ያደረሰን አምላክ ምስጋ ስለሚገባው ነው ይህንን የመሳሰሉ ሁሉ ሕዝበ ክርስቲያን እንዲያስቡ ታዘዋል

6➡ 🌺 ከምሽቱ 3 ሰአት በዚህ ሰአት አንድ ክርስቲያን እንዲያመሰግን የታዘዘበት ምክንያት (ሚስጥር)

1 በዚህ ሰአት እራሱ ጌታችን መድሀኒታችን እየሱስ ክርስቶስ ስርአተ ፀሎት አሳይቶበታል አንድም በዚህ ሰአት ጌታችንን አይሁድ በይሁዳ ጠቁዋሚነት ተረበርበው የያዙበት ሰአት ስለሆነ ነው አንድም በዚህ ሰአት አንድ ክርስቲያን ከመተኛቱ በፊት በሰላም ያዋለንንና ያስመሸንን አምላክ አመስግኖ መተኛት አለበት ይህን ሁሉ እያሰበ እንዲፀልይ ታዝዋል

7⃣ 🌺 መንፈቀ ሌሊት ከሌሊቱ 6ሰአት በዚህ ሰአት አንድ ክርስቲያን እግዚአብሔር አምላኩን እንዲያመሰግንበት የታዘዘበት ምክንያት (ሚስጥር)

1 በዚህ ሰአት ጌታችን መድሀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተወልዶበታልና ነው አንድም ጌታችን መድሀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሙስና መቃብርን ድል አድርጎበታልና(ተነስቶበታል) በመዝሙረ ዳዊት አመሰግንህ ዘንድ በመንፈቀ ሌሊት እነሳለው ባለው መሰረት ጳውሎስ ሲላስ በእስር ቤት ሆነው ወደ እግዚአብሔር የፀለዩበት ስለሆነ ነው አንድም የሰው ልጅ የሚመጣበት ጊዜ ማታ ይሁን መንፈቀ ሌሊት ይሁን ዶሮ ሲጮህም ይሁን ሲነጋም ቢሆን አይታወቅምና ባለው አምላካዊ ቀል መሰረት በመንፈቀ ሌሊት አንድ ክርስቲያን እንዲፀልይ ታዝዋል

💞💞💞💞💞💞💞💞💞

🌺 ወስብሀት ለእግዚአብሔር💞
🌺 ወለ ወላዲቱ ድንግል💞
🌺 ወለ መስቀሉ ክብር💞

02/07/2018

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Yefikr ENAT የፍቅር እናት posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Place Of Worship

Send a message to Yefikr ENAT የፍቅር እናት:

Share